ከፖለቲካ ነፃ የሆነ አንድም ሰው የለም ፣ በሀገር ጉዳይ ገለልተኛ መሆን አይቻልም!

በቶማስ ሰብስቤ
ሀገር የፖለቲከኞች ብቻ አይደለም።በአንድ ሀገር ከፍተኛ ድርሻ ያለው ህዝብ ነው።ከህዝብ የተውጣጣ ፖለቲከኛ ደግሞ አደራ የሚወጣ አካል ነው።ህዝቦች ሀገራቸው ሁሌም በቅርበት የመከታተል ግዴታ አለባቸው።የትኛውም ህዝብ በሚኖርበት ድንበር ውስጥ በሚፈጠር የትኛውም ነገሮች የመጀመሪያ ሰለባ ነው።ሀገር ስትጠቀም ህዝብ ይጠቀማል  ፤ ሀገር ስትከስር ህዝብ ኪሳራ ያወራርዳል።ይህን እውነታ ወደ ጎን ትቶ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ማለት አደጋው ከፍተኛ ነው።ማንም ሰው በአንድ ሀገር የሚወጣው ህግ የሚጎዳው ቢሆን ነፃ ነኝ ያለ ሁላ ከመጎዳት አይድንም።የሚመራው መንግስት ሀገር አፍራሽ ፖሊሲ ቢያወጣ ነፃ ነኝ ያለውም ይቀምሳል ገፈቱን።እርስ በእርስ የሚያፋጅ ሰርአት እየመጣ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ቢሉ ከስቃይ  አያመልጡ።
በሩዋንዳው የእርስ በእርስ እልቂት ያለቁት ከ800  ሺ በላይ ሰዎች ፖለቲከኞች አይደሉም ፣ ንፁሃን ሰዎች እንጂ።በእልቂቱ ወቅት ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ያለ ከጭፍጨፋው አልተረፈም።ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ይውጣም አልተባለም።ምን አገባኝ ፖለቲካ ያለም ፣ያላለም አለቀ።
ዮጎዝላቪያ ስትበታትን ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ያለ ከችግር እና ከሰቆቃ አልተረፈም።ሀገሩ ዪጎስላቪያ ትንንሽ ሀገር ሆና ስትቆረስ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ እዚው ይኑር አልተባለም።ሰባት ቦታ ከመከፋፈል አላመለጠም።አንድነትን የፈለጉ ዮጎዝላቪያዊያን በፖለቲከኛ መሪዎቻቸው ተቆራርጠው ዛሬ ያቺ ሀገራቸው የለችም።ዮጎዝላቪያ ምድር ላይ ጠፍታለች።አንድ ሀገር ነበረች ተብሎ ነው የሚተረተው።ዛሬ ዮጎዝላቪያዎች ኮሶቮ፣ቦሲኒያ፣ሰርቪያ፣ክሮሺያ በሚሉ ትንንሽ ሀገራት ተወክለዋል።ትልቅ ሀገራቸው ጠፍታለች እንደ ዳይኖሰር።ታዲያ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ ፣ስለ ሀገሬ ገለልተኛ ነኝ ያሉ ዮጉዠላቪያኖች አሁን የት ናቸው? ከመከፋፈል ተረፉ? ከፖለቲካ ነፃ መሆናቸው ከመጣው ችግር ነፃ አደረጋቸው?……ከፖለቲካ ነፃ ነን ባሉበት አንደበታቸው አልቅሰዋል ፣ተሰደዋል ፣ሞተዋል።የረፈደ እንባ ስለሆነ የአንድነት ሰአቱ አልቆ ያው ተበትነዋል።
ከፖለቲካ ነፃ መሆን ሀገር ያለመውደድ ነው።ሀገር የአንድ ህዝብ ህልውና ነው።ህዝብ ለመቀጥል የሀገሩ ክብር እና አንድነቷ መጠበቅ እና ማስቀጠል አለበት።አለበለዚያ ማንምን ስለሚያፈራው ልጅ መጨረሻ አያውቅም ፣ማንምን ነገር እርግጠኛ ሆኔ ማደር አይችልም ፣ማንም ነገ የሚመጣው እሳት መቆጣጠር አይችልም።በፍርሃት እና ያለዋስትና መሬት መርገጥ ነው ኑሮው።የነገ ልጁን ፣የነገ ቤተሰቡን እና የትላን ሀገር ክብር እና ዳር ድንበሩን ለማስጠበቅ ከፖለቲካ ነፃ መሆን የለበትም። ማንኛወወም ህዝብ በሚኖርበት ሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለው የሀገር ህልውናን የሚንድ እና ሀገሩን ከሚያጠፋ ነገር ሲያይ መነሳት አለበት።ሀገሩን በቅርበት መጠበቅ ግዴታው ነው።
የትኛውም የመንግስት ፖሊሲ ላይ ጥልቅ የሆነ ሀሳብ ባይኖረውም ሀገሩ ላይ እየተከናወነ ያለው ደባ ባየ ጊዜ መጠየቅ ፣መቃወም እና መነሳት ግድ ይለዋል።ሀገሩ እየተበተነች ፣ሀገሩ ላይ ሽር እና የነገ ጥፋት እየተዘራ እየተመለከተ ምን አገባኝ ያለ ችግሩ ሲመጣ ከፖለቲካ ነፃ ነው ተውት አይባልም ነገ።በሀገራችን ምንም ስለ ሀገሩ ፖለቲካ ሳያውቁ በዘር ፖለቲካ ግጭት ፣በድንበር ይገባኛል ግጭት ፣በብሄር ማንነት ግጭት ህይወታቸው ያለፈ ህፃናት ፣ሴቶች ፣አረጋዊያን አሉ።ከፖለቲካ ነፃ መሆናቸው ከሞት አላተረፋቸውም ። ሁሉም ሰው የፖለቲካ ፓርቲ አይመሰርትም ፤ ሁሉም ሰው የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይሆንም ነገር ግን ሁሉም በሀገሩ የነገ ቀጣይነት ላይ ግን ፖለቲከኛ ነው።በሀገር የነገ አንድነት ፣በጋራ ተቻችሎ እና ተዋዶ አንድ ሀገር ማስቀጠል ላይ ህፃን ፤ አዋቂው ፖለቲከኛ ነው።እዚህ ጋር ገለልተኛ ሆነ ነፃ ሰው የለም።ሁሉም ያገባዋል።
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት የሚመጣን ሁሉ ማቆም ፣ምላሽ መስጠት እና አያገባኝም የምንለውን አቁመን ማሸነፍ አለብን።ኢትዮጵያዊነት እየወደቀ እና እየጠፋ ከፖለቲካ ነፃ ሰው የለም።ሀገራችንን እያጠፋ ካለው ፀረ ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ ህግ እና ተግባራት ለማሸነፍ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን የለብንም።ኢትዮጵያን ወደ ትንንሽ ሀገር ለመቀየር የሚሰራ መንግስትንም ፣ተቃዋሚንም ማጥፋት አለብን።ልካቸው ለማሳየት በእያለንበት መስራት ይጠበቅብናል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለውን የዘር ፣የሀይማኖት እና የቋንቋ ልዮነት መከባበር እና መቻቻል አለበት።በፍቅር ልዮነታችንን አንድ ማድረግ ይጠበቅብናል።ነገር ግን ዘራች እና አንደበታችን ልዮነት መሰበኪያ እና የጎሳ ፖለቲካ መፍጠሪያ መሆን የለበትመ።ይህም የሆነበትን የአሁኑኑ ስርአት እምቢ ማለት ይኖርብናል።ልዮነታችን ለእራሳችን የግል እና የቡድን ጥቅም ይሁን እንጂ ከሀገር ለመለየት ምልክት አይሆንም።ሀገራችን የሁላችንም ስለሆነች ያገባናል።ነፃ የሆነ ሰው የለም።አሁን ያለው የጎሳ ፖለቲካ ዝም ብለነው ረጅም አመት ከቀጠለ እኛም ዘረኛ ሆነን እጅጉን ከሄድን ከ፣ከሀገር በላይ የዘር ድንበር እና የዘር ታሪክ ካስጨነቀን ፣ከሀገር በላይ እርስ በእርስ ካልተስማማን ፣ሀገርን ትተት በጎሳ መደራጀቱ ካዋጣን ነገ የሚመጣወወ እሳት ከባድ ነው።
የጎሳ ፖለቲካ ነገ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጭፍጨፋ ቢያመራ የሚተርፍ የለም።ከፖለቲካ ነፃ ነበርኩ ብትል ባትል የጭፍጨፋው ስለባ ከመሆን አተርፍም።ስለዚህ እንደ ሀገር ለመቆም ነፃ ነኝ ከፖለቲካ ያልን ሁላ ቆም ብለን ነገን አስበን ለሀገራችን አንድነት የበኩላችንን እንወጣ።ገለልተኛ እና ነፃ መሆን ከሀገር አይቻልም።በልዮነት ጥላቻን እንተው።አንድነት ለሁላችንም እንዲበጅ አድርገን እንነሳ።ልዮነታችን  ለመራራቅ አንጠቀምበት።በእርስ በእርስ ጭፍጨፋ እና የጎሳ ፖለቲካ ደም እንጂ ፉሪደም የለም።ማንም ጀግና ብሄር የለም ፣ማንም የሚገደል ብሄር አይኖርም።ትልቁም ትንሹም  አንድ ሀገር ብሎ ከኖረ ትልቅ ነው።አንድ ሀገር ለማፍረስ የሚሰራ ገዢ መንግስት ሆነ ተቃዋሚ ትንሽ ሀሳብ ስለያዛቹ ትንሽ ትሆናላቹ።ኢህአዴግ ካመጣህው የጎሳ ፖለቲካ ውጣ ፣ ህዝብን አሰቀድም እና ውረድ።የተቃዋሚ ሰፈር ደሞ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመራ ጭንቅላት ይዘህ የራስህ ትውልድ አና ሀገር አድን ፖሊሲ ይኑርህ።
ከፖለቲከኛ ነፃ ነኝ የምትል ፣የምትይ ሁላ ግን ወደድሽም ጠላሽም ከፖለቲካ ነፃ አይደለሽም።ኢትዮጵያዊ ውስጥ አሁን በተፈጠረው የዘር ፖለቲካ እልቂት ቢጀመር ከፖለቲከኛ ነፃ ነኝ ያልሽ ሁላ የምተርፊ ይመስልሻል? ያገባኛል በሉ!!
ኢትዮጵያ አንድ ሀገር ፣ኢትዮጵያ ሁሌም ትቅደም
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ባንዲራ-የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ዓርማ ነዉ - ማላጂ
Share