May 6, 2017
2 mins read

«ደሸት» የብርሃን እውነት! -ወለላዬ ከስዊድን

«ደሸት» የብርሃን እውነት!

የማጂ፣ የጅማ፣ የመንዲ፣ የመደባይ አባት

የማራ፣ የዥማ፣ የገንቲ፣ የአራቲ.. አያት

የአማራው፣ የኦሮሞው፣ የዘር ግንድ አውራ

የመተሳሰሪያ እውነተኛ ምንጭ አሻራ!

«ደሸት» ኢፋ ዱጋ ፍጥረተ ማለዳ

የዘር ሀረግ ገመድ ሚስጢራዊ ጓዳ

አባ ቃሉ

አባ ውሉ

አያ ፍቅሩ

ትስስሩ

ዘረ ሸጋ

ኢፋ ዱጋ

መሆንህን አምኖ አማራ ኦሮሞ

ስምህን በስሙ አትሞ

«ደ» ን ደግ ብሎ አንብቦ

«ሽ» ን ሸበበ ብሎት አንግቦ

«ት» ን ትስስር ይለዋል ውልደቱን ከትቦ

«ደሸት» የዘር ምንጩ

አባ እቅጩ

ስመ ክብሩ

ውስጠ ሚስጢሩ

«ደሸት» የብርሃን እውነት (ኢፋ ዱጋ)

ዘሩን ሲያበዛ ሲዘረጋ

ማጂ፣ ጅማ፣ መንዲ፣ መደባይ

ብሎ ሰይሞ የዘር ሲሳይ

መደባይ ስሙን ከስሙ መዞ

ኦሮሞ ብሎ መጠሪያ ይዞ

በደሸት አያትነት ሲኮራ

የጅማ ልጅ ማራ

አ -ማራ ወይም ሃ-ማራ

ብሎ ራሱን ጠራ

ማራ  የሱባ ቃል ትርጉሙን

ማ- ማለት እውነት መሆኑን

ራ- ትርጉሙ ብርሃን መያዙን

አረጋግጦ ተቀብሏል

ማራ እውነትና ብርሃን ነው ብሏል

እንዲህ ነው የዘር ግንዱ

እንዲህ ነው አወራረዱ

እንግዲህ አማራን ከኦሮሞ ኦሮሞን ከአማራ

በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ስፍራ

ማንም አይችል ሊበታትን  ሊለያየው

ደሸት የብርሃን እውነት (ኡፋ ዱጋ) ነው።

……………………..

ደሸት «የአማራና የኦሮሞ እውነተኛ የዘር ምንጭ» በተባለው መጽሐፍ ላይ

የኢትዮጵያ ነገዶች አባት መሆኑ ተጽፏል።

ማስታወሻ

ለመጽሐፉ ደራሲ ለፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ

መታሰቢያ

ለደራሲው ጽሁፍ መነሻ ለሆኑት  መሪራስ አማን በላይ

 

 

 

 

2 Comments

  1. minew tefash enkan dehina metash you come by best professor fikre tolosa the true son of Ethiopia oromo.

Comments are closed.

teddy afro11
Previous Story

አንድ ሀገር ከብዙ አመታት በፊት እቆመበት ቦታ ላይ አሁንም እንዴት ሊቆም ይችላል?

75954
Next Story

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ የማራቶን ውድድር ድል ቀናቸው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop