May 12, 2017
1 min read

ገድለህ ማረው

ወለላዬ ከስዊድን

የሰራህን በዓይንህ አይተህ
ሲወሻክት ወይም ሰምተህ
ልታቆመው ብትነሳ
በዝምታ ፊት ብትነሳ
አፍሮ ይተው እንዳይመስልህ
ስምህን ነው ሚከትፍልህ

ከዛ – ይልቅ
ነገርህን አ’ርገህ ድብቅ
ትንሽ ጊዜ ብትጠብቅ
እንደ ወትሮው ሱሱን ሊያደርስ
ካ’ንዱ ሊቀምስ
ካ’ንዱ ሊልስ
ከሰው ጋራ ሲቀላቀል
ባልታሰበ የፊት ተንኮል
ተይዞልህ ፊትህ ሲቀል
መፋረጃህ ያን ጊዜ ነው
ተቀላቅለህ አብረህ በለው
ወይንም በዓይንህ ገድለህ ማረው

0fcb8632f6d8474b7ede04ebf2d12118
Previous Story

የላቲን ፊደል ለኦሮሞዎችና ኦሮሞኛ ማደግ እንደማይጠቅም የተሰጠ አስተያየት – ተፈራ ድንበሩ

Next Story

ከፖለቲካ ነፃ የሆነ አንድም ሰው የለም ፣ በሀገር ጉዳይ ገለልተኛ መሆን አይቻልም!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop