ሶስቱ የህወሃት ቀለበቶች ታወቁ! ዳገት ላይ ሰው እንዳይጠፋ ይሁን !

መስቀሉ አየለ

የትግራዩ ገዥ ጉጅሌ ላለፉት አራት አስርተ አመታት የተጓዘባቸው “የብሄር ብሄረሰቦች ጭቆና” ወዘተ የሚለው የፖለቲካ ድሪቶ ሞቶ የተቀበረ መሆኑን በራሱ የውስጥ ግምገማ ተማምኗል። ከዚህ ቦሃላ የኢትዮጵያን ህዝብ የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት አግኝቶ አንዲት ስንዝር የሚያራምደው የፖለቲካ አጀንዳ እንደሌለ እርግጠኛ ሆኗል። በመሆኑም ከደደቢት ጽንሰቱ ጀምሮ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የተጏዘባቸውን መንገዶች አሁን ከተፈጠረበት ህዝባዊ ማእበል አንጻር እንዴት መደምደም እንዳለበት ቁጭ ብሎ በሶስት ደረጃ አስልቶ በመጨረስ ወደ ስራ የገባ መሆኑን ህዝቡ ከልብ እንዲያስተውልና ለቀጣዩ ትንቅንቅ እንዲዘጋጅ ያስፈልጋል።

ስቴጅ

እንደ ህወሃት ግምት ይኽ አሁን ድርጅቱ ያለበትን ሁኔታ የዲተረንስ ስቴጅ ብሎታል። በዚህ ቀለበት ውስጥ አልፎ ነገሮችን ለመፍታት እንደ ግብአት እየወሰደ ያለው በተቻለ መጠን ስጋት አይሆኑብኝም የሚላቸውን እስረኞች በመፍታት አንድም ለብሄራዊ እርቅ የተዘጋጀ በመስለል በአንድ በኩል የተፈጠረበትን የዲፕሎማቲክ ጫና በማርገብ በዋናነት ግን የህዝቡን ቁጣ በመባረድ እኛን ከትግል እያዘናጋ ግዜ የመግዛት ሁኔታን መፍጠር ነው።ቢሆንም ግን በዚህ ደረጃ ህወሃት እራሱ ከገመተው በላይ እንደተጏዘ ነገር ግን በዚህ ቀለበት ውስጥ ይገኛል የተባለው አንጻራዊ መረጋጋት እንዳልተገኘ ይልቁንም ይበልጥ ቀኑ በገፋ ቁጥር ሂደቱ ይበልጥ ውስብስብ እየሆነ መሄዱን ነው የተረዳው። በመሆኑም ወደ ሁለተኛው ቀለበት ወይንም ስቴጅ ፪ በመሸጋገር ላይ ነው።

ስቴጅ

በራሱ የግዜ ስሌት ውስጥ ሄዶ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ያወጀው የህወሃት የኮብራ ግሩፕ የመጀመሪያውን ቀለበት ሙሉ ለሙሉ እያሟጠጠና ወደ ሁለተኛው ዙር ቀለበት ውስጥ ለመግባት የምጥ መጀመሪያ ላይ የቆመ ሲሆን አለም በአይኑ ብሌን እየተመለከተውም ከሚንስትሮች ምክርቤት እስከ ፓርላማ ያለው መዋቅር ሳያስፈልገው በቁራጭ ወረቀት በቀጥታ ለሚዲያ በወረደ ትእዛዝ የአስቸኩዋይ ግዜ አዋጁን መጫኑ ወደ ሁለተኛው ዙር ቀለበት ውስጥ ለመግባት ያስችለኛል ያለውን ጭምብል በህግ ሽፋን ለማጥለቅ እየተጏዘበት ያለው ሂደት  መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብአዴንና ሌሎቹ ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ ከሚገኘው ሕወሃት ጋር እየተባበሩ ያሉት ወገኖች በድንቁርና ነው

እንደ ህወሃት ኮብራ ግሩፕ እስትራቴጅ ሂደቱ ወደዚህ ቀለበት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ሲገባ ተከታታይነት ያለው ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት (ሄቪ ኢንተርቬንሽን) ይጠበቃል። አገሪቱ ውስጥ አስፈላጊ በሆነው ቦታ ሁሉ የራሱ የቁርጥ ቀኔ የሚላቸውን የወታደር ክፍል ከመጠቀም  ጀምሮ  በመላ አገሪቱ የሚገኙትን የወታደራዊ ተቋማት ሳይቀር በቀጣይ ለሚፈጸሙ የጅምላ እስር እያዘጋጀ በሂደት ለሚፈጠሩ ተጋትሮዎች በታንክ ጭምር የተደገፈ የከተማ ውስጥ ወረራ በማድረግ “ድምጽ በራማ ተሰማ ያልወልዱ ጡቶች ያላጠቡ ማህጸኖች ብጽአን ናቸው” ተብሎ የተነገረለትን የሄሮድስን ጌሎቲን ሰይፍ በመምዘዝ ቀይ ሽብርን ተረት በሚያደርግ ፋሽዝም  ወደ ለየለት የጅምላ ጭፍጨፋ ለመሄድ ዝግጅቱን በማጧጧፍ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያውያን በአንክሮ ሊያውቁት ይገባል። ዛሬ ታማኝ የተባሉትን ቅልብ ጦር እስከ አፍንጫው እያስታጠቀ ከሰሜን ግምባር  ወደ መሃል አገር መግባት መጀመሩ የዚሁ የሁለተኛ ቀለበት እቅድ ቅድመ ዝግጅት አካል መሆኑ ነው።

 

ስቴጅ

እንደ ህወሃት ግምገማ ከህዝቡ የሚጠብቀው ትንቅንቅ ሁለተኛውን ቀለበት አልፎ መውጣት ከቻለ ወደ መጨረሻውና ሶስተኛው ቀለበት ለመሄድ ይገደዳል ማለት ነው። በዚህም እስከዛሬ ድረስ ለይስሙላም ቢሆን የነበረውን የሲቪል የሚመስል አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በማውረድ  በታንክ አጅቦ የወታደሩን መንግስት በአራት ኪሎ ላይ ያቆማል ማለት ነው።

ለዚኽም ስኬት እስከዛሬ እርስ በርሳቸው እጆቻቸውን ቃታ ላይ አኑረው በይነ ቁራኛ ሲጠባበቁ የነበሩት የሳሞራና የጌታቸው አሰፋ ክንፎች በእነርሱ እምነት ሁለቱንም ጠርጎ ሊወስዳቸው የመጣውን ህዝባዊ ሱናሜ ለመቋቋም ሲባል ጊዜያዊ የመቻቻል ስምምነት ላይ የደርሱ ሲሆን ገለልተኛ በሆነ ሶስተኛ ቦታ እየተገናኙም መረጃዎችን በማቀላጠፍና እቅድ በማውጣት ላይ ተጠመደዋል። ያም ሆኖ ግን ሁኔታዎች ሲያመቹዋቸው ደግሞ አንዳቸው አንዳቸውን ከመብላት እንደማይመለሱ ሁለቱም ያውቁታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይሄ ሰውዬ በርግጥም በሽተኛ ነው፤ “አትግደሉኝ” ማለት በየትኛው ሒሣብ ነው የሥልጣን መያዣ አቋራጭ መንገድ የሚሆነው? ይነጋል በላቸው

ውድ ኢትዮጵያውያን ምናልባት ተጽእኖ የማድረግ አቅም ያላቸው የውጭ መንግስታት ይኽ እኩይ ስርአት ሊሄድበት ያለውን የመንገድ እርቀት አስቀድመው ተረድተውና በዚያው ልክ ያላቸውን ሌቬረጅ ሁሉ ተጠቅመው ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ካልገፉት  ወይንም ከተራው ወታደር በሚፈጠር ማፈንገጥና ከህዝብ በሚመጣ መቀናጀት ሂደቱ ሌላ መልክ ካልያዘ በስተቀር ይኽ ህወሃት የተባለ መሰሪ ቡድን እቅዱን ሁሉ ደረጃውን ጠብቆ ተግባራዊ ከማድረግ እንደማይመለስ በእርግጠኝነት ሊታወቅ ይገባል።

 

5 Comments

  1. I think the TPLF rule is coming to its inevitable end. The TPLF can not militarily control the two restive regions (Oromo and Amhara). In due course the uprising will spread to and cover more regions. It has already become clear that the TPLF is losing control over the Oromo region. The Tigre led Amhara organizationm, the ANDM is very fragile because the middle and lower level functionaries are mainly composed of the Amhara nationals. The prospect of the Tigre top commanding the loyalty of the Amhara nationals at the lower ranks is non-existent if the Amhara activists effectively mobilize the Amhara youth. The Amharas must exchange experience and strategies with the Oromo activists who have been efefctive in dismantling the TPLF`s repressive structure in their region.

  2. What ever means and methods it uses,the TPLF will lose its power and will be ejected from the Menelik palace. The time for reconciliation that includes the TPLF is now overdue because its leaders have chosen the path of destruction, killings and are soaked in the blood of the peaceful citizens. They will be tried for crimes against humanity for the massacres they have committed in different parts of the country. All the victims of the TPLF deserve justice.
    The heinous crimes such as emasculations of the male prisoners in the TPLF prisons is the crimes that can never be pardoned and deserve justice.

  3. Most of the Military are now against TPLF. They are hearing
    from their relatives what is happening in the country, and
    the soldiers are getting angry on Woyane every passing day.
    If TPLF tries to bring the soldiers to the cities and towns,
    most of the soldiers will finally stand with the people and
    shoot TPLF Generals and cadres. This will shorten Woyane’s
    life in Ethiopia! Just watch!

  4. DO NOT CRY LIKE A SISSY GIRL BABY !

    TPLF is an organization of millions of wise , brave , dedicated and professional visionaries !

Comments are closed.

Share