የህውአት መቀበሪያው የት ይሆን? አንቦ ወይስ ጎንደር ወይንስ አዲስ አበባ ላይ። (ከተማ ዋቅጅራ)

ህውአታውያን በውጭም በአገር ውስጥም ተወጣጥረዋል። አሁን ያለው የፖለቲካ ጡዘት የሰሩት   ግፍ። በቆፈሩት የጥፋት ጉድጓድ ውስጥ ሊከታቸው ገፍቶ ገፍቶ ጫፍ አድርሷቸዋል። በዚህ የተነሳ ያለ የሌለ ሃይላቸውን ህውአትን ለማዳን ታላቅ መፍጨርጨር ውስጥ ገብተዋል። አቅማቸውን በሙሉ አሟጠው በመጠቀም የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ  ናቸው። በኢትዮጵያ ምድር የተነሳው የለውጥ ማእበል ህውአትን የቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ቀብሮ ካልሆነ መቆሚያ እንደማይኖረው በሚገባ ተገንዝበዋል። ይሄም ሁኔታ እጅግ በጭንቀት እንዲወጠሩ አድርጓቸዋም። በዚህ ምክንያት አዋጅ በማወጅና የቀድሞ ታጋዮችን በመሰብሰብ የመጣባቸውን የህዝብ አብዮት ለመቀልበስና ህውአት እንደከዚህ ቀደሙ የበላይነቱን አስጠብቆ የማስኬድ ስራዎችን በማድረግ ላይ ናቸው። በዚህ ባለቀ ሰአት እንኳን ክመሃላቸው መልካም አሳቢና ብልህ ሰው ማጣታቸው ቢያሳዝነንም የህውአት የተሳፈሩባት መርከብ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ስጥማ መጥፋቷ በይፋ የሚነገርበት ግዜ እሩቅ አይደለም። ህዝብ ከዳር እስከዳር በከፍተኛ ቁጣ በመነሳት የስርአት ለውጥ በሚጠይቅበት ሰአት ህውአት ግን  ተመልሰው ጥያቄአችሁን በሰላም ጠይቁ ይመለስላችኋል የምትለውን ያረጀች ስልታቸውን ይነግሩናል።

በዚህ የተነሳ ጥያቄዎቻችሁ በሙሉ ይመለሳሉ በማለት  ህዝቡን ካረጋጋን በኋላ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበሩት በሙሉ አድነው በማጥፋት ወደቀድሞ ነውርነታቸው በመመለስ አሁንም የህውአትን የበላይነት ለማስጠበቅ በሰላማዊ መንገድ ጠይቁ  የምትለውን የወያኔ ዜማ እያስተጋባት ይገኛሉ።
ሲጀመር ህውአትን የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቆዎችን መጠየቅ የጀመረው ዛሬ ነው ወይ? ህዝባችን ጥያቄውን በአደባባይ ሲጠይቅ በአጋዚ ሲገደሉ ለገዳዮቹ ከህውአትያውያን የሚሰጣቸው ጀጋናይ የሚል ነው እንጂ በሚፈጽሙት ወንጀል ሊያስከፍላቸው የሚችለውን ከፍተኛ ዋጋ አስቦ መልካም ንግግር የሚናገር ህውአታውያን የለም።

የሰላማዊ ጥያቄ ትግል በመታገል ጥያቄአቸውን ለአመታት በመጠየቅ የመጀመሪያዎቹ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ናቸው። ለጠየቁት ጥያቄ የተሰጣቸው ምላሽ ምንም የለም ጭራሽ የሃይማኖቱን መሪዎች አሸባሪ በማለት ፈርዶባቸው በእስር ማሰቃየት እንጂ ከህውአትያውያን በሰላማዊ ጥያቄ የሚመለስ ነገር እንደሌለ ብዙ የምናቃቸውና የምንጠቅሳቸው ቢኖሩም ቅሉ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የሰላም ጥያቄ እና የህውአት መልስ የማንነታቸው መገለጫ መሆኑን ፍትው አድርጎ ማሳያ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥቁር - ጠበንጃ  ወይስ ጥቁር -ሙጃ

አለም በቃኝ ብለው በገዳም የሚኖሩትን አባቶች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮችንስን አሸባሪ ብሎ በእስር ማሰቃያ ማሰቃየትስ በየትኛው ህግ ነው ብእርና ምንኩስና ህዝብን የሚያሸብሩት። አሸባሪ መንግስት በስልጣን ለይ ካለ ሰላማዊ ሰውና እውነት ተናጋሪዎች   ሽብርተኛ ናቸው። ታድያ ከየት ያመጣውን ባህሪ ነው የሚነግረን?  የሰላም ጥያቄና የሰላም ትግል እንዳይኖር አድርጎ ከጨረሰ በኋላ የሰላም ታጋዮችን አስሮና ገሎ ክአገር አሳዶ ከጨረሰ በኋላ ህዝቡ የራሱን መብት ለማስከበር ከዳር ዳር ሲነሳና ጭንቅ ውስጥ ሲገቡ የሚያደርጉትን መፍጨርጨር በየትኛው ህብረተሰብ ነው ተቀባይነት የሚያገኘው። ታማኝ  በየነ እንዳለው እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም እንዳለ ህውአትም እንደዚሁ ነው።

ህውአቶች  ያላወቁት  ነገር አዋጅ ባወጣ ቁጥርና የአፈና ተግባሩን አጠናክሮ በቀጠለ ቁጥር እዲሁም ግድያ በፈጸመ ቁጥር ህዝብን የበለጠ እንዲቆጣና እንዲጠንክር በማድረግ የህውአት መጥፋትን እንዲያፋጥን ያደርገዋል እንጂ ተሸማቆ አልያም ፈርቶ ወደኋላ የሚል ሊኖር እንደማይችል ያወቁ  አልመሰለኝም። ጋዜጠኛው የህዝብን ብሶት ሲጽፍ አሸባሪ እያሉ ሲያስሩ ፖለቲከኞች የህዝብን ሃሳብ ይዘው ሲቀርቡ አሸባሪ እያሉ ሲያስሩ የሐይማኖት አባቶችን ለአገርና ለህዝብ የሚለምኑትን አሸባሪ እያሉ ሲያስሩ በመጨረሻም የመረረው ህዝብ ግፍን በደሉን የሚናገርለት ሲያሳጡት 100 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ አድርገውት አረፉት።

ዛሬ የ6 አመቱም ጨቅላ ህጻን የ20 አመቱ ወጣት የ70 አመቱ አዛውንት ጥያቄአቸው ፖለቲካዊ መሆኑ እንደ አገር ሲታሰብ በጣም ከባድ ነገር እንደሆነ እንረዳለን። የፖለቲካ እውቀት ያለው ህዝብ ጥያቄው በሙሉ ፖለቲካዊ ነው ማለት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንግዲህ ተረጋግቶ የሚቀመጠው በሰላም መንገድ  ያቀረበው ፖለቲካዊ ጥያቄ ሲመለስ ብቻ ነው። ዛሬ ይሄንን የፖለቲካ ጥያቄ እየጠየቀ ያለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይሆን ከዳር እስከዳር ከሊቅ እስከደቂቅ 100 ሚሊዮን የኢትያጵያ ህዝብ ነውና በታህድሶ ጥገና አልያም በግዜአዊ አዎጅ የሚመለጥበት የህውአታዊ ግዜ አብቅቷል። ህዝቡ የጠየቀውን ሙሉ በሙሉ የስርአት ለውጥ በውድ አልይም በግድ የህዝብ ጥያቄ ህዝቡ እራሱ እንደሚያመጠው ጥርጥር የለንም ምክንያቱም ህዝቡ ውስጥ የገባ የፖለቲካ ጥያቄ አንባ ገነነኖችን በመቅበር የነጻነት ጫፍ ላይ ሳይደር አይቆምምና ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንቢታዊ መልእክት ከቆሼ – ያየያየ ይልማ

ህውአት  የከፋፍለህ ግዛ ዘመኑ ጨልሞበታል  እራሳቸው ወልደው ባመጧት   የመከፋፈል ሴራ ቀስቶቹ በሙሉ ወደእነርሱ  ዞረዋልና በምን ያህል ፍጥነትና በምን ያህል ክብደት ህውአት ላይ እንደሚያርፍ ከወዲሁ መገመት ባይቻልም ቅሉ  የህውአት ዘመን  እስከወዲያኛው  አብቅቶለት  አደጋዎች በሙሉ በራፋቸው ላይ እንደደረሰ ማወቅ ይቻላል።

የፖለቲካ ጡዘቱ በተለያዩ ታክቲክና ስልት ህውአትን እያሽመደመደው ይገኛል። ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ነገ ህውአትን  ወደማስገደዱ የሃይል እርምጃዎች እንደሚኬድ ግዜው ይናገራል። ምክንያቱም የህውአታዊ ግዜ አልቋልና ነው።

ከተማ ዋቅጅራ
17.03.2018
Email- waqjirak@yahoo.com

3 Comments

  1. የህውአት መቀበሪያው የት ይሆን? አንቦ ወይስ ጎንደር ወይንስ አዲስ አበባ ላይ።

    ወንድሜ ከተማ ዋቅጅራ አንቦ ፣ ጎንደር ውይንም አዲስ አበባ የህወሓት መሞቻ እንጂ መቀበሪያ አይሆንም። ምክንያቱም መሬታችን በነርሱ ሬሳ እንዲረክስ አንፈቅድም።

  2. ችግሩ ህዋሃት ብቻ ነው ብሎ ማሰብም ሆነ ማመን ከህዋሃት በህዋላ የምትኖረው ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለባት እንዳናስብ ያደርገናል። ህዋሃትን የወለደው የትግራይ ብሔረተኝነት ነው። የትግራይ ብሔረተኝነት ደግሞ ብዙዎች እንደሚሉት ትናንትና በስልሳዎቹ የተማሪዎች ዕንቅስቃሴ ጊዜ የተወለደ ሳይሆን ቀጥታ ከምንሊክ ንግስና ጋራ የተቆራኘ ክስተት ነው። ዮሃንስ ሲሞቱ ትግሬዎች የዮሃንስን ልጅ ነበር እንዲነግስ የጠበቁት። ያ አልሆነም። ትግሬዎች የሸዋ ህዝብ ላይም ይሁን ምንሊክ ላይ ያላቸው ጥላቻ አጥንት እና ደማቸው ዉስጥ የተዋሃደ የሆነውም ለረጅም ጊዜ የቆየ ቂም በመሆኑ ነው።
    ያሁኖቹ ትግሬዎች ደግሞ ፣ አንድ የአረቦችን የመሰለ የተጨማለቀ የአስተሳሰብ መስመር ይከተላሉ:: ይህን እየሩሳሌም ውስጥ በሙስሊሞች እና በክርስቲያኖች መካከል ተፈረመ የሚባለውን የኡማር ውል ማወቅ የትግሬዎችን የአስተሳሰብ መስመር ለማወቅ ይረዳል። አረቦች አንድ ጊዜ መካከለኛውን መስራቅ እና ኢስያን በጦርነት ከተቆጣጠሩ በሁዋላ ፣ ሌላውን የአካባቢ ነዋሪ ግብር አስከፋይ ሆነው ነው የቆዩት። ይህ ሁኔታ በኦቶማኖችም ጊዜ የኖረ ነው።
    Pact of Umar *https://en.wikipedia.org/wiki/Pact_of_Umar#Origin_and_authenticity

    ትግሬዎችም ከትግራይ ውጭ ያለውን መሬትም ይሁን ህዝብ የሚመለከቱት እንደ ጦር ምርኮ አና ምርኮኛ አድርገው ስለሆነ ፤ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ለነሱ ሊያሸረጉድ እና ግብር ሊከፍላቸው ትክክል ነው ብለው ያምናሉ። ህዝብ ማፈናቀሉ ፣ የሃገር ድንበር መቀያየሩ ፣ ያለህዝብ ፈቃድ ከጎረቤት ሃገሮች ጋራ በምስጢር ድንበር ማካለሉ ፣ ህዝብን በተለይ ድግሞ አማራን እና ኦሮሞን ባደባባይ ማዋረዱ ሁሉ የዚህ ቂም የውለደው ጊዜያዊ የበላይነት ስሜት የሚፈጥረው ነው።
    የትግራይ ብሔረተኝነት መነሻው እኩልነትን የመሻት ተራማጅ አስተሳሰብ ሳይሆን ፣ ግዛታዊ ተስፋፊነትን እና የበላይነትን የሚመኝ አጥፊ ፊውዳላዊ አስተሳሰብ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ህዋላ ቀር አመለካከት ቸል በማለት ፣ አመለካከቱ የፈጠረው ህዋሃት ላይ ብቻ ማተኮሩ ዘላቂ መፍሄ ኣያመጣለትም። ከሰሜንም ይምጣ ከደቡብ የዘመነ መሳፍንት ጊዜ የነበረውን ወራሪነት እና ተስፋፊነት መዋጋት አልብን።

Comments are closed.

Share