የአንድ አገር ህዝቦች ሁለት ዜግነት – ቬሮኒካ መላኩ

ትናንት መሰለኝ በተመሳሳይ ቀን ፣ በተመሳሳይ ሰአታት በአንድ አገር ፣ በአንድ ጀምበር ሙቀት ክልል ሁለት ለማነፃፀር የሚከብዱ የ”ልማት ” ዜናዎች አነበብኩኝ ።
ዜና 1 ~ ትግራይ ክልል የ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣበት የመኪና ፋብሪካ አስመረቀ ” ይላል ።
ዜና 2 ~ የአማራ ክልል በደብረታቦር ለ7 ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል ያስገነባውን ማረሚያ ቤት ( እስር ቤት) አስመረቀ ” ይላል ።

ይሄ ፖለቲካዊ ትራጄዲ ምን ይባላል? ወያኔ በክልሎች መካከል የተደረገ ተመጣጣኝ ልማት ማለት ይሄ ነው ይለዋል።
ወያኔ 5ሚሊዮን ለማይሞላ የትግሬ ህዝብ የመኪና ፋብሪካ ሲገነባለት ልማቱ ተመጣጣኝ ይሆን ዘንድ ከ 40 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ላለው አማራ ህዝቡን እንደ ጋማና ቀንድ ከብት የሚታጎርበት እስር ቤት አስመርቋል ።
ምንም አይነት ተአምር ያዘለ ሎጅካዊ ድያሌክቲክም ቢደሰኮር ይሄን አይነት ስግብግበነትና አድሏዊነት ሊያስተባብል ይችላል ማለት ድፍን ስህተት ነው።

” እኛና ” እና ” እነሱ ” በአንድ አገር ብንኖርም አንድ ጀምበር የምታፈልቀውን ሙቀት ብንጋራም በመሰረታዊ ባህሪያችን ግን እንለያያለን ። እነሱ በቃኝን የማያውቁ ስግብግቦች ሲሆኑ እኛ ያለችንን ኩርማን እንኳን ቆርሰን የምንሰጥ ነን ።

በአገራችን እነዚህ አልጠግብ ባይ ሰፍሳፎች እስካሉ ድረስ በፍፁም ሰላም ሊኖር አይችልም ። በሰዎች እና በብሄሮች መካከል የጋርዮሽ የሆነ ነፃነት ፣ ፍትህ ፣ፍቅር ፣ርትእ … ሊኖር አይችልም ። የአንዱ ክልል ህዝብ በሃብት ጠግቦ ቁንጣን ሲያማቅቀው በአንፃሩ 95 በመቶ የሆነው ህዝብ በረሃብ ጠኔ ተጠብሶ ያልቃል ።
ህገ_ ሞራልንም ሆነ _ህግጋተ አለምን ጥሶ ከሚኖር ጋጠ ወጥ ሰፍሳፋና ጀብራራ ማህበረሰብ ጋር የአንድ አገር ዜጋ መባልም አሳፋሪ ነው።

አንድ ህብረተሰብ ባላሰበው እና ባልጠበቀው አይነት ከአንድ መራራ የፖለቲካ ፣የኢኮኖሚና የሶሻል ቀውስ እና ክስረት ውስጥ በድንገት በተዘፈቀ ጊዜ በግለሰቡም ሆነ በማህበረሰቡ ላይ ብዙ አሳዛኝና አስቀያሚ ድርጊት ይፈፀማሉ ። ይሄ የተለመደ ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ግን የበዛ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  39ኛ የካቲት ለማክበር ሽርጉድ እና የተሟጠጠው የትግራይ ህዝብ ስሜት

ይሄ አይነቱ ክስተት ከመቸውም የታሪክ ዘመን በከፋ በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ ድህረ ግንቦት 20 ኮድኩዶ ካስወለደው የቀውስ ዱብዳወች ውስጥ ዋናው ክስተት ነው። አሁን ግልፅ እየሆነ ነው ።
የአንድ አገር ህዝብ ፣የአንድ አገር ዜጋ ብንሆንም ጎራችን ለየቅል ነው ። የአንድ ወጥ ባህል ልምድና አካባቢ ውልዶች ብንሆንም ግባችን የተለያየ ነው። ጠላዥና ተጠላዥ ፣ መጥማጭና ተመጥማጭ ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆነን የምንቀጥልበት ምክንያት አይኖርም ። የማህበረሰብ ችግር መንስኤዎችና መፍቻ ቁልፎቻቸው ግልፅ ነው መጣጭን ከተመጣጭ የግድ ገንጥሎ የመጣል ዚቅ ብቻ ነው ።

ይሄን ለማድረግ የፈለገው የጭቆና ገመድ ቢተበተብ ህዝቡን ሊሸብበው አይችልም። የፈለገው የመሰናክል ወጥመድ ቢኮለኮል ሊያደናቅፍ አይችልም። ለዚህ ተፈፃሚነት በአለም የተመሰከረለት ተኩሶ የማይስት ፣ ተናግሮ የማይሳሳት ፣ ጠላት ይዞ የሚወቃ ተቃራኒውን የሚደቃ ህዝብ አለ ። ዲቦይስ የተባለው ምሁር “ተነስ ታገል የምታጣው ነገር ቢኖር የታሰርክበትን ሰንሰለት ነው ” እንዳለው ዲቦይስ ብትነሳ የሚቀርብህ ብቸኛ ነገር እግር ከወርች የታሰርክበት ሰንሰለት ብቻ ነው ።

1 Comment

  1. Dear Veronica ,
    It has been said more than enough how evil
    The Weyane’s are and the amhara Paid dearly, still are.
    The key to stop is to get organizedand that is the only way out.
    Do not forget wayane get where it is now

    simply by getting organized.
    How evil they are they are on target what they intialy started to do for tigrai.

Comments are closed.

Share