በዳዊት መላኩ
በዛሬው ዕለት መጋቢት 01 ቀን 2013 እ.ኤ.አ በጀርመን ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የሀይማኖት አባቶች የተገኙበት ፍራንክፈረት በሚገኘው የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት
ከቀኑ 13፡00 ሰዓት ጀምሮ ለ3፡00 ሰዓት የዘለቀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዱዋል፡፡ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው ከነበሩ የተለያዩ መፈክሮች ውስጥ የኢትዮጵያ አንድነት በወያኔ ሴራ አይደናቀፍም፤የምንታገለው የወያኔን ስርዕት እንጅ ግለሰቡችን አደለም፤የታሰሩ ጋዜጠኞችን ፖለቲከኞች ይፈቱ፤ወያኔ ያካሄደውን የፓጥርያሪክ ምርጫ እናወግዛለን፤አቡነ ማቴያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን እምነት አይወክሉ፤በክርሰትና እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚካሔደው አፈና እና የመብት ረገጣ ይቁም፤እኔም ለእምነቴ አቡበከር ነኝ የሚሉ ይገኙበታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ቆንስላ ጽ/ቤት የሰልፈኞችን ማናነት ለመለየት ከህንጻው ሁለተኛ ፎቅ ላይ በስውር የተገጠመውን ቪዲዮ ካሜራ በመጠቀም ፎቶ ግራፍ ሲያነሳ ውሏል፡፡ይህም ተግባር ሰልፈኞችን ይበልጥ ለቁጣ አነሳስቷቸው ወያኔ ሌባ፣ሌባ፣ሌባ እያሉ አካባቢውን በጩኸት አደባላቀውታል፡፡
የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ልኡል ቀስቅስም በኢትዮጵያ ያለው ዘረኛ እና አንባገነን ስርዓት እስክልተወገደ ድረስ ተቃውሞአቸውን አጠናክረው እንደቀጥሉ ለሰልፈኞች አሳስበዋል፡፡