ሰባተኛው ንጉሥ ጉድ አፈላ! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ቀድሞ ማመስገን ለተከታይ ወቀሣ አመቺ አለመሆኑ ተዘውትሮ ይጠቀሳል፡፡ ቢሆንም የየዕለቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ተለዋዋጭ እንደመሆናቸው በዚህ ነጥብ ረገድ ግትርነት ወይም ይሉኝታ አስፈላጊ አይደለምና እውነቱን ተናግሬ እመሸብኝ ማደርን መርጫለሁ፡፡ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሊን ወደማምለክ ደረጃ የደረሳችሁ ሰዎች ታገሱኝ ወይንም ይህንን ጽሑፍ አታንብቡ፡፡ እኔም ላመልከው ደርሼ ነበርና በሀገራችን ሰውን ማምለክና ለሰው መስገድ ብርቅ አይደለም፡፡ ከቅዠት ቶሎ መንቃት ግን ከተጨማሪ ውርደትና ጥቃት ይታደጋል፡፡ አምልኮት መጥፎ ነው፤ ያሳውራል፤ ምክንያትንም ያጠፋል፡፡

ዐቢይ አህመድ አፈ ጮሌ ነው፡፡ የሰውን ስሜት ቀፍድዶ በመያዝ ጎበዝ ነው – I wish him a good job in hypnosis after his death in politics which will take place very soon. He is a nice hypnotizer. በሌላ በኩል ግን የሊቀ ሣጥናኤል መልእክተኛ መሆኑን ለመረዳት ብዙ ጊዜ ፈጅቶብኛል፡፡ አምላከ አማልክት ዶ/ር ዐቢይ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ቀልብ የገዛው ገና ወደ ሥልጣን በመጣ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነበር፡፡ ከነዚያ እርጉማን ደቂቃዎች ጀምሮ ሰማይና ምድር ለዚህ ብላቴና ተንበረከኩ፤ ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቹ በስተቀር ከሞላ ጎደል ሁሉም በፍቅሩ ተንበረከከ፡፡ ታማኝ በየነ ሰገደለት፤ ፕሮፌሰር አልማርያም ተማረከለት፤ ፕሮፌስር መስፍን አለወትሮው በፍቅሩ ወደቀለት፤ የሆነውን ሁሉ ማስታወስ ለቀባሪ ማርዳ ነውና ይቅር፡፡ (የውስጥ ጠላቱ ዘርን መሠረት አድርገው “ዛሬና ነገ የኛ ናቸው” ብለው በሥልጣን ጥም የታወሩ ነገን ግን በጭራሽ የማያውቁ ድኩማን አማካሪዎቹና የራሱ የሥልጣን ‹ኢጎ› ሲሆን የውጭ ጠላቶቹ ደግሞ ወያኔዎች ናቸው፡፡)

ዐቢይ መቼም ቢሆን አይሳካላቸውም እንጂ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሌት ከቀን የሚማስኑት ኢሉሚናቲዎች ወኪል ነው፡፡ ይህን የፈጠጠ ገሃድ እውነት ዐቢይ ራሱም ላያውቀው ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ኢሕአፓ እንኳን ባቅሟ አፈ ጮሌንና በትምህርት ጎበዝ የሆነን ሕጻን ሳይቀር ትመለምል ነበር፡፡ ስለዚህም አደገኛ ምሥጢራዊ ቡድኖች (cabalists or secret societies such as the Illuminati and related satanic groups and organizations) በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተወዳጅነት ያላቸውን ሰዎች በኅቡዕ በመመልመል ለዓላማቸው ሥሙርነት ማሰማራታቸው የተለመደና የታወቀ እንጂ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በዐቢይ የምታመልኩ እንግዲህ ዕበዱ፤ እውነቱ አሁን የምለው ነው – ሌላ አይደለም፡፡

አፈቅቤ ልበ ጩቤው ዐቢይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎትና የልብ ትርታ ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል፡፡ ለራሱ ሳይኖር ለዚህ ብቻ ኖሯል፡፡ ብዙ አንብቧል፤ ብዙ ጽፏል፡፡ ለዚህ ልዩ ተሰጥዖውና ራሱ ያዳበረው አስደማሚ ችሎታው የዕድሜ ልክ አድናቂው ነኝ፡፡ ከመጻሕፍትም፣ ከሰውም፣ ከሕይወት ውጣ ውረድ ገጠመኝም ብዙ ተምሯል፡፡ ስለዚህም ነው ለራሱ ሳይኖር ለዓላማው ሲል ከዕድሜው በላይ ኖሯል የምለው፡፡ መለስም እኮ በዕውቀት አይታማም፡፡ ዐቢይ መለስን የበለጠው በትንሽ ነገር ነው – እኔም አንተም ልናደርገው በምንችለው መለስ ግን ዘግቶበት ባላደረገው ትንንሽ ነገር ዐቢይ መለስ ዜናዊን ዘረረው፡፡ በተራው ግን ዐቢይም በስድስት ወራት ውስጥ ተዘረረ – እምብዝም ስለት ይቀዳል አፎት ነው ነገሩ፤ “የማያድግ ልጅ በአባቱ ብልት ይጫወታል”ም ይባላል ዐቢይን መሰል አሰለጥ ለመተቸት፡፡ መለስስ በጭካኔው ከ20 ዓመታት በላይ በሥልጣን ቆይቷል፡፡ አሳዛኙ ዐቢይ ግን አንድ ዓመት የሚደፍን መሆኑ እጅግ ያጠራጥረኛል፡፡ መቼም ስድስት ሰዓት ከገዛው ከንጉሥ አዙር በልጧል፡፡ የሚገርም ነገር!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፋኖ ተጋድሎ ሁለት ገጽታዎች

በነገራችን ላይ “ከብዙ ትርምስና ሁከት በኋላ ለሦስት ወር ወይም ግፋ ቢል ለሦስት ዓመት አንድ የእስላም ንጉሥ ኢትዮጵያን ይገዛል” የተባለው ትንቢት ምናልባት ይህ ሰው ሊሆን እንደሚችል እጠራጠራለሁ፡፡ ሆነም አልሆነም የኢትዮጵያ ነፃ መውጣት የጊዜ ጉዳይ እንጂ እጅግ ተቃርቧል፤ ምልክቶቹ ሁሉ ታይተዋል፡፡ ትንሽ ትንቢት ቢጤ በመጨረሻ አካባቢ ጣል ማድረጌ አይቀርም – “Who minus who?” “ማን ከማን ያንሳል?” ለማለት ነው – ደግሞ ለመተንበይ!

የሣጥናኤል ግብ እውን እንዲሆን የተሰለቸው ወያኔ በአዲስ ወያኔ መተካት ነበረበት፡፡ አሮጌው ወያኔ ለነባሩ የዲያቢሎስ ፍላጎት ስኬት አልተመቸም፡፡ ስለዚህ የተረት አባት ዐቢይ ራሱ እንዳለው “ዕንቁላል ከውስጥ ሲሰበር ሕይወት፣ ከውጭ ሲሰበር ሞት” ነውና ሌላ አካል ከውጭ መጥቶ ኢትዮጵያ ነፃ እንዳትወጣና ሃይማቱንም ፖለቲካውንም እንደልቡ የሚዘባነንበት ሊቀ ሣጥናኤል ከኢትዮጵያ ተዋርዶ እንዳይወጣ ሲባል ይህ ታላቅ ሤራ ሊጎነጎን በቃ፡፡ አበሻ ቁርጥህን ዕወቅ ሤራው ግልጽ ነው፡፡

ዐቢይ ወደ ሕዝብ ልብ ውስጥ እንዲገባ የድርሰታቸው ጊዜ በጣም አጭርና ፈጣን የሆኑ ድራማዎች ወደ መድረክ ብቅ ማለት ነበረባቸው፤ ያን ሕዝባዊ ዐመፅና እምቢታ በቶሎ ማብረድ አስፈላጊ ነበር፡፡ ብዙ አማካሪዎች አሉ፤ ብዙ ተዋንያን አሉ፤ ብዙ አሽቃባጮችና የሀሰት ወሬ አናፋሾች አሉ፡፡ እነ ባህታዊ ተብዬዎቹ ገ/መስቀልና እነ ታምራት ገለታን የመሳሰሉ ሣተና ጠንቋዮች እንኳን ስንትና ስንት የወሬ ቱሪናፋ የሚነዙ ተከፋይ ምልምሎች ነበሯቸው፤ አሏቸውም፡፡ የትክለ ሰውነት ግንባታ ቀድሞ ካልተካሄደ አስጠንቋይ ወደ ጠንቋይ፣ ተጠባይ ወደ ጠበል፣ ታካሚ ወደ ሀኪም፣ “ነቢያትንና ፈዋሾችን” ፈላጊ ችግረኛ ወደ “ቸርች” … አይሄዱም፤ ይቺ ምድር የትያትር ዓለም መሆኗን ከዘነጋን የለንም፡፡ ስለዚህ በመንግሥት ወጪ ፈንድ የሚደረግ ዝናን ገምቢና ስብዕናን አግዛፊ ሆዳም በመሙላቱ ሳቢያ ስመ-ጥርነቱ በጥቂት ጊዜያት እየገዘፈ የመጣው ዐቢችን አሁን ይሠራውን አጣና ሀገራችን ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ ተዘፍቃበት ወደነበረው የዘረኝነት አዙሪት መልሶ በባሰ ሁኔታ  ዘፈቃትና ዐረፈው፡፡ ይሁን፡፡ ሁሉንም ማየቱ ጥሩ ነው፡፡ ያች ሴተኛ አዳሪ “አጭበርባሪ አይተኛኝም” ያለችውን ግን መርሳት የለብንምና የሀገራችን ትንሣኤ የሚመለከተን ዜጎች ሁሉ ጥንቃቄ እናድርግ፡፡

ከውጭ ሀገራት የታሰሩ ሰዎችን ይዞ መጣ – በአንድ አውሮፕላን ሊያውም “ሰልፊ” የሚሉትን ዘመነኛ ፎቶ አብሮ እየተነሣ፡፡ “እንዴት ያለ መሪ አገኘን!” ብለን ጉድ አልን፡፡ በቤት ውስጥ የታጎሩትን በሽዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ግን ረሳናቸው፡፡ ሰሞኑን እንኳን የአዲስ አበባ ወጣቶች ባልታወቀ ሥፍራ ታስረው አባሰቸውን እያዩ ነው – “ዐቢያችን” በምትሃቱ አሳውሮናልና ይህንንም እንደበጎ ወሰድንለት፡፡ በትግራይ ጉድጓዶች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተለይም እኚህ የፈረደባቸው አማሮች በጨለማ ታጉረው ይሰቃያሉ – ይህ “መሢህ” ስለነዚህ ሰዎች የተነፈሰው የለም፡፡ ኤርትራ ሄደ፡፡ የዘመናት ቁርሾ ሊያስወግድ ሞከረ – ግሩም ነው፡፡ ግን አንድም እስረኛ አላመጣም – ለዘዴ ነው ብለን ዝም አልንለት፡፡ እንዲያውም የሀገራችንን ኢኮኖሚ በተለይም የትግራይን ሕዝብ ኑሮ ይበልጥ አመሰቃቀለው፡፡ ያዘነችን ዜጋ ዕንባ ጠረገ፤ “ሆ! እንዲህ ዓይነቱን ሩህሩህ መሪ የት ደብቀህብን ኖርህ?” ብለን በደስታ ሲቃ እያነባን ፈጣሪን አመሰገንን፤ አይቻልም እንጂ ቢቻል ኖሮ ከየዕድሜያችን እየቆነጠርን ለዚህ ደግ መሪ ለመስጠትም ወረፋ ልንይዝ የዳዳን ብዙዎች ነን፡፡ ግን አሁንም በኢትዮጵያ ውስጥ በፍትህ ዕጦትና በርሀብ፣ በወምበዴ ፖሊስና በወያኔዎች ሸርና ተንኮል የሚያለቅሱ ሚሊዮኖች አሉ፡፡ ይህ ሁሉ የማስመሰል ተግባር የተቋጨው ግን በሰሞኑ ሽህሞት ነው – ሹመት፡፡ ሕይወት እንዲህ ናት ምዕመናን፡፡ “አፍ ያለው ያግባሽ ገንዘብ ያለው?” ተብላ ተጠየቀች አሉ አንዷ፡፡ “አፍ ያለው” ብላ መለሰች፡፡ እንደኛ ጉድ ስትሆን ለማልቀስ፡፡ ከዳግም ልቅሶ ይሠውረን፡፡ ዐይናችንን ይግለጥልን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

ዕድሉን ባገኝ ከዐቢይም ጋር ሆነ ከተወካዩ ጋር መከራከር እችላለሁ፡፡ ሌላ ሌላው የማስመሰል ሥራው ይቅርና ይህ ሹመት ብቻውን የዐቢይን ማንነትና የሣጥናኤል ልዑክነት በግልጽ ይመሰክራል፡፡

ማሳሰቢያ – እኔ እገሌ ተሾመ አልተሾመ ጉዳየ አይደለም፡፡ በዘርና በጎሣ የምጠብና የምኮማተርም አይደለሁም፡፡ እንዲያውም ከኢትዮጵያ ሹመት ሞት እንደሚሻል አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በሹመቱ አሰጣጥና የሰዎች አመላመል ዙሪያ የተሰማኝን ቅሬታ ለመግለጽ እንጂ “ደቻሣ ተሹሞ ለምን አጎናፍር ሳይሾም ቀረ?” ከሚል ጠባብ የጎሠኝነት ስሜት ተነስቼ እንዳልሆነ ሁሉም ሊረዳልኝ ይገባል፡፡ እውነቴን ነው፡፡

ሚኒስትሮች መቀነሳቸው ጥሩ ነው፡፡ በድሃ አገር ዱሮውንም ይህን ያህል የካቢኔ አባላት ሊኖሩ ባልተገባ – ወያኔ ሰዎቿን ለመሰግሰግና ለመጥቀም ብላ እንጂ በአስፈላጊነቱ አምናበት እንዳልነበር መገመት ይቻላል፡፡ በእግረ መንገድም የፓርላማውና የሕዝብ ተወካዮች ተብየውም መቀመጫ ተንዛዝቷል፡፡ ለደናቁርት እንቅልፋም ፓርላማ ከ80 እና 90 በላይ አያስፈልግም፡፡ አንድ ሰው እንደፈለገው ለሚጫወትበት ፓርላማና የተወካዮች ንክር ቤት ማለትም ምክር ቤት ይህን ያህል ማይም መሰብሰብ አግባብ አይደለምና ዐቢይ በዚህም ላይ ቆራጥ እርምጃውን በቅርቡ እንደሚወስድበት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ከስሜታዊ አጻጻፍ ለመውጣት አንድ ቀን አሳልፌያለሁ፡፡ ወዲያውኑ ብጽው ኖሮ አንድም አንባ አላገኝም ነበር፡፡ እንዴ! ሥራቸው እኮ የሚገርም ነው፡፡

አሥሩ ሚኒስትሮች ሴቶች ናቸው፡፡ የአዲሱ መንግሥት ምክንያቶች ደግሞ ደስ ይላሉ – ለዚህ የተሰጠው መልስ “ሴቶች መምራት መቻላቸውን እንዲያረጋግጡ” ተባለልኝ፡፡ ውሸት ነው፡፡ ዘይኑ የሚሉት ያኛው ቀርፋፋ የፖሊስ አዛዥ ደግሞ “የአዲስ አበባ ወጣቶች የታሰሩት ማለትም ወደማሰልጠኛ የገቡት ሊሰለጥኑ ነው” አለንና አሳቀን፡፡ እንዴት እንደሚንቁን ስገነዘብ ኢትዮጵያዊነቴን ብቻ ሳይሆን ሰው መሆኔን ጭምር እጠላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከውሸታም ፖለቲከኛ ውጪ ላይገዛት፣ ከውሸታም የቴሌቪዥን ጣቢያ ውጪ ላይኖራት ተረግማ ይሆን?

ጥሩ ነው፡፡ አሥሩ ሴቶች ናቸው፡፡ በዕድሜ፣ በትምህርት፣ በተሞክሮ፣ በችሎታ … እነዚህ ሴቶች ማለቴ ሰዎች ምን ያህል ለቦታው ይመጥናሉ? ብሎ መጠየቅ ብልኅነት ይመስለኛል፡፡ ዐቢይ ግን ማንን ነው “እየቀፈለ” ያለው? እጃችን እስኪላጥ ስናጨበጭብለት ጊዜ አጠገቡ እንዳሉትና ቤተ መንግሥት የገባ አምባገነን ሁሉ እንደሚጫወትባቸው የፓርላማ አባላት የለዬልን ደናቁርት መስለነው ይሆን? ማን ያውቃል እንደነሱ ቆጥሮንም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን አይደለንም፡፡ወደዚያ የሚሄዱት ወያ የሚመርጣቸው ጅሎችና ሆዳሞች ማይማንም ጭምር መሆናቸውን ንገሩት፡፡ ኢትዮጵያውያን ማን መሆናችንን ቆንጆዎቹ ሲወለዱ ያየናል፡፡ እስከዛው ይጫወትብን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፍንክች አይሉም እኛም ፍንክች አንዳንል ያስፈልጋል - ሉሉ ከበደ

እስኪ ስማቸውን እንይ –

  1. ወ/ሮ ሙፈሪያት ዐቢይ አህመድ
  2. (ወ/ሮ?) ኢንጂኔር አይሻ ዐቢይ አህመድ
  3. ወ/ሮ ፈትለወርቅ አባይ ፀሐዬ
  4. ወ/ሮ ዳግማዊት ገዱ አንዳጋቸው
  5. ዶ/ር ሒሩት ዐቢይ አህመድ
  6. ዶ/ር ኤርጎጌ ዐቢይ አህመድ
  7. ዶ/ር ሂሩት ዐቢይ አህመድ
  8. ወ/ሮ አዳነች ዐቢይ አህመድ
  9. ወ/ሮ ያለም ዐቢይ አህመድ
  10. ዶ/ር ፍጹም ዐቢይ አህመድ (ይህ ስም ወንድን ከወከለ ይቅርታ)

 

እነዚህና ሌሎቹም ከኦሮሞ ነገድ የመጡ ዜጎች ለዐቢይ ቅን ታዛዦች እንደሚሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዐቢይ በካቢኔው ውስጥ ያሉት እንደራሴዎች ከአሥር በላይ ናቸው፡፡ በዐይን ጥቅሻና በስልክ የሚያሽቆጠቁጣቸውን ገራገር ሴቶች ማለትም ሰዎች መርጦ ለሹመት ማስቀመጡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከመለስ በላይ እንዴት እንደሚንቀው ያሳያል፡፡ በነገራችን ላይ ተፎካካሪ እያለ በንግግር የሚያሽሞነሙናቸው ተቃዋሚዎችስ ኢትዮጵያ ሀገራቸው አይደለችም እንዴ? ከነሱስ መርጦ ቢሾም ከማን ያንሳሉ? ሀገሪቱን እንዲህ መጫወቻ ከሚያደርጋት – እንዲህ መሳቂያና መሳለቂያ ከሚያደርገን አንድ ሁለት ሦስት ያህል መርጦ ሚኒስትሮች ቢያደርጋቸው ምን ነበረበት? እነሱ ከነሙፈሪያት አንሰው ነው? ለአብነት ለገንዘብ ሚኒስትርነት ከብርሃኑ ነጋና ከአህመድ ሽዴ የትኞቹ ይቀርባሉ? እንዲያው ለመሆኑ ኢትዮጵያ የማን ናት? አይዞን! ኢትዮጵያ የሰማንያውም ጎሣና ነገድ ሀብት ንብረት የምትሆንበት ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ወደ ፈጣሪ እንመለስ፤ ከክፋት እንራቅ፤ በጎ ሰዎች እንሁን፤ እንጸልይ፡፡

ልጨርስ መሰለኝ፡፡

ጦጣና ጉሬዛ ፍቅራቸው ያበቃል፡፡ ሥልታዊ ኅብረት የፈጠሩበትን ቃል ኪዳናቸውንም ያፈርሳሉ፡፡ ጦጣ የሰበሰበችውን አትበላም፡፡ ይልቁንም ጉሬዛን ለማጥቃት ያከማቸችውን ገንዘብ ከየጎሬዋ እያወጣች ጉሬዛን ትረብሻዋለች፡፡ ይህ መተናኮሏ ለጉሬዛ ሕልምና ቅዠት መኮላሸት ዋና ምክንያት ይሆናል፡፡ የኋላ የኋላ በዱባ ጥጋብ የነበረረው ጉሬዛ በሀብት ብዛት በሰከረችው ጦጣ ተሸንፎ “አጉራሽ ጠናኝ” ይላታል፡፡ በመጨረሻ ግን አንበሣ ከየት መጣ ሳይባል በሁለቱም መካከል ዕርቅ እንዲወርድና ጫካና ደኑ ሰላም እንዲወርድበት ያደርጋል፡፡ አንበሦች ካልመሰላቸው ጥንቸልም በፊታቸው ትሄዳለች፤ ዐይጥም በጆሯቸው ትመላለሳለች፡፡ ዐይጦችና ጥንቸሎች የአንበሣን ትግስት ወደ ፍርሀት ይለውጡታል፡፡ አንበሣን ያሸነፉ እየመሰላቸው በአንበሣው ፊትና በሰውነቱ ላይ ጭምር አክሮባት ሊሠሩ ይዳዳሉ፡፡ ከአእዋፍ ጩኸት፣ ከደኑ ስፋት፣ ከከዋክብት ምህዋራዊ አቀማመትና ከዓለም አቀፍ እንስሳት የርስ በርስ ንትርክና አለመግባባት የተነሣ መላ ሰውነቱ ዝሎና ግራ ተጋብቶ የነበረው አንበሣ ወደ ቀድሞ ጥንካሬውና የአስተዋይነት ቁመናው ይመለሳል፡፡ ያኔና በመጨረሻው ሁሉም የርሱ ምርኮ ይሆናሉ፡፡ አሁንም ያኔና በመጨረሻው መጨረሻ ደኑና ጫካው ማንም እንደፈለገው በጥጋብና በዕብሪት እየፈነጠዘ የሚያውከው ሳይሆን እውነተኛው ሰላም የሚያረብበትና ፍትህና ርትዕ የሚሠፍንበት ይሆናል፡፡ አበቃ፡፡

12 Comments

  1. You and those like are always seek if they see something positive in Ethiopia political landscape. Abiy Ahmed is not there to fill you wish by bringing back the “golden” time of Haile Silasie. Those politicians on your wish lists are only competent for you. You are foolish and backward. Keep on your stupidity and dreaming your unfulfilled wishes.

    If you want to solve the problems of the Empire state of Ethiopia seriously. First, you have to denounce all the bad deeds of all past and present repressive systems. Second, make sure for yourself that the hegemony of the Habesha will not have place in Oromia henceforth.

    By the way, who are discrediting the Ethiopian politics of nations with the connotations of clan politics and where come it from? Such narratives come always from narrow nationalists and primitive minded individuals who are still against the democratic rights of the different nations in Ethiopia. Thrse individuals are Amhara by default and have been promoting Amaharanism as an Ethiopian identity. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the nations in Ethiopia. Most of them are the worshipers of Menilik and the offsprings of the ex-Neftegnas. Those individuals are desperate and hopeless. They are toxic and anti-unity.

    The politics of one language, one culture and a single nation cannot be accepted any more in Ethiopia. Don’t forget that such demands have no room in today’s Ethiopian politics. But now temporally you can make noise here and there. That is all what you can do right now.

    De-Amharanisation of the whole Ethiopian politics is indispensable and absolutely necessary in order to reform and reshape Ethiopia as a country of multinational state. The politics of one language, one culture and a single nation cannot be accepted any more. Also there is no Ethiopian identity as some idiotic individuals try preach us those like the chameleon Ermias Legesse. It is a fake identity and ridiculous.

    Dissociating Ethiopia from the politics of Menilik is indispensable for emancipation of all the nations.

    The creation a new national flag is crucially important in order to build a national consensus. The new flag should have reflect a true multinationality of that country.

  2. Who is this lunatic?? Zar alebet??
    He is telling us Dr.Abiy has ten daughters and son …as old as him ??
    Go to Washer for your poor Qinee! You are “Anbessa” only in cyberspace. Mujelam!

  3. ቅሬታህ አልገባኝም፡፡ የራሱን እና ወያኔን ሾመ ነው የምትለው? ብርሃኑ ነጋን ጠቅሰሃል እና የግንቦት ሰባትን ብርሃኑን ነው የምትለው? ኧረ ዶ/ርን ተወው በናትህ፡፡ ድርጅቱን በእግሩ ያቁም መጀመሪያ አንድ G7 ነው አይን የሚገባ የፓለቲካ ድርጅት ያለው ሌሳው ቄሮ ቆርቆሮ ብቻ ነው፡፡ lol

    ፕ/ሚሩ ላይ ምን ታይቶ እንደምታንቋልጡለት ሁሌ እንቆቅልሽ ነው የሚሆንብኝ፡፡ እስከአሁንም ከወሬ በስተቀር የጊዜውም ማጠር ሊሆን ይችላል ወይም ወያኔ ጠፋ ብለን አፋችንን ሞልተን መናገር ስላልቻልን ይሆናል በተስፋ ነው ያለነው፡፡ እንዲያውም የህዝብ መፈናቀል መጤ እየተባለ መሰደድ ዛፍ ላይ ሰው መስቀል መቼም ታይቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ወንጀሎችን በኦሮሞው መሪያችን ዐብይ ዘመን ነው እያየን ያለነው እናም ሃላፊነት ወስዶ ያደረገውም ነገር የለም፡፡ የ15 ደቂቃ ማስተዛዘኛ ለዜና ፎቶግራፍ ሙቪ ሰርቶ ይሰወራል፡፡ ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም እስቲ በትእግስት እንጠብቃለን፡፡ እስከ ሁለት ዓመት ይፎግረን አብሽር አያለ፡፡

    ሹመቱን በሚመለከት ግን የመከላከያዋ ሴትዮ ትንሽ ታስፈራለች፡፡ መከላከያን የሚያህል ነገር የሴቶች የጽዋ ማህበር ይመስል ለሴት መስጠት እንዳይስደፍረን ያሳስበኛል፡፡ አገራችን ገና አባወራ የሚሰማበት አገር ነው እና ጊዜው አሁን አይመስለኝም ለሴት እንደእዛ አይነት ሃላፊነት ለመስጠት፡፡ በእርግጥ ችሎታ ያለውና የተማረ ማግኘት አገራችን ቀላል አይሆንም በዛ ላይ ተምሮ ፓለቲካንም የሚፈልግ ሰው ማግኘት፡፡ የሴትየዋን ችሎታ አላውቅም ግ ን ጾታዋ ለቦታው የማታስፈልግ ይመስለኛል፡፡

    በቡርካ ለባሽ የተክበበው ጃዋርን እና ቢጤዎቹን ለማስደሰት ነው ወይስ ምርጫው ለሳውዲ ፓርላማ ነው፣ ወይስ ፓርላማውንም ሳውዲ ሊወስደው አስቦ ነው? የቡርካ ለባች ጋጋታ የማውቃትን አገሬን አልመስል እያለኝ ነው፡፡ አይ አገሬ! በተለይ መውፈሪያ የምትባለው የሆነች ዝፍዝፍ ነገር ካለሷ የተማረ ሴት አጥተው ነው እሷኑ ነው መላልሰው የሚያመጧት፡፡

    ሹመት የትውልድ አገር እየተጠራ መስጠት ግ ን በጣም የሚያስፍርና የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ማንንም ይሹም የትውልድ ሥፍራ ጥሪ የወያኔ ልክፍት ለቆን እንዳልሄደ ምልክት ነው፡፡ ኦሮሞዎቹ “እኛ ” እያሉ ስጡን ስለማይሰለቻቸው ይሄ ሹመት አፋቸውን ያስይዝልናል፡፡ለምን ለዚህ አገር ሰው አልተሰጠም ከማለት ይልቅ አስተዳደሩን ግልጽና ሃላፊነት እንዲወስድ ማበረታትና መፈተሽ አለበት፡፡

    ዋናው ፕ/ሚሩ የአዲስ አበባን ጉዳይ በደንብ አስረግጦ ነው የተናገርው፡፡ ፊን ፊኔ እያለ የሚበላቀጠውን ሁሉ ፕምሩ በንግግሩ አዲስ አበባን ለማስደግ ለማሻሻል የአፍሪካ መዲና ስለሆነች ወደፊት ነው ያለው፡፡ እሱ ባይስክል መንጃ፣ ለእግረኛ መንገድ፣ መናፈሻ ለመስራት ነው ችግሩ እንጂ የፈጠራ ወሬ እመዬ ሚኒልክ አባሮኛል ጂኒ ቁልቋል አሉባልታ መስሚያም ግዜ የለው፡፡ አዲስ አበባን ለማሳደግ ወደፊት ብቻ ነው አላማው፡፡ The verdict is in! CASE CLOSED!

    Addis Ababa is made by Addis Ababaians for Addis Ababian!!! end of story!

  4. Gammadda, you are biting the dust very soon.Stop your hatered against Amharas! Your verbal diahrrea takes you no where other than the noose. And stay clear. Ok wally!!!

    • Yes, I know verbally are a hero and tiger on computer. But practically you are a rabbit. I have respect for those true Amahra like colonel Zewudu, Gedu, Demek and others. Keep on holding your backward thinking and sentiments .

  5. Abiy Ahmed is chairman of EPRDF. Abiy Ahmed is doing everything in his power for EPRDF to win the 2020 vote by keeping the fauls of EPRDF’s crimes inside secrets .The competitor G7 and alike are offlimits from governmental files. Berhanu Negga Ginbot7 laid down his armed struggle,now Ginbot7 is being denied permits to hold public meetings in various parts of the country. Ginbot7 is a contender or competitor of EPRDF and same as how merkato shopowners do keep their trades within their circles EPRDF is making sure only EPRDF is in the cabinet.

    • What armed struggle?
      His so called jeles were herding goats in the Eritrean deserts, if any. His supporters were trying to evict the Oromo people from Finfine. While he was allowed to hold rallies in various cities in Oromia, he will not win elections– he may have to go back to where he came from. He better control his supporters or else things will get ugly for them.

  6. donkoro mehayim be endante ayinet nifit chinkilat sile abiy ahimed sitawora atafirim demo sile eminetu litawora yamirehali ende esu ye geta liji newu endante ayinetu hagerin lemekefafel ena wode elkit lememirat keni ena lelit enkilf yatachu tesfahin kuret kengidi bewala minim bifeter ayisakalachum ante ena yihe zehabesha yemibal dire gesti abrachu gedel gibu adibachu kalitekemetachu gin abiy ena ye abiy mengist sayhon engaw rasachin korariten gehanem enketachiwalen

  7. Where are the comments?Are they invisible? The template states that there are 7 comments but none of them are displayed under the article.

  8. Dagmawi,

    You thought Abiy is going to fulfill your dreams of rejuvenating the Neftegna system? You are dead wrong. We will not let him. You have no recourse either. We will work with all nations and nationalities including our Tigrian brothers and sisters. The Amharas cant take it or go to hell. There is really nothing you can do unless you want a bloody nose. You subhuman scumbags why didn’t you show your ugly faces during the struggles against the wayane forces? Let me guess, you were hiding under your mothers’ dresses. You have an inflated view of yourselves. But make the wrong move and you you will be dealt with. Now we are happy that you showed your selves. We are ready so be ready!

  9. I think it is time to think twice before we post non-sense things. For those who want to live in a democratic and prosperous country, posting such nasty things is counterproductive. Whether we liked it or not we have one country where all of us live peacefully, respecting human rights, accommodating each other, confessing what had happened in the history of Ethiopia, denouncing bad doers, appreciating those with positive thinking. Otherwise, if you simply think of old ways and posting old-fashioned saying quoting from the false and baseless fabricated history written by arrogant “debteras” we end up in turmoil and chaotic situation which will never stop. Do you want such bad situations to prevail in your Ethiopia? I don’t think any one wanted to suffer further.
    Don’t forget that Dr. Abiy is EPRDF and he become the prime Minster by EPRDF. He wanted to serve his party. How can he bring your “Birhanu Nega” to mistrial level under EPRDF?
    Please refrain from simply posting hate speeches as these are counterproductive for the New Ethiopia that all its people irrespective of the so long existing false history told to every nations, nationalities and people living within the boundaries of today’s Ethiopia. For that to happen a consensus is needed; but imposing false and fabricated common history and heritage!

Comments are closed.

Share