የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ በሚገርም ፍጥነት አዳዲስ ክስተቶችን እያሳየን ወደ ለውጥ ጫፍ እየወሰደን ይገኛል። በኢትዮጵያ ምድር የነጻነት ፀሐይን በነጻነት የምንሞቅባት ግዜ እሩቅ አይደለም። ግዜው የለውጥ ነው ወያኔም እንደ ደርግ ነበሩ ተብለው ታሪካቸው ሊነገር የቀረን ግዜ የባከነ የሚባለው ግዜ ነው። የመጣውን ስር ነቀል ለውጥ ወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው የትኛውም መፍጨርጨር ወይንም ጥገናዊ የሹም ሽር ለውጥ አያስቀረውም። የትኛውም የወያኔ ተለጣፋ ድርጅቶች ስርአቱን ማስቀጠል አይችሉም።የለውጥ ማዕበሉን ማስቆም የሚችል ምንም ኋይል የለም።
2010 በኢትዮጵያ ውስጥ በተፋጠነ መልኩ አዳዲስ እና ከበባድ የሚባሉ የለውጥ እና ፖለቲካዊ ክንውኖችን እያየን ነው። ከተራራ ላይ እንደሚከባለል ድንጋይ በፍጥነት እየተንከባለለ እየመጣ ነው። ድንንጋዩን ተራራው ላይ እንዲቆይ አቅፎ የያዘው ሳሩና አፈሩ ከከዱት ደግፈው ካልያዙት እየተንከባለለ ወደታች መውረድ ነው ያኔ ታድያ ካገኘው ነገር ጋር እየተጋጨና እየተላተመ ነው የሚወርደው። አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲህ ነው እስቲ የተከወኑትን ነገሮ ከብዙሃኑ ዋና ዋና የምንላቸውን እንይ።
1. ኤች አር 128 የሚባለው የአሸባረነት ህግ በወያኔ ላይ በአሜሪካ ፖርላማ ሊጸድቅ መሆኑ።
2. እስከ ጀረናልነት የሚደርስ የትላልቅ ወታደራዊ ሹመቶችን መሾም።
3. በአሸባሪነት ስም ከሶ ያስራቸውን የፖለቲከኛ እስረኞች በብዛት መፍታት።
4. የጠቅላይ ሚንስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመልቀቂያ ማመልከቻ ማስገባት።
5. የ6ወር ግዜአዊ አዋጅ በማወጅ አገሪቷን በወታደራዊ ስርአት ውስጥ ማስገባት።
6.የአይማራውና የኦሮሞው ህዝብ በተቀናጀ መልኩ በመናበብ ተቃውሞውን በጋራ በማድረግ ፋኖ እና ቄሮ የሚል ስም በመስጠት የማያቋርጥ የለውጥ ትግል ውስጥ መግባት።
ከላይ በጠቀስኳቸው ነጥቦች ላይ የኔ ግምት
ወያኔዎች ኢትዮጵያን እንደበፊቱ አንዱን ከአንዱ እያናከሱ ኢህአዴግ በሚለው ጭንቢል ውስጥ የበላይ ሆነው የሚቀጥሉበት አሰራር መቶ በመቶ የከሸፈ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል። ከእንግዲህ ወዲያ የኢትዮጵያ ህዝብ መምራትም ሆነ ማስተዳደር የማትችሉበት በምንም ጥገናዊ ለውጥ የማትድኑበት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በመሆናችሁ ነጻና ገለልተኛ ድርጅቶች ገብተው በኢትዮጵያ ህዝብ ለይ የተሰራውን ግፍና በደል ትክክለኛው መረጃ እንዲታወቅ መፍቀድ ነበረባችሁ።
ህዝቡ ከፍርአት አለም ወጥቶ ለለውጥ ፊት ለፊት በሚጋፈጣችሁ ሰአት ለማስፈራራትና ጀግና ወታደሮች አሉኝ ለማስባል የሄዳችሁበት አካሄድ ድርጅታችሁ ውስጥ እውነትን ተቀብሎ በምን መልኩ ማስኬድ የሚችል ሰው አለመኖሩን የታየበት ሲሆን መሆን የነበረበት ግን በዚህ ቀውጢ ሰአት ህዝብን የገደሉትን እና ያሰቃዩትን ወደ ስልጣን ሳይሆን ወደ ፍርድ በማቅረብ ለተጎዳው ህዝብ መድረስ ነበረባችሁ።
የፖለቲካ እስረኞችን የፈታችሁት በህዝብ ቁጣ እና በውጪ መንግስት ጫና እንደሆነ እየታወቀ እናንተ ግን የፖለቲካ ትርፍ በመፈለግ ህዝቡ በደስታ ይቀበለናል የምትለውን እሳቤ የያዘ መሆኑ ቢያሳዝነንም ቅል መሆን የነበረበት ህዝብ የመረጠውን ማሰር ሳይሆን እንደ ህዝብ ፍላጎት መፈጸም ነበረባችሁ።
ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለ ማርያምን በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ በማስባል ወደ ሌላ ስህተት መሄድ ሳይሆን ህዝቡ በነጻነት የተሳተፈበት ምርጫ በማድረግ በዲሞክራሲያዊ መንገድ መሪን ወደስልጣን ማምጣት መልካም ነበር።
የ6ወር አዋጅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በማንሳት ህዝብን በነጻነት የመናገር፣ የመቃወምና ሃሳቡን የመግለጽ መብቱን በማክበር ከእንግዲህ በአጋዚ ወታደር አንድም የሚገደል ኢትዮጵያዊ እንዳይኖር የአጋዚ ወታደሮችን ከህዝብ መሃል በማውጣት የህዝብ መብት ማክበርና ጥያቄዎችንም በመመለስ አገሪቷን ወደትክክለኛው የስልጣን ሽግግር በመውሰድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምን ማምጣት ይቻላል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንድ እርምጃ ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በአሁኑ ሰአት መራመድ የምትከፍሉት ዋጋ እጅግ የከፋ ይሆናል።
ሊሆን የሚገባው፦
የኤች አር 128 ህግን ከተቀበሉ እና በገለልተኛ ወገን ማጣራት ከተደረገ የደበቁት ዘግናኝ ምስጢር በሙሉ ሊወጣ ስለሚችል መፍቀደን አልፈለጉም። በተሰጣቸው የ28 ቀን ገደብ ካለፈች አልያም ገለልተኛ ወገን ገብቶ እንዲያጣራ አንፈቅድም የምትለውን ምላሽ እንዳይሰጡ አሸባሪ መንግስት ተብለው በአሜሪካ መፈረጁን ፈሩ። ስለዚህ አጭበርብረው የሚያልፉባትን ዘዴ መጠቀም ነበረባቸውና መፍታት ባይፈልጉም የፖለቲካ እስረኞችን በሙሉ ፈተናል ስለዚህ ከእንግዲህ ችግር የለም እንደ ዲሞክራሲ ጀማሪነታችን መጠን ይሄ ትልቅ ስራ ነውና ጉዳዩን እኛ ያለምንም ጣልቃ ገብነት የማጣራት ብቃት አለን የምትለዋን ለአሜሪካን ለመንገር ነበረ። ነገር ግን የፖለቲከኛ እስረኞች መፈታት ወያኔ የጠበቀው ሳይሆን ያልጠበከው ክስተት በማስከተሉ ከድጡ ወደማጡ በመግባት አገሪቷን በወታደራዊ ህግ ስር እንድትተዳደር አደረገው።
ወያኔ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታቱ መፍታት ፈልጎ ሳይሆን በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው እስረኞችን በመፍታት ከውስጥም ከውጪም አጣብቂኝ ውስጥ የከተተውን ክስተት የማለፊያ ዘዴ መስሏቸው ነበረ። ነገር ግን ከተፈቱ በኋላ ህዝቡና የፖለቲካ ታሳሪዎቹ ያደረጉት ውህደትና የህዝቡም የፖለቲከኛ ተፈቺዎችም ያደረጉት ጠንካራ ግኑኙነት ስላሰጋው ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ በመግባታቸው በፍጥነት ግዜአዊ አዋጅ በማወጅ ወደከፋው ችር ውስጥ ገብተዋል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ ያለግዜው የመልቀቁ ምስጢር የኔ የሚሉትን ሙሉ በሙሉ ሊያምኑት የሚችሉትን ለመሾም ነው። የቀድሞ ጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ የመልቀቂያ ግዜአቸው ሳይደርስ በመሞታቸው ምክትል የነበረው ሃይለማርያም ዋና ጠቅላይ ምኒስትር እንዳደረጉት ሁሉ ዛሬም ምክትል ጠቅላይ ምኒስትር የሆኑት ደብረ ጽዮን ወደ ዋና ጠቅላይ ምኒስትር የማምጣቱን ሂደት ሊከውኗት እንደሆነ እንገምታለን ምክንያቱም የተሰራው ቀመር የኔ የሚሉትን በቦታው ላይ ማስቀመጥ ስለሆነ።
የ6 ወሯ አዋጅ እየሆነ ያለው ነገር በጣም ስላሰጋቸውና ስላስደነገጣቸው በወታደራዊ አዋጅ ስር በማስገባት ከመጣብን መአበል እናልፋለን ብለው በማሰብ አዋጁን አውጀውታል። የህዝብን ጥያቄ እና በአገሪቷ የተከሰተውን የፖለቲካ ችግር ለመፍታት የሚሄዱበት መንገድ አገሪቷን ወደአደጋ ወያኔዎች ደግሞ ወደመቀበሪያቸው መሆኑን አንባቢው ልብ ይበል። ግዜ ፈራጅ እዚህ አድርሶናል።
ከተማ ዋቅጅራ
18.02.2018
Email- [email protected]