October 11, 2017
12 mins read

ማንን እንመን? – ገብርኤል ብዙነኀ

 ይህ ጥያቄ እኔ ባደባባይ ላውጣው እንጅ በያሉበት ሆነው ባንድ ጉዳይ ላይ የተለያዩ  ነገሮችን የሚዘበራርቁትን ጳጳሳት  መምህራን የሚሉትን በቤተ ክርስቲያናችንውስጥ ያለውን ብቻ ሳይሆን በሩቅና በቅርብ ያለውን ተመልካች እየታዘባቸው አማኙን እያሳዘነ ነው።  በየ ቤተ ክርስቲያን በህዝብ ፊት እየቆሙ የሚያሰራጩትመዘበራረቅ የማያመውና የማይሰማው እኔ ምና ገባኝ ብሎ ዝም የሚል ክርስቲያን እንደምን ያለ ክርስትና ነው? የሚል ጥያቄ ከተለያየው ህዝብም በየቦታው እያስነሳነው።

ቀሲስ አስተርዕየ
ማንን እንመን? - ገብርኤል ብዙነኀ 1

የውጩ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ የቀድሞው ቆሞስ አባ ወልደ ትንሳዔ ያሁን ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስ “ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ጠበቃ አማላጅ ነው” ይላሉ።

 የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን  እወክላለሁ የሚሉት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል ፤ “የውጩ ሲኖዶዶስ ክርስቶ በሥጋው ፍጡር ነው ስለሚል ከእንግዲህ እርቅ የለም” ይላሉ።

የውጩ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስያትል የሚኖሩ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ የሚባሉት በበኩላቸው የራሳቸው ሲኖዶስ አባል የሆኑትን “አቡነ በርናባስን እስልምና እንኳ ፈራጅ ብሎ አያምንም ክደው አማላጅ ነው በማለታቸው መናፍቅ ናቸው” ብለው አውገዘዋል።

ቆሞስ አባ መአዛ በየነ የሚባሉትም ቤተ ክርስቲያናችን ከምትለው ውጭ የሚወቀሱባቸውና የሮማ ካቶሊክን እስታቹ በቤተ መቅደስ መተከልንና ብዙ የዘበራረቁት እንዳለ ሆኖ፤ አሁን በተነሳው ነገርም፤ እነ ዶክተር አክሊሉን እየጠቀሱ ተከሰተባቸው እያሉ አቡነ በርናባስን በመደገፍ ይናገራሉ። 

 በገለልተኝነትን ሽፋን በማድረግ ለሳቸው የተመቻቸውንና ደስ ያላቸውን ብቻ እየመረጡ ነው ማለት ነው የሚናገሩት? አሁን የሚናገሩትን ትክክል ይሁኑ አይሁን ሊመሰክሩላቸው የሚችሉት ባንዲት ቅንጣት ብቻ የሚስማሟቸው ሰዎች ካልሆኑ ማነው የሚመሰክርላቸው።  በግላቸው ስለሚያደርጉት ያፈነገጠ ነገር ትክክል ስለመሆናቸው ማነው የሚያረጋግጥላቸው?  ከማን መምህር ከየት ጉባዔ ተማሩት?

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ የሚባሉም፦  የኛ ሊቃውንት አባቶች የማይጠቅሷቸውን የጣሊያኖችን ሰዎችና እነሱ የሚሉትን እየደረደሩ አኀት አብያተ ክርስቲያናትናት ከነሱና ከእሱ  እንዲማሩ በድፍረት እየተናገሩ ነው። ይህም ባብነቱ ትምህርት ነበርን በሚሉ ሁሉ ትልቅ ውርደት ያስከተለባቸው ወቅት ነው። የተዘበራረቀ የሚናገሩት ሁሉ የሊቃውንት ጉባዔ የሚባለው ጭራሽ እነደሌለ ነው።የተመለከተውን ሁሉ እያስገረመው ነው። ተሃድሶዎች ጋር በውጊያ ስንጠመድ ሳናውቀው ቀኝ እግራችን ካቶሊኮች ግቢ ዘው ብሎ መግባቱን ይሆን?

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽህና የAugustine “Immaculate Conception” በኋላም 1854 የሮማ ካቶሊክ Pope Puis ዶክትረን አድርጎ የወሰነውን የኦርቶዶክሶች እምነት ነው አትናትዮስም ከሺህ አመት በፊት የተናገረው ነው ን ነው ካቶሊካዊ አገላጽ እና ፍጽም ከኦርቶዶክስያልሆነና አትናትዮስም “On the Incarnation by St. Athanasius” በሚለው መጽሃፉ ውስጥ የማይገኝ ነው። ይህንን የAugustine የስህተት ትምህርትመላው ኦርቶዶክሳውያን በተለይም ከእኛ ጋር የእምነት አንድነት ያላቸው Oriental Churches (አሃት አብያተ ክርስቲያናትን) በፍጹም እንደማይቀበሉት የካቶሊክብቻ እምነት እንደሆነ ሳይገልጹ ጭራሽ የአትናትዮስም እምነት ነበር አሉን ካቶሊቶሊኳዊውን እምነት የእኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክቤተክርስቲያን  ለማድረግ  ነውን !

በዚህች አጭር ጽሁፍ የተገለጹት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚታየውን ወዲህ ወዲያ ወዲህ  የተዘበራረቀ ነገር እየተናገሩ እርስ በርሳቸው በመደባደብ ህዝቡን  የርስ በርሳቸው መደባደቢያ ብትር የሚታገሉበት ሜዳ አደረጉት። ከማዳመጥ በቀር የምትናገሩትን ሁሉ ከየት አመጣችሁት? ብሎ ህዝቡ እንደማይጠይቃቸው ተረድተው፡ በዚች ኢትዮጵያቤተ ክርስቲያን ፤ በመነኩሴ በጳጳስ  በሰባኪ ስም ራሱን ሸፍኖ በመደባደብ እየዞሩ ህዝቡን በመከፋፈል ችግሩን እያጋጋሉ  እያሰለቹን ቤተ ክርስቲያንን እያናወጣት ያለው የተዘበራረቀ ንግግራቸው ግራ ለተጋባነው ማነው እውነቱን ሊገልጽልን የሚችለው? የጥንት ሊቃውንት ያብነቱ መምህራን ይህን የተዘበራረቀ ነገር እንዴት  ያስተካክሉትና ያስታርቁት ነበር?ማነው የዋሸው?

የሚነገረንና የምንሰማው ምንድነው? ወዴትስ እየተመራን ነው? እርስ በርሳቸው በሚደርጉት ሽኩቻ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነገረ መለኮት ራሳቸው እየሳቱና ህዝቡንም እያሳቱ ናቸው።ለቅድስና መወዳደርና መነጻጸር እጅግ አስፈላጊ ሆንም፤

ቅዱስ ጳውሎስ እራሳቸውን ከገዛ ራሳቸው ጋራ እያነጻጸሩ እኛ ብቻ በማለት እራሳቸውን እያገነኑ ከተግዳሮት እንደወደቁ ሰዎች አንሁን። ራሳቸውን ከራሳቸው ጋራ የሚያነጻጽሩ ሰዎች የሚናገሩትን አያውቁም” ብሎ ያስጠነቀቀውን ባለመርሳት፤

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሄርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ተጠንቀቁ ። ከሄድኩህ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ደቀ መዛሙርትን ወደ ኋላ ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገረን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሱ እኔ አውቃለሁ” ( የሐዋ ፳፡፳፰᎗፴) እያልን ወደፊት የሚከሰተውን ሳይቀር እየተናገርን እንደ እነ ቅዱስ ጳውሎስ፤ ያለፈውን ካለው ጋራ እያነጻጸርን፤ ዘመናችንን እየዋጀን፤ የሚመጣውንም እየገመትን፤ የተኩላ ባህርይ ካላቸው ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን በትጋትና በቅድስና ለመጠበቅ በታሪክ የሰማናቸውን እንደነ አቡነ ጴጥሮስ የነበሩትን ሰማእታት ሳንረሳ፤ ክርስቶስ የዮሐንስን ደቀ መዛሙርት አነጋግሮ ከሸኘ በኋላ ሰዎች ከእምነቱና ከወቅታዊውችግር ጋራ የማይገናኝ ነገር ሲነጋገሩ ሰማና “ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆ ወይስ ቀጭን ዋብስ የለበሰው ሰው ለማየት ነው  የመጣችሁ?” እያለ አቋም የለሽነታቸውንና አላማ ቢስነታቸውን በምሬት  ነገራቸዋልና።

ቀሲስ አስተርአየለመሆኑ እሰዎ  እንዴትስ ያስታርቁታል?  በእምነታችን ላይ የዘራውን የጥርጣሬ መንፈስእንዴት ይመለከቱታል? መታለፍ በሌለባቸው  ነገሮች ላይ የግብጽ ይህን ይላል አኀት አብያተ ክርስቲያናት ይህን ይላሉ፤ የሮማ ካቶሊኮች ይህን ይላሉ፤ ከማለተዎ  በፊት ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት አስተማሩኝ ከሚሏቸው ሊቃውንት አባቶች የተማሩት ካለ ይንገሩን። የተነሳውን ዝብርቅርቅ አብራርተውና አፍታተው ለመግለጽ ካቅመዎ በላይ ከሆነ፤ የማያውቁትና ያልተማሩት ከሆኑ አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ወቅ ነውና በዝምታወ ይቀጥሉ። 

ዝምታ ወርቅ ነው የሚባለው ባላወቁትና ባልተረዱበት ነገር እንደ ሰንበት ተማሪዎች ዘሎ መግባትን ለመቃወም እንጅ፤ የተማሩትንና  ያመኑትን፤ ውሎ አድሮ ለህዝብ መገለጡ አይቀርምና ቢገለጥ የማያሳፍረውን የመናገር ደግሞ  የሊቃውንት የምሁራን የክርስቲያኖች ነውና።ምን ብሎ እንዲጠይቅ የሚያደርግ ነው። ይልቁንም የቤተክርስቲያኒቱ አካል ነኝ ለሚል በግሌ ምን ማድረግ ይገባኛል? ብሎ ራሱን እንዲጠይቅ የሚገፋፋና የሚያስገድድድ ይመስለኛል።የተዋህዶው ሃይማኖት እምነት መሠረት የሆነው ነገረ መለኮት የተዛባበት ጥያቄ ላይ የወደቀበት ወቅትነውና።

ይህ የምንገኝበት ዘመን እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ጥያቄ ይቀሰቅሳል። እምነቱና ችሎታው ሳይኖራቸው ከቦታው ጋራ የተገናኘውን ክብርና ጥቅም ለመሰብሰብ ሲሉእየዘለሉ በገቡ ሰዎች ላይ የሚመጣው ፍርድ እጅግ በጣም ያስፈራል።ይህ የሜዳ ጨዋታ አይነት ጫጫታና ሁካታባቢሎናዊ ዝብርቅርቅ ምስቅልቅል ማንን እንመን?

ሰላም! ሻሎም!

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop