November 28, 2018
4 mins read

የአቶ ሌንጮ ለታ ፓርቲ ከኦዴፓ ጋር ተዋሃደ

በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና የቀድሞው ኦህዴድ የአሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኦዴፓ) ጋር ተዋሃዱ።

የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ከቀትር በኋላ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ የውህደት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ተዋህደው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙት ከኦዴፓ አቶ ለማ መገርሳ ናቸው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እና የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ፤ ”በአንድ አዕምሮ እና ልብ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል። ኦዴፓ በወጣቶች የተሞላ ፓርቲ ነው። ከኦዴግ ጋር ስንዋሃድ ጠንካራ ተቋም ይወጣናል” ብለዋል። የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አመራሮች ወደ ሃገር ከመምጣታቸው በፊት ”ሲረዱን” ነበር ያሉት ፕሬዚዳንት ለማ፤ አብረን ለመስራት እድሉን ስላገኘን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

”ለአንድ ኦሮሞ ህዝብ ከ10 በላይ ሆነን ከምንታገል፤ ከእኛ ጋር አንድ አይነት ዓላማ እና ሰልት የሚከተሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን መጥተው ቢቀላቀሉን አሁንም ለመቀበል ዝግጁ ነን። ይህም ለኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን ለሃገርም ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው።” ብለዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ በበኩላቸው ”የመበታተን ባህል ወደ ችግር እና ድህነት ነው የሚወስደን” ብለዋል። አቶ ሌንጮ ጨምረው ”ዛሬ ላይ የፓርቲዎች ውህደት ብቻ ሳይሆን የህዝብ አንድነት ጭምር ያስፈልገናል፤ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን እንደዛሬ ነው ማሰብ ያለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

የኦዴፓ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ስምምነቱን አስመልከቶ እንደተናገሩት ሁለቱ ፓርቲዎች የኦሮሞ ህዝብ አንድ እንዲሆኑ ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ሊዋሃዱ ችለዋል፡፡ ‹‹የኦሮሞ ህዝብ ለፓርቲዎቹ አመራሮች አንድ ሆናችው ወደ እኛ መምጣት አለባችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፏል›› ያሉት አቶ አዲሱ ኦዴፓ ከኦዴግ ጋር የህገ ደንብ፣ የስትራቴጂ እና የፕሮግራም ልዩነት የሌለው በመሆኑ በጋራ ለመስራት እንደማያስቸግረው ጠቁመዋል፡፡ በዛሬ የስምምነት ሰነዱ ቢፈረምም ወደፊት ከሁለቱ ፓርቲዎች ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቁሞ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት የኦቦ ሌንጮ ለታ ኦዴግ ቀደም ሲልም ከኦዴፓ ጋር መስራት ጀምሯል:: ወደ ሃገር ቤት ከገቡት አመራሮቹ መካከልም ሹመት አግኝተው እየሰሩ አሉ::
ሌንጮ ባለፈው ሳምንት በፓርቲ አመራርነት እንደማይቀጥሉ ሆኖም ግን ከፖለቲካው ዓለም ሕይወታቸው እስከሚያልፍ እንደሚቀጥሉ መግለጻቸው ይታወሳል::

ዶ/ር አብይ አህመድ ትናንት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ሰማንያ አንዱ ፓርቲዎች ወደ ሦስት እና አራት ተዋህደው ዝቅ እንዲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ዘግበናል::
https://www.youtube.com/watch?v=DKNGEfUvzgA

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop