ህ.ወ.ሓ.ት እና ኢትዮጵያ ( ገብረመድህን አርአያ)

December 20, 2017

የህ.ወ.ሓ.ት.ወያኔ መሪዎች አሁን በስልጣን ያሉ ፤ ከድርጅቱ የተባረሩ መሪዎች ጨምሮ ሁሉ፤ ያ የተፈጥሮ ባህሪያቸው የሆነው ቅጥ አልባ ውሸት ትልቁ መሳሪያቸው ፤ተጠቅመው ፤በየሄዱበት በተሰበሰቡበት በህዝብ ፊት አይናቸው በጨው አጥበው የሚዋሹት ፤ህ.ወ.ሓ.ት. በኢትዮጵያ ዲሞክራሲና ፍትሕ ለማምጣት ለ17 ዓመታት ከደርግ ጋር የነበረው ውጊያ ፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች መስዋእትነት ከፍለዋል ፤እያሉ የውሸት ጡሩምባቸው ሲነፉ እስከ አሁን ድረስ ይደመጣሉ ።በሃገራችን አንድ ተረት አለ ፤ ፥ይህም ‹፤” ደሮን ሲያታልልዋት በመጫኛ አልዋት”ወደ ሚል ተረት ተረት ፤ ያመጣናል ፤በመሰረቱ ህ.ወ.ሓ.ት. ፀረ ኢትዮጵያና ህዝብዋ እንጂ ወዳጅ አይደለም ። ኢትዮጵያ በነሱ አጠራር ደግም የአበሻ ሃገር ብለው የሚጠርዋት ትግሉ ከመጀመራቸውና ትግሉም እንደ ጀመሩ ፤የጠላት ሃገር ብለው ፈርጀዋታል ፤ኢትዮጵያ የጠላት ሃገር ከሆነች ወያኔዎች ለምን ብለው መስዋእትነት ይከፍላሉ ? ወያኔ ለኢትዮጵያ ብሎ አንዲት የደም ጠብታ አልከፈለም አላየንም ፤ማን ይናገር የነበረ ነውና ፤ እንግዲህ እውነታው ይህ ነው ።ህ.ወ.ሓ.ት. ባውጣውና በሚከተለው ፖሊሴ (ፕሮግራሙ )ተከትሎ ፤ ኢትዮጵያ ህልውናዋን ሉአላዊነትዋን ለማፍረስና ለመናድ ፤ ህዝብዋን ጭምር ለክፉ መከራና ለማያባራ ችግር ዳረጋት እንጂ ፤ ህ.ወ.ሓ.ት. ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. እንድ የኢርትራ ጋዜጠኛ በ1ኛው ቀን ይህ ማለት ግንቦት 22 ቀን 1983 ዓ.ም የ90 አመቱ ዘራፊ ሌባ ሙሰኛ ስብሃት ነጋ ደሴ ከተማ ባንክ እና ሌሎች የገንዘብ ተቋሞች ሲዘርፍ አግኝቶት ፤አቦይ ስብሓት ኢትዮጵያ ተቆጣጠራቹሁ ምን ችግር ገጠማቹሁ ፤ውግያ ነበር ሌላም ካለ ይግለፁልኝ? በማለት ሲጠይቀው ፤ የሽማግሌው መልስ ፤ቅንጣት ታክል ችግር አልገጠመንም ፤ዘው ብለን ገባን በቀላሉ ኢትዮጵያን ተቅጣጥረናል ፤ከመቀሌ ጀምሮ ታጋዮቻችን በአውቶቡስና ሸራ በተሸፈኑ መኪናዎች ነው ያጓኋዝነው ፤አንዲት የጥይት ተኩስ አልተሰማም ፤ሲለው ፤ጋዜጠኛ ቀበል አደረገና >» እሞ በለስ ቀኒዓትና እያ በሉኒ > ( እና በለሱ ቀናን ይበሉኝ ) በመጠጥ ሰስ የተኮማተረው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ፊቱ እያሸ ሄደ ።

ኢትዮጵያ እጅግ አረሜኔ ደመኛ ጠላትዋ ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት.ቅኝ ግዛት ሥር ወደቀች ፤ህዝቡም በማያባራ የወያኔ ፋሽሽት አገዛዝ ወደቀ ።

ዛሬ ኢትዮጵያ በክፉ መልኩ የተጎዳች ሃገር ሆናለች ፤ በወያኔ ዘረኛ ስርአት ወድቃለች፤ ይህን ክፉ ጉዳትና መከራ ያንዣበባትም ገና ከ1967 ዓ.ም. ወያኔ የተባለው ፀረ ኢትዮጵያ ባእዳን ኃይሎች እርዳታና ድጋፍ ተመስርቶ ።የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. ደደቢት በረሃ ወርዶ የትጥቅ ትግሉን እንደ ጀመረ በፀረ ኢትዮጵያ ፤በፀረ ህዝብ አንድነት ፤በፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ፤የተደራጀው ቅጥር ፀረ ሃገርና ፀረ ህዝብ ፤የማፍያ ባንዳ ‹ቡድን ። ታላቅዋን የትግራይ ዲሞክራሲያዊት ሃገር መንግሥት › እንመሰርታለን በለው ፤የኢትዮጵያ የታሪክ እምብርት የሆነችው ትግራይን ለመገንጠል የተነሳው ቡድን፤ደደቢት በረሃ ተሰባሰቡ ይህች ገናናዋ የትግራይ መንግሥት የምትመሰረተው በአማራው ከርሰ መቃብር ላይ ነው ፤ተብሎም በመሪው በኩል ታወጀ ።= ፀረ ኢትዮጵያ የህ.ወ.ሓ.ት. ቡድን በድርጅቱ መሪ አረጋዊ በርሄ በኩል የቀረበው የተስፋፊነት ፖሊሲ በወቅቱ የነበሩት መስራቶች ተቀብለውበሙሉ አፀደቁት ፤ በትግራይ አካባቢ የሚገኙ አዋሳኝ ጠቅላይ ግዛቶች ጎንደር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ ግዛት፤ አፋርን ጨምሮ ፤ ሰሜን ጎንደር እንዳለ በሙሉ ፤ደቡብ ወሎ እንዳለ በሙሉ ፤የትግራይ ግዛት ነበር ፤አጼ ዮሓንስ ከሞቱ በኋላ ምኒሊክ መንግሥታዊ በትረ ሥልጣኑ ከያዘ፤ በአማራው መንግሥት ሃገራችን ትግራይ ነፃነትዋ ፤ተነጥቃ ፤ በአማራው ቅኝ ግዛት ቀንበር ወደቅን ። ብለው ፤የሁለት ጠቅላይ ግዛቶች ፤እጅግ ሰፋፊና ለም መሬት ወደ ትግራይ በማጠቃለል በካርታ አዘጋጅተው ያዙ ፤ይህ ብቻ አይደለም በዚህ ላይም አማርኛ የጠላት ቋንቋ ነው ተብሎም ተነገረ ፤ማነም እንዳይናገሩ ፤የጎንደሬው አማራ ፤ማንነት፤ ባህልና ወግ እንዳይጠቀም እንዳያነሳ በወያኔ ተከለከለ ፤ በመስቀል፤ገና ፤የአዲስ ዓመት መለወጫ ወ.ዘ.ተ. የቤተ ክርስትያን በዓላት በየአመቱ የሚከበሩ ጭምርም ታገዱ ። -በዚሁ የአማራው ፤ የጎንደር ፤የወሎው አማራ ከዘር ዘራቸው ተዋልደው የመጡ ፤ኢትዮጵያውያን ዜጎች ፤ማንነታቸውና ባህል ወጋቸው ተደፍሮ የማያውቅ ፤ በህ.ወ.ሓ.ት. የተስፋፊነት ፖሊሲ ፤የወያኔ ባንዳ መሪዎች ለምትፈጠረው ታላቅዋ የትግራይ መንግሥት ፤ህብታምና ለም የበለፀገች ሃገር እንድትፈጠርላቸው ፤ግዛታቸውም እንዲሰፋላቸው ፤በ1967 ዓ.ም. የተዘጋጀው ፕሮግራማቸው ተጠናክሮና ተዘጋጅቶ ፤ የካቲት ወር 1968ዓ.ም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት ፖሊሲ ( ፕሮግራም ) በሚል ስያሜ ይፋ አደረጉት ።

ከዚህ ጊዜ ተነስቶ ነው በአማራው ሲኦል የወረደበት ዘሩን ማጥፋት በህ.ወ.ሓ.ት. በወቅቱ መጠሪያው ፤ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.)አማራ ደመኛ ጠላት በለው የውያኔ መሪዎች የፈረጁት ።የመጀመሪያው ተጠቂ ግን የትግራይ ህዝብ ነበር ፤ምክንያት የወያኔ ፕሮግራም አንቀበልም እናንተም ለትግራይ ህዝብ አትወክሉቱም ፤ወካይ ተወካይ የሚባል ነገር አንፈልግም ፤በማለቱ ህ.ወ.ሓ.ት. 1ኛ በህዝብ ግኑኝነት በኩል እያሳፈነ 2ኛ ክርቢት ተብሎ የተቋቋመ ጠላፊና አፋኝ ገዳይ ቡድን ፤ 3ኛ አጥፍቶ ጠፊ ሽብርተኛ ፈዳያን ተብሎ የሚታወቀው ቡድን አሰልጥኖ የከተማው ህዝብ የገጠሩም ህዝብ በጠራራ ፀሃይ የፈጀው 4ኛው በድርጅቱ በተቋቋመው ህቡእ የስለላ ቡድን የትግራን ህዝብ በመግደል ህዝቡን ጨረሱት ፤ዛሬ በትግራይ ውስጥ ታሪክ ነጋሪ የለም ፤ አጥፍተዉታል ። በወቅቱ የትግራይ ህብረተሰብ እንዴት እንዳጠቁት እጅግ አሰቃቂና ነበር ፤ ህፃናት ፤ ሽማግሌው፤ እንት፤ አባት፤ ወጣት፤ ፆታን ሳይለዩ አርደዉታ ገድለዉታል። ወያኔ ቀዳሚ መእራፉ በትግራይ አጠናቅቆ ወደ አማራው ፊቱ በማዞ ር የዘር ማፅዳት (GENOCIDE )ገባ ፤በአማራው ላይ ህ.ወ.ሓ.ት. የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይህች ዓለም ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን በዚች ዓለም በሌላ ሃገር ታይቶዋል ተከስተዋል የሚል ታሪክ የለም ፤ይህ ልዩ ነው ፤አገዳደሉ ባለ ብዙ ዘርፍ ብልሀትና ዘዴም ጭምር ነው ።ቀኑ ብቻ ይውጣ ።ኋላ ኋላ ግን ለወያኔ በሰፈረው ቁና ትሰፈራለህ ነውና ።

እንግዲህ ይህ ፕሮግራም (ፖሊሲ ) ነው ፤ለኢትዮጵያና ህዝብዋ መቅዘፍትና ሲኦል ፤ችግር ፤ርሃብ ስደት ፤ ለእስርና ሰቆቃ ግድያ የዳረገው እያደረሰበት ያለው ። የአንድ ኢትዮጵያዊ ማንነት፤ባህልና ወግህ ተነጥቆ ፤ተወልደህ እትብትህ ከተቀበረበት መሬትህ አፈናቅሎ ፤ ተወልደህ ያደግበት መሬትና ቦታ ለውጭ ባእዳን ተሽጦ ፤ሱዳን በዋናነ፤ ለመከራ የተዳረከው ። ዛሬ በፋሽሽት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ኢትዮጵያን በቅኝግዛት ስርአቱ ወድቃ ፤ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ ፤ ህገራችን የስቃይና ሲኦል መሬት ሆናለች ፤ ነዋሪ ህዝብዋ በጨለማ የህ.ወ.ሓ.ት. ፋሽሽት የአፓርታይድ ስርአት ኢትዮጵያዊነቱ ተገፎ ይኖራል ።

እስከመቸስ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በዚሁ የሶቆቃና የችግር ማእበል የሚኖረው ?ወያኔዎችና፤ አባላቸው ፤ደጋፊዎቹ ፤ኢትዮጵያን ተቆጣጥረው ፤በምቾትና በሃብት ዝርፍያ ተጥለቅልቀዋል ፤ሃገራችን ፤ኢትዮጵያም ለሽያጭ እያቀረቡ ፤ተቆርጣ ተቆርጣ ለገብያ እየቀረበች ተሸራርፋ ልታልቅ ትንሽ ቀራት ፤መላ በል ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሃገር ዳር ድንበር ሲደፈር የሁሉ ኢትዮጵያዊ ጉዳትና ጥፋትም ነው //

ዛሬ ኢትዮጵያ የሚገዛ ያለው ስርአት የህ.ወ.ሓ.ት.ፋሽሽት የደደቢት በረሃ ማፍያ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ህዝብ ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ፤ከአንድነቱም ኢትዮጵያ ከብዙ ወራሪ ባእዳን ጠላቶችዋ ተፋልሞ አንድነትዋን ሉአላዊነትዋን አስከብሮ ጠብቆ ፤ተከታትለው ለሚመጡ ልጆቹ አስረክቦ ታፍራና ተከብራ ለሺህ ዘመናት በጠላት ሳትደፈር የመጣች ሃገራችን ፤አሁን በወያኔ ስርአት ፤ተደፍራ ዓለም አቀፋዊ ድንቦሮችዋ ተንደው ፤የባሕር ደንቦሮችዋ ተነጥቃ ዝግ ሃገር ሆናለች።

ኢትዮጵያ ለዚሁ ውድቀት የተዳረገችበት ዋናው ምክንያት በ1967 ዓ.ም የተፈጠረው የወያኔው ቡድን ፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር አልነበረችም የዛሬዋ ኢትዮጵያ በምኒሊክ ዘመነ መንግሥት የተፈጠረች ሃገር ናት ፤በማለት ህ.ወ.ሓ.ት. ፀረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳው በጽሁፍ ፤በቃል አስተምህሮ በማካሄድ የዛሬው የኢትዮጵያ ቅኝ ገዢው ስርአት ፋሽሽቱ ወያኔ ከተፈጠረው ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬው ዕለት አመራሩ ሁሉ ተከታትለው የመጡም በዚሁ የፀረ ኢትዮጵያ ህልውና ሰፊ ዘመቻ በመክፈት ሃገርና ህዝብ ክፉኛ አጥቅተዋል ፤ኢትዮጵያን አፍርሰዋል ድንበርዋ በጥንታዊ ጠላትዋ ሱዳን ተደፈር ነው ፤ ኢትዮጵያዊው የአማራ ህዝብም ከትውልድ ቦታው ከእርሻው ፤ከሞኖሪያ ቤቱ ቀዩ እያፈናቀሉት ይገኛሉ ፤እየገደሉትም ነው ።በረሃ በነበርንበት ፤በ1975ዓ.ም የኢትዮጵያ ለምና እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን መንግሥት ለጊዚያዊ ጥቅማቸው ሲሉ የሽጡት ወያኔዎች ፤ በወቅቱ ትግራይ ነፃ እናወጣት አለን ብለው በሚንቀሳቀሱባት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት ያላገኙ ፤በህዝቡ ከፍተኛ ሲወገዙ ፤የነበሩበትም ጊዜ ነው ፤በዚሁም ላይ የትግራይ ህዝብ ከደርግ ጎን በመቆም ሲወጋቸው የነበር ወቅትና ጊዜም ነበር ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከነ አካቴውም ወያነ ህ.ወ.ሓ.ት በፍፁም በፍፁም አያውቀዉም ።በዚሁ ጊዜ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች እጅግ ከባድ የሃገር ክህደት ወንጀል ፈፅመዋል ። ዝርዝሩን ቀጥለን እንመልከት።

የተፈጸሙት ወንጀሎች

ከዚሁ ህ.ወ.ሓ.ት. ቀደም ሲል በትግራይ ህዝብ የፈፀማቸው ወንጀሎች ፤በአማራው ላይ የተፈፀሙ የዘር ማጥፋት እና አሰቃቂ ግድያዋች በሃይማኖትም በእስልምና በክርስትና ሁለቱ የኢትዮጵያ እምነቶች ለማጥፋት ሲያካሂደው የነበረ ዘመቻ ። ህዝብ አፈናቅሎ ገድሎ አጥፍቶ ፤ታላቅዋን ትግራይ ለማስፋፋት እና የታላቅዋን ትግራይ መንግሥት ለመመስረት ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔ የፈፀመው ፋሽሽታዊ ግፍ ወንጀል በይቀርታ የምይታለፉ ናቸው። ሃገር ለባእድ አሳልፎ ለጊዝያዊ ጥቅሙ የሸጠ የዘር ማጥፋት በህዝብ ላይ የፈፀመ ሌላም ወ.ዘ.ተ በዝምታ ሊታለፍም አይገባም ፤ የወያኔ ቡድን በኢትዮጵያና በህዝብዋ የሰራቸው ጥቁር ታሪክ ከኢትዮጵያ ታሪክና ከኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ ሊፋቅ አይችሉም ።አንዳንድ የዋሃን ግን ደግሞም ሆን ብለው አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወያኔ ቀደም ብሎ የፈፀመው ጥፋት እንርሳውያለፈው አልፈዋል ፤አሁን ወያኔ ለድርድር እንዲቀርብ እናርገው ወ.ዘ.ተ. የሚሉት በእጅጉም ስህተት ነው ። ፤ያ በዚሁ ፋሽሽት ወያኔ በዘር ማጥፋት ወንጀል የፈሰሰው ደምስ ፤ የትግራይ ደምስ ፤የኦርሞው ደምስ ፤የጋምቤላው፤ አኝዋክ ደምስ ወ.ዘ.ተ. አሁንስ በአማራው ፤በኦሮሞው ፤በጋምቤላው ወ.ዘ.ተ. እንደጎርፍ የሚፈሰው ያለ የንፁሃን ኢትዮጵያውያን ደምና ሂወት ወኋላ ገሸሽ ተደርጎ መርሳት ተገቢም ትክክል አይደለም ።በታሪክ በሕግ ጭምርም ያስጠይቃል ።እኔና ዘመዶቼ ጉዳቱ ስላልደረሰብን የሌላው ምኔ ማለት ነው ። ከህ.ወ.ሓ.ት. ፋሽሽትድርጅት ድርድር ፈፅሞ አያስፈልግም አይቻልም ፤ተፈጥሪያዊው ባህሪውም አይፈቅድለትም ።ህዝብ ሃያል ነውና በህዝባዊ ሃይል መቃብሩ መግባት አለበት ። ያች እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበርዋ ለስንት ሺህ አመታት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፤ አማራው ፤ኦሮሞው ፤ጋምቤላው ፤ ትግሬው ፤ አፋሩ ፤ጉራጌው ፤ድፍን ኢትዮጵያዊ ደሙ እያፈሰሰ በሂወቱ ከባድ መስዋእትነት እየከፈለ ያቆያት ኢትዮጵያ ፤ ከሃዲው የህ.ወ.ሓ.ት. ቡድን ለሱዳን መንግሥት የሸጠው ከ1600 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው ከሁመራ ተነስቶ ሙሉ በሙሉ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ከ40 እስከ 80—100–ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ የገባ ፤የኢትዮጵያ ግዛት ባለ ታሪክ ላም ሰፊ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ሽጠው ሃገርና ህዝብ አስደፍረዋ ፤ኢትዮጵያ በዛሬው ትውልድ ተደፍራለች የጥንት ጠላቶችዋ አመቺ ጊዜ አግኝተዋል ፤ኢትዮጵያን የምናጠቃት የምንወራት አሁን ነው ብለዋል ። ወያኔም በኢትዮጵያ በለሱ ቀንቶት ስልጣኑ እንደጨበጠ በ1975 ዓ.ም. ከሱዳን መንግሥት በገባው ውል መሰረት ለዛሬ የሱዳኑ መንግሥት በጀነራል አልበሽር የምትመራው ሱዳን አሳልፎ በመስጠት የኢትዮጵያ ዳር ደንበር ተደፍሯል ፤ይህ ለሞላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቃት ሞትም ነው ።በነዚህ ቦታዎች ያለው አማራ ልቀቅ ይህ የሱዳን መሬት ነው እየተባለ ከትውልድ ቦታው ከሃገሩ ኢትዮጵያ በሱዳንና በወያኔ ጦር ሃይሎች ከባድ የጥቃት እርምጃ እየተወሰደበት ህዝብ እየተሰቃየ ይገኛል ። ከዚህ ከሃዲ ስርአት በምኑ ባህሪያቱ ነው የምትደራደረው ? ህ.ወ.ሓ.ት. በተፈጥሮው ባህሪው ፤ፀረ ኢትዮጵያ ፤ ፀረ ህዝብ ፤ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ፤ ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ነው ፤ያልተፈጠረው ባህሪ ፤አሁን ሊያመጣ አይችልም ፤ ድንጋይ ወደ አምባሻ ይለወጣል ? በምንም ታአምር አይለወጥም ። ወያኔ ማለትም ይህ ድንጋይ ነው ።ይህ ከወያኔ ተደራድረን በሥልጣኑ እንዲቆይ እናደርጋለን የሚል ሃሳብ የሚመነጨው ግልፅ ነው ። ከተባረሩ የወያኔ ከፍተኛ ሃላፊዎች የነበሩ ከነ አረጋዊ በርሄ ፤ግደይ ዘርአጽዮን ፤ ወ.ዘ.ተ. ሌላውም ጥቅም ፈላጊ ተጣቃሚ ነው ። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቅልበሽ አለች ነው ። ወሳኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው ፤ ህዝብም በወያኔ ላይ ትግሉ አጠናክሮ ቀጥሎበታ ፤እኛም ክህዝብ ጎን እንቁም ።እነዚህ የህ.ወ.ሓ.ት. አንጋፋ መሪዎች በሃገርና በህዝብ ከባድ ወንጀል የፈፀሙ ፤ኢትዮጵያን ለዚሁ ክፉ መከራና አደጋ የዳረጉ መሪዎች ናቸው ፤ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ችግር ፈጥረዋል፤ መቋጫ የሌለው ። በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ግን መፍትሄው ያገኛል ። የኢትዮጵያ ሉአላዊነትም በህዝብዋ መስዋእትነት ዳግም ክብረ ወሰኑ ይቀዳጃል ።ጥርጥር በሌለው ። የወያኔ መሪዎች በወንጀለኛ ድርጊታቸው እንዳይጠየቁ የማምለጫ ዘዴያቸው ብዙ ነው ።እውቁ ኢትዮጵያዊው ጋዜጤኛ ሳዲቅ አህመድ ሁል ጊዜ የሚናገራት ጥቅስ “ ልብ ያለው ልብ ይበል” እውነተኛ አነጋር ፤ አሁንም “ ልብ ያለው ልብ ይበል “ ከመቸ ነው እነ አረጋዊ እነ ግደይ ለኢትዮጵያና ህዝብዋ ተቆርቋሪ የሆኑት? የአማራው ህዝብ የጨረሱት ዘሩን ያጠፉት ፤አማራ ደመኛ ጠላት የትግራይ ፤ ብለው ፈርጀው በወልቃይት፤ በጠለምት ፤በጠገዴ ፤ በየትም ቦታ የተገኘው አማራ ከ1969 ዓ.ም. እስከ 1978ዓ.ም የፈጁት ያጠፉት ፤ እነዚህ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች አይደሉም እንዴ ?” ናቸው “ናቸው” ። እነዚህ መሪዎች እይደሉም እንዴ ? የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ለጊዜዊ ጥቅም ሲሉ አሳልፈው የሸጡ ? “ ናቸው “ ናቸው “ ዛሬ ከባድ ችግር ኢትዮጵያዊ አማራ ክመሬቱ እየተፈናቀለ እየተገደለ ውጣ ፤ይህ የሱዳን መሬት ነው እየተባለ የቁም ስቃይ በአማራው ወርዶበት ያለው ? እነዚህ ፤ አረጋዊ በርሄ ና ግድይ ዘርአጽዮን በፈጠሩት መዘዝ አይደለም እንዴ ? ነው ። የሌባ ደረቅ ልብ ያደርቅ ፤እንደሚባለው አሁንም ኢትዮጵያ ገብተው ሚኒስተር-፤-ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን ይዳዳቸዋል ፤ ወንጀለኛ ነህ ቢሉህ በሰማህ ፤ አሉ አንድ ትልቅ አዛውንት ፤ ሁሉ ኢትዮጵያዊ እነዚህ ወንጀለኞች እነ ግደይ ዘርአጽዮን አጥብቆ መከታተል ሃገራዊ ግዴታው ስለሆነ ፤ መታለል የለበትም ።ዛሬ የወያኔው ስርአት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተተፋ ፤የተወገዘ ስርአት ፤እምቢ ለወይኔ ብሎ ህዝብ በተነሳበት ፤ወያኔ በመቃብሩ አፋፍ ባለበት ሁኔታ እነ ግደይ፤ አረጋዊ ፤ወ.ዘ.ተ. ከገብሩ አስራት በስተቀር የወያኔን ሂወት ለማዳን በድርድር እንፈታዋለን ማለታቸው እነዚህ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ወክለው ለምናገር መብት የላቸውም ። አይፈቀድላቸውም ። የዜጎች ደም ያፈሰሱ ሃገር የሸጡ ወጀለኞች ናቸው ። በወያኔ ፋሽሽታዊ አገዛዝ ህዝብ አምርሮ፤ በቃኝ የወያኔ አገዛዝ ብሎ እየታገለ ባለበት ጊዜ ። የሃገር ከሃዲዎች የወያኔ ዕድሜ ለማዳን ለማትረፍ ፤ የሚያካሂዱት ያለ እንቅስቃሴ በውጭ ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እነዚህን ፀረ ሃገርን ፀረ ህዝብ ከማንኛውም መድረክ ማግለል አለበት ፤ግዴታውም ጭምር ነው ።የኢትዮጵያ ህዝብ ተግሉ የወያኔ ስርአት አስወግዶ ፤ነፃነቱን ለመቀዳጀት እንጂ ከወያኔ እየተደራደር እየ ሞተ እየተገደለ መኖር አይፈልግም ።

5. ህ.ወ.ሓ.ት. ከ1968 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የእስልምና የክርስትና ሃይማኖቶች ለማጥፋት የተሰማራ ሲሆን ሐይማኖት የግል ነው የሚል መርህን በመፃረር በሐይማኖቶች ጣልቃ በመግባት ገዥው ስርዓት ወያኔ ህ.ወ.ሐ.ት.የራሱ አገልጋይና በመሳሪያነት ሊጠቀምባቸው ስለሚፈልግ ዛሬ በኢትዮጵያ የእስልምና ሐይማኖት የግፍ ሰለባ ሆኖ የሐይማኖቱ መሪዎች በየወህኒ ቤቶች በእስር እየማቀቁ ሲገኙ ቀሪው የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ በየመንገዱ እየተገደለና ቀሪውም ወጣቱ ከየመንገዱ እየታፈሰ በየወህኒ ቤቱ ታስሮ ይገኛል ። በክርስትና ሐይማኖትም ህዝብ በመክፋፈል የወያኔ ስርዓት ተሰማርቶ ሕይማኖቱ እያዳከመው ይገኛል።ይህም የሰባአዊ መብት የሚፃረር ነው። በአለም ሕግም ያጠይቀዋል:

6. ህወሓት የኢትዮጵያን ታሪክ ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳ፣ በእንክብካቤ ተይዘው የቆዩትን የቤተክርስትያናት ቅርሶችን፣ ታሪካዊ መጽሓፍትን እና መዛግብትን በመሸጠ በማቃጠል የሃገር ታሪካዊ እሴቶች በማጥፋት በማውደም ተስማርቶ የኢትዮጵያ ታሪክ እያጠፋው ይገኛል ።

7. ህወሓት በአማራው ላይ በመድሃኒት አማካኝነት ዘርን በማምከን የዘር ማጥፈት ወንጀል ፈጽሟል፣እየፈጸመም ይገኛል ።

8. ህወሓት የሕዝብ ሃብትና ንብረት ወርሷል፣ የሕዝብን ሃብትና ንብረት በመዝረፍም ተሰማርቶ የራሱ የህ.ወ.ሐ.ት የግል ንብረት የሆነው ኢ.ፈ.ር.ት.፡ለማጭበርበር እንዲመቸውም በትግራይ ህዝብ ስም ት፣ እ፣ም፣ት፣ ማለት ትካል እግሪ ምትካል ትግራይ የሚል ሽፋን በመስጠት 1ኛ በትግራይ ህዝብ ስም ማጭበርበር የህዝብ ማንነትና መብት የሚፃረር ከመሆኑ የትግራይ ህዝብ በኢ.ፈ.ር.ት .ተጠቃሚ በማስመሰል የህ.ወ.ሓ.ት. ካድሬዎች የውሸት ወሬ በማሰራጨት ፤የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊ ወንድሙ እህቱ እንዲ ጠላ እንዲገለል ሰፊ ዘመቻ አካሂደዋል አሁንም ከዚሁ ወራዳ ተግባራቸው አልወጡም ፤ ህ.ወ.ሐ.ት. ምንም መብት የሌው በህዝብ ስም መሽቀትና ማወናበድ ዓለም አቀፍ ሕግ የጣሰ ወንጀለኛ ተግባር ነው።

የደርግ ቀይ ሽብር ለወያኔ ትልቅ አስተዋፀኦ ያበረከተም ነው።ቀይ ሽብሩ እንደተፋፋመ በስንት ሺህ የሚገመት ወጣት ሴት–ወንድ የትግራይ ልጆች ተቀላቀለ ፤በወያኔ ውስጥ ሶቆቃ፤እስራት ፤ግድያ የሌለ ምስሏቸው ፤ ወያኔ ጉልበቱም እንዲ ፈረጥምም አደረጉት ፤ በዚሁም ላይ ድሀው የገበሬ ልጅ በሀይል በማስገደድ ትግሉ ተቀላቀል እየተባለ በስንት ሺህ የሚቆጠር የገበሬ ልጅ በማቀላቀል ህ.ወ.ሐ.ት. አሁን ግዙፍ የተደራጀ ድርጅት ሆኖ ወጣ ። ወደ ኢርትራ በቀይ ኮከብ ዘመቻ ውግያ በመላክ ወጣት ሴት ወንድ ኤርትራ ሳሕል በረሃ ሻዕብያን ለመርዳት ተልከው በውጊያው ሞተው ቀልጦው ቀርተዋል ።

የኦሮሞ ህዝብ

ኢትዮጵያዊው የኦሮሞው ህዝብ የህ.ወ.ሓ.ት.የጥቃት ሰለባ የሆነው ከ1985 ዓ.ም .የጀመር ሲሆን ፤ህዝቡ እጅግ ክፉ ሶቆቃና መከራ ደርሶበታል ፤አህንኑም ንፁህ ኢትዮጵያ ኦሮሞው የጥቃት ሰለባ በመሆን ስቃይ እየደረሰበት ይገኛል ።
የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ዋልታና መከታ በመሆን እናት ሃገሩ ኢትዮጵያ በተለያዩ ብርካታ ባእዳን ጠላቶች ፤በኢትዮጵያ ወረራ ለማካሄድ በተነሱበት ወቅት ለምሳሌ ድርቡሾች፤ግብፆች፤እንግሊዞች ፤ጣልያኖች ፤ወ.ዘ.ተ. ተደጋጋሚ ወረራዎች ሲፈጸምባት የኦሮሞ ህዝብ ሃገሬ ኢትዮጵያ በውጭ ጠላት አትደፈርም ብሎ ግንባር ቀደም መሪ በመሆን ለእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ከወገኑ፤ አማራው፤ጋምቤላው፤ትግሬው፤አፋሩ ፤ጉራጌው ፤ኩናማው ፤አጎቡ ፤ወ.ዘ.ተ. በመሆንና በመተባበር ወራሪ ጠላቶች ቅስም ሰብሮ አሸንፎ የእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ዳር ደንበር ያስከበረ ኢትይጵያዊ ነው ። ወያኔ በለሱን ቀንቶት በአሜሪካ እና በእንግሊዝ ተደግፎ ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ስርአቱ እንደወደቀች የአማራው ዘር ማጥፋት ከትግሉ መነሻ የጀመረው የአማራው ህልውና አመናምኖ ለማጥፋት ከደደቢት ይዞት የመጣው ፖሊሲው በመቀጠል ።የአሮሞ ህዝብም በዚሁ የህ.ወ.ሓ.ት. የጥቃት ዘመቻ ቀለበት ውስጥ ገባ ።

የአሮሞ ህዝብ ጥቃት

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፤የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ አለኝታ መሆኑ ፤በሃገሬ ኢትዮጵያ አትምጡብኝ ሃገሬ እና የሃገሬ ህዝብ ለክፉ መከራ አሳልፌ አልሰጥም የሚል በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ህዝብ መሆኑ ይገነዘባል ፤ያውቃል ። ወያኔው ህ.ወ.ሓ.ት. ይህ አሮሞው፤ አማራው ፤ ካለ በቅኝ ግዛት የተቆጣጠርኩዋት ሃገር ለመኖር አያስችለኝም ፤በማለት ልክ በአማራው ያካሄድኩት የዘር ማጥፋት ፤በኦሮሞውም ይደገማል የሚል መፈክር ይዞ በመነሳት ።ለኦሮሞ ህዝብም በተለያዩ የጥቃት ዘዴዎች አቀነባብሮ አስልቶ ጥቃቱን ጀመረ ። አተገባበሩም ።

1ኛ የኦሮሞ መሬት ፤የእርሻ መሬቱ ፤ የከርሰ መሬት ማአድናት ወርቅ፤ብር፤ወ.ዘ.ተ. ያከማቸ በኢንቨስትመንት ስም በመንግስት ይዞታ አጠቃልሎ በመያዝ ህዝብ አፈናቅሎ በመሸጥ በመለወጥ ወያኔ ተሰማራ ።የኦሮሞ ህዝብ ሜዳ ላይ ተጣለ ።

2ኛ የሚመካበት ጫካዎች ዱሮች ወ.ዘ.ተ. በልማት ስም ማውደም ።

3ኛ ከሚኖረው ወረዳው ፤ቀበሌው በልማት ስም በግዴታ በወታደር ሃይል ማፈናቀል መኖሪያና መዳረሻ ማሳጣት ።

4ኛ በኦሮምያ ውስጥ ወንዞችና አነስተኛ የጅረት ወንዞችም በብዛት ስላሉ ህዝቡም ከአመት እስከ አመት በእርሻ መስኖ ተጠቃሚ ፤የተለያዩ አትክልቶች ፤የአትክልት ፍሬዎች ተጠቃሚ ሆኖ የኖረ በመሆኑ ፤ይህ ትልቅ የሃብት ማግኛ፤ መሬት የመንግሥት ስለሆነ ፤ በመሆኑም ፤በመንግሥት ስም ውርስ ተደርጎ ፤በአካባቢውም የሚኖር ኦሮሞዎች ሁሉ በመንግሥት ወታደር በሃይል ተገዶ ቦታው እንዲለቅ መደረግ አለበት ተብሎ ከየቦታው አፈናቀሉት በወታደር ተገዶ ለቀቀ ፤ወያኔ ወረሰው ፤የመሬቱ ባላባት ህዝብ ወድቆ ቀረ ።ዛሬ 90%የኦሮሞ ህዝብ መሬት አልባ ያደረገው ።ለስደት መከራ የዳረገው ።ይህ በተፈጥሮ ሃብታም መሬት ህ.ወ.ሓ.ቶች ተከፋፍለው በመያዝ ፤ሳውዲ ስታር ፤ሌሎች የውጭ ሃገር ቱጃሮች ተከፋፍለው በመያዝ ፤የአሮሞ ህዝብ አውላላ ሜዳ ተጥሎ ችግር ላይ ወድቆ ይገኛል ።

5ኛ የጫት ንግድም በመንግሥት ቁጥጥር መግባት አለበት ተብሎ የወጣ ፖሊሲም ፤ተግባራዊ በማድረግ የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር የነበረው በሞት የተቀዘፈው የባንዳ ልጅ ራሱም ባንዳ መለስ ዜናዊ እና ሚስቱ አዜብ መስፍን እጅ ገባ ።

6ኛ ከጉሊት ንግድ እስከ ትልቁ የንግድ እንቅስቃሴ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. አባል ያልሆነች/ ያልሆነ ፤ከንግድ እንቅስቃሴው መታገድ አለበት ተብሎ ታገደ ።ብዙ የእገዳ ውሳኔዎችና ተግባሮችም ተወሰነበት በተግባርም ዋለ ።

7ኛ በ2007 ዓ.ም. የኦሮሞ ህዝብ የገዳ በአል ባህሉና ወጉ በሚያከርበት ዓመታዊ በአል ብሸፍቱ ፤በአጋአዚ ልዩ ኮማንዶ በበአሉ ቀን ከ1000 ሺህ (ከአንድ ሺህ ) አሮሞዎች በአንዲት ጠራራ ፀሃይ ቀን ተገድለዋል ፤በብዙ መተዎች ቆስለዋል ።በእንደዚህም በሌላም ነው ኦሮሞው በወያኔ እያለቀ ያለው ።

ከላይ በትንሹ የተጠቀሱ የመብት ነጠቃ የዜግነትና ማንነት ነጠቃ በአሮሞ ህዝብ እየተፈፀሙ ናቸው ፤ይህም ሁሉ በጋምቤላ ህዝብም ተግባራዊ እንዲሆኑ ስለተወሰነ ፤በጋምቤላ ህዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ፤ተፈፅሞበታል ።ይህ የጋምቤላ ህዝብ 90% መሬቱ ተቀምቶ ለህ.ወ.ሓ.ት አባላት የሆኑት ትግሬዎች ታድሎ ፤የጋምቤላ ህዝብ ተፈናቅሎ ውጣ ተብሎ በአጋአዚ ወታደሮች ተገድሎ ተጨፍጭፎ ፤ሂወቱን ይዞ ያመለጠም ለስደት ተዳርጎ በሞት ሽረት ይገኛል ።

እንዚህ ከላይ በትንሹ ባጭሩ የተጠቀሱ ሁሉ የዘር ማጥፋት ወጀሎች ናቸው ።በተባበሩ መንግሥታት ሕግም በማያሻማ መንገድ ገልጾታል ፡”የአንዲት ሃገር ህዝብ ፤በመንግሥት ስልጣን ያለው ስርአት ህ.ወ.ሓ.ት. ፤ህዝቡ ከሚኖርበት ፤ቦታው ፤ከእርሻው፤ከቤት ንብረቱ ማፈናቀል ፤ህዝብ ለችግርና መከራ ፤ለርሃብና በሽታ ፤ ለሞት ፤ያፈራው ሃብት ንብረት ማውደም ብሎም በጉልበት በመሳሪያ ኃይል መንጠቅ መዝረፍ ያፈራቸው የጋማ እንስሣትም ለሞት ጥፋት ተዳርገው ፤ይህ ሁሉ ተደምሮ ስርአቱ “ በህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት(GENOCIDE ) ወንጀል ፈፅመዋል ። በተ.መ.ድ .የተወሰነ ሕግም ይህ ነው ። በዚህ ድርጊቱም በከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ነው ፤ይላል የተ.መ .ድ. ።በአሮሞ ህዝብ ህ.ወ.ሓ.ት. ይህ የዘር ማፅዳት ተግባርም በትክክል ፈፅሞታል ። ስለሆነም ኢትዮጵያዊው የኦሮሞ ህዝብ በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመበት ።

የህ.ወ.ሓ.ት. ፋሽሽት ገዢ ቡድን ፤ የአሮሞን ህዝብ “” ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ “” እንደተባለው የኦ.ነ.ግ. ሽብርተኛ ድርጅት አባልና ደጋፊ ናችሁ ብሎ በውሽትና በስም ማጥፋት ሞላው የአሮሞ ህዝብ ወንጅሎ ፤ህዝብ ባልፈፀመው ድርጊት ፤ከየቤቱ ፤ ከስራው፤ከእርሻው ከተለያዩ ቦታዎች ወጣቱ ፤ ሽማግሌው ሴት ወንድ ሁሉ በፖሊስ ፤በህ.ወ.ሓ.ት.ደህንነቶች ፤በአጋአዚ ጦር ፤ተለቅሞ ፤በሁሉ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወህኒ ቤቶች በመቶ ሺዎች ኦሮሞዎች ታስረው አሰቃቂ የቶርቸር ተፈፅሞባቸው ፤በዚሁም በተለያዩ በሽታዎች ለሞት ሰላባ ሆነዋል ፤አሁንም የህ.ወ.ሓ.ት. አገዛዝ በኦሮሞው፤ በአማራውም ፤ በጋምቤላው ፤በአፋሩ ወ.ዘ.ተ. እንደዚሁ በስፋት ቀጥሎበታል ። ህዝብ እያለቀ ነው ።

የህ.ወ.ሓ.ት.እና የሱዳን መንግሥት፤ግኑኝነት ከትግሉ ፤መነሻ

እስከ ዛሬ 
ህ.ወ.ሓ.ት ገና ትግሉ ሳይጀምር በዝግጅት እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኘው የሱዳን ኢምባሲ ይፋ ባልሆነ ፤ውስጣዊ ድጋፍና ትብብር ትንሽ የገንዘብ እርዳታም በድብቅ ያደርግ ነበር ።ቀጥታዊ ግንኙነቱም ከአረጋዊ በርሄ ምሲጢራዊ በሆነ መልኩ ይገናኝም እንደ ነበር የቅርብ ትዝታ ነው ። የወያኔና የሱዳን መንግሥት ግኑኝነት ወያኔ ደደቢት በረሃ ሲወርድ እንደወረደም ጎልቶ አይታይም ነበር ።ነገር ግን ሱዳኖች የወያኔን እንቅስቃሴ ፤ በቀጥታም በጥሞና ይከታተሉት ነበር ፤ሱዳን ውስጥም በሻዕብያ ሽፋን እንደሚንቀሳቀስ ያውቁ ነበር ፤እያወቁም የፈጠሩለት ትፀእኖ ወይም ችግር አልነበረም ።

ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ የሱዳን መንግሥት ኦፊሶልያዊ ባልሆነ መንቀሳቀስ በካቱም ፤ገዳሪፍ እንደሚያደርግ ያውቃል ፤ ትንሽ ጉርሻም ጭምር በሚስጢር ይሰጣቸው እንደነበር ከስብሃት ነጋ ስምተናል ።

በአካባቢ ያሉትን ሀገራት ይህን ቀን ከሌሊት የህ.ወ.ሐ.ት እንቅስቃሴ ፀረ ኢትዮጵያ ያጠናሉ ይክታተላሉ።ይህ እየሆነ ባለበት ይህ ድርጅት እስከ 1974ዓ.ም በሱዳንም ሆን በሌሎች የአረብ ሀገሮች እውቅና አልተቸረውም ነበር ፤ የሚሰጡት መልስ አቅማቹና ሀይላቹህ ማየት አለብን በመጀመሪያ ግን ተስፋ አትቁረጡ ትግሉ ስትጀምሩ ቃል ገብተናል።ሆነም ተረፈም ሻእብያ ብቻ ነበር የሚረዳው የሚተባበረው። በ1969 ዓ.ም ደግሞ የሱማሊ መንግሥት በዘይድ ባሬ የሚመራው መንግሥት ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ፤የወያኔው መሪ አረጋዊ በርሄ ከሞቃድሸው መሪ ዘይድ ባሬ መንግሥት ግንኞነት ፈጠረ፤ከዚሁ በመነሳት ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቅ ለወያኔ መስጠት የጀመረበት ጊዜም ነው ።

1974ዓ.ም የሱዳኑ ፤ገዳሪፍ ; ጠ/ገዥ እና የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ግኑኝነት
የገዳሪፉ ፤ስብሰባ

ህ.ወሐ.ት. እንደጎለበት ሕዳር ወር 1974 ዓ .ም የሱዳን መንግስት ደብዳቤ ለህ.ወ.ሐ.ት አመራር ላከ የተላከው ደብዳቤ ለአረጋዊ በርሄ ደረሰ ። አረጋዊ በርሄና፤ ስብሀት ነጋ ከሸራሮ ተንስተው ሱዳን ገዳሪፍ ገቡ : ከገዳሪፍ ባለስልጣናት (ሱዳን ) ተገናኙም ፤ የቀረበላቸው ጥያቄ ኢትዮጵያ በሐይል የሱዳን መሬት ቀምታ በግዛትዋ ውስጥ በማካተት ነጥቃናለች ዛሬ የናንተን እርዳታና ትብብር እንፈልጋለን ፤ በኢትዮጵያ የተቀማን መሬታችን እንድታስመልሱልን በአንክሮት እንጠይቃችሁ አለን ፤ የሱዳን መሆኑም ማስረጃ አለን ፤ የናንተ ድጋፍ ወሳኝ ነው ለሱዳን መንግሥት ። የሱዳን መንግሥትም ሙሉ እርዳታና ድጋፍ ይሰጣል ከሁሉም በላይ፤ ለT.P.L,F. ሙሉ እውቅና ካላ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይሰጣል።የተለያዩ የአረብ ሀገራትም እውቅና ሰጥተው በሙሉ ነፃነት እንድትንቀሳቀሱ የትግራይ ህዝባችሁም እንድታደራጁ እናደርጋለን በሱዳን ያላችሁ ነፃነት እዛም ታግኙት አላችሁ ።እኛን ብቻ ተባበሩን። ብለው ለአረጋዊ በርሄና ለስብሃት ነጋ ተማፀኑ ሁለቱ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎችም በደስታ ይህን ሃሳብ ተቀበሉት ፤የጊዜ ቀጦሮ እስቀምጠው ። ከቀሪዎችን የህ.ወ.ሐ.ት. አመራር ፖሊት ቢሮ ለማነጋር ለማሰባሰብና የተገኘው ከሰማይ የወረደ ዜና ይዘው ወደ ትግራይ ተመልሰው መጡ።ስዩም መስፍን የውጭ ጉዳይ ሃላፊው ሱዳን ውስጥ ነበር ፤እሱም እግረ መንገዳቸው ጠርተው ተከቶ ገባ፤በረሃ ትግራይ ውስጥ የነበሩ 1ኛ ግደይ ዘርአፅዮን የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር 2ኛ አባይ ፀሃየ የፖለቲካው ክፍል ሃላፊ 3ኛመለስ ዜናዊ ። ማሳሰቢያ መለስ ዜናዊ በዚሁ ጊዜ የፖሊት ቢሮ አባል አልነበረም የነበረው ማእከላይ ኮሚቴ ነው ሃላፊነት የፕሮፓጋንድ ( የፖለቲካው) ክፍል የአባይ ፀሃየ ምክትል ሃላፊ ነበር።ነገር ግን አረጋዊ በርሄ የስብሐት ነጋና የመለስ ዜናዊ ጥብቅ ሚስጥረኞች ከመጠን ያለፈ ግኑኝነት ሰለነበራቸው የነብስ አባታቸው ከመሆኑ የተነሳ ፤ ማንም ነገር ፖሊት ቢሮ የሚወስነው መለስ ዜናዊ ሳይጨመርበት አይወሰንም።ይህን ሁሉ ጣጣ የሚፈጥረው አረጋዊ በርሄ ነው።ይህ ብቻ አይደለም ለከፍተኛ የሥልጣን እርከን ያደረሳቸውም አረጋዊ በርሄ ነው።

በሃገር ክህደት ሤራ የድርጅታቸው ጊዝያዊ ጥቅም ለማስከበር ሲሉ ፤ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት በመፃረር ዳር ድንበር ሃገርና ህዝብ በመክዳት ፤ ለሱዳን መንግሥት የሸጡ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊት ቢሮና አንድ ማ/ኮሚቴ አባል ነበር እነዙህ ናቸው ።

1ኛ አረጋዊ በርሄ ፖሊት ቢሮ አባል ወታደራዊ አዛዥ የህ.ወ.ሓ.ት.ዋና የበላይ ሃላፊ ፤
2ኛ ስብሃት ነጋ ፖሊት ቢሮ አባል የህ.ወ.ሓ.ት. ሊቀ መንበር እና የሓለዋ ወያኔ ሃላፊ ፤
3ኛ ግደይ ዘርአፅዮን ፖሊት ቢሮ አባል የህ.ወ.ሓ.ት. ም/ሊቀ ፤መንበር እና ም/የሓለዋ ወያኔ ሃላፊ ፤
4ኛ አባይ ፀሃየ ፖሊት ቢሮ አባል የፖለቲካ ክፍል ሃላፊ
5ኛ ስዩም መስፍን ፖሊት ቢሮ አባል የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ፤
6ኛ መለስ ዜናዊ ማእከላይ ፤ኮሚቴ አባል የፖለቲካ ክፍል ም/ ሃላፊ ፤

-ከሱዳን አረጋዊ በርሄ ና ስብሐት ነጋ እንደተመለሱ ትግራይ በረሃ እንደገቡም ሁሉም ተሰብስበው በዚሁ ፀረ ሃገር ሤራ በሚስጢር ተነጋግረው ካለ ምንም ልዩነት በሱዳን የቀረበው ጥያቄ በደስታ ተቀብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።ተግባራዊ እንደሚያደርጉትም ያረጋገጡበት ወቅትም ነው ።በሚስጢራዊት ግን ሊደበቅ አልቻለም ይህ የእነ አረጋዊ ሱዳን የተጓዙበት ።
ምክንያት ሰብሓት ነጋ ለሚቀርበውና ለሚያምነው ታጋይ ሁሉ ሱዳን በኢትዮጵያ መንግስታት መሬትየን ተነጥቄ አለሁ ተባበሩኝ እርዱኝ ብላ ስለጠየቀችን እኛ የመሬት ችግር የለንም ሱዳን የምትጠይቅው እንፈፅማለን የምንፈልገው በሱዳን መንግሥት T.P.L.F እውቅና ማግኘት ቅድሚያ የምንሰጠው ለትግላችን ወሳኝ በመሆኑ ትልቅ ፍላጎታችን ነው ፤ከዚህም በላይ በብዙ ነገሮችም እንደሚተባበሩን ነግረዉናል በሙሉ ቃል አረጋግጠውልናል እኛ የምንፈልገውም አግኝተናል ። የሚል ዜና ስብሕት አዳረሰው። ለኔና ለሌሎችም ንግሮናል።በኋላ ኋላ ግደይ ዘርአጽዮን ፤አባይ ፀሃየ በግልፅ ነበር የሚናገሩት ፤በመሪሕ ባእታ ፤ካድሬ ስብሰባ ጊዜም በየፊናቸው ተናግረዉታል ።ከሃዲው ፀረ ኢትዮጵያ ግደይ ዘርአጽዮን ይህ በግልፅ የፈጸሙት ፀረ ኢትዮጵያ ከባድ ወንጀል ፤ክህደት ፤ ግን ይክዳል ።ሱዳን ሄደው የፈረሙት ረስቶታል ።

ይህንም በስፋት ያሰራጨው ፤ ሲናገረው የነበረም መለስ ዜናዊም ጭምር ለመሪሕ ባእታ ( vanguard cadre) በየስብሰባው በግልፅ ተናግሮታል ሱዳኖች ኢትዮጵያ የሱዳን መሬት በጉልበትዋ ነጥቃናለች የናንተ ትብብርና እርዳታ እንፈልጋለን በለውናል እትዮጵያ የዘረፈችው መሬትም በግዴታ መሬታቸው ማግኘት አለባቸው በማለት እያስተጋባው የነበሩበት ጊዜና ወቅት ዛሬ አረጋዊ በርሄም ፤ግደይን፤ ቢክዱ ነገ ሐቁን ያጋልጠዋል። እውነት ተደብቃ አትደበቅም ፤የወያኔ መሪዎች እነ አረጋዊ በርሄ ይህን ሊደብቁት አይችሉም በግልጽ በይፋ የተነገረ የታወጀም ነው ።ሶስት ጊዜ አራት ጊዜ የፈረመበት አረጋዊ በርሄም ሆነ ሌሎቹ በሰነድ የተያ ዶኩመንት ነገ ይፋ ይወጣል ፤ኢትዮጵያ ውስጥም በወያኔ ደኮሜንት እንደሚገኝ በሙሉ ልብ እተማመን አለሁ ።ቅንጣት ጥርጥር የልኝም ።የሱዳን መንግሥት የፅሁፍ ሰንድ ነው ።መለስ ዜናዊም ይህች ሰንስድ ይዞ ነው ለኢትዮጵያ ፓርላማ ሱዳኖች ለቡዙ ጊዜ ታግሰዉናል መሬታቸው በኢትዮጵያ ነገሥታት ተነጥቀው ፤አሁን ግን ፍትሕ ከኛ እየተጠባበቀ ናቸው መሬታቸው እንሰጣቸው አለን እናስረክባቸው አለን ያለው ።የጎንደር ጠ/ግዛት መሬት የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ከሱዳን ዳር ድንበር የሚዋሰን ነው ። የወያኔ መሪዎች በ1975 ዓ.ም የፈረሙ እነ አባይ ፀሃይም እኮ የዚህ ሰነድ ሱዳኖች ደግፎ ሲያቀብ እነሱም አብረዉት በፓርላማው ስብሰባው አሉ ፤ታድያስ የነ አረጋዊ ክህደት ምን ፋይዳ ሊያመጣ ነው ። አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘራፅዮን በአማራው ሰሜን ጎንደር በወልቃይት፤ጠገዴ ፤ጠለምት ወ.ዘ.ተ. የፈፀማችሁት የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከ 1977 ዓ ም መጨረሻ .ለመካድም ሞክረዋል ህዝብ ያያቸው ህዝብ የመሰከረላቸው አማራው የጨፈጨፉ ክህደታቸው ሊሳካ አልቻለም ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ ፤ ፤በናንተ መሪነት ያለቀው አማራ ህልቀ ስፍር የሌለውየ ህዝብ ንፁህ ደም ፈሶ በከንቱ አይቀርም። በተለይ አረጋዊ እና ግደይ ለዚሁ የጎርፍ ደም ግንባር ቀደም ተጠያቂ ስትሆኑ የጎንደርን አዋሳኝ ከሱዳን ድንበር የሚገናኝም በመደራደር የሸጣችህ ዋና ተጠያቂዎች መሆናችሁን እ ማወቅና መገንዘ አለባቹህ ። በዚሁ ደንበር የተነሳው የድንበሩ አካባቢ ኢትዮጵያዊያን የጎንደር ህዝብ ነዋሪዎች ፤የወይኔ ሠራዊትና የሱዳን ሠራዊት ግንባር ፈጥረው ኢትዮጵያዊ ዜጎች ተፈናቅለዋል እየተገድሉ ናቸው ፤የቁም ስቃይ ሰለባ ሆኖዋል ፤ ሃብት ንብረታቸው ወድመዋል ፤ይህም ችግር የመጣው እናንተ የሃገር ከሃዲዎች ሃገር ሽጣቹህ ለሱዳን ፈርማችሁ በማስረከባቹ የመጣ መፍትሄ የሌለው ችግር ነው ።

ሱዳኖች ተቀማን የሚሉት የ1902ዓ.ም. ሕገ ወጥ የሆነ ካርታ በማቅረብ የወያኔ መሪዎች ከላይ በስም የተዘረዘሩ ለጊዝያዊ ጥቅም አሳምነው ፤ወያኔዎችም አምነው ። በወቅቱ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ኤርትራ ውስጥ ይካሄድ ስለነበር ህ.ወ.ሕ.ትም. ሙሉ ተሳታፊ ስለነበር የሱዳኑ ቀጠሮ በማዘጌት የቆየው መስከረም ወር 1975 ዓ.ም. የህ.ወ.ሐ.ት. አመራር 1ኛ አረጋዊ ብርሄ የህ.ወ.ሓ፣ት.ቡድን መሪ ሰብሳቢና አስተባባሪ 2ኛ ስብሐት ነጋ 3ኛ አባይ ፀሃየ 4ኛግደይ ዘርአፅዮን

5ኛ መለስ ዜናዊ 6ኛ ስዩም መስፍን ሁኔታውን ሲያመቻች የነበረው ሱዳን ውስጥ እዛው ሱዳን ተቀላቀላቸው።በመስከረም ወር 1975 ዓ.ም ከገዳሪፍ ወደ ካርቱም የስብሰባ ቦታው ተሸጋግሮ ከሱዳን ባለ ስልጣናት ሱዳን በፕረዚዳንት ጃእፋር ኒሜሪ በወቅቱ የምትመራ የነበረችው ሱዳን መሬትየን የህ.ወ.ሓ.ት.አመራር በእምነት ተቀብለዉታ ይህም ተግባራዊ የሚደረገው ።

እልባት የሚያገኘው ትግራይ ከኢትዮጵያ የቅኝ አገዛዝ ነፃነትዋ ስትቀዳጅ በተግባር ይፈፀማል ፤ተብሎ ፤ተፈራርመው ፤ የተፃፈው በሚስጢር ተይዞ ይቀመጥ ተብሎ ተሰንዶ ተቀመጠ ።

ህ.ወ.ሓ.ት፤ በኢትዮጵያ ምንም ሀላፊነትና እውቅና የሌለው ማፍያ ፀረ ኢትዮጵያ ድርጅት ይህ የሱዳኑ ጥያቄ አምኖ ተቀብሎ-የኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት አሳልፈው ለባእድ ሃገር የሽጠው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መስከርም ወር 1975 ዓ.ም. ነው ።አሁን ጎንደር ዳር ድንበሩ ከሁመራ አንስቶ እስከ ታች የጎንደር ድንበሮች በሱዳንና በወያኔ ሠራዊት ሁለቱ ተባብረው በዚሁ ኢትዮጵያዊ ህዝቡ ላይ ግፍ እየተፈፀመበት ነው ፤ በአማራው የሚደርሱት ያለ ጥቃት መፈናቀል ውጡ የሱዳን መሬት በወረራ የያዛችሁት ልቀቁ እየተባሉ በህዝብ የሚደርሰው ያለው ግፍና መንገላታት የሁሉ ኢትዮጵያ ችግር፤ ዳር ደንበሩ የሁሉ ኢትዮጵያዊ እንጂ የጎንደር ብቻ አይድለም ።

ፌርማው ከተጠናቀቀ በሱዳን መንግሥት በላንድ ሮቨር መኪና ተጭነው 1 አባይ ፀሃየ 2 ስዩም መስፍን 3 መለስ ዜናዊ አስቀድመው ሸራሮ ሲገቡ።

የሱዳን መንግሥት ለህ.ወ.ሓ.ት. ያሳለፈው ውሳኔ ለመቀበል ደግሞ እዛው የቆዩት አመራር 1 አረጋዊ በርሄ 2 ስብሃት ነጋ 3 ግደይ ዘራፅዮን የሱዳን መንግሥት ለህ.ወ.ሓ.ት.የቸረው ውሳኔ ተቀብለው በ3ኛ ቀን በሱዳን መንግሥት ላንድ ሮቨር መኪና ተጭነው ሸራሮ ገቡ ።የሱዳን መንግሥት የሰጠው ውሳኔ ። የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ ለT.P.L.F. ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሱዳን መንግሥት ሙሉ እውቅና መስጠቱ።
2ኛ ከተለያዩ የአረብ ሃገራት ፤ ተነጋግረና ባጭር ቀናት ውስጥ ሙሉ እውቅና ለ T.P.L.F.ይሰጣሉ በኛ በኩል ደብዳቤው ይደርሳችሀል።ያለቀም ጉዳይ ነው ። ይህም በቀናት ውስጥ ተግባራዊ ሆኖ ፤ለህ.ወ.ሓ.ት. ይደረርሳል ።በዚሁ መሰረት ፤የእውቅና ደብዳቤ በፍጥነት ከላኩ መካከል ፤ሊብያ ፤ግብፅ፤ሲሪያ ፤ኢራቅ ፤ሊባኖን (ቤሩት )ግንባር ቀደም ሲሆኑ እንግሊዝ ፤ጣልያንም ላኩ

3ኛ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች እርዳታውም በተመለከተ የሱዳን መንግሥት በገንዘብ በመድሀኒት በሕክምና መሳሪያ በተቻለ አቅሙ ለ ህ.ወ.ሓ.ት. ይረዳል በእርዳታውም ሙሉ ትብብሩ እስከ መጨረሻው ይቀጥላል ።
በጦርነት የተጎዱ በሌላም በሽታም ታጋዮቻችሁየሚደርስባቸው ጉዳትም ሆነ በሽታ ነፃና ሙሉ ሕክምና በሱዳን የሚገኙ ሆስፒታሎች ሙሉ አገልግሎት ይሰጣሉ ።ይታከማሉ ።

T.P.L.F ከዚህ ወር ጀምሮ በየትኛውም የሱዳን ግዛት ቢሮዎቹን ይከፍታል፤ የትግራይ ህዝብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ የማደራጅትና የማሰባሰብ ሙሉ ሀላፊቱ የድርጅቱ ነው። ለሚከፈቱ ቢሮዎች የሱዳን መንግሥት የቤት ኪራይ ላልተወሰነ ጊዜ ይክፍላል። ፓስፖርት በተመለከተ ለ T.P.L.F. አመራር የሱዳን መንግሥት ወጪው በመሸፈን ያዘጋጃል ለህ.ወ.ሓ.ት. አመራር የዲፕሎማት ፓስፖት ይሰጣል ፤ ።ለሌሎችም በየአስፈላጊ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ታጋዮችፓስፖርት ያዘጋጃል ።
የT.P.L.F. ታጋዮች በስራም ሆነ ለህክምና ሱዳን ሲገቡ በፀጥታ ሀይሎች ስለሚጠየቁ ችግር እንዳይገጥማቸው T.P.L.F.የመታወቅያ ካርድ በማዘጋጀት ለደህንነት ቢሮችን በማቅረብ ተቀባይነት ስለሚሰጠው ሰለሚያገኝ የህ.ወ.ሐ.ት ታጋይን አባልም ጭምር በሙሉ ነፃ በሱዳን ለመንቀሳቀስ ይችላል፤ መታወቅያ ካርዱ በመንግስት እውቅና ስለተስጠው። አጠቃላይ ነገር ሁሉ ከተጠናቀቀ ፤ እነ አረጋዊ በርሄ ሁሉን ጨርሰው የቆዩት የአመራር ጉጅሌም ተመልሶ ትግራይ ሸራሮ ገቡ ። ሱዳንም ለህ.ወ.ሐ.ት ሙሉ እውቅና እንደሰጠች በአዋጅ አስነገረች። የወያኔም አመራር ለታጋዩ የሱዳን መንገስት ለህ.ወ.ሐ.ት. ሙሉ እውቅና ከዛሬ መስከረም ወር 1975 ዓ.ም እንደሰጠ አወጁ ።ከላይ የተጠቀሱ ስምምነትም በሙሉ በተግባር ተፈፀሙ ተግባራዊነቱም በግልፅ ታየ ወያኔም በሱዳን ማነህ ሳይባል ከ1975ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ እለት እንደልቡ የሚንቀሳቀስባት ሶዳን ሀገር ብቻ ናት ።

የሱዳን መንግሥት እውቅናን ለመስጠት ለአረብ ሀገሮች ያቀረበውም በሳምንታት ውስጥ ሊብያ፣ግብፅ፣ በይሩት፣ፍሊስጤም ኢራቅ፣ሶሪያ፣ ሳውዲ አረቢያ T.P.L.F. ሙሉ እውቅና መስጠታቸው ለሱዳን መንግሥትም አሳወቁ።የወያኔው አመራርም ከሱዳን እየተነሱ እነዚህ ሀገራት ይመላሱ ነበር ።ጣልያንም ጨምሮ ።

ዛሬ በኢትዮጵያ ፤ ፤በሱዳንና በወያኔ ሠራዊት ትብብርና ቅንብር በህዝቡ የሚደርስ ያለ ጥቃት ዘግናኝ ፤ነው ።እነ አረጋዊ በርሄም ይህ ሁሉ ችገርና መከራ በህዝብ አድርሰው ፤አሁንም ስለ ኢትዮጵያ ይናገራሉ ፤ይብቃቹ ማለት ፤አስፈላጊ ነው ፤ይህም የሚያደርጉት ያሉ ከንቀት የተነሳ ነው ።

ህ.ወ.ሓ.ት. እና የዝያ ባሬ ሞቃድሾ መንግሥት ዝምድና / በ1969 ዓ.ም.

ህ.ወ.ሓ.ት. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ከሁሉ የከፋ ጠላት ነው ። ኢትዮጵያን ለመበታተንና ለማፍረስ የተፈጠረ እኩይ ድርጅት ነው ። የኢትዮጵያ ባእዳን ጠላቶች መሳሪያ ድርጅት ነው ። የሱማሊ መንግሥት በዘይድ ባሬ የሚመራ ኢትዮጵያን ወሮ ኦጋዴንን ወደ ሶማሊ ግዛቱን ለማቀላቀል በ1969ዓ.ም.በከፈተው የወራር ጦርነት በወቅቱ፤የወያኔ አመራር ለወራሪው ዘይድ ባሬ የሱማሊ መንግሥት ሙሉ ድጋፍ አበርክተዋል ። የነበሩ አምራር አመራር 1 አረጋዊ በርሄ የድርጅቱ ሊቀ መበርና ወታደራዊ አዛዥ 2 ስብሐት ነጋ 3 ግደይ ዘርአፅዮን ም/ሊቀ መንበር 4 ሥዩም መስፍን 5 አባይ ፀሃየ እነዚህ (የተ.ሓ.ህ.ት ).ህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊት ቢሮ ሲሆኑ በወቅቱ ተለዋጭ ማእከላይ ኮሚቴ የነበሩ መለስ ዜናዊ ፤ ስየ አብርሃ ፤አውዓሎም ወልዱ ፤ሸዊት (አፅብሃ ) ዳኘው ፤ አልቆየም ወዲያውኑ በስብሃት ነጋና በመለስ ዜናዊ ተገደለ ፤ ሆነው ተባብረው ከሶማሊያ መንግሥት የግንኙነት መንገድ ፈጥረው ለዚሁም በዋና አስተባሪነት ግደይ ዘርአጽዮን በማድረግ ወደ ሱማልያ የሚላከው መእክተኛ ደብዳቤውም ጭምር ተዘጋጀ ለዘይድ ባሬ የተጻፈው ደብዳቤ በስየ አብርሃ መሪነት ከብዙ ቀናት ጉዞ መቃድሾ(ሱማሊ)ዋ ና ክተማ በመግባት በህ.ወ.ሐ.ት.የተላከው ለፕረዚዳንት ሰጠ።በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ይዘቱ ኢትዮጵያ ወራሪና ተስፋፊ ሀገር መሆንዋ የሚታወቅ ነው ።ትግራይም ልክ እንደ ኦጋዴን በአማራው መንግስት በሀይል ተጎብጣ ዛሬ በአማራው ቅኝ አገዛዝ ውድቃለች ፤የትግራይ ሃገራዊ ነፃነት ፤ በአማራው መንግሥት በምኒሊክ የሚመራው ተነጥቀን ፤በአማራው ቅኝ አገዛዝ ወድቀን በስቃይ እንገኛለ ። በትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት እየተመራ የትግራይ ህዝብ መሳርያ ታጥቆ ፀረ ወራሪው አማራ ብረት አንስቶ ሃገራዊ ነፃነቱ ለመቀዳጀት በትግል የሚገኘው ። ሱማሊም የግዛትዋ መሬት ኦጋዴን በአማራው መንግሥት ተነጥቃልች። ስለሆነም የሱማሊ መንግሥትና በትግራይ ነፃ አወጪ ድርጅት የሚያካሂደው ያለ ትግልና በሱማሊው የሚካሄድ ፀረ ወራሪው የአማራ መንግሥት በዓላማና በአቋም አንድ ነው። የተ.ሓ.ህ.ት. አመራርና ድርጅቱ በሙሉ አቋም ደግፎታል ።ከዚሁ በመነሳት ተጋድሎ ሐርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሐ.ህ.ት.) ኦጋዴን የሱማሊግዛት መሬት እንደመሆኑ ፤የሱማሊያ መንግሥት ፤የሃገሩ የግዛት ወሰን ለማስከበርና ለማስመለስ ፀረ ኢትዮጵያ የምታካሂደው ያለ ጦርነት ፍትሓዊነቱን በማድነቅና በፖሊሲ መሰረትም እንደግፋለን ። እኛም የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ድጋፍ ለመስጠት የተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ ተዋጊ ሠራዊት ለመላክ ተዘጋጅተናል።

ወታደራዊ ትጥቁና ሌላው ለናንተን በመተው የምንልከው ሠራዊት የጉዞው ሁኔታ ይዘጋጅልን። ት.ሐ.ህ.ት።

የሶማሊው ፕረዚዳንት ሰይድ ባሬ ይህ ደብዳቤ ካነበበው የተሰማቸው ደስታ ከፍተኛ በመሆኑ ከዚሁም በመነሳት ለተ.ሐ.ህ.ት. አመራርና ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ የዲፕሎማት ፓስፖርት እንዲፈቀድላቸው ተወሰነ፤ የመሳሪያ ትጥቅ ካላሽን፣አርፒጂ፣ቦምብ በየዓይነቱ ተፈቀደ ፤ ሌላም ዓይነት መሳሪያ ሰጡ። ገብሩ አስራት የህ.ወ.ሐ.ት ከፍተኛ አመራር የነብረም ይህን በተመለከተ ሏአላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ መፅሃፉ በግልፅ አስቀምጦታል። ይህን ሃሳብ ለማስረጃ እንዲሆን የማቀርበው ያለሁ ወያኔ ህ.ወ.ሐ.ት.ለጊዜያዊ ጥቅሙ ሲል የኢትዮጵያ ሏላዊነትና አንድነት በመፃረር ሀገር ለመሸጥ፤ ለማፍረስና ለባእዳን አሳልፎ መሸጥ የጀመረው ገና ከጥዋቱ መሆኑን ለማስረገጥ ነው።የዚሁ ሁሉ ችግር ፈጣሪው በየካቲት ወር 1967ዓ.ም ተከትለዉት የመጡ ፕሮግራም ሆን ተብሎ የባእዳን ድጋፍ ታክሎበት በወያኔ አመራር ተቀነባብሮ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ የህዝብዋን አንድነት በሚፃረር መልክ የትዘጋጀ ፀር ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ፀር ህዝብ አንድነት ፕሮግራሙም ሆኖ በመዘጋጀቱ ነው ። ያዘጋጁት ሰዎች የፀር ኢትዮጵያ ባእዳን ጉዳዩን በባለቤትነት ለመፈፀም የተነሱ ፕሮግራሙን በማዘጋጀት በኢትዮጵያ ሏላዊነት ከባድ ችግር ፍጥረዋል።ለዚሁ መከራና ችግር በኢትዮጵያና በህዝብዋ በህ.ወ.ሐ.ት. እየደረሰስ ያልው ሲኦል እነማን ይዘዉት ደደቢት በረሃ ወረዱ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች የህ.ወ.ሐ..ት ፖሊት ቢሮ አመራር በሙሉ በተለይም አረጋዊ በርሄ፤ ግደይ ዘራጽዮን ፤ስብሃት ነጋ ፤መለስ ዜናዊ ፤አባይ ጸሃየ፤ ሥዩም መስፈን ፤ዛሬ ኢትዮጵያን አሁን ለምትገኘው ውድቀትን የህዝብዋን መበታተን የሃገር ሏላዊነት መፍረስ ግንባር ቀደም ተጠያቂ እነዚህ ናቸው ፤ እየተከታተሎ የመጡና አሁን በኢትዮጵያ በሥልጣን ያለው ገዢው ስርአት ህ.ወ.ሓ.ት በአባይ ወልዱ ሲመራ የነበረው ፤አሁን በደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ፤ከነአረጋዊ በርሄ ተያይዞ የመጣው ታልቅዋን የትግራይ መንግሥት ለመመስረት መሥፋፋት ሃገር የመበታተን ፤የኢትዮጵያን ሃበት ንብረት የመዝረፍ የህዝብ ማንነት መንጠቅ ኢትዮጵያን አዳክሞው በታትነው ፤የበለጸገች የትግራይ (መንግሥት ) ለማቋቋም ነው ።ይህ እምነትና አመለካከትም የፀና የማይለወጥ የሁሉ ከእነ አረጋዊ በርሄ አስከ እነ አባይ ወልዱ፤ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፤የፀና የማይለወጥ የአቋም ፖሊሲ ነው ።በየወቅቱ በሥልጣን ለረጅም አመታት የመሩ እነ አረጋዊ በርሄ ናቸው ፤በመካከላቸው የተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻ ቢባረሩም በአቋም በፖሊሲ የሚከተሉት ግን የጤፍ ፍሬ የምታክል ልዩነት የላቸውም ፤ህ.ወሓ.ት ከሥልጣኑ እንዲወገድ አይፈልጉም ፤በፈጸሙት ወንጀል ማለት የኢትዮጵያ ሏላዊነት በመፃረር ኢትዮጵያ ሏላዊነትዋን አፍርሰዋል፤የኢትዮጵያ ዳር ለሱድን ሸጠዋል ፤በዘር ማጥፋት ወንጀል በደም ታጥበዋል ፤የአማራው የማንነት ክብሩን ነጥቀዋል ፤ታላቅዋን የትግራይ መንግሥት ለመመስረት በተስፋፊነት የአማራው መሬት በስፋት ወረዋል ፤ከወሎም እንደዚሁ ከአፋር ፤የኤርትራ ሃገር አሰብን ለመውረር በእቅድ ይዘዋል ፤ይህም እቅድ አሁን በሥልጣን ያለው የህ.ወ.ሓ.ት. ገዢ ቡድን እና የቀድሞዎቹ የአመራር ቡድን የነበሩ ሃሳብና እቅድም ነው ፤አሰቡን ከኤርትራ ሃገር ወረራ ታላቅዋን የትግራይ መንግሥት የባሕር በር ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ ወራር ነው። እንጂ ለሌላ አስበው ተቆርቁረው እይድለም ። ኢርትራ ነፃ ሃገር ናት ፤ይህ ፋሽሽት የወያኔ አገዛዝ እንዴት ሲጠግብ ነው ነፃ ሃገር የሚወር ? ዛሬ አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘራፅዮን እነ ስየ አብርሃና ፃድቃን ገብረተንሳይ ስለ ኤርትራ በዙ ይገራሉ ይጽፋሉ ያወግዛሉ ፤እነ አረጋዊ በርሄ የሻዕብያ ምንጣፍ ተሸካሚ እንዳልነበሩ። ፤ለኤርትራ ነፃነት ብለው የትግራይ ወጣት ወንድ ሴት እስከ 160000( እንድመቶስድሳ ሺህ )የትግራይ ልጆች በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅትና በተለያቱ ጊዜም ጭምር ልከው የሄደው ሁሉ በሣሕል በረሃ ሙቶ በአሸዋ ተቀሮ የቀረ ወጣት የትግራይ ዜጋ ፤ዛሬ የትግራይ ወላጅ ደም እያለቀሰ የሚገኘው ።ብዛቱ አናውቀውም እንጂ ወደ ሱማልያ የላኩት ፤ከመቃድሾ መንግሥት ጎን ተሰልፎ ፀረ ኢትዮጵያ ሠራዊት እንዲዋጋም በኦጋዴን ሙቶ የቀረም አለ ።ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. በኢትዮጵያና በህዝብዋ የፈፀመው ወንጀል ዋንጫው ሞልቶ እየፈሰሰም ነው ።ግፈኛው ፋሽሽት አርአት የኢትዮጵያ ሏላዊነት ዳር ድንበር ሸያጭ ህ.ወ.ሓ.ት ነው ።

የማንነት ጥያቄ የመብት ጥያቄ ነው። የመብት ጥያዌም የመኖርና አለመኖር ቁልፍ የተፈጥሮ ሕግ ጥያቄ ነው።የእርሻ መሬትህ ኑሮህ ልጅ ወልደህ ማሳደግ ሃብትና ንብረት ማፍራት በሰላም መኖር በነፃነት በፈለግከው መንቀሳቀስ ይህ በአንዲት ሃገር ሕገ መንግሥት ቁልፍና የሕገ መንግሥቱ መሶሶ ነው። በዘረኛውና ፋሽሽት ሽብርተኛው ስርአት ወያኔ ይህን አይቀበለውም። የሕገ መንግሥት አንኳር የህዝብን መብት የሚያስከብር አንቀፅ በዚሁ በሃገራችን ያለው የደደቢቱ መራሽ ማፍያ ወያኔ ቦታ የለውም። ለምሳሌ እንኳን ብንመለከት በአማራው ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ጠለምት፤ቃፍታ ሑመራ የማንነት ጥያቄው ከተነሳ ከ42 ዓመታት ወያኔ ለትግሉ ከተነሳ ጀምሮ የኔ ማንነት አማራ እንጂ ትግሬ አይድለሁም በማለቱ በጣም ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል በህ.ወ.ሕ፣ት፣ ተፈፅሞበታል አሁንም አማራ የተባለው ሁሉ ከየአለበት በወያኔ እየተለቀመ ዘሩ እየጠፋ ነው። ይህም በዓለም ሕግ ያስጠይቃል።የኦሮም ህዝብም መሬቱ ተንጥቆ ኢትዮጵያዊነቱ በወያኔ ተገፎ ከመሬቱ ተፈናቅሎ መፈናፈኛ ያጣ ህዝብ ሆነ ፤የጋምቤላ ህዝብም በአማራውና በአሮሞው የደረሰው ጥቃት ደርሶበታል ዛሬ በወያኔው የሲኦል አለንጋ በስደት በችግር እየተሰቃየ ይገኛል ።

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ

አሁን ያለህበት አሁን እየደረሰብህ ያለው ችግር ፤መከራ ፤ከተወለድክባት ተወለድህ እትብትህ ከተቀበረባት መሬትህ ፤ከቤት ንብረትህ ፤ከእርሻ መሬትህ ከመስኖ እርሻ መሬትህና ይዞታህ ተፈናቅለህ ፤በክፉ ፈተና ችግር ወድቀሃል ።አንተ በርሃ ላይ ተጥለህ በብርድ ፤በሽታ ፤ርሃብ ፤ውሃ ጥም ፤እየትሰቃይህ ፤የወልድካቸው ልጆችህም ለስደት ተዳርገው በየ በረሃው እየሞቱ ፤በሊብያ እየታረዱ ፤ በሊብያ ለባርያነት እየተሸጡ አጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በችግርና መከራ የሶቆቃ ኑሮ ወድቆ ይገኛል ።ይህ ሁሉ መከራ ጣጣና መዘዝ ይዞልህ የመጣው ከደደቢት ፈርጥጦ የመጣው ወያኔው ህ.ወ.ሓ.ት. ነው ።ይህ ድርጅት ሆን ተብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ለማጥፋት የተፈጠረም ነው ።አሁንም ኢትዮጵያና ህዝብዋ በፋሽሽታዊ የአፓርታይድ ስርአቱን እያሰቃየ የሚገዛ ያለ የህ.ወ.ሓ.ት. ድርጅት ነው ።የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. በለሱ ቀንቶት ኢትዮጵያን በግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ተቆጣጥሮ በዘረኛ መሪዎቹ አጃቢነት ኢትዮጵያና ህዝብዋ በቅኝ ግዛት ስርአቱ ወደቁ ።አሁን 27 ዓመቱ ህ.ወ.ሓ.ት. ኢትዮጵያን እየገዛ ያለ ይህ እኩይ የባንዳ ስብስብ ነው ።በዚሁ 27 ዓመት የወያኔው የግዛት ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ የደረሰብህ ጉዳትና መከራ ችግር ፤ሰቆቃ ራስህ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ታውቀዋለህ ።ነጋሪ አያስፈልግህም ።የተሰቃየህ ህዝብ ነህ ።ስቃይህ ደረቱን አልፎ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰም ያለህበት ወቅትና ጊዜ ነው ፤ ፤እንተም አልቻልኩም መረረኝ፤በቃ ለወይኔ አልገዛ እምቢ ለወያኔ ስርአት ብልህ በቆራጥነት ተነስትሃል ።በኦሮሞው የተነሳው ሰፊና አድማሳዊ የንቅናቄ ትግል ፤በቃኝ ለወያኔ አገዛዝ ፤ወደ አማራውም ተሸጋግሮ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ፤በማት እነዘህ ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ ትግላቸው በአንድነት አጣምረው ፤አቀናጅተው ፤ዛሬ ህ.ወ.ሓ.ት.ወያኔ በመቃብሩ አፋፍ ይገኛል ።የኢትዮጵያ ነፃነትም እየደረሰ ነው፤ ብርሃኑም ተስፋ ይዞ እየሰነጠቀ ነው ።በዚሁ ጊዜና ስአት ፤የኢትዮጵያ ህዝብ እጅና ጓንት በመሆን በአንድነት ተባብሮ የዚሁ የወያኔ አፓርታይድ ( ፋሽሽትና ፤ዘረኛ ፤ከፋፋይ )ስርአት በጀመረው ቁርጠኛ ትግሉ ፋታ ሳይሰጥ አሁን በያዘው ቀጥሎ ፤ወያኔ እና ስርአቱ ከመሰረቱ ነቃቅሎ ከሃገራች ኢትዮጵያ እንዲያስወግደው ፤ወደ መቃብሩም እንድትከተው ፤ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሬን ሳቀርብ ፤ አባቶቻችን በአድዋ ፤በማይጨው ጦርነት መስዋእትነት ከፍለው ነው ፤ኢትዮጵያ ከወራሪው ፋሽሽት ጣልያን ነፃ ያወጥዋ ። ካለ መስዋእትነት፤ ነፃነትህ ፤የማንነት መብትህ አይገኝምና ።

ለማጠቃለል በአሁኑ ጊዜ የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛት ውስጥ ለምና ሰፊ መሬት የህ.ወ.ሐ.ት ገዥው ስርአት የሱዳን መሬት ነው በማለት ለሱዳን መንግሥት ለማስረከብ ላይና ታች እያለ ይገኛል ። ይህ በ1975 ዓ.ም በተቋጨው ወል እና ስምምነት በተፈራረሙበት መሰረት ነው። ሌላው በግንዛቤ ውስጥ መያዝ ያለብን ነገር የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ይህን ጎንደር ጠ/ግዛት እና ሱዳን የሚያዋስን 750 ኪሊ ሜትር የኢትዮጵያ ግዛትና ድንበር ነው ።ህ.ወ.ሓ.ት. የትግራይ ህዝብ እንኳን እውቅና ያልሰጠው ፤ያልተቀበለው ።ማንነቱ የማይታወቅ ፤ማፍያና የባንዳ ስብስብ በጎንደር የኢትዮጵያ ዳር ድንበር አሳልፎ ለማንም ባእድ ሃገር በምንም መልኩ ለመስጠት አይችልም መብትም የለዉም ።አሁን ለተፈጠረው ችግር ፤ከላይ የተጠቀሱ ስድስት የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች በሕግ ይጠየቁበታል ። በሱማሊያ የተጠናከር መንግስት ቢኖር ኑሮ የኦጋዴን የኢትዮጵያ ግዛትም አሳልፈው እንደሚሰጡት አንጠራጠር። ወያኔ በተቻለው አቅም ሁሉ ኢትዮጵያ አውድሞ አፈራርሶ ወደ መጣበት ትግራይ ሊመለስ ነው እቅዱ። ሌላው ለማስገንዘብ የምፈልገው ለጁቡቲ መንግሥት በሊዝ ሽፋን ስም በጣም ሰፊ መሬት ከኢትዮጵያ በወያኔ የተሰጠ መሬት አለ ይህም ለወደፊቱ የሚፈጥረው ችግር በእምነቴ በጣም ያስፈራኛል በዚሁም ከባድ ስጋት አለኝ ።እነዚህ የወያኔ መሪዎች ኢትዮጵያን ለማጥቃት ለማጥፋት ታጥቀው የመጡ ጠላት እስከሆኑ ድረስ ለጅቡቲ መሬት ለመስጠት ሲፈራረሙ በይዘቱና በውስጡ የቋጠሩት የፃፉት እትዮጵያን ለማጥቃት የተንኮል ሴራ ይኖርበታል የሚል ስጋትም አለኝ ለምን ቢባል ጠላት ጠላት ነውና። ልብ ያለው ልብ ይበል ( ሳዲቅ አህመድ )

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ድል ለተቀደሰች መሬት እናት ኢትዮጵያ

ገብረመድህን አርአያ
አውስትራሊያ

4 Comments

 1. ውድ ወንድሜ አቶ ገብረመድህን አርአያ – እንዴት ከርመሃል? ያው ከደርግ ጊዜ ጀምሮ በተለያዮ መድረኮች ላይ የወያኔን አጥፊነት ለህዝባችን ሳትሰለች ተናግረሃል፤ በመናገርም ላይ ነህ። አሁንም ጭብጥ የሆኑ የውስጥና የአለፈ ታሪክ ትውዝታን ተመርኩዘህ የወያኔን ከጅምር እስከ አሁን ላልሰሙና ሰምተው ለዘነጉ ወገኖቻችን ወያኔ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመውንና በመፈጸም ላይ ያለውን አሰቃቂ ግፍ እየነገርከን ነው።
  ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ባቀረብካቸው ሃሳቦች ላይ እንዳልኩት ሁሉ ከጅምር እስከ አሁን ያለውን በመጽሃፍ መልክ ጽፈህ ለህዝባችን እንዲዳረስ ማደረግ አለብህ። ያለዚያ እንዲህ በተባራሪ የምትለቃቸው ሃሳቦች ብልጭ ብለው እየጠፉ በኢንተርኔት ዋሻ ውስጥ ገብተው ይቀራሉ። መጽሃፉን ለመጻፍ በሃሳብ/በገንዘብ/ያንተን ሃሳብ ውሽት ሳይጨመርበት አጣፍጦ ለአንባቢ እንዲመች አድርጎ በማቅረብ የሚተባበሩህ አዕላፍ ወገኖች አሉ። ያንተ ድርሻ ንድፈ ሃሳቡን በወረቀት ላይ ማስፈርና እርዳታ መጠየቅ ብቻ ነው። የወያኔ ሴራ ከደደቢት እስከ አዲስ አበባ ….አንተ ብቻ የምታስታውሳቸውን ሳይሆን የዛን ጊዜ የትግል አጋር የነበሩትን፤ የውጭ ሰዎች ለምሳሌ በተራዶኦ መልክ ገብተው የነበሩ ነጮች ፎቶዎች/ ቪዲዮዎች፤ ወያኔ የትግራይን ህዝብ ከቀየው ካፈናቀለ በህዋላ በሱዳንና በሌሎችም የመጠለያ ሰፈር የሰሩ ሃበሾች/የእርዳታ ድርጅቶችና የዓለም የዜና አውታሮች የዘገቡትን ሁሉ አንድ ላይ በመጨመቅ እውነቱን ለህዝባችን በመጽሃፍ መልክ እንድታቀርብ እለምንሃለሁ። ጊዜ እየመሸ በመሆኑ ለነገ ለዛሬ ብለህ የምትተወው ነገር አይደለም። ብዙዎች የድርጅት ሚስጢር ነው በማለት ነገርን በሆዳቸው ይዘው ምስጥ የበላቸው አሉና! ቶሎ ጻፈው! በርታ!!

 2. Respect to Ato Gebremedhin Araya for his unfailing chronicling of all the evils done by the TPLF narrow people who under the guise of the Freedom For Tirgreans have done buodless and egregious catastrophe on Ethiopians and Ethiopia!!! Respect to this true son of Ethiopia. Let millions like you be born our of Ethiopia!!!
  Long live Gebremedhin Araya,

  When Ethiopia is rebuilt on the sepulchres of the parochial corrupts, and bandas, you will be decorated with highest medal the country can offer. Let the God of Ethiopia give you longevity, and your name will be written in Gold by the God of Ethiopia under whose protection, Ethiopia lives forever!!!

 3. ሰላም ጤና ይስጥልን አቶ ገብረመድህን አርአያ
  ከሁሉ በማስቀደም ጤናና እድሜ እመኝልሀለሁ ውድ ወንድማችን እውነቱን ሳትደብቅ ለምታቀርባቸው መረጃዎች አድናቆቴን እየገለጽኩ ከላይ አቶ ተስፋ የሰጡትን በማጠናከር ለትውልድ የሚተላለፍ ታፍሰው የማያልቁ መረጃዎችህን አንድ ላይ በማድርግ አንድ መጽሐፍ ብታወጣ መልካም ነው። የምትረዳው ነገር ካለ ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይረዳሃልና ጊዜህን ተጠቀም።
  እንዳንቆጭ አደራ።

  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

 4. ኣቶ ገብረመድህን፣ ሰላም እያልኩ በእድሜ ስለሚበልጡኝ ኣንቱ ልልዎ ተገቢ ነው።
  ፩ ተሓህት/ህወሓት ከጅምሩ ነበሩ። ድርጅቱ ሲጀመር የመገልንጠል ኣልነበረም። ማእከላይ ኮሚቴ ስራ ተመድቦ ሲሰራ ኣባይ ጸሃየ፣ ስብሃት ነጋ ፣ ስዩም መስፍን ተባብረው ነበር የመገንጠል ፕሮግራም ጽፈው የበተኑት። ኣረጋዊ በርሀ እና ግደይ ዘረሓጽየን ስብሰባ ጠርተው ለምን ብለው ሲጠይቁ ተሳስተናል ብለው ኣረሙት። ግን ከልባቸው ኣልነበረምና ቀስ በቀስ 8 ኣመት ሰርተው ኢትዮጵያውያን ኣረጋዊ እና ግደይን እንዲባረሩ ኣደረጉዋቸው።
  ፪ እርስዎም የዚህ ሰለባ ሁነው ወደ ሱዳን ተሰደዱ፣ ወደ ኢትዮጵያም ገቡ፣ ከዛም ተሰደዱ።
  ፫ ኣፍሪካ እያሉ ኣረጋዊ እና በርሀ ሓጎስ እየረዱኝ ነው ልወጣ ነኝ ብለው ነግረውኝ ነበር።
  ፬ ስለ “ገራዓልታም” ብዙ ኣስተምረውኛል።
  ፭ የመለስ ቤተሰብ ባንዳነት ኣስረድተውኛል። England ያለው ወንድምዎ ሓይለስላሰ የኢህኣፓ ታጋይ እነደነበር፣ የተወደዱ ኣባቱም የራማ ኣስተዳደር እንደነበሩ እና የመለስ ኣባትን ሚስት ከመደፈራ መሆናቸው በዚሁ የተረጋገጠ መረጃ ያገኙ እንደነበር ኣስረድተውኛል።
  ፮ ምን ነው የኢህኣፓ በሁለት መከፋፈል ኣይግቡበት ብልዎት፣ ኣንደኛው ወገን ደግፈው ሌላኛው ለማጥላላት ኣረጋዊ ስላለበት ኣረጋዊን እንደዚሁ የስም ማጥፋት ዘመቻዎ? ማንንስ ይጠቅማል? በቡና ገንዘብ የሚታለሉ ኣይመስሉኝም ነበር። የኢስኣፓ ወጣት የጨረሱ እኮ ናቸው የሚያመልኩዋቸው ያሉት። ወይስ እንደ ኣብርሃም ያየህ እርሾ ጠጥተዋል ልበል።
  ኣረጋዊ እንደዛ ቢሆንስ እርስዎ “የገራዓልታ” ያጫወቱኝ ምን ልዩነት ኣለውና፣ ለኔ ስላጫወቱኝ እኔ ቃሌን ኣላጥፍም፣ እርስዎ ከወስላታነት ታግሰው ከእድሜዎ ጋር የሚሄድ ምክር ቢለግሱ ይሻላል የከሰሩት ግለሰቦች መጫወቻ ኣይሁኑ። እኔ ቃሌን ኣላጥፍም፣ እርስዎ ከወስላታነት ታግሰው ከእድሜዎ ጋር የሚሄድ ምክር ቢለግሱ ይሻላል የከሰሩት ግለሰቦች መጫወቻ ኣይሁኑ።

Comments are closed.

Previous Story

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተናገራቸው እየተፈጸሙ ይሆንን? n- ከተማ ዋቅጅራ

Next Story

ሃላፊነት የጎደለው ስር አትን  ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ለማስወገድ መሞከር አደገኛነቱ  አጠያያቂ አይደለም – ጊሸይ ጊሻ

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop