ዛሬ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ተፈታታኝና ወጣሪ ሁኔታ ኢ.ሕ.አ.ፓን መተንኮስ ለምን አስፈለገ? (ፍየል ወዲህ፣ ቅዝምዝም ወዲያ!)

ታምሩ ባልቻ

 

ኢትዮጵያ ሕዝብ ልጆቹ እየተፈጁበትም አዳዲስ ትውልድ መተካቱን አያቆምም። ዛሬ በሀገራችን ዉስጥ እያደገ፣ እያወቀና እየጎመራም በመምጣት ላይ ያለው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ስለ ቀዳሚው ትውልድ፣ መጥፎውንም ሆነ ጥሩውን ታሪኩን ማወቁ የማይቀር ነው። ኢ.ሕ.አ.ፓን ጭምር ስላካተተው ትውልድ፣ በተለይም የትውልዱ ፈርጦች ከነበሩት፣ ከኢ.ሕ.አ.ፓ አባላት የሀገራዊ ለውጥና ዕድገት ራዕይ፣ እምነትና ገድሎች ትክክለኛውን ነገር አዲሱ ትውልድ ማወቅ ይገባዋል:: ኢትዮጵያችን እንደ ሀገር፣ ኢትዮጵያውያንም እንደ ሕዝብ ላባዕዳን ተገዥም ተንበርካኪም አልነበሩም። የአድዋ ድል ባለቤቶችንና ወራሾቻቸውን ያፈራች ሀገር ነች። እነራስ አሉላ አባ ነጋን፣ አፄ ቴዎድሮስንም ያፈራች ሀገር ነች። በርካታዎቹ የኢህ አፓ አባላትም የነዚያን ጀግኖቻችንን በጎ ዓርአያ የተከተሉ አናብስት ነበሩና ኢትዮጵያን የሚጠሉ ሁሉ ክፉኛ ነው እነሱንም የጠሏቸው!? ዛሬ ባዕዳን ሃይሎች ሌላ በራሱና በማንነቱ የሚኮራ፣ እነሱንም “ዞር በሉ የሀገሬ ባለቤት እኔው ነኝ” የሚላቸው ሃይል፣ እንዲበቅል ይሻሉ ማለት ዘበት ነው። የሚዳፈራቸው የጥቁር ሀገር መሪና ትውልድም መቼም በየትም፣ ግድ ካልሆነባቸው በስተቀር፣ ማየት አይፈልጉምና!! የጥቁር ሕዝብ፣ የአፍሪካ፣ የኢትዮጵያችንም ታሪክ በደም ጎርፍ የረሰረሰ ነው። አዲሱ ትውልድ ከኢሕ አፓ ስህተቶችም ሆነ አኩሪ ገድሎች፣ ራሱ መርምሮና አበጥሮ እንዳያውቅ፣ በተለይም በጎውን ጎኑን እንዳይወስድ ሙሉ ታሪኩን ጠለሸት በማልበስ ለማዳፈን የሚሞከረው። ማናቸውም ባዕዳኑ፣ ወይም ሀገር-ጠል የሀገሪቱ ተወላጆች፣በአጋፋሪዎች መሣሪያነት በኢሕ አፓ ጀግኖች ገድል ላይ የረጩትን በካይ አሉባልታ ማምከን፣ ያወረዱትን ጭጋግ መግፈፍ ያስፈልጋልና በመጀመሪያ ስለ ኢሕ አፓ (የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ) አባላትና “ስለዚያ ትውልድ” ከፊሉ፣ ለየት ያለ ታሪክ ስላላቸው ስለጠባቦቹ ሳይሆን፣ ስለአብዮታውያኑና ሀገር-ወዳዶቹ፣ በመጠኑ የምንለው አለን።

በታተሙ አያሌ መጻሕፍት፣ በምንባቦችና በቃል ትረካዎችም “ያ ትውልድ” በመባል የሚታወቀው፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1960ዎቹ እስከ 1980ዎቹ ዓ.ም. ድረስ በነበረው ወቅት ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ አዲስ-አበባ ዩኒቨርስቲና በሁሉም የሀገሪቱ ኮሌጆች ዉስጥ እንዲሁም በውጭ ሀገሮች ለከፍተኛ ትምህርት ተልከው ከነበሩት አብዛኛዎችን፣ በወጣትነት የዕድሜ ክልል የነበሩትን ምሁራንና የመንግሥት ሠራተኞችን፣ በአገልግሎትና በየፋብሪካዎችም ሠራተኞች ከነበሩት ሰፋ ያለውን ክፍል ያካተተ ስለሆነም በወቅቱ ከነበረው ወጣት ትውልድ በርከት ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል የያዘ ነበር። በየትምህርት ተቋማት ዉስጥ እየተማሩ የነበሩትን በስፋት ያሳተፈ፣ በሥራ ላይ ተሰማርተው ከነበሩት ደግሞ ለመሠረታዊ ለውጥ የቆሙትን የማይናቅ ቁጥር የያዘና በትግሉ ያሳተፈ፣ ሠፊ የኅብረተሰቡ ክፍል ስለነበር በዉስጡም ልዩ ልዩ ሃሳቦችን ያነገቡ ክፍሎች ነበሩ። ከዚህ ለለውጥ የተነሳሳ ሠፊ ትውልድ ዉስጥ ነው፣ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰባዊና ባህላዊ ለውጥ ለማምጣት ከሚፈልገው ክፍል የፖለቲካ ንቃታቸው ላቅ ያለው ቀዳሚነቱን የያዙት በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ዉስጥ ተደራጅተው መንቀሳቀስ የጀመሩት። ከእነዚህ መሐል ጎልተው የወጡት ሁለት ማርክሳዊ የነበሩ ድርጅቶች፣ ኢሕ አፓና መ ኢሶን ነበሩ። አሁን በዚህ አጭር መጣጥፍ የምንናገረው የኢትዮጵያ ግልጽና ስውር ጠላቶች በጣም ስላተኮሩበት፣ ከሁለቱ አንዱ ስለሆነው፣ ስለኢሕ አፓ ነው። በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ የተፈጠሩ፣ በቋንቋ፣ በዘር፣ በሃይማኖት ወይንም በጾታ ልዩነቶቻቸው ላይ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው፣ በሀገርአፍቃሪነታቸው፣ በለውጥ ፈላጊነታቸው፣ ለእኩልነት፣ ለማኅበራዊ ፍትኅና ለሁለንታዊ ለውጥና ዕድገት ባላቸው ራዕይ ላይ በመመሥረት፣ ነበር አብዛኛዎቹ ተፈላልገው በመገናኘት፣ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (....) ዉስጥ የተደራጁት። በርካታዎቹ በቅድመ-ፓርቲ ምሥረታ በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና በትምህርት ተቋማቱ  ዉስጥ የመተዋወቅ እድልም ነበራቸው። በወቅቱ በሀገራችን ዉስጥ የነበረውን የጉልተኛ ሥርዐት ለመለወጥና፣ በተለይም ለሠርቶ-አደሮችና ለሠፊው ጭቁን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚበጅ ሥርዓት ለመፍጠር፣ … አስበው፣ ዐልመው፣ ቆርጠው ተነስተው አምርረው ታግለዋል፣ እጅግ ከባድ መሥዋዕት ከፍለዋል። የእነሱን ትግልና ሁኔታዎች መገምገም የሚገባው ታዲያ ያኔ በነበረው የኢትዮጵያ፣ የአካባቢያችንና የአፍሪካ፣ ከዚያም ሰፋ ያለውን የዚያን ጊዜውን የዓለም ሁኔታ ጭምር በማገናዘብ ሊሆን ይገባል። የእነዚያን አብዮታውያን ተግባሮች ለመተቸት ደግሞ ቢያንስ ተችው ኢትዮጵያዊ ሰብእና ያለው፣ ራሱ በዚያን ወቅት ቀይ ደምም ሆነ ቀይ እምባ ያላስፈሰሰ፣ ቀናና ሚዛናዊም አስተሳሰብ፣ ማለትም የሞራል ብቃት ሊኖረው ይገባል እንላለን።

እንደ ዕውነቱ ከሆነ በወቅቱ ኢሕ አፓ  የታገለው ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩትን ጉልተኞችንና ሥርዓታቸን ብቻም አልነበረም። እነሱን ያግዙ የነበሩትን የውጭ ሃይሎችንም ጭምር ነበር። አንዳንዶቹ ወገኖቻችን፣ ተታለውና መስሏቸው፣ ወይንም ዐምነው አለዚያም በጥቅም ተገዝተው፣ ይታዘዟቸውና ያገለግሏቸው የነበሩትን፣ አሜሪካንና ሌሎችንም የምዕራብ ኢምፔሪያሊስቶችም ኢትዮጵያ ላይ የነበራቸውን ጫና ጭምር በመቃወም ነበር ያያኔው ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊና ሀገር-ወዳድ ትውልድ፣ የኢሕ አፓም አባላት ጭምር የታግሏቸው። ኢሕ አፓ በዚያን ጊዜ “የሶቭየት ኅብረት” ይባል የነበረውንም “ሶሽያል ኢምፔሪአሊስት” አዝማሚያዎች ስለነበሩት፣ በእሱ ይመራ የነበረውን ጎራም፣ በምዕራባውያኑ ምትክ ኢትዮጵያ ላይ ጫናውን እንዳይፈጥር ይፈልግ ስለነበር ራሱን ከእነሱም “ወዳጅነት” እየተከላከለ ነበር የሚጓዘው። በቻይናና መሰሎቿ ጭፍን ቀኖናዊ አስተሳሰብ ስር ሳይወድቅ፣ ሆኖም ግን ግንኙነቶችን ከአብዛኛዎቹ ሶሽያሊስት ሃይሎች ጋር ፈጥሮ ነበር ኢ ሕ አፓ ይጓዝ የነበረው። በኢትዮጵያውያን የራስን ነፃነትና ክብርን የመጠበቅ እሴት ትልቅ ዕምነት፣ የነበረውና ዛሬም ያለውም ድርጅት ነው። ራሱ ትክክል ነው ብሎ በሚያምንበት አስተሳሰብና አተረጓጎም፣ በማርክሲዝም ሌኒንዝም  ርዕዮት፣ እየተመራ ለማንም ሳያጎበድድ፣ የማንም ታዛዥና ሎሌ ሳይሆን ነበር ኢሕ አፓ ይታገል የነበረው። ከሁሉም የውጭ መንግሥታት ጋር፣ ከዋናዎቹ ኢምፔሪያሊስቶቹ መንግሥታት በስተቀር፣ በየሀገሩ ከነበሩ በርእዮተዐለም ከሚቀራረባቸው የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግንኙነቶች ነበሩት። ሠፊ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ ስለነበረው፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ኤምባሲዎች ያሏቸው መንግሥታት ደግሞ፣ ይህንንም ያውቁ ነበርና ኢሕ አፓ የመንግሥት ሥልጣን ሊጨብጥ ይችላል ከሚል ግምታቸው አኳያ የውጭ መንግሥታትን ለመገናናኘትም ችግር አልነበረውም። ከውጭ መንግሥታት ጋር ሲገናኝ ደግሞ አምባገነኑን ደርግ ማስፈቀድ አያስፈልገውም ነበር!

ኢ.ሕ.አ.ፓ. ያለምንም ጥርጥር የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ የነበረው፣ በመላ ሀገሪትዋም ቅርንጫፎች የነበሩት፣ ኅብረብሔር ፓርቲ ስለነበረ፣ በዚያን ጊዜ ስለነበረችውና ስለወደፊትዋ ኢትዮጵያ የሚያስብና የሚጨነቅም ፓርቲ ነበር። በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት ላይ ከማንም ባዕድ ጋር፣ ወይንም ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተቋቋመ የብሔር/ብሔረሰብ ነፃ-አውጭ ነኝ ከሚል ድርጅት ጋር፣ ያልተደራደረና ያልተጎናበሰም፣ ለመላው ሕዝብ የጋራ መብት፣ ለእኩልነቱም ጭምር እንዲሁም ለሀገሪቱ አንድነት ሉዓላዊነት ክብርና ጥቅም የቆመና የተፋለመም  ፓርቲ ነው።   ስለኢሕአፓ ትክክለኛ አቋሞችና በወቅቱ በርካታ መስዋዕት የከፈለባቸው አኩሪ ተግባሮች ለአዲሱ ትውልድ ይረዳ ዘንድ አንዳንድ ሃቆችን ከዚህ በታች በማሳያነት እንጠቅሳለን።

አንጎላቸውን በወታደራዊ ጡንጫቸው የቀየሩት የደርግ አባላትም (መኮንኖችና ባለሌላ ማዕረጎች)፣ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያንን ሁሉ ጥፋት አድርሰው እስከዛሬ ይዋሻሉ፣ ዛሬም ወጣት አብዮታውያኑን አድነው እየጨፈጨፉ “የፍየል ወጠጤ ….. “ የሚል ሞት-አርጂ መዝሙራቸውን እያዘመሩ የሚፎክሩም፣ የሚያቅራሩም ይመስላሉ። የተወሰኑት ደግሞ፣ ለውጥና ዕድገት ታሪካዊ ክስተቶች መሆናቸውን፣ አዲስ ትውልድ አዳዲስም የተለመዱም ጥያቄዎችን ሊያነሳም እንደሚችል ካለማወቅ፣ ያ ትውልድ፣ በተለይም እንደ ኢሕ አፓ ዐይነት የፖለቲካ ድርጅቶች “ለለውጥ ባይነሳሱ ኖሮ …” ብለው የሚያስቡ፣ ከኋላቀርነት በመንደርደር ለውጥ በአንዱ ወይንም በሌላው መልክ እንደሚመጣ ካለመረዳት፣ ከዐዕምሮ እንጭጭነት፣ ሊሆን ይችላል። ከፊሉ ደግሞ ከርእዮተ ዓላማዊ ባላንጣነት፣ወይንም ከተንበርካኪነትና የባዕዳን “ኒዎ-ሊበራል” አስተሳሰብን “ያመነ ይድናል” ብለው፣ ሃሳቡ አዲስና ዕውነት መስሏቸው፣ ፈቅደው የኢምፔሪአሊስቶቹ  አገልጋይ የሆኑ ወገኖችም አሉ። ሁሉም ደግሞ እንደ ውዳሴ የሚያዜሙት፣ “የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት፣ እስከመገንጠል” የሚለውን ሀረግ ያመጣው፣ ያቀነቀነው፣ ያስለመደው፣ ወ.ዘ.ተረፍ ኢ ሕ አ ፓ ነው እያሉ ነው። ይህ ቀመራቸው ግን ሙሉ በሙሉ ሃሰት ነው። ዓላዋቂዎች ወይንም ዋሾዎች ናቸው ማለት ነው። ሀረጉ ኢሕአፓ ከመመስረቱ (1964 ዓ.ም.) በፊት ሀገራችን ዉስጥ ገብቶ ነበር።  ኤርትራን ለመገንጠል የተነሱት “የነፃነት-ግንባሮች” ኢሕ አፓ ከመመሥረቱ በፊት ነበር ተደራጅተው የትጥቅ ትግል የጀመሩት። ኦጋዴን ውስጥ በክተል ጣሂር ይመራ የነበረው እንቅስቃሴም ከኢሕአፓ ምሥረታ በፊት ነበር የተነሳው።ግልጥ ባለ በብሔረሰብ ነጻ-አውጭ ስም ባይሆንም ጸረ ብሄር ጭቆና እንቅስቃሴ በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን “በሜጫና ቱለማ የባህልና የልማት ማኅበር” ስያሜ ይደረግ የነበረው ኢሕ አፓ ከመመሥረቱ በፊት ጀምሮ ነበር። በኋላም በዋቆ ጎቶ ይመራ የነበረው የባሌ እንቅስቃሴ ከኢሕአፓ ምሥረታ በፊት የነበረ ነው።

በርግጥም ኢሕ አፓ በተደራጀበት ጊዜ በማርክሲስት-ሌኒኒስት አስተሳሰብ ይመራ ስለነበር፣ በዚያን ጊዜዋ ኢትዮጵያም ዉስጥ የብሔር ጭቆና አለ ብሎም ያምን ስለነበር፣ በርግጥም “የብሄር ብሄረሰብን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን፣ እስከ መገንጠል” ያለ መብት፣ በመርኅ ደረጃ ኢሕአፓ ተቀብሎት ነበር። አንደኛ ለብሔር ጭቆናው ሃላፊነቱን ያስቀመጠው “የመሳፍንት ወይም ፊዩዳል ገዥ መደቡ” ላይ ነበር፤ አንድ ብሔር ላይ ብቻ አይደለም። ሁለተኛ ሃሳቡን ያቀነቀነው በመርህ ደረጃ እንጂ በተግባር ከኢትዮጵያ የመገንጠልን ጥያቄ ለማንም ድርጅት ወይም ሃይል ወይም መንግሥት፣ ምንም ጊዜ አልደገፈም፣ አልተቀበለም። ኢሕ አፓ ምንም እንኳን የብሔር ጭቆናን ማወቅና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን ማወቅ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እንደሚያቀራርብና በመሀከላቸውም መተማመንን እንደሚፈጥር ቢያውቅም፣ መብቱን ካወቀ በኋላ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። በዚያው መጠን ኅብረ-ብሔራዊ ድርጅቶች ተጠናክረው በመታገል በሀገሪቱ ዉስጥ መላው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቱንና እኩልነቱን እንዲቀዳጅ ለማድረግ ከታገሉና፣ ሕዝቡም መብቱን ከተቀዳጀ የመገንጠሉ ጥያቄ አቀንቃኞችን የሚደግፍበት ምክንያት አይኖረውም። ሕዝቡ ጭቆናው አለ ብሎ ስለሚያምን፣ የለም አልተጨቆንክም ማለቱ ትክክልም ተገቢም አልነበረም። ለነገሩ እስከዛሬም ምንም ጭቆና አልነበረም የሚሉም አሉ። በርካታው ሕዝብ ጭቆና መኖሩን ዕውነትም ስለሆነ አምነህ አብረን በጋራ ትግል እናጥፋው ስትለው ድጋፉን ይሰጥሃል፣ ወደ ተገንጣዮች ሊሄድ የሚችለው ድጋፍም እየቀነሰ ይመጣና ጥያቄውም፣ የዴሞክራሲያው መብት መረጋገጥ፣ የእኩልነት፣ የፍትኅ ይሆናል።  የተገንጣዮች አስተሳሰብና ጎራም እየተዳከመ በመምጣት እንደሚመክንም ኢ.ሕ.አ.ፓ. አጥብቆ ያምን ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የገንዘባችን ዋጋ ስንት ነው?

በረጅም ታሪኩ ዉስጥ እርስ-በርሱ እየተዋሀደና እየተጋመደ የመጣውን የኢትዮጵያ  ሕዝብ አስተባብሮ፣ አደራጅቶ በማታገል የሀገሩ፣ የእኩልነቱና የሌሎችም መብቶቹ፣ የነፃነቱ፣ የክብሩ፣ የጥቅሞቹም ሙሉ ባለቤት ማድረግ ነበር ዋናው የ ኢሕአፓ ዓላማ። የመገንጠል ሃሳብ ያቀነቅኑ የነበሩት ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ድርጅቶች እንዲሁም እነሱን ይደግፉና ይረዱም የነበሩ የውጭ መንግሥታት ከደርግ የበለጠ የፈሩትና የታገሉትም፣ የሁሉንም ብሄረሰቦች ድጋፍ እያገኘ የመጣውን፣ ኢሕአፓን ነበር። የየብሔረሰቡን አካባቢ “እየከለሉ”፣ ሕዝቡንም በየብሄሩ ነጣጥለው ሊይዙት የሚፈልጉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ያቆጠቆጡ ራሳቸውን “የየብሔረሰቡ ነፃ-አውጭ” ያደረጉ ቡድኖች፣ ሁሉም ማለት በሚያስችል ደረጃ፣ ኢሕአፓን እንደ ተቀናቃኝ ብቻ ሳይሆን እንደ ጠላት ነበር ያዩት። እነሱ ኢትዮጵያዊነቱን አስጥለው ሌላ ሊያደርጉት የሚፈልጉት ሕዝብ፣ በሁሉም ብሄረሰቦች ዙሪያ ግን ኢሕአፓ ጥሩ ወዳጅነትና ፍቅር ተችሮት ስለነበር፣ ጠባብ ብሔረተኞቹና ተገንጣዮች ሊገነቡት ያሰቡትን ግድግዳ እየናደባቸው ስለነበር ነው። ሕዝቡን በመቅረብ፣ በማሳመን፣ ከውስጡም አባላቱን በመመልመል፣ በማደራጀት፣ የወደፊትዋን በሕዝቡ እኩልነት ላይ የተመሠረተች ኢትዮጵያ በኅብረ-ብሄራዊ ድርጅቶችና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ አውድ አማካይነት መፍጠር ስለጀመረ ነበር የጠባብ ብሔረተኞች ጠላት ተደርጎ የታየው። እዚህ ላይ መጠቀስ ያለበት ጉዳይ፣ ያኔ እንደ አሁኑ በህ.ወ.ሓትና በሻዓቢያ ሆን ተብሎ በተፈጠረ ጸረ-ኢትዮጵያ አረንቋና ዝብርቅርቅ ያለ ሁኔታ ሳይፈጠር፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኅብረ-ብሄራዊ ኅላዌ፣ የሕዝቡ አንድነት፣ የሀገር አንድነት ጉልህ ዕውነታዎች እንጂ አዲስም አስቸጋሪ ነገሮች አልነበሩም፣ የአብሮነት ታሪካችን ጥሩ ምርቶችም ስለሆኑ!!

ደርግ የተባለ ወታደራዊ ቡድን፣ በኢትዮጵያ አብዮታውያን ከተነሱት መፈክሮች ጥቂቱን ቀምቶ መጠቀሚያው ለማድረግ እየሞከረ፣ አብዮታውያኑን ራሳቸውን ግን ያለ አንዳች ርኅራሄ እየጨፈጨፈ፣ ኢትዮጵያን ለዛሬው ሁኔታ አበቃት። ከአብዮታውያኑ ዋና ዋና ጥያቄዎች፣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን መከበር ጭምር፣ ተቀብሎ ቢሆን ኖሮ ሀገራችን ዛሬ ለምናየው የአጥፊዎች መለማመጃም አትሆንም ነበር። ሀገራችን ዉስጥ የተካሄደውን ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ አብዮት ደርግ በእመቃ፣ ግድያና ጭፍጨፋ ነው ያሰናከለው። ከህዝቡ መሠረታዊ ጥያቄዎች መሀል አንገብጋቢ የነበረውን መሬትን ለአራሾች አከፋፍሎ ሲያበቃ፣ ሕዝቡ የጠየቀውን የዴሞክራሲ፣ የእኩልነት፣ የፍትኅ፣ ጥያቄዎች ግን ባለመመለስ፣ የሥልጣን አባዜ ይዞት፣ አተብቶትና አቅበዝብዞት፣ አምባገነናዊ ሥርዓቱን በመላው ሕዝብ ላይ ጫነ። አፈና፣ ድብደባ፣ እስራት፣ ሰቆቃ፣ ጅምላ-ጭፍጨፋ መብት በጠየቁ ወጣት አብዮታውያኑ ላይ ለዐመታት “ቀይ ሽብር” ብሎ የሰየመውን መተራ በማካሄድ፣ ሀገሪቱን ለውድመት፣ ለትዝብትና ለውግዘትም አበቃት። ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አብዮትም በጸረ-አብዮታዊ ዘግናኝ ግብሮች አስጨነገፈው!! እነዚህ ነፍሰ-ገዳዮችና ሰው-በላዎች፣ አንድ ትውልድ፣ ያውም የወገንና የሀገር ፍቅር ያንደገደገው አብዮታዊ ትውልድ፣ መተሩ። አንዳንድ የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣኖች፣ ያኔ የሠሩት ግፍ እያባነናቸው ይመስላል ወደር-በሌላቸው የኢትዮጵያ ብርቅ ልጆች ላይ፣ በአርበኞችና ጀግኖች ላይ ይኸው ዛሬም፣ ያኔ ትውልዱን በሙሉ ገድለው ስላልጨረሱ ተቆጭተው የሚቀባጥሩ በሚያስመስል ደረጃ፣ እየታገሉ ባሉት፣ የኢሕ አፓ አባላት ላይ፣ የሀሰት ክሶችን ይደረድራሉ። ያውም ከደርግ የከፋ፣ ኢትዮጵያውያኑን ርስብርስ አጋጭቶአንደኛውን ብሄረሰብ በሌላው ላይ አነሳስቶና አስታጥቆም፣ አንዳንዴም ራሱ አንዱን መስሎ ሌላውን በመውጋት፣ እያጫ ያለናያለምንም ርህራሄ የሚቃወሙትን ሁሉ በሚያዛቸው የፀጥታና የታጠቀ ሃይሎች ሊጨፈጭፍ በዝግጅት ላይ ያለ፣ የሀገሪቱን አንድነትና ኅላዌም የቻለውን ያህል እያጠፋ ያለ አምባገነናዊ እኩይ የዘውግ ቡድንየኢትዮጵያችን ገዥም አጥፊም ሆኖ በሚገኝበት ወቅትና ሁኔታ፣..  የደርግ ነፍሰ-ገዳዮች ርስ-በርሳቸው ከሚቀባበሉት የሃሰት ክስ ውጭ አንድም ማስረጃ ሳያቀርቡ፣ ማስረጃ የለምና ከየትም ሊያመጡ አይችሉም፣ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ደጋግመው ይተነኩሱናል። በተለይ መልካም ተግባርና ጥሩ ገጽታዎች እየራቁት እመጣው፣ አሜሪካ ጉያ የተወሸቁት አንዳንድ አወዛጋቢ ሰብዕና ያላቸው ግለሰቦች መዘባረቃቸውን አቁመው አርፈው መቀመጡ ይሻላቸው ነበር። በሀገር-ወዳድነት ሌላውን ሊከሱ ይዳዳቸዋል። “የአባዬን እከክ በማዬ ልክክ” ይሏል ይህ ነው። ልትደብቁት የማትችሉትን ነውራችሁን ማዝረክረክ ከባድ አይሆንም።  አሁን በጣር ላይ ያለውን፣ ህ.ወ.ሓ.ትን ለማገዝ፣ በነዚያ “ኢትዮጵያን ቢያጠፋ ምን ቸገረን፣ ለእኛ የጸረ-ሽብር ትግል መሣሪያችን ሆኖ እስከተላላከንና እስካገገለን ድረስ ድረስ” የሚሉትን ዛሬም በድጋሚ የነሱኑ ተልዕኮ ተቀብላችሁ ይሆን?! የአሁኑ ወቅት ያለጥርጥር፣ ሁሉም  ሀገር ወዳድ ተባብሮና ተከባብሮም ዋናውን የጥፋት ሃይል ለመታገል ቅድሚያውን መስጫው ወቅት ነው። በተለይም ደግሞ ሤረኛ፣ ጎሠኛና በርግጥም ፀረ-ሠላም፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ህዝብዋም የሆነውን የህወሓትን ገዳይ ቡድን በመታገል ላይ መረባረብን ነውና ወቅቱ የሚጠይቀው። ታዲያ በጥባጭ ካሉ ጥሩ ወሀ አይጠጣም እንደሚባለው፣ አንዳንድ ወቅትና ሁኔታን ማገናዘብ የተሳናቸው፣ ወይንም ሌላ ዓላማ ያላቸው ተንኳሾችና ነውረኛ ግለሰቦች በትግል ሜዳ በወደቁ  ጀግኖችና ሀገር-ወዳድ የኢሕአፓ አባላት ላይ የውሸት ክምር በዚቹ በአሁንዋ ወቅት ስለቆለሉ፣ ዕውነቱን፣ የነበረውን ሁኔታ፣ የጀግኖችን ገድል በከፊልም ቢሆን፣ ይፋ አውጥቶ በመናገር ይህንን የተነዛውን ሃሰት ባዶነት ማሳየት የኛ በሕይወት ያለነው ጓዶቻቸው የሞራልና የፖለቲካም ሃላፊነት ስለሆነ፤ የነዙትን የውሸት ትቢያ ዕውነተኛውን የኢሕአፓን የያኔ ጊዜውን አኩሪ ታሪክ፣ በመጠኑም ቢሆን በማሳወቅ፣ የከንቱዎችን የማጠልሸት ግባቸውን ማምከን ግድ ሆኖብን ነው።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ሲፈጠርለት ሁሉንም በየስራው እየመረመረ ሊዳኘው ይችላላ፤ ወቅቱም እየቀረበ እንጂ እየራቀ በመምጣት ላይ አይደለም። አሁን ሁላችንም ወገናችንን እንወዳለን፣ የተወለድንባትንም ሀገር ባንወዳት እንኳን አንጠላትም ካልን፣ እስቲ ርስ-በርስ መቋሰሉን ለጊዜው ተወት አድርገን፣ ሀገርንና ሕዝብን እያጠፋ ያለውን፣ ህ.ወ.ሓ.ትን፣ የወቅቱን ዋና ጠላት እንደየችሎታችን  እንታገል። የደርግ ባለሥልጣናት የነበራችሁና ኢ.ሕ.አ.ፓን፣ አላጠፋችሁትም፣ ምን ጊዜም አታጠፉትም፣ ታዲያ ይብቃችሁ፣ ተወት አድርጉን። “ጥፋት እስከ መቃብር” ቢያስነውር እንጂ አያኮራም። አንድ ጀግና ትውልድ፣ ያውም ሀገሩንና ወገኑን አጥብቆ የሚወድ፣ ትውልድ መትራችሁ ሀገሪቱን ባዶዋን አስቀራችኋት። ጀግኖችን በመግደል፣ ሀገሪቱን የሀገር-ወዳዶችና የጀግኖች ደሀ አደረጋችኋት። የዛሬዎችን፣ ሀገር አጥፊዎች፣ የተፈጠሩባትን ውድ ሀገራችንን ለማጥፋት ሳይታክቱ እየተውተረተሩ ያሉትን፣ የህ.ወ.ሓት ባንዳዎችንና፣ አጃቢዎቻቸውን፣ አምርሮ እየታገለ፣ ከፍተኛ መስዋዕት እየከፈለም እየተዋደቀ ያለውን የዛሬ ወጣት ትውልድ፣ ስለ ኢሕአፓ እናንተ የምትዋሹትን ሳይሆን ትክክለኛውን ታሪክ፣ ሃቁን እንዲረዳ ከመፈለግ ብቻ በመነሳት፣ (ሆን ብለው የሚዋሹትን ለማሳመን ሳይሆን)፣ ከኢሕአፓ ዕምነቶችና አቋሞች፣ ፈተናዎችና ገድሎች አንዳንድ ምሣሌዎችን እናንሳ።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ) ከኤርትራ ግንባሮች፣ ከሁለቱም ዋና ዋናዎቹ ጋር፣ ግንኙነችና ዉሱን ትብብሮች ቢያደርግም፣ ምንም ጊዜ ከማንኛቸውም ጋር፣ ሀ) “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነበረች” የሚለውን ጥያቄያቸውን ኢሕአፓ እንደ ድርጅት ተቀብሎት አያውቅም፣ ለ) የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ ተግባራዊነት (ከንድፈሃሳብ ውጭ) አልደገፈም፣ ሐ) በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1982 ዓ.ም. ጀምሮ የኤርትራ ጥያቄ በኢትዮጵያ ዉስጥ በፌዴራላዊ ሥርዓት ምሥረታና በአንዲት ኢትዮጵያ ማዕቀፍ ሊፈታ ይችላል የሚል ይፋዊ አቋም ሲያራምድ ቆይቷል፣ መ) ኤርትራ በሀገር በቀል አስገንጣዮች፣ በባዕዳን አጋፋሪነት፣ ባዕዳኑን በሚታዘዙ መሣሪያነት፣ ነፃነትዋን ካወጀችም በኋላ ኢሕአፓ እስከዛሬ ያንን ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ በሌለበት የተደረገ “ሬፈረንደም”ና ውጤቱን ዕውቅና አልሰጠም። ሁለቱም የኤርትራ ግንባሮች በተለያዩ ወቅቶች ካደረጉለት ትብብሮች የገዘፉ አያሌ መሠናክሎችንም በተለያዩ ወቅቶች ደቅነውበታል፣ ጉዳቶችንም አድርሰውበታል። ደርግ እየተሸነፈም እያለ ኢህአፓን ከመዋጋት ተቆጥቦ አያውቅም ነበር። በ 1983-84 ዓ.ም. በህ.ወ.ሓ.ት.፣ በሱዳን መንግሥትና በህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሻዓቢያ) የተጣመረ ሃይል ነው ኢሕአፓ/ኢሕ አሠ ጎጃምና ደቡብ-ምዕራብ ጎንደር ዉስጥ በተደረጉ በርካታ፣ ከባድ ጦርነቶች ተዋግቶና ከባድ መስዋዕት ከፍሎ ነው በመጨረሻ በጥምረቱ ሃይል የተሸንፈው?! ደርግ ፈራርሶ፣ መሪዎቹ ሀገር ጥለው ከሸሹም በኋላ ኢሕአፓ ከህ.ወ.ሓ.ትና ተባባሪዎችዋ ጋር ይዋጋ ነበር። ሃቁ ይሄ ነው።

ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር፣ በኋላ ህዝባዊ ወያናይ ሓርነት ትግራይ ከተባለው፣ አሁን ኢትዮጵያን እየገዛ፣ እየመዘበረና እያጠፋትም ካለው ግንባር ጋር፣ ኢሕአፓ የነበረው ግንኙነት በአመዛኙ የጠላትነት ግንኙነት ነው። ከህ.ወ.ሓ.ት ምሥረታ ቀደም ብሎ ኢህአሠ ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሠራዊት ትግራይ ዉስጥ፣ አሲምባ ላይ መሽጎ ነበር። ስለሆነም ሁለቱም ድርጅቶች ትግራይ ዉስጥ ይንቀሳቀሱ ከነበሩበት ወቅት ጀምሮ በመሐከላቸው የነበሩት ግንኙነቶች፣ በውጥረት፣ በጠብ፣ በግጭቶችና በጦርነቶች ይገለጡ የነበሩ ናቸው። ኢሕአፓ/ሠ በሠላማዊ መንገድ ችግሮቹን ለመፍታት ቢጥርም ጠባብ-ብሔረተኛው ህ.ወ.ሓ.ት. ግን፣ ኢሕአፓ ለማምጣት የሚፈልጋት ትልቅነትዋን የጠበቀች፣ እኩልነትና ፍትኅ (ማኅበራዊ ፍትኅ ጭምር) የሰፈንባት፣ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ስለማይዋጥለት፣ በእነሱ በኩል በሚስፋፋ ጥላቻ፣ በእነሱ በሚደረግ ትንኮሳ፣ በኋላም በእነሱና ምናልባትም በሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሻዓቢያ) ትብብር በተከፈተ የኢሕአፓን ሠራዊት፣ ኢሕአሠን፣ ከትግራይ የማስወጣት ጦርነት፣ ከዚያም በኋላ ከወልቃይትና ጠገዴ ጀምሮ እስከ እስከ አርማጮሆ፣ ጭልጋና ጎጃም ከኢሕአፓ/ኢሕአሠጋር ለአያሌ ዓመታት የቀጠሉ፣ ብዙ ሕይወቶችንም የቀጠፉ ጦርነቶች ተካሂደዋል። ኢሕአፓ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት በመቆሙም ነበር ይህንን ዕምነቱን በነሱ ታጋዮች ዘንድ ለማስጠላት፣ ኢሕአፓን “ዓብይ ኢትዮጵያ” ወይንም “የትልቂቱ ኢትዮጵያ አቀንቃኝ” እያሉ ነበር የሚጠሩት። የጥላቻቸውም ዋና መሠረት ይሄው ትልቅነትዋ ለተጠበቀ ሆኖም ዴሞክራሲያዊት፣ ዜጎች በኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለማምጣት የሚታገል መሆኑ ነው። ይህ እንዴት ይዋጥላቸዋል!?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውድ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች "እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል አደረሳችሁ!" ጌታቸው ወልዩ (ከሜክሲኮ ባህረ-ሰላጤ)

ከሶማሌ ሕዝብ፣ ሶማሊያ ዉስጥ ካሉ የፖለቲካ ሃይሎችና በየጊዜው ከሚመጡ መንግሥቶች ጋር፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ሁሌም ግንኙነቶች ሊኖረን ይገባል። በኢትዮጵያ ሕዝብና በሶማሌ ህዝብ መሀል ደግሞ በተቻለ መጠን ሁሌም ጥሩ ግንኑነት መኖሩ አስፈላጊ ነው። ኢሕአፓ የሶማሌ መንግሥትን ማንነት ያውቅ ስለነበረ፣ ከሶማሌ መንግሥት ጋር የነበረው ግንኙነት በዝቅተኛ ደርጃና በጥንቃቄ ይደረግ የነበረ ነው። ደርግን የመሰለ መቅሰፍት እየታገለም ስለነበር መሸሺያም ያስፈልገው ነበርና!! የእንግሊዞች የቅኝ ግዛት የነበረው ሰሜኑ ሶማሊያና በጣሊያኖች ተይዞ የነበረው ደቡቡ ነፃ ወጥተው ከመዋሃዳቸው ከ1960 (እንደ ግሪጎሪያን ዐመት አቆጣጠር) በፊት በመርዘኞች የእንግሊዝ ቅኝ ገዝዎች ሥር የተቋቋመና የሚበረታታም “ሶማሌ ዮዝ ሊግ” የሚባል ድርጅት አርማውን፣ “ሶማሌ ለዘላለም ትኑር” ከሚል መፈክሩ ጋር ኢትዮጵያ ጅጅጋ ዉስጥ ጭምር እንዲሰቅል አድርገውት ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ የጣሊያን ፋሽስት ወራሪ ጦር ከኢትዮጵያ ሲባረር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የነበረው የእንግልዝ ጦር በኢትዮጵያ ቆይታው መርዙን ተክሎ ነው የወጣው። የተወሰነውን፣ ሶማሊኛ ተናጋሪዎች የነበሩበት የሀገራችን ክፍል፣ “ዘ ሃውድ” በሚል ይታወቅ የነበረውን፣ ሕጋዊ ቁመናው (ስቴቱስ) ያልለየለትና የኢትዮጵያ ወይም የሶማሊያ መሆኑ ወደፊት የሚለይ አስመስሎ አቆይቶት ነበር። ዓላማው ሁለቱ መንግሥቶች ወደፊት የሚጋጩበት መዘዝ መፍጠሩ ነበር። የነፃዪትዋ ሶማሊያ መንግሥት ከተመሠረተ ጀምሮ፣ በነሱ እምነት ሶማሊኛ ተናጋሪዎችን ሁሉ በአንድ ሀገር የመሰብሰብ ግልጽ ፍላጎትና ግብ ነበራቸው።

በ1969 ዓ.ም. (ግሪጎርያን) ሲያድ ባሬ አንድ ሶማልያዊ “ደርግ” መሥርቶ፣ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላ፣ “የምእራብ ሶማሌ ነጻ-አውጭ ግንባር” የሚባል በማቋቋም፣ ሶማልኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበትን የሀገራችንን ክፍል በጦርነት የመገንጠልና፣ የመውሰድ ዓላማውን ማራመድ ጀመረ። ታዲያ በመንግሥት ደረጃ ጦሩን ከማዝመቱ በፊት በቂ ዝግጅት አድርጎ ነበር። የሶማሌ መንግሥትና በሱም የተቋቋሙትና የሚታዘዙት ወገኖች ምን ዓላማ እንዳላቸው የኢሕአፓ መሥራች አባላትና ሌሎቹም ፍንትው አድርገውም ያውቁ ነበርና ስለሶማሌ መንግሥት ዓላማ ኢሕአፓ ሊሳሳት የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም።

በሌላ በኩል ኢሕአፓ የብሔር ጭቆና ደርሶብናል በሚሉ ማናቸውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍሎች ከጭቆና ነፃ ለመውጣት የሚያደርጉትን ትግል በመርኅ ደረጃ ይደግፍም ስለነበረ፣ የሕዝቡን ብሶት ጆሮ ሰጥቶ ለማዳመጥ ይሞክር ነበር። ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች ይደርስብናል ብለው የሚያምኑትን ጭቆና ወዲያ ማዶ የሶማሌ መንግሥት ስላለ ችግራቸውን ማዳመጥ፣ ከጭቆና የመላቀቅ መብታቸውን አለማወቅ ስህተት ነውና ኢህአፓ አያደርገውም። በየትም ጭቆና ካለ ያንን ጭቆና ተጠቂው ሕዝብ እንዲታገል ማገዝ እንጂ በሰበብ አስባቡ አይቶ እንዳላየ መሆን ተገቢም ትክክልም አይሆንም። የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነውን የሶማሌ መንግሥት የተስፋፊነት ዕምነትና ሚናን ወገናችን ከሆነው፣ ኢትዮጵያውያን/ት ሶማሌዎች ጭቆናን የመታገል መብት፣ ሁሌም ለይተን ማየት ይገባናል ብሎ ኢሕአፓ ያምናል። ኢ.ሕ.አፓ በዚያን ጊዜ ሶማሊያ ዉስጥ የነበረው መንግሥት፣ ደርግን የሚመስል፣ ወታደራዊን አምባገነናዊም እንደነበረ ፍንትው አድርጎ ያውቃል። ሆኖም ኢሕአፓ የብሔር ጭቆናን የሚመለከተው አቋሙንና ሌሎችንም የፖለቲካ አቋሞችን እንደ ገበያ ሸቀጥ አይመለከትም።

ኢሕአፓ እንደ ድርጅት ለማንም ሌላ ሃይል፣ ተንበርክኮም፣ ተገዝቶም፣ ሆነ አጎብድዶ በጭራሽ አያውቅም።  የሶማሌ መንግሥት ኢትዮጵያን የመገንጠል ተግባሮች አልደገፈም፣ አልተባበረም። ኢሕአፓ ከሌሎች የፖለቲካ ሃይሎችና መንግሥታት እንደሚገናኘው ከሶማሌዎችም ጋር ይገናኝ ነበር። ሃቁን ማወቅ ለምትፈልጉ፣ በሲያድ ባሬ መንግሥት በኩል ኢሕአፓን ለማግባባትና እዚያው ሶማሌ ውስጥ ደሊጌሽን ጋብዘው ከምእራብ ሶማሌ ነፃአውጭ ግንባርጋር ለማገናኘት የተደረገውን ጥረት፣ “የምእራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር” የተባለው ሃይል፣ በሶማሌ መንግሥት የተመሠረተና  ከአሰያየሙ ጀምሮ የሶማሌ መንግሥትን ተስፋፊነት ያዘለ ስለነበርኢሕአፓ ጥያቄውን አልተቀበለውምተገናኝቶ እንኳን ከግንባሩ ጋር አልተነጋገረምኢሕአፓ ሶማሊያ ዉስጥም በኅቡእ ነበር የሚንቀሳቀሰው።  

በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ዉስጥ፣ ኦጋዴን እየተባለ በሚጠራውና በሌሎችም አካባቢዎች ልክ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ የሶማሌ ብሔረሰብ ተወላጆችን ኢሕአፓ ይመለምልና ያደራጅም ነበር፣ አንዴም በኢትዮጵያዊነታቸው ላይ ጥርጣሬ አልነበረውም። በከፍተኛ የሀገርና የወገን ፍቅር የታገሉትን የኢሕአፓ ጀግኖች ገድል ማኮሰስ፤ አባላቱን መወንጀል፣ ያውም አንዲት ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርቡ፣ ጥሩ ዐዕምሮ ካለውና በነፃነት ከሚያስብ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አይጠበቅም።

“የወፍ ምስክሯ ድምቢጥ!” እንደሚባለው፣ አንዱ ዋሾ ደርግ የሌላውን ደርግ ቃለ ከመመላለስ ውጭ እስቲ አንድ ተጨባጭ መረጃ አምጡ። “አንዲት ትንኝ እንኳን አልገደልኩም” እንዳለው መንግሥቱ፣ ክህደት የተካናችሁበት ስለሆነ፣ የሃሰት ድርድረቻሁ ይብቃን! እናንተ አብዮታውያኑን በሀገር ዉስጥ ስትጨጭፉ እኮ የሲያድ ባሬው መንግሥት በቂ ጊዜ አግንቶ፣ ሰፍፊ ዝግጅት አድርጎ ነው ኢትዮጵያን የወረረው። ያኔ የዉስጥን ግድያና ጭፍጨፋውን በማቆም፤ የታሰሩትን በመፍታት፣ ለሁሉም ዜጎች፣ ለኢሕአፓም ጭምር፣ ሀገራዊ ጥሪ ማድረግ ነበረባችሁ!

የዚያድ ባሬ መንግስት “የምዕራብ ሶማሊያ ነፃ አውጪ ግንባር”ን (ኦጋዴን ዉስጥ) አቋቁሞ፣ የኢትዮጵያን ጦር በጉንተላ ከአዳከመ በኋላ ነበር ወረራውን የጀመረው። የፖለቲካ ሥልጣኑን ያፈቀረው ደርግ በሀገር ዉስጥ በሕዝቡ ላይ ሽብርንና ግድያን ሥራው አድርጎ የነበረበት ወቅት ነው።  የሶማሌ መንግሥት ከ1969 በፊት ጀምሮ፣ መጀመሪያ በመክተል ጣሂር ይመራ የነበረውን ኦጋዴን ዉስጥ የተነሳውን ተቃውሞ፣ በኋላም የነጄነራል ዋቆ ጎቱን ይመራ የነበረውን የባሌ ኦሮሞ እንቅስቃሴ በመደገፍ የሃይለ ሥላሴንና የደርግን መንግሥቶች የማናጋት ሥራዎቹን ሠርተዋል። በርግጥም የኦሮሞ ተወላጆች በፈለጉበት መንገድ እንዳይደራጁ፣ “ራሳቸውን ሶማሌ አቦ” ብለው እንዲሠይሙም የሶማሌ መንግሥት ያደርግ የነበረው ጫና በራሱም በሶማሌ ፖሊሲ ላይ ችግሮችን ፈጥሮበት ነበር።

ጄነራል ዋቆ ጉቱና ሌሎች የኦሮሞ ታጋዮች ለእስራትና ለእንግልት ተዳርገውም ነበር። በዚህ የተነሳም ጄኔራል ዋቆ ጎቱ ተላልከው በጄኔራል ጃካማ ኬሎ አማካይነት ከንጉሱ ምኅረት አግኝተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰውም ነበር። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርነት ግንባር በሚል ስያሜ በውጭ ሀገር ተደራጅቶ የነበረው፣ በሼህ ሁሴን ይመራ የነበረው፣ በአመዛኙ ከባሌው እንቅስቃሴ ታጋዮች መሥራችነት የተቋቋመው ከሶማሌ መንግሥት ጋር ከነበሩት አለመግባባቶች የተነሳም ነበር። ነብሳቸውን ይማርና ሼህ ሁሴን ትልቅ ኢትዮጵያዊና ሀገር-ወዳድ ሰው ነበሩ። የዚያድ ባሬ መንግሥት፣ እንደ ሌሎቹ የዐረብ ሀገር መንግሥታት ሁሉ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚፈጠሩትን ማንኛቸውም ችግሮች የራሳቸው መጠቀሚያዎች ለማድረግ ነበር የሚጥረው። ዐረቦቹ በአመዛኙ የኢትዮጵያ መንግሥት ከእስራኤል መንግሥት ጋር በነበረው ወዳጅነት የተነሳ፣ ኢትዮጵያን መጉዳት ይፈልጉ ነበር። ሁለተኛም ምን ጊዜም ለኢትዮጵያ የማትተኛዋ የግብፅ ሚና ነበር። የሶማሌ መንግሥት ደግሞ እርዳታ የሚሰጠው ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ፣ እገነጥላለሁ ለሚሉት ነበር።የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር፣ የሶማሌአቦ ግንባር፣ የሲዳማ ነፃ አውጪ ግንባር፣ የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጪ ግንባር ወዘተ.. በሱማሌ ሪፐብሊክ ውስጥ ሕጋዊ ጽሕፈት ቤቶች ነበሯችው። በዚህን ወቅት የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት የኤርትራን /ቤት በደባልነት ይጋራ ነበር። የነዚህ ተገንጣይ ድርጅቶች አባላት በመላው ሶማሊያ የመዘዋወር ነፃነታቸው የተከበረ ከመሆኑም በላይ ከአፍሪካ ውጪ ሊዘዋወሩ የሚያስችላቸው የሶማሊያ ፓስፖርት ነበራችው። እንዲያውም አንዳንድ የህወሃት መሪዎችና የኤርትራው ግንባር መሪዎች ወደ መጨረሻው አካባቢ የሶማሌ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እስከ ማግኘት ደርሰው ነበር። የሶማሌ መንግሥት ከነዚህ ግንባሮች ጋር በዕውነትም ኢትዮጵያን የማፍረስ የጋራ ስትራተጂ ነበራቸውና!!

አንድ ውስጥ አዋቂ የነበረ ግለሰብ፣ ከጻፈው ዉስጥ “በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ከሱማሌ ጎን ተሰልፈው ኢትዮጵያን የወጉ በካራማራና በኦጋዴን በርሃ የረገፉ የሻአቢያና የወያኔ አባላት ብዙዎች ናቸው ። ቆስለው በመቃድሾ ሆስፒታል ሲታከሙ የነበሩና የመዳን እድል ያገኙት በተለያዩ የአረብ አገሮች በኩል ወደ ሳሕል በርሀ (የሻዓቢያ ዋና ሠፈር) የገቡ ሲሆን በሞት ከተለዩት መካከል ገሚሶቹ የቀብራቸው ሥነ-ስርአት በመቃድሾ ከተማ ተፈጽሟል። በወያኔና በሻአቢያ ጥምር ሥራ ኢትዮጵያን አፈራርሰው የየራሳቸውን “መንግሥት” ከመሰረቱ በኋላ  በሱማሌ ምድር የተቀበሩ የሸአቢያ ተዋጊዎች አጽማቸው ተሰብስቦ ወደ ኤርትራ ተስዷል” ይላል። ትብብራቸውን ቢያውቅም በጦር ሜዳ አብረው መሰለፋቸውን ከታሪክ ዕውነታዊነት አኳያ ኢሕአፓ ራሱ የሚያውቀው ዕውነታ ስላልሆነ ይህንን ጉዳይ እንደገና ማጣራት ያስፈልጋል ብሎ ያምናል።

የኢሕአፓ አባላት የኢትዮጵያ አንድነት እንዳይሸረሸር በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች፣ ብቻ ለብቻ እንኳን ከወራሪው ጦር ጋር በግንባር ተዋድቀዋል። በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር እንደሆነው። የሶማሌን የጥፋት ዘመቻ ለማክሸፍ የዜግነት ግዳጃቸውን ሲወጡ የተሰዉ፣ የተማረኩ፣ በተለያዩ የሱማሌ እስርቤቶች ታስረው የማቀቅቁ፣ አባላቶቹ ነበሩ። አሁንም የፋሺስታዊን ደርግ ኢሕአፓን በሕዝብ ለማስጠላት ሲል ያኔ በስለላ መዋቅሩና በካድሬዎቹ በውስጣዊ መመሪያ መልክ ያሠራጨውን የቆረፈደ የማስመሰል-ክስ፣ እስከዛሬ ራሳቸው የፈጸሙት የጭፍጨፋ ወንጀል ባባነናቸው ቁጥር፣ መልሰው መላልሰው ያላዝኑታል። የሲያድ ባሬ “ስትራተጂክ ዝምድና ከኢሕአፓም” ጋር የመፍጠር ሙከራቸው ከከሸፈባቸው በኋላ፣ እንዲያውም የሶማሌ መንግሥትና “የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር” ኢሕአፓን እንደ ጠላት ቆጥረው በርካታ ጉዳቶች አድርሰውበታል። በርካታ የኢሕአፓ አባላትን አስረዋል፣ አሰቃይተዋል፣ገድለዋል። የኢሕአፓን አባላት ከደርግ ግድያ እያመለጡ በመሸሽ ላይ የነበሩትንም ጭምር፣ ሶማሌዎች እየያዙ እስከ ሶማሊያ ወስደው ያስሩዋቸው ነበርና የታሠሩ አባላቱን ለማስፈታት ጭምር ኢሕአፓ ወደ ሶማሊያ በተደጋጋሚ ሉዕካን ልኳል። የታሰሩበትን አባላት የስም ዝርዝራቸውን ይዘን እንዲፈቱልን የጠየቅናቸውን እንኳን በሙሉ አልፈቱልንም። መቅደሾ፣ ቆርዮሌና ሸለምቦጥ፣ በሌሎችም ማጎሪያዎች በርካታ ጓዶችን አስረው ጉዳት አድርሰውባቸዋል፣ ደብዛቸውንም ያጠፏቸው አሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡነ ኤርምያስ ሆይ፣ ቤተክሲያን በክብር የደፋችልወትን ቆብ በክብር ያውልቁ! 

ኢሕአፓን ጠንቅቀው የሚያውቁ ወገኖች አብዛኛዎቹ የኢሕአፓ አባላት ለአንድ ሀገር ኅላዌና ለሕዝብዋ በእኩልነት አብረው መኖር ካላቸው ጽኑ ዕምነት በመነሳት ነበር የታገሉት። የኢሕአፓ አባላት ለመብት፣ ለነፃነት፣ ለሕዝቡ እኩልነት፣ ለማኅበራዊ ፍትኅ፣ ሲታገሉ ከባድ መስዋዕት ከፍለዋል።  ኢሕአፓ ጭቆናን አጥብቀው ከሚቃወሙ፤ በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ፤ ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከሚታገሉ ወገኖችን በመደገፍ የትግላቸው አጋር ሊሆን ይችላል እንጅ የባንዳ ሥራ ሠርቶም አያውቅ ወደፊትም አይሠራም ። ኢሕአፓ ትናንትም ዛሬም ወደፊትም አገርን በሚንድ ሕዝብን በሚያዋርድ ነውረኛ ተግባር ዉስጥ አልተሳተፈም፣ አይሳተፍምም ።

የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ወቅት የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን ከሱማሌ ጦር ጋር አብረው ሊቆሙ ይቅርና በሶማሊያም ዉስጥ ጭምር እየተሳደዱ ነበር። የስደተኛነት መብት እንኳን ተነፍገው ነበር። ህይወታቸውን ከሰው-በላው ደርግ ለማትረፈ ሸሽተው፣ ከእሥር አምልጠው፣ ወደሶማሊያ ገበተው የነበሩት የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች በሶማሊያ እስርቤቶች ውስጥ መከራን ሲገፉ እንደነበር ሁሉም ዕውነተኛ ዜጋ የሚያወቀው ጉዳይ ሆኖ ሳለ ኢሕአፓ ከሶማሊያ መንግሥት ጎን ተሰልፎ ውድ አገሩን ወግቷል የሚለው በሬ-ወለድ ዓይነት ውሸትና የሃሰት ውንጅላ ከዚያ ከሶማሊአ የእሥር ሲዖል የተረፉ የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዮች በሕይወት እያሉ መስማታቸው ለጆሮ የሚቀፍ ለኅሊና የሚዘገንን ነገር ነው። ኢሕአፓ. ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦ.ኤል.ኤፍ) ጋር፣ በድርጅት ደረጃ የቅርብ ግንኙነትም ሆነ ትብብር የረጅም ጊዜ ትብብር ኖሮት አያውቅም። አልፎ አልፎ የተደረጉ ውይይቶችና በግንባር ደረጃ ለመተባበር ወደ መድረኮች የኦ.ነ.ግ. አመራር አባላት ብቅ ብለው እንደገና ስለሚሸሹ፣ (ለምሣሌ ኢ.ተ.ፖ.ድ.ኅ. የሚባል ኅብረት ፓሪስ ዉስጥ ሲመሠረት፣) አብዛኛውን ጊዜም የያዙትን የመገንጠል አጀንዳ ስለሚያራምዱ፣ በኋላም በብዙ ዕምነቶቹ እነሱኑ ከሚመስለው ከህ.ወ.ሓ.ት. ጋር ተሳስረው አሁን ሀገራችን ዉስጥ የተፈጠረውን የብጥብጥ ሁኔታ እያመጣ ያለውን የመገንጠልና የማስገንጠል ቋሚ ስጋት በሀገራችን አመጡ። ኦነግ ራሱን ለውጦ ኢትዮጵያዊነቱን መቀበል ስላዳገተው፣ ዘላቂና አስተማማኝ ግንኙነቶች ከኢህአፓ ጋር እንኳን ለመፍጠር አልቻለም ። የመገንጠል አጀዳን በግልጥ የመይቃወሙ ቡድኖችንና ድርጅቶችን እያነፈነፈ ሲፈልግ ነው የኖረው። ኢሕአፓ የኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነትን፣ አንዴ አጥብቆ የሚይዘው፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅማ-ጥቅም ወይንም ሀገራዊ አንድነትን የሚጠሉትን ለማባበል በማሰብ፣ ይህን “አታንሱብኝ” እያለ የሚዘባበትበት አይደለም። ኢትዮጵያን ሀገራዊ አንድነቷን ጠብቀን፣ ዴሞክራሲያዊት አድርገን፣ የህግ የበላይነትን አስፍነን፣ በተጨማሪም ማኅበራዊ ፍትኅ የሰፈነባት ሀገር እናድርጋት፣ ሕዝቡን ባለመብት እናድርግ ነው የሚለው። ይህ ታዲያ ለጠባብ ብሔረተኞችና ለአድር ባዮች አይመችም።

ኢሕአፓ. ከሱዳን መንግሥት ጋር የነበረው ግንኙነት በርካታ ውጣውረዶች የነበሩት ነው። መጀመሪያ የኤል ኑሜሪ መንግሥት በነበረበት ጊዜ ሱዳን ዉስጥ በይፋ የሚደገፉት የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረትንና እንዲሁም በእንግሊዝኛ መጠሪያው ኢ.ፒ.ዲ.ኤ. ይባል የነበረው፣ በአሜሪካን ይደገፍ የነበረውን፣ ድርጅት ነበር። ይኸም በኢትዮጵያ ዉስጥ ደርግን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የግራ ዝንባሌ ያላቸውን የፖለቲካ ሃይሎች ከምዕራባውያኑ፣ ከዐረብ አድሃሪዎች፣ ከኢራኑ ሽህ ፓህሌቪ ጭምር ፀረ ግራ ትልቅ ሤራ ስለነበረ። ሆኖም ምናልባት በኢሕአፓና በደርግ መሐከል በነበረው ልዩነትና ግጭቶችም የኢትዮጵያን መንግሥት ከማናጋት እሳቤ፣ ኢሕአፓንም አይቶ እንዳላየ የመመልከት አዝማሚያ ስለነበራቸው ኢሕአፓም በሁኔታው ድምጡን አጥፍቶ ይጠቀምበት ነበር። ለበርካታ ዓመታት ቢሮ አልከፈተም ሆኖም ያደራጅና ይንቀሳቀስም ነበር። በኋላ አጋር ያደርጓቸው ድርጅቶች እየተዳከሙ መጥተው ኢሕአፓ ግን እንደተመኙት ሊጠፋላቸው ስላልቻለ አሁንም ደርግ እንዲወድቅ ይፈልጉ ስለነበረ ኢሕአፓም የበለጠ ዕውቅና ሊያገኝ ችሎ ነበር።
በኋላ ሱዳንም ከኢሕአፓ ዕምነት አኳያ ደጋግሞ፣ ከአንዴም ሁለቴ፣ “ወጥ-ረገጠ”! አንድ ጊዜ በደርግ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የማድረስ ዕቅድ አውጥተው፣ ለሁሉም ኢትዮጵያ ዉስጥ ያኔ ይንቀሳቀሱ ለነበሩ፣ “ነፃ-አውጭ” ይባሉ የነበሩ ድርጅቶች የተወሰኑ ወታደራዊ ዒላማዎችን እንዲያጠቁ የተቀነባበረ ስትራተጂ አወጡና አከፋፈሏቸው። ምናልባት በእነዚሁ ግንባሮች ምክር ሊሆን ይችላል፣ በሀገር ዉስጥ ኢሕአፓ የኅብዕ ድርጅታዊ መዋቅር ጥንካሬ ስለነበረውም፣ የኢሕአፓን የአመራር አባል አስጠርተው፣ ያኔ የሱዳን ምክትል ፕሬዜዳንት በሆነ ግለሰብ አማካይነት፣ “የዐባይን ድልድይ እንዲደረምስ” ጠየቁት። ይህ ታዲያ ከፍተኛ የሀገርና የወገን ፍቅር ላለው ኢሕአፓ የሚዋጥለት አልነበረምና፣ እዚያው ፊትለፊት ወዲያውኑ “ይህንንማ በፍፁም አናደርግም” ነበር ያልናቸው። ድልድዩ እኮ የሕዝቡ መገልገያ ነው። የሰሜኑና የደቡቡ ሕዝብ ሁለንተናዊ ትስስርና ግንኙነት ይጎዳልና ኢሕአፓ ሕዝቡን የሚጎዳ ጥፋትማ አያደርስም አልናቸው። ጠባችን ከደርግ ጋር እንጂ ከሽዝባችን ጋር ስላልሆነም! አስፈራሩን። በእምቢታችን ፀንተን፣ እነሱም እንደተመኙት፣ “መሣሪያቸው” ሳያደርጉን ቀጠልን። ጊዜ እየጠበቁልን አድብተው ቆዩ።

ለሁለተኛ ጊዜ ደርግ በጣም እየተዳከመ መጥቶ በሰሜናዊው የሀገራችን ክፍሎች በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠር ተስኖት ነበር። ኢሕአፓ ታዲያ ከገጠሙት አያሌ ችግሮቹ ወጥቶና አገግሞ እንደገና በመጠናከር በደቡብ ጎንደርና በበርካታ የጎጃም አውራጃዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ ነበር። ማዕከሉን ቋራን ሳይለቅ በርካታ አካባቢዎችን ነፃ አውጥቶ ሕዝቡም ራሱን ማስተዳደር ጀምሮ ነበር። ያኔ ኢሕአፓ ሱዳንም ዉስጥ በመጠኑም ቢሆን ላላ ብለውለት ቢሮዎችን ከፍቶ መነቀሳቀስ ችሎ ነበር። አሁንም ሱዳን የደርግን መዳከም በመረዳት ሌላ ሙከራ ላይ ተሰማራ። ከመተማ እስከ አይማ ወንዝ ያሉትን፣ ወሀ ገብና ለም፣ ደን ለበስ የኢትዮጵያ መሬት፣ አሁን ከህ.ወ.ሓ.ት. የተቸሩትን የድንበር አካባቢዎችን፣ በሀብታም ገበሬዎች እንዲታረሱ ለማድረግ ጥበቃ የሚያደርጉ ወታደሮችን መርትይራድ፣ በሚባል የወሰን አካባቢ ላይ በማስፈር ለመስፋፋትና ስፍራውን ለመያዝ መንቀሳቀስ ጀመረ። የአካባቢው ሕዝብና ኢሕአፓም ይህ ወረራ በዝምታ የሚታለፍ ሊሆን እንደማይገባው ተማምነው የታጠቁ አርበኞች ሱዳናውያኑን ለማስለቀቅ እርምጃዎችን መውሰድ ጀመሩ። ያኔ ታዲያ የሱዳን ባለሥልጣኖች ኢሕአፓን  እንደገና ማስፈራራት ጀመሩ። “ቢሮ አችሁን እንዘጋለን!” ይሉ ገቡ። የኛ መልስ ሕዝቡ እኮ መሬቱ የኛ ነው እያለ ነው፤ አልናቸው። እነሱም “ያለ እናንተ ይሁንታ ይህ አይሆንም” ማለታቸውን ቀጠሉ። ደፈር ብለውም እነዚያን የታጠቁ አርበኞች ለመጉዳት በወታደራዊ ሃይል ወደ ነፃ አካባቢያችን ጎራ አሉ። ከኢሕአፓ ሠራዊት አይቀጡ ቅጣት፣ ገጠማቸው። ጉዳት ደረሰባቸው፣ አፈገፈጉም። ያኔ የነበራቸው አማራጭ፣ አድብተው ጊዜ መጠበቅ ነበርና ለጊዜው ሽንፈት ተቀብለው ተባረሩ። ህ.ወ.ሕ.ትንና ሸ ዓቢያን አሰባስበው በ1991 ላይ በኢሕአፓ ላይ እስከዘመቱ ድረስ ያንን አካባቢ አልደፈሩትም ነበር።

በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በሃይልና በጉልበት ራሱን ጭኖ የነበረውን፣ የተቃወመውን ቀርቶ ልዩነት ያሳየን ሁሉ ያስር፣ ያሰቃይ፣ ያርድና ይጨፈጭፍ የነበረውን፣ የመደራጀትና የመነቀሳቀስ መብት ነፍጎ ተቃዋሚዎችን ሁሉ ወደ አመፅ  የገፈተረውን ወታደራዊ ደርግ፣ በሕዝብ ያልተመረጠ በመሆኑ ለኢሕአፓ “… ሕገወጥ፣ አምባገነናዊ፣ በተግባሮቹም ፋሽስታዊም” ነበር። ስለሆነም መቼም ኢሕአፓ ማንኛውንም ድርጅት ወይንም መንግሥት ሲገናኝ፣ ደርግን ማስፈቀድ እንዳልነበረበት አዕምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አይስተውም። ዛሬ ሀገራችን ውስጥ ያለውን አስከፊና አስጊም ሁኔታዎች በትግሉ ለመለወጥ የተነሳን ወጣት ትውልድ ማሳወቅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። የቀዳሚ ትውልዶች አባላት የሚያውቁትን ሁሉ ዕውነቱን፣ ሳያውገረግሩ፣ ሳይዋሹ፣ እንዲነግሯቸው፣ እንዲያስተምሯቸው፣ ጽፈው እንዲተዉላቸውም ይጠበቃል። በሙሉ የማይታወቅ፣ የሚጠራጠሩት ነገር ሲኖርም ጉዳዩን በጥርጣሬ መልክ ማስቀመጥ ይጠበቃል።ያለምንም ማስረጃ ግን ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን፣ ስለማንወዳቸው ብቻ፣ ወይንም ከሌላ ተልዕኮ ተነስተን፣ በሃሰት መክሰስ ወጣቱን ትውልድ መበከል እንጅ ማስተማር አይሆንም።

የመደብ ልዩነትና ተዛማጁ የርዕዮተ ዐለም ልዩነት ኢትዮጵያ ዉስጥ በፊትም ነበር፣ አሁንም አለ፣ ወደፊትም ይኖራል። በተለያዩ መንገዶች ሃብት ያፈሩ፣ የከበሩ፣ የናጠጡም ከበርቴዎች በየሀገሮቹ አሉ። በሌብነት፣ የሕዝብ ሃብት ስልጣናቸውን ተገን አድርገው የሚዘርፉ አሉ። “ሀብታም ከሆኑት” መሐል ስግብግቦችና በሃብት ላይ ሃብት ማፍራት ብቻ ዓላማቸውም፣ ህልማቸውም የሆነ ክፍሎች አሉ። ለምሳሌ ፋብሪካዎች ስለሚያደርሱት ብክለትም ሆነ መሰል አካባቢ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ ስለ ሠራተኞች የኑሮና የጤና ሁኔታ፣ ወ.ዘ.ተረፍ ቁብ የማይሰጡ አሉ። ቀረጥ ላለመክፈል ሃብታቸውን ከቀረት-ነፃ በሆኑ ደሴቶች የሚሸጉቱ ሞልተዋል። በየሃሰ ሳንደረድር የሃሳብ ፍጭት ማድረግ ነው የሚጠበቅብን። ደርግ በተባለው መቅሰፍት ቡድን ዉስጥ በአውራ ተዋናይነት ተሠልፋችሁ የነበራችሁ፣ በቅድሚያ ጥፋታችሁን እመኑ። ላደረሳችሁት ጭፍጨፋ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ ጠይቁ። “ቀደም ብሎ አንድ ሌላ ታጋይ ትውልድ” ከመተሩ፣ ከህ.ወ.ሓ.ት. ነፍስ-ገዳዮች ከማይሻሉ፣ የሌላ ጊዜ ወንጀለኞች፣ ለአዲሱ ትውልድ ምክር ለመለገስ ከመሞከራችሁ በፊት፣ ያውም በቅጥፈቶች አጨማቃችሁ ለመበከል ከመንደርደራችሁ በፊት፣ የራሳችሁን ጥፋቶች አምናችሁ፣ ክፉኛ ከበደላችሁት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ያስፈልጋችኋል። የደርግና የባዕድ ተላላኪዎች ውሸት ይጋለጣል!!

የኢሕአፓ ጀግኖች ትክክለኛ ታሪካዊ ይወደሳል!!

ቄሮ፤ ፋኖ፤ዘረማና ነብሮ በኢትዮጵያዊነት ያሸበርቃሉ!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቸንፋል!!

 

Tbalcha7@gmail.com

 

11 Comments

  1. ውይ አላችሁ እንዴ? ሞት አይርሳችሁ እንጂ እናንተማ ራሳችሁን አትረሱ።

  2. የዚህ ሁሉ በኣካባብያችን ያለው ችግር ኢህኣፓ ተጠያቂዎች ናችሁ በዚህ ሳይወሰን በደርግ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችም ኣልቋል በትግሉ ግዜ በኣሲምባ ከትግራይ ይሁን ከኤርትራውያኖች ጋር በኣንድነት ደርግ ከመዋጋት ይልቅ እኛ ነን ጎብለል በሚል ከንቱ እምነት ከሰራዊቱ ወጥተው ወደወያኔ ለመኮብለል የመረጡት ይበቃል ስንት በተናገርን ይቅር

  3. Taye, Asmare and Solomon are you trolls or homo sapiens or even neanderthal….If not for sure you or member of your family was a fascist puppy….as puppies you always bark..and forget puppies are dogs….

    • እናንት ሐገር ሻጭ ቅጥረኞች አሁንም እንደገና The Tower in The Sky!!!
      Conmen

  4. Abebaw ከስድብ ይልቅ ለምን እንዴት ስለምን ብለህ ብትጠይቅ መልካም ነበር እኔው ራሴ ኣሲምባም ይሁን ጎንደር ደሴ ስለነበርኩ ምንም ሳላውቅ ኣልጽፍም ስለዚህ ኣሁንም ያኔ የነበሩት መሪዎች ትክክል እንዳልነበሩ ሁሌም እናገራለሁ

  5. The true face /history/ of EPRP —Please read this book “ENAT HAGER !!! YE EHABA ENQUQULISH ”
    ]By DR. Ayalew Mergiaw Gobena . /Amazon./

  6. long live EPRP; the most courageous generation who defeat fear and died for better Ethiopia. I know those genociders attack EPRP because of their history of crime.they don’t come with their real identity they hide with nicknames and ethnic organizations which uses as their crime shelter.

  7. What do we expect from illiterate Banda and literate Banda too? Those who want to kill Ethiopia are always against EPRP. EPRP never let bandas sell Ethiopia or destroy Ethiopia.

  8. EPRP conducted itself with Dignity while Hirelings of the Military Junta lost status, self-esteem and reputation and finally they were sent home in disgrace. In other words, they served DERG and became extinct shortly after Mengistu left for Harare and TPLF took over power in Addis Ababa . While in power, however, they were pledged to eliminate the entire youth and have done so, so to speak and that is what their history appears to be in a few words. The Bloody Butchers! Come what may, we shall never forget our history and must be told as it is now and as well must be passed down to the generation yet to come.

    Yes, history has it that that nearly every family in Ethiopia was behind EPRP. The party all cynics love to hate then had also a total confidence in its ability to organize the youth and had enjoyed the support of the vast majority of Ethiopian people as opposed to those paid hirelings and doubting Thomases. In fact, it did not take him long to become big and wide in Ethiopian political landscape. EPRP moved swiftly and of course with a great deal of organizing skill and became a nightmare for DERG in no time. EPRP proposed Provisional Government comprising different factions of different views including DERG and civil and professional organizations like ETA and others to take place in Addis. DERG on the other hand had set up PMAC single handedly and ignored the call of EPRP and the youth at large and instead it had formed its own PMAC. And it continued to control the nation as a whole following a coup d’état it carried out against Hilesslase. And then the so-called PMAC (the Provisional Military Administrative Council) had formed SEDED and WOSELEAGUE as political wings under its own command. As Intellectuals and professionals as they were, both SEDED and WOSELEAGUE became the two sides of DERG”S political wings. Eventually, though they happened to be at the core of DERG”S political helm and continued to train new recruits and expand the operations of their own political units across the nation of Ethiopia. And in next to no time, MESON, ECHAT, and MALERED followed the series to join the club and had begun to slay the generation thereafter.

    Realistically, though EPRP and the Youth were highly motivated by the lofty notion of Democracy, Land to the Tiller, unity based on equality and social-justice for all as opposed to hirelings’ falsified publications against EPRP. On the contrary however, Hirelings were motivated not by freedom but by money and power trip which are menial and unpleasant cause so to speak for one to die for. As a result, the sphere of EPRP’S influence became invasive and persistent in terms of winning the hearts and minds of the Broad mass. At the end of the day, however, hirelings realized that the pervasive nature of the moment led by EPRP was beyond them to control. Wasn’t that the reason why they became green-eyed and resentful and continue to be bitter about the same party called EPRP to this date? Be that as it may, the party that made all cynics felt devoid of love and grace had won the general level of confidence and optimism of the people and became far more formidable than the Military Regime and its hirelings. That was when they felt that EPRP was embraced by the public at large and had gained far more superior willpower than their article of faith and direction as well. That was also when DERG had grown to be wary and nervous about the development it was forced to accept the sustained political advance of EPRP and the youth. That is the fact! The paranoid tendency lies at the very root of DERGE’S character; a character it basically inherited from his combatant profession and post became evident when it employed an excessive force against the youth and has done all it can to destroy our generation. Literally though DERG had begun to take an arbitrary action against whoever it thought was against him without provocation. Afterward, the Military Junta in cooperation with those sub-groupings clustered beneath him under the umbrella of EMALEDH were also suspicious of any movement around them. They were totally shattered with fear of becoming secluded from the community and family of their own. Obviously though they knew that EPRP’S popularity was beyond them to avert. Worst of all, they even became more insane when learned that EPRP’S infiltrators inflicted every center of operation they were in to conduct their reign of terror against EPRP. You see, in this case it was the people in general and EPRP in particular that put a match to the burning oil and ignited the Revolution across the land of Ethiopia . Consequently, turbulence among the youth, the intellectuals, workers and the peasants across the country reached a new pitch. It was due to this momentum though DERG launched a bloody campaign called Red Terror against the entire generation including the workers, the peasants, the educators, teachers and students across the country.

    After all, power was what the junta was failing in love with and the cadres were there serving the powerhouse of DERG. The CADRES were part and parcel DERG”S Loyal Order, a core group assigned to control the community for the same Military Junta, a Junta that merely knew how to hunt and kill its opponents, and the CADRES’ main line of duty was also nothing but stifling the voice of the public by guarding against the activities of the youth and of the EPRP. But to their disappointment, every which way both the cadre and the junta spun around not only the humans, the birds and every moving creature in the land of Ethiopia were there to protest against their cruelty. As a result, the junta together with its several sub-groupings had grown to hate their ugly image on the mirror when compared it to EPRP’S grace. The good reputation, the high opinion and the good name of EPRP won him recognition allover while the discarded and deprived cadres that the junta happened to fall in line with were became completely rootless. They were too weak to keep on harassing and irritating the hostile youth in every frightening neighborhood in which they were once treated as cynic and agnostic. Isn’t that the reason why they became extinct along with the system they built in?

    Shortly after DERG brought the cynics together with the pretext of unity under the umbrella of EMALEDIH, which EPRP then dismissed it as of no use, was turned out to be a scene of carnage for themselves. DERG himself killed, imprisoned, tortured and abused them the same exact way they themselves have done it to the youth. DERG has done so all these cruelties not in self-defense or with any other extenuating circumstances recognized by law but to monopoly power. Isn’t that what happened even to them as well? Shortly after he wiped out those who resisted its power he converted others to be ESEPA and have them served to the last minute of his time in power. Well, for our surprise the same cadres that had been hunting down EPRP & affiliates began to emulate EPRP with their own word of mouth, saying that unlike them EPRP is the only one that dies with grace and with its own belief and vision intact. The party some continue to hate remains strong and alive to this very day. But the rest are already no more to be seen in Ethiopian political landscape no more.

    And yet, whoever was identified as member of anyone of those sub-groupings, and mouthpiece of the DERG as MESON, ECHAT, WOS_LEAG, SEDED Kebele Officers had been totally rejected by the mass and were totally graceless before the eyes of the entire community. And even they were subject to punishment and correction by non-other than their own family including and up to eviction. It was really more of a family matter and a neighborhood sort of link that made the movement led by EPRP unique at that point in time.

    In conclusion, unfortunately, what the junta use of its entire apparatus and the resource of the nation as a whole was to kill the generation indiscriminately including his loyal recruits and outstanding generals. Although some like to refuse to go along with this true picture of our recent history, we still have to tell it as it is so to pass the true version of our history to the younger generation and the generation to come. It was not even one or two organizations alone that had been wronged, mistreated and prosecuted by DERG and hirelings. It was rather the entire generation including hirelings themselves suffered torture and persecution at the end. The young, old male or female you name it was there to suffer Red Terror. And it is those cadres including those who are working with the current oppositions that committed this horrendous human carnage against EPRP and the public at large. But in this case what made hirelings more responsible when it comes to the holocaust was that they were readily took shape in response to DERG’S request to carry out the Red Terror campaign that massacred the generation. To that end, all of them bore unusual names: ECHAT, MESON, MALERED, WOSE LEAGUE, SEDED and many others. Nearly all appealed to the poor and disinherited classes and some made a special bid for the support of nation and nationalities questions and have been competing to be the best of the best in a world of Marxism and Leninism of that era. But finally, all of them have been consumed by Red Terror themselves. And yet EPRP is still around enjoying the same status it enjoyed then.

    Justice shall prevail in the land of Ethiopia!

Comments are closed.

Share