September 8, 2017
14 mins read

 ኦሮሚኛ ተናጋሪ የኦነግ ጠባብ ብሔረተኞችና በአክቲቪስት ስም የተደራጁ አክራሪዎች!  (በመርዕድ ከተማ) 

ለስልጣን የቋመጡ ሃገር በቀል ኦሮሚኛ ተናጋሪ የኦነግ አክራሪ ጠባብ ብሔረተኞች በኪስ በሌለው የሬሣ ሣጥናቸው ያጨቋቸውን መናጆና መንጋ ጀሌዎችን በፈጠራ ታሪክ በመተብተብ ያለ ልጓም ይጋልቧቸዋል:: ምኞትና ፍላጎት እየተጋጩ እረፍት ይነሷቸዋል:: እውነታን፣ምክንያታዊነትን፣ማስረጃንና መረጃን ሣይሆን ስሜትንና ህልምን እያስጨበጡ ይነዱዋቸዋል:: ያለ ንፋስ የሚበተን አቧራ ያለ ሙቀት በበረዶ የሚቀልጥ ደመና መኖሩን እየሰበኩና በቀን ቅዥት ተሸፍነው እኛ ለናንተ <<ህልም>> አለን ይሏቸዋል:: የያዙትን ኢትዮጵያዊ ማንነት አስጥለው የማያውቁትን ዓለም እንዲቋምጡ በማድረግና በማስጨበጥ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅኝት የ19ኛውን ክፍለ ዘመን የፈጠራ ትርክታቸውን ይግቷቸዋል:: ዛሬ ላይ በወያኔ የተጫነባቸውን ጭቆናና የአፓርታይድ ሥራዓት ሣይሆን ጥንት በግል ደረሠብን የሚሉትን <<ጉዳትና ቁስል>> እያወሡ ከዛሬ ጋር ሣይሆን ከትላንት፣ከእውነታ ጋር ሣይሆን እነርሱ እራሣቸው ከማይፈቱት ህልምና ቅዠት ጋር ግብ ግብ እንዲይዙ በዘገምተኛ ህሊናቸው ይሠብኩዋቸዋል:: በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሆነው ከ19ኛውን ክፍለ ዘመን ጋር ያዋጓቸዋል::እነርሱ በሠማንያ የተጋቡትን የህልም እንጀራና የህልም ዕይታን (wishful thinking & wishful seeing) ምስኪን ደቀመዝሙሮቻቸውን ይጋብዟቸዋል:: የቀቢፀ – ተስፋ ናና ከረሜላ እያስላሡ መርዛማ አረንቻታ ይግቷቸዋል:: በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅኝት የ19ኛውን ዘመን በምናባቸው ያስዳስሷቸዋል:: ከነባራዊው ዓለም እውነታ ጋር ያፋቷቸዋል:: አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገር፣ አንድ ዓይነት ሃይማኖት ወይም ስነልቦና ያለው

የኦሮሞ ማህበረ-ሕዝብ ብቻውን ከኖረ ከጭቆና ተላቆ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ይሆናል እያሉ በቅዥት ባህር ይቀዝፏቸዋል:: ዛሬ ላይ ሆነው ነገን እንዳያልሙና ለነገ እንዳያቅዱ ችካልና ግርዶሽ ይሆኑባቸዋል:: እነኚሁ ጭፍን ጠባብና አክራሪ ብሔረተኞች ጥሬ ያልሠጧትን ዶሮ እንቁላል ማስፈልፈል፤ ሣር ያልቀለቧትን በቅሎ ማስገር እንደሚችሉ በመለፈፍ ጀሌዎቻቸውን ኮርቻ ጭነው በቅጥፈት ይገሯቸዋል:: ገና ከፅንሳቸው ኢ-ዲሞክራሲያዊ የሆኑ ለግል ዝናና ጥቅም የሚራወጡ በገደብ ዐልባ ስሜታዊነትና የግል ዝና የመቃተት ህመም (Histrionic Personality Disorder – HPD) የሚሠቃዩ ቋንጣ እንዳየችው ያቺ ድመት ቀቢፀ ተስፋን ብቻ አንግበውና የአብሮነቱን ጣራ ደርምሠው ዜጎችን ከጋራ ጎጆ ለመበተን የሚቃትቱ ገመምተኞች የህዝብን መፃዒ ዕድል በራሳቸው ወስነው የዋህ እርግቦችን ከሠፈሩበት ዛፍ አውርደው የሠለለ ቅርንጫፍ ላይ ለማሣረፍ እንደሚደክሙና እንደሚታገሉ ያመላክቷቸዋል:: የተጠናወታቸውን የግል የበታችነት ስሜት ከህዝቦች ፍላጎት ጋር እያጋቡና እያጋጩ የነርሱን ከንቱ ህልም ታቅፈውና ተደግፈው ኢትዮጵያዊነትን እንዲንዱ ኢትዮጵያ ሃገራቸውን እንዲያፈርሱ ይገፏቸዋል:: ሽረባና መርዝ ቀምመው ቂም፣በቀልና ደም ያቃቧቸዋል (በዊሊያም ሼክስፒር ድርሠት ውስጥ ኦቴሎ ሚስቱን ዴዝዲሞናን የገደለውና በኋላም ተፀፅቶ እራሱን የገደለው በላጎ የቅጥፈት ወሬ ተታሎ እንደነበር እናስታውስ!።) ይህን መሣዩን ከንቱ ቅዥት ቃዥተውና ምስኪን አሸብሻቢዎቻቸውን አሸክመውና ነድተው በተመሣሣይ ቀመር ከዚህ ቀደም ለስልጣን የበቁ እንደ ወያኔና ሻዕቢያ ያሉ <<የነፃ አውጪ ግንባር>> ተብዬዎች የሠበኩትን ፍትህና ዲሞክራሲ ነፍገው ለስልጣን ጥማቸው መወጣጫ የተጠቀሙትን የምልዐተ-ህዝቡን ትከሻ ተመልሠው በባሠና በከፋ መልኩ ሲወቅሩና ሲረግጡ አሁን ማየት ብዙ አላስቸገረም ወይም ነቢይ መሆንን አልጠየቀም:: ይህ ጭፍን ጠባብና አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች ቅዥት እውንና ገቢር መሆን ቢችል ኖሮ የነፃነትና የፍትህ ተጋድሎው ለአንድ ዓይነት ቋንቋ፣ሃይማኖትና ስነልቦና ለመፍጠር የሚደረግ ትግል በሆነ ወይንም አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገር ፣አንድ ዓይነት ሃይማኖት ወይም ስነልቦና ያለው ማህበረ -ሕዝብ ከውልደቱ ቀን አንስቶ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ነበር:: ለዚህም ነው <ቄሣር ክሊዮፓትራን ባይወድ የዓለም መልክ አንድ ይሆን ነበር> በሚል ዓይነት ምልከታና እራስን ብቻ በሚያገለግል ብዥታ(self-serving bias) የሚደፍቋቸው!

በጅምላ ፍረጃ (Hasty Generalization)የተካኑት እነዚህ በህልም የሠከሩ ጠባቦች ትላንት ከሚገድሉት ጋር ሲገድሉ፣ከሚቀድሱትና ከሚዘይሩትጋር አብረው ሲጨፈጭፍ፣ሲይስጨፈጭፉና ሲያሸበሽቡ የነበሩ ኦሮሚኛ ተናጋሪ አክራሪ አክቲቪስት ተብዬዎች ዛሬም ተከታዮቻቸውን እየማገዱና በነሱና በነፃነታቸው ስም እየቸረቸሩ ያሉ ፖለቲካዊ በታኝ ሃይሎች (Political centrifugal forces)ናቸው:: ውጤቱ ወይም ጦሱና መዘዙ (unintended consequences) ባይገባቸውም በተግባርም ሊያሣኩ የሚፍጨረጨሩት ሂሣቡ የተወራረደውን፣በተደጋጋሚ በሽንፈት የተገባደደውን ኢትዯጵያን የማፍረስ የቅኝ ገዢዎችን ምኞት ገቢር እንዲሆን ነው:: ጠባብ ብሔረተኞቹ የወያኔ ገዢዎች ድሮም ሆነ አሁን <<በነፃነት ግንባር>> ስም ያንቀሣቀሱዋቸውንና የሚያንቀሣቅሱዋቸውን ባንዳዎችና ሹምባሾች የተጓዙበትን መንገድ እንዳለ በመቅዳትና በማቀንቀን (copycat) ሊተገብሩም የሚቃጣቸው ጥንታዊውንና ዘመናዊውን ቅዠት ነው:: ሊንዱትና ሊዋጉትም የሚዳዳቸው ረቂቅና ሚስጥራዊ ሐሳብ ወይም የእምነት ቃል የሆነውን ኢትዮጵያዊነትና የመሠረተ-ሃሣቡ ማህተም የሆነችውን የቁርጥ ቀን ልጆቿ በደም በአጥንታቸው እነርሱ ሞተው የታደጓትንና ያኖሯትን ኢትዮጵያን ነው:: ለዚህም እኩይ ተግባራቸው ያሠለፉት በአክቲቪስት ስም በበጎች የተደራጀና በጎች የሚመሩት የጥፋት ብርጌድ ነው::ታዲያ ምን ያደርጋል ታላቁ አሌክሣንደር አንድ ወቅት <በጎች ከሚመሩት የአንበሣ ሠራዊት ይልቅ አንበሣ የሚመራው የበጎች ሠራዊት ይሻላል> ብሏቸው ነበር::

ሌላው እኔን የሚገርመኝና የሚያስታውሰኝም <የእንሠሦች ዓመፅ (Animal Farm)> በተሠኘው ልበ ወለድ መፅሐፉ ጆርጅ ኦርዌል የዜጎችን ፍፁም እኩልነት እናሠፍናለን ብለው ስልጣን፣ልዩ መብትና ጥቅም ለጥቂት ምርጦች ጀባ የሚሉ ግብዝ መንግስታትን የተቸበት ምፀት ውስጥ በእንሠሦቹ የመጀመሪያ የአመፅ እንቅስቃሴ ምዕራፍ እንሠሦቹ ሁሉ ተግባብተውበት የነበረው “ሠባቱ ትዕዛዛት (Seven Commandment)” በተሠኝውና በአሣሞቹ የተነደፈው መተዳደሪያ ሠነድ ላይ የተደነገገው(ልክ እነደ ወያኔ «ሕገ-መንግስት) <ሁሉም እንሠሦች እኩል ናቸው (All animals are equal)> የሚለው መመሪያ ያለ እንሠሦቹ እውቅና ወይም ይሁንታ(awareness & approval) ጮሌዎቹ አሣሞቹ(ልክ እንደ ወያኔ) ሥልጣን መንበር ላይ ከቆናጠጡ በሗላ የበላይነታቸውን በሚያሠፍንና በሚያረጋግጥ መልኩ ተሻሽሎና ተለውጦ <ሁሉም እንሠሦች እኩል ናቸው::አንዳንዶቹ ግን ከሌሎቹ የበለጠ እኩልነት አላቸው (All animals are equal,But some animals are more equal than others)> በሚል አዲስ መመሪያ/motto/ ተተክቶ የአሣማዎቹ መንግስትና አሣማዎቹ ቁንጮ ሆነው በመውጣት በትረ-ሥልጣኑን በመቆጣጠር ያገዱዋቸውንና የነዱዋቸውን እንሠሦች ነው::በዚሁ መፅሃፍ <ናፖሊዮን> የተሠኝው አሣማ <አንዱ እንሠሣ ሌላውን ፈፅሞ መግደል አይችልም> ሲልና ሲደነፋ ቆይቶ ‹ለዓመፅ ተነሳስታችሁ ነበር› በሚል ሠበብ በውሾቹ ያስገነጣጠላቸውን የዋህ እንሠሦችን ነው:: <የሠው ልጅ ሁሉ ጠላታችን ነው> በሚል ሸውራራ ዕይታ ከአላማጆቻቸው ጋር የነበራቸውን መስተጋብር አፍርሰው የበተኗቸውን እንሠሦች ነው::የዚህ መፅሓፍ ይዘትና ምፀት ወያኔ በቋንቋ ፌደራሊዝምና በጎሣ ስም አደራጅቶ የነዳቸውን እንደ ኦነግ ያሉትን ሃይሎች ነው።

አሁን የማየው ትይንትም ከዚህ ያልሸሸና ያው ጠባብ ብሔረተኞቹም ሆኑ ገዢዎቹ የወያኔ አሣሞች፤ተናካሾቹም የኦሮሞ አክራሪ ጠባቦች ያው የናፖሊዮን ውሾች መሆናቸውን ብቻ ነው::የኦሮሞ አክራሪዎችም ሆኑ ወያኔዎች ጠባብ ብሔረተኞች ናችው።ሁለቱም ግንኙነታቸው የአዞና የወፍ ነው።ሁለቱም የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው።ሁለቱም የሚዋጉት ኢትዮጵያዊነትን ነው።መፍትሄውም ለጋራ ጠላቶቻችን የጋራ ግንባር መፍጠር ብቻ ነው።መፍትሄውም ሁለቱንም በጋራ መታገል ነው።

ብደምረው፣ብቀንሰው፣ባባዛውና ባካፍለው ዜሮ እየሆነ ያስቸገረኝ ስሌትም ይህ ብቻ ነው!!
=====
” ማንኛውም የተሽከርካሪ ጎማ ወይም መሪ ምንም ያህል ወደ አንድ ወይም ሌላ አቅጣጫ ቢገፋ:ቢዞርና ቢንጋለል ሚዛኑን ጠብቆ በመሽከርከር በፊት ወደነበረበት እንደሚመለሠው ሁሉ: ከቶውን ሊቀለበስ የማይችል መስሎ የሚታይ ግዙፍ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከተከናወነ በሁዋላ ሁሉም ነገር እንደገና ወደ ድሮ ቦታው ዞሮ ማፈግፈጉ ወይም ወደ መጀመሪያ ቅርፁ ተመልሶ በነበረበት መዳከሩ ላፍታም አያጠራጥርም”
1984
(ጆርጅ ኦርዌል)

“… Even after enormous upheavals & seemingly irrevocable changes,the same pattern has always reasserted itself,just as gyroscope will always return to equilibrium,however far it is pushed one way or the other ”
1984
(George Orwell)
~~~~XXX~~~~

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop