March 30, 2017
11 mins read

ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን? – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

አርብ፣ መጋቢት ፳፪ ቀን፣ ፳፲፱ ዓመተ ምህረት ( 03/31/2017 )

አሜሪካ ለሩስያ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ናት።

የአሜሪካ ርዕዩተ ዓለም ከሩስያ ርዕዩተ ዓለም የተለየ ነው።

በአሜሪካ፤ ከሀገሪቱ የግለሰብ የሃሳብ የነፃነት የተነሳ፤ ከሀገራቸው ይልቅ ራሳቸውን የሚያስቀድሙ ሰዎችም በመንግሥት መዋቅርም ይሁን በንድግ ተግባሩ ውስጥ በኃላፊነት የሚገኙ አሉ። ይህ የግል አመለካከታቸው፣ የራሳቸው ከመሆኑም በላይ፤ በማንም ግለሰብ፤ የበላይ አለቃቸውም ሆነ ለነሱ ተጠያቂ በሆኑ ግለሰቦች ዘንድ፤ አያስገምታቸውም። በአንጻሩ፤ እንደሩስይ ባሉ የአምባገነኖችን የበላይነት በሚያመቻቹና በሚያሞግሱ ሀገራት፤ ( ይህ አብዛኛውን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ያጠቃልላል። የኢትዮጵያውን የትግሬዎች ወገንተኛ ወራሪ ቡድንንም ይጨምራል። ) ነዋሪዎቹ፤ ግለስብ ግለሰብነቱን አጥቶ፤ በገዥዎቹ ፍላጎት የሚተረጎም ማንነትን እንዲቀበሉ ስለሚገደዱ፤ የገዥዎቻቸው አገልጋዮች ናቸው ማለት ይቻላል። ከዚህ የተነሳ፤ ለገንዘብ ሊያድሩ የሚችሉ ግለሰቦች በየትኛውም ሀገር ያሉ ቢሆኑም፤ እንደሩስያ ያሉት ሀገሮች በኃላፊነት የሚያስቀምጧቸውን አበጥረው ተገዥ የሚሆኑትን የሚያወጡ ሲሆን፤ እንደ አሜሪካ ያሉት፤ ክፍትነታቸው ለብዙኀኑ ባደባባይ ያን የግል አመለካከታቸውን ለማወጅ አመቺ ነው።

እንግዲህ በመካከላቸው ባለው ልዩነትና ውድድር የተነሳ፤ አሜሪካና ሩስያ፤ በየትኛውም መስክ ቢሆን፤ ፉክክራቸው ቅድሚያ ይይዛል። ለዚህም፤ ሩስያ፤ በመንግሥት ደረጃ አሜሪካን ለማዳከምና የራሳቸውን ጥቅም ለማስቀደም፤ ሌት ተቀን ይሠራሉ። አሜሪካ ይሄን አታደርግም ማለት አይደለም። ነገር ግን፤ አሜሪካ የበላይነት አለኝ የሚል እብሪት ስላላት፤ “እኔ የምለው ሁልጊዜም ተቀባይነት አለው!” በሚል ጋቢ ተጎናፅፋ፤ “ዓለምን የምመራው እኔ ነኝ፤ ሩስያ ደካማ ናት!” በሚል፤ በሩስያ ላይ ዕቀባ መጣልና የመሳሰሉትን በቦታው አስቀምጣለች። በተወሰን ደረጃም አብረው የሚሰለፉላት ምአንግሥታት አሉዋት። በዚህ የፖለቲካ ጨዋታ መካከል ነው የሩስያን ጣልቃ ገብነት የምናየው።

ሩስያ፤ በአሜሪካ መንግሥት የሚደረገውን ውሳኔ ማወቅ ብቻ አይደለም፤ ከቻለች፤ በውሳኔ አሰጣጡ ላይ እጇን ማስገባት ትፈልጋለች። ማን የጠላቱን እንቅስቃሴ ማወቅ የማይፈልግ አለ? በየሀገሩስ ያሉት ኤምባሲዎች ዋናው ሥራቸው ምን ሆኖ ነው! ሩስያ ግን የሞትና የሽረት ጉዳይ አድርጋ ነው የያዘችው። አያስገርምም። ዓለም መተሳሰርና መተባበር ለእያንዳንዱ ሀገር የሥልጣኔ ግስጋሴና የቴክኖሎጂው እድገት ወሳኝ በሆነበት ወቅት፤ ከህዝቡ ነፃነት ይልቅ የራሳቸውን በሥልጣን መሰንበት የሚያስቀድሙ ሀገሮች፤ ተገደውም ሆነ ወደው ለብቻ መቀመጣቸው፤ አስጊ ነው። ሰሜን ኮሪያ፣ ኤርትራ፣ ሶሪያ፣ ይአትግሬዎቹ ገዥ ቡድን የነገሠባት ኢትዮጵያ፣ የዚህ ባለቤቶች ናቸው። እናም ያንን ሚዛን መድፊያ የግድ ማቀድ፤ ለሩስያ ግድ ሆኖባታል። ታዲያ የሩስያን መሯሯጥ የሚረዳ አካል ደግሞ፤ በአሜሪካ ውስጥ ይገኛል። ይሄም፤ በአሜሪካ ያሉ የራሳቸውን ጥቅም ከሀገራቸው ጥቅም አስበልጠው የሚገኙ ግለሰቦች ናቸው። እንደነዚህ ያሉ ግለሰቦች፤ ለገንዘብ ሲሉ፤ በሰላይነት፣ በተቀጣሪነት እናም መሳሪያ በመሆን ተገዝተው ለሩስያ የሚያገለግሉ ናቸው። ለግልሰብ ጥቅማቸው የሚንሰፈሰፉ ሰዎች በግል አይኖሩም። በጎናቸው መሰሎቻቸውን ይኮለኩላሉ። እናም የብርታታቸው ምሰሶዎች፤ ሌሎች እንደነሱ ያሉ የግል ጥቅም አሳዳጆች ናቸው።

ከግለሰብ ጥቅም አንጻር፤ ግለሰብ ዶናልድ ትራምፕ፤ ራሳቸውን ወዳድ፤ ማንንም ረጋግጠው ወደ ላይ ለመውጣት ቅንጣት የማይሰቀጥጣቸው ናቸው። እናም፤ ማንም በሚፈልጉት መንገድ ወደሚፈልጉት ቦታ ለመሄድ እንቅፋት የሚሆንባቸውን፤ ከሰይጣንም ጋር አብረው ለማጥቃት፤ ወደኋላ አይሉም። ይህ የሩስያ ጉጉትና የትራምፓ ራስ ወዳድነት፤ ባንድ ላይ ተጋጥመው መገኘታቸው ነው፤ ለዚህ አሁን ላለንበት የሩስያ ጣልቃ ገብነት መሠረቱ።

የሩስያ አሜሪካን የመቦርቦር ጥረት አዲስ አይደለም። እስከዛሬም ስታደርገው የነበረ ነው። የትራምፕም ጥቅሙን ማሳደድና የሀገሩን ጥቅም ወደ ትቢያ መጣል አዲስ አይደለም። የነበረ ነው። ምንም ታክስ አለመክፈሉ ብቻ ሳይሆን፤ አሁንም የታክስ መዝገቡን አላሳይም እንዳለ በእብሪት መቀመጡ፤ ምስክር ነው። በዚህ ስሌት፤ የቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩትን ሄለሪ ክሊተንን ለማቸነፍና ፕሬዘዳንት ለመሆን፤ ከሩስያ ጋር ለማበር ፈላጊ ሆኖ ቢገኝ፤ ሩስያም አደገኛ ይሆኑብኛል ያላቸውን የአሜሪካን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ኃላፊዎን ሄለሪ ክሊንተንን ለማስወገድና እንደ ፈረስ እጋልበዋለሁ ብለው የተመኙትን ዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዘዳንትነት ለማብቃት፤ ሁለቱም ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት አጋጣሚ ነበር። እናም ሌት ተቀን ሠሩበት። በሂደቱም ዶናልድ ትራምፕ ተመረጠ።

ውሎ አድሮ ግን፤ የአሜሪካ ልዩ የሆነ መንግሥታዊ አወቃቀር፣ አሰራርና በውስጡ የተሰገሰጉ ሀገር ወዳዶች፤ “ዝም ብለን አናይም!” በማለት፤ ውስጥ ውስጡን ሚስጢር በማውጣት፤ ይሄው እንዲጋለጥ አደረጉት።

ከዚህ የምናነበው፤ በታጋዩ ወገናችን ውስጥ የሚካሄደውን ክስተት ነው። በውጥረት ላይ ያለው የትግሬዎች ገዥ ቡድን፤ በውስጥና በውጪ ያለበትን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመከላከል፤ በሀገር ውስጥ፤ ፍጹም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ፤ ትክክለኛ ያልሆኑ ሕጎችን በማውጣት፣ አላግባብ ሰዎችን አጋፎ በማሰር፣ ሕጉን አጣሞ ፍርድ በመሥጠት፤ የለ ርህራሄ ሕዝቡን እያሰቃየ ነው። በውጪ ያለውን ተቃውሞ ደግሞ፤ ከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ፤ የትግል አንድነት እንዳይፈጠር፣ ሆድ አደሮችን ሰግሰጎ በማስገባት፤ ትግሉ ባለበት እንዲቆም አድርጎታል። ምንም እንኳን ከመቼውም የከፋ ሥርዓት በሀገራችን ቢሰፍንም፤ ምንም እንኳን ብዙኀኑ በዚህ በትግሬዎች ገዥ ቡድን ተጠቂ ቢሆንም፤ ምንም እንኳን ታጋዩ ብዙ ቢሆንም፤ አንድነት ከመቼውም በላይ ርቆ ሄዷል። የትግል አንድነት ቀርቶ፤ ተቀራርቦ የመነጋገር ዕድሉ እንዳይሆን ሆኗል። የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን ሊኮራ ይገባዋል። ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ይህ የተደረገው በትግሬዎቹ ገዥ ቡድን የገንዘብ ፍሰትና የግለሰቦች ሆዳምነት ብቻ ነው ባይባልም፤ በአንድነት የመታገሉን ሁኔታ ያደቀቀው፤ በአብላጫው፤ የዚሁ ተወጣሪ ቡድን ጭንቀትና የሆዳሞች ስግብግብነት መሆኑን መካድ አይቻልም። በርግጥ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክሩና፤ እኔ ብቻ ነኝ ትክክለኛ ባይነቱ ሚና አለው። ሌላም ተጨማሪ፤ ለዚህ ጸሐፊ ያልታየው ሁኔታ ሊኖር ይችላል። ባጠቃላይ ከሩስያ ጣልቃ ገብነት የሚታየው ይህ ነው።

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop