May 4, 2017
4 mins read

የአርበኞች ግምቦት 7 አመራር አቶ ታደሰ ብሩ ለሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት የሰጡት ምላሽ – “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ”

ታደሰ ብሩ

ሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት፣ በኔ ግምት አገራችን የገባችበትን ማጥ በጥሩ ሁኔታ የተነተነ ጽሁፍ አቅርበዋል። የጽሁፉ አጠቃላይ ይዘት መደምደሚያ ላይ በቀረቡት የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ማጠቃለል ይቻላል።

“አገራችን የገጠማት ችግር ተራ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳይሆን፣ እንደ አገር ቆሞ የመቀጠልን ሥጋት የጋረጠ ከፍተኛ የደኅንነት አደጋ [ነው] …. መወያያትና መነጋገር ያለብን ከሕገ መንግሥቱ በታች የፖሊሲዎች ቁንጮ በሆነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ዙርያ ነው። … የደኅንነታችን ዋና የሥጋትም የኩራትም ምንጭ ውስጣዊ የዴሞክራሲና የልማት ሁኔታ መሆኑ በመገንዘብ፣ የችግሩን ሥረ መሠረት ትቶ አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተንጠላጥሎ የሚመጣ ለውጥ ሊኖር እንደማይችል መረዳት [አለብን]።”

https://zehabesha.info/?p=75797

ሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት አገዛዙ አገራችንን ወዴት እየመራት እንደሆነ በትክክል ያብራሩ በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል። ይሁን እንጂ ችግሩን በተገነዘቡበት ጥልቀት ልክ ለመፍትሄ ሲተጉ አልታየኝም። ለመዋቅራዊ ችግር መዋቅራዊ መፍትሄ የሚያስፈልገው መሆኑ ተቀብለው እያለ “ይህን መዋቅራዊ መፍትሄ የሚያመጣው ማነው? እንዴት ነው?” የሚሉትን ቁልፍ ጥያቄዎች አድበስብሰው አልፈዋቸዋል። እሳቸው መፍትሄ ብለው ያቀረቡት ሃሳብ ሲጨመቅ የሚከተለው ነው “እያጠናሁት ነው የሚለው የፖሊሲ ክለሳም ሆነ ጥልቅ ተሃድሶ … የፖለቲካዊ ፓርቲዎች፣ የሲቪልና የሙያ ማኅበራት፣ የክልል ምክር ቤቶች፣ ወዘተ. ተሳትፎና የተለያዩ አስተያየቶች ተጨምሮበት መሆን ይገባዋል።”

ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት የሚከተሉት ጥያቄዎችን እንዲያጤኑልኝ እጠይቃለሁ።

1. እምነትዎ ”እያጠናሁት ነው” በሚለው አካል ነው። የችግሩ ፈጣሪ የመትሄው አምጭ ይሆናል ብለው እንዴት ሊያምኑ ቻሉ?
2. “የፓለቲካ ፓርቲዎች” ሲሉ እነማንን ነው? በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች አሉ ወይ?
3. “የሲቢክና የሙያ ማኅበራት” ሲሉስ እነማንን ነው? በኢትዮጵያ ውስጥ የሲቢክ ማኅበራት አሉ ወይ? በኢትዮጵያ ነፃ የሙያ ማኅበራት አሉ?
4. የክልል ምክር ቤቶችስ ያው “እያጠናሁት ነው” የሚሉ ሸንጎዎች አይደሉምን?
5. የችግሩ ጥልቀት ስር ነቀል የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ የሚሻ መሆኑ ትንተናዎ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። እርሶ መፍትሄ ይሆናል ብለው ተስፋ ያደረጉት ”የብሔራዊ ደህንነት ፓሊሲና የአመራሩ መግባባት” ውጤት የሆነ “የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ“ ነው። ለእርስዎ ቁልፍ መፍትሄ የሆነው ይህ ፓሊሲ እንዴት በክለሳና በተሃድሶ ይመጣል? ይህንን ትልቅ ተቃርኖ እንዴት ዘለሉት?
6. እርስዎ በመፍትሄነት ያቀረቡት ፓሊሲ የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ይሻል። የራስዎ ትንተና ወደሚመራን መፍትሄ ከመሄድ ማፍግፈግን ለምን መረጡ? “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” አይሆንም ወይ?

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop