March 29, 2017
23 mins read

ወያኔ ጠላቴ ነዉ ያለዉ አማራን እንጅ ኢትዮጵያን አይደለም::አንተ ከዬት አምጥተህ ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያም ጠላት ነዉ እያልክ የምትጽፈዉ?  – ሸንቁጥ አየለ

ጥያቄ:-
ወያኔ ኢትዮጵያ ጠላቴ ናት ብሎ አልተነሳም::ኢትዮጵያ ጠላቴ ነች ሲልም አልተደመጠም:: የተነሳዉ አማራ ጠላቴ ብሎ ነዉ::አንተ ግን ወያኔ ኢትዮጵያን ጠላቴ እንዳለ አድርገህ ትጽፋለህ እሳ ? ይሄን ከዬት አምጥተህዉ ነዉ? የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይመጣልኛል:: በተለይም በመደብ ትግል የሚያምኑ በመደብ ትግል ይወድማሉ ከሚለዉ የሰሞኑ ጽሁፌ ጋር ተያይዞ ይሄ ጥያቄ ደጋግሞ እየመጣ ነዉና መልስ ይፈልጋል:: እናም ወደ ጥልቁ ገብተን እዉነታዉን እየቀዳን እንነጋገር::ላይ ላዩን ሳይሆን::ጭብጡን ይዘን እናዉጋ::
የወያኔ ሙሉዉ መርህና ፍልስፍና ባጭሩ በሚከተሉት አምስት ነጥቦች ሊጠቀለል ይችላል:-
1. ክህደት አንድ እና የጠላትነት ምሰሶዉ:-
ወያኔ ህዝባዊ ሀርነት ትግራይ/የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ/ ብሎ ሲነሳ የመጀመሪያዉ በጠላትነት የተፈረጀዉ ኢትዮጵያን ነዉ::ዋናዉ ግብ ከኢትዮጵያ ነጻ መዉጣት ነዉ::የዚህ ነጻነት ዋና አስፈላጊነትም ኢትዮጵያ በጠላትነት ትግራይን ይዛዋለች የሚል ታሳቢ ነዉ::በራሳቸዉም ሰነድ “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቆና እና ባርነት ነጻ ካልወጣ” ህልዉናዉ አይረጋገጥም ሲሉ አዉጀዉ በሰነድ ጽፈዉ ነዉ የተነሱት::ወያኔዎች ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ በግልጽ አቋማቸዉን ያስቀመጡት ኢትዮጵያ የምትባል የመቶ አመት ታሪክ ያላት እና በወራሪዉ ምኒሊክ የተፈጠረች ሀገር የትግራይን ህዝብ ታሪክ ነጥቃ እና ክብሩን አዋርዳ ባርነት ዉስጥ አስቀምጣዋለች ብለዉ ያትታሉ::የብስራት አማረን የህዉሃት ገድል እና የራሱን የወያኔን ማኒፌስቶ ማንበብ በቂ ነዉ::በነሱ ትረካም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚባል የለም::ኢትዮጵያ የምትባል ወራሪ ሀገርም የለችም:: ወራሪዉ ሚኒልክ ጠፍጥፎ የሰራዉ ነገር ነዉ እንጅ:: እናም ኢትዮጵያ የሚለዉ ስም መደምሰስ ያለበት ነዉ:: ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት ከዚህ በላይ ጠላትነት ምን አለ?ከጥንት ጀምሮ በመጽሀፍ ቅዱስ ሳይቀር የሚታወቀዉን ሀገር ክዶ ከመነሳት የከፋ ሀሰት እና ጠላትነት ከወዴት አለ?
2. አማራ የገዥ መደብ – የትግራይ ህዝብ ጠላት
ወያኔ ሁለተኛዉን የትርክት ምሰሶዉን ያቆመዉ በአማራ ህዝብ ላይ ነዉ::በወያኔ ትንታኔ አማራ የሚባለዉ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህልዉና የበለጠ ተጠቃሚ በመሆኑ የሌለችዉን ኢትዮጵያ እንዳለች በማስመሰል ይተርካል::ስለዚህም የትግራይ ህዝብ አማራን ሊዋጋዉ እና አማራ የሰራትን ኢትዮጵያ ሊያፈራርስ ይገባዋል::ወያኔ አሁንም ዋና ማጠንጠኛዉ አማራን ማንበርከክ: አማራን ማጥፋት እና አማራን ማሸነፍ ብሎም ኢትዮጵያ ከምትባል የጭንቆና ቀንበር ነጻ መዉጣት የሚል ታሳቢ ነዉ::
በወያኔ ትረካ መሰረትም የአማራ እና የኢትዮጵያ ትስሥር በብስራት አማራ (የህዉሃት ገድል መጽሀፍ ) እንደሚከተልዉ ቀርቧል::” አማራ ባሪያ ህዝብ ነዉ::ይሄ ባሪያ ህዝብ ከሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ባሪያ ህዝቦች ጋር ( ማለትም ከኦሮሞዎች: ከሲዳማዎች: ከጉራጌዎች እና ከሌሎችም) እየተቀላቀለ እና እየተቀየጠ ኢትዮጵያ የምትባል የዉሸት ሀገር ፈጥሯል::ይሄ አማራ የሚባል ህዝብ በምንም መልኩ የሰለሞን ነገስታት ዘር አለኝ የሚለዉ ሀሰት ነዉ::ምክንያቱም አማራ ባሪያ ነዉ እየተቀየጠ እና እየተቀላቀለ ያለዉም ከባሪያዎች ጋር ነዉ::” ብስራት አማረ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዴት እንደሚጠላዉ እና የህዉሃት የፖለቲካ ፍልስፍና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን እንደሚመስል ለማወቅ የፈለገ ሰዉ የብስራት አማረን መጽሀፍ ያንንብብ:: በብስራት አማረ መጽሀፍ ዉስጥ አማራ የበለጠ የተሰደበ እና የተረገመ ሆኖ ቢገኝም ዋናዉ ግብ እና አላማ ግን አማራዉ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በዉህደት የፈጠራት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርን የለችም : መጥፋት አለባት: ባሪያዎች ተሰባስበዉ ሀገር ሊመሰርቱ አይገባም የሚል ታሳቢ ነዉ::
አንዳንዱ ደንቆሮ ህዉሃት ስለ ብሄር እኩልነት ስታስጨፍረዉ እዉነቷ እየመሰለዉ አብሮ ይዘላል:: አንዱን ብሄረሰብ በሌላዉ ላይ ስታስነሳ እዉነት እየመሰለዉ በወንድሙ ላይ ሰይፍ ይመዛል:: የህዉሃት ፍልስፍና ግን በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የጠላትነት ስነልቦና ነዉ::ሌላዉ ቀርቶ እንደ ዋለልኝ አይነት የአማራ ልጆች አማራን በህዉሃት ፍልስፍና (ከአባታቸዉ ከሻቢያ እንደተማሩት) የኢትዮጵያ ጠላት ነዉ : የብሄር ብሄረሰብ መብት የተረገጠዉ በአማራ ህዝብ ነዉ በሚል የፈጠራ ታሪክ ሲከሱት የነበረዉ የጠላትን የተራቀቀ ሚስጥርን ካለመረዳት ነበር::
የኢትዮጵያዉያንን ማህበረሰብ እና ብሄረሰቦችን እኩልነት የዲሞክራሲ እና ሰበአዊነት መብት ለማወጅ ኢትዮጵያ መዉደም የለባትም::ህዉሃት : ሻቢያ እና ከነሱ የተማሩት እነ ዋለልኝ ግን የተቀኙት ኢትዮጵያን በመደምሰስ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ማረጋገጥ ወራሪዋን ኢትዮጵያን ማፍረስ በሚል ቅኝት ነበር:: ይሄ ሁሉ የተንኮል ትርክትም ሻቢያ እና ወያኔ የሚያልሙትን ነጻነት ለመቀናጀት እንዲያስችላቸዉ የተጎነጎነ ሲሆን እነዋለልኝ የሚባሉት መናጆዎች ደግሞ በገልቱነት የተጎነጩት መርዛማ አስተምሮት ነበር::
በዚህ ሂደትም ዉስጥ የበለጠ ይሄን እዉነት ይጋፈጥብኛል: ይቃወመኛል ብላ ያሰበችዉ አማራ ላይ ወያኔ የዘር ማጥፋት በራሷ እና በሌሎች ብሄሮች እንዲክከናወን ሰፊ የቤት ስራ ሰርታለች:: አማራዉን በአንድ በኩል ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር ጨፍልቃ ባሪያ ነዉ: ከባሪያ ጋር ይጋባል: በዉህደትም ኢትዮጵያ የምትባል የሀሰት ሀገር መስርቷል እያለች የምትወቅሰዉ ወያኔ በሌላ በኩል ደግሞ አማራዉን በሌሎች ብሄሮች ለማስጠላት ሰፊ የቤት ስራ ሰርታለች::እየሰራችም ነዉ::ወያኔ ግቧን በአንድ አቅጣጫ አታከናዉንም::በብዙ መልክ እና መስክ እንጅ::
3. ወያኔን ከተቃወምክ ከየትኛዉም ብሄር ብትሆን ያዉ የወያኔ ጠላት ነህ
እዚህ ጋ የኦሮሞ ማህበረሰብን ጉዳይ እንደ ማሳያ ማንሳቱ ተገቢ ነዉ:: ሶማሌን እና የጋንቤላን ማህበረሰብም እንደ ማጣቀሻ ማቅረቡ ጥሩ ነዉ::ወያኔዎች ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻ ብቻ ሳይሆን አንግበዉ የመጡት የተሳሳተ ሀሳብንም አንግበዉ ነዉ የመጡት::ለምሳሌ አማራን በቀንደኛ ጠላትነት ፈርጀዉ የዘር ማጥፋት እንዳወጁበት ሁሉ የኦሮሞን ማህበረሰብ እያታለሉ እንዳሰኛቸዉ የሚያቄሉት እና የሚገዙት መስሏቸዉ ነበር::ከወያኔዎች ይልቅ ፕሮፌሰር ሌቪይ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ የስነልቦና አንድነት በደንብ ያዉቃል::ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪይ ታላቋ ኢትዮጵያ የብዙሃን ሀገር በሚለዉ መጽሀፉ እንደተረከዉ ኦሮሞዎች እና አማራዎች ስልጣንን: ጦርነትን: ባህል እና ታሪክን በተመለከተ አንድ አይነት ስነልቦናዊ ይዘት አላቸዉ::ባህላቸዉም አንድ ነዉ ሲል ያትታትል:: ሲቀጥልም ሁለቱም ወገኖች ጥሩ ጦረኞች ናቸዉ ሢል ያብራራል::ዶናልድ ሌቪይ እንደሚተርከዉም ኦሮሞዎችም ሆኖ አማራዎች ሰላማዊ እና ሌሎችን አክብረዉ መኖር የሚችሉ ታላቅ ህዝቦች ናቸዉ:: ከነኳቸዉ እና ካጠቋቸዉ ግን ለክብራቸዉ የሚዋደቁ ጦረኞች ናቸዉ::
ወያኔ ግን ይሄን እዉነታ ክዳ የኦሮሞ ህዝብን እንዳሰኛት እንደምትጫወትበት በማሰብ እና እንዳሰኛት ለማሞኘት ብዙ ጥራለች::ሆኖም እዉነታዉ ወዲያዉ ነዉ የተገለጠዉ::ኦነጎች ያነገቡት ኢትዮጵያን የማዉደም ፍልስፍና ሸዉራራ ቢሆንም ወያኔን መቃወም እና ወያኔን ቁም ስቅሏን ማሳዬት የጀመሩት ወያኔ ገና ስልጣኗን በአግባቡ ማደላደል ሳትጀምር ነበር::ከዚያ ብኋላ ላለፉት ሀያ አምስት አመታታ ሙሉ የኦሮሞ ተቃዉሞ በወያኔ ላይ እንደነደደባት ነዉ::ኦሮሞዎች በሰላማዊ ትግልም ሆነ በጦርነት: በልዩ ልዩ ፓርቲም በመደራጀት ወይም ከራሷ ከወያኔ መዋቅር ዉስጥ ተሰግስገዉ በመግባትም ቢሆን ወያኔ እንዳሰበችዉ የማንም መጫወቻ እንዳልሆኑ አስመስክረዋል:: ወያኔም በመጨረሻ ይሄ እዉነታ ሲገለጥላት የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ ማሰር: መግደል እና ማፈናቀል ይዛለች:: የወያኔ የበቀል በትር በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከተመዘዘ ብኋላ በአንድ ቀን እንኳን ከሽህ በላይ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላትን በመግደል (ያዉም የሀይማኖት ክብረ በአል ላይ) ጠላትነቷን አስመስክራለች:: ወያኔ አሁን በምስራቅ ኢትዮጵያ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ላይ የማፈናቀል እና የማሰቃዬት ስራዋን ተያይዛዋለች::
በተመሳሳይ ወያኔን የሶማሌ ማህበረሰብ ሲቃወማት የተወሰደበት የጅምላ የዘር ማጥፋት እርምጃ አሰቃቂ ነበር:: አሁን ወያኔ አንዱን የሶማሌ ጎሳ መርጣ ከኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር ደም እያቃባችዉ ነዉ::በዚህም ወያኔ ጥንድ ትርፍ ታተርፋለች::በአንድ ሰይፍ ኦሮሞና ሶማሌ እንዲጫረስ ስታደርግ በሌላ ሰይፍ ደግሞ ወያኔ ገላጋይ ሆና ስልጣኗን አደላድላ ኢትዮጵያን መበዝበሯን ትቀጥላለች:: የወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላትነት በዚህ አይበቃም::የጋምቤላን ማህበረሰብ ሆን ብላ እሁለት ከፍላ አኝዋኮች ላይ ይሄ ነዉ የማይባል የዘር ማጥፋት እርምጃ ወስዳባቸዋለች::ይሄ ሁሉ እጅግ ብዙ መራራ እዉነት እያለ ይሄን ሁሉ የህዝብ ጠላትነት መካድ አይቻልም::ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና ብሄረሰብ ጠላት ናት::
4. ኢትዮጵያ :- የወያኔ ጋለሞታ
አንዳንድ ሰዉ ዝም ብሎ ላይላዩን እንዳዬ እድሜዉን ይገፋዋል::አሁን ወያኔ ኢትዮጵያን ወራ ይዛ ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር የምትመራ የሚመስለዉ ሰዉ አለ:: ወይም ይሄ ሁሉ ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ላይ የሚወርደዉ መከራ በኢትዮጵያ የሚፈጸምበት የሚመስለዉ ሰዉም አለ:: እዉነታዉ ግን እንደሱ አይደለም::ኢትዮጵያን ወያኔ እንደ ጋለሞታ ነዉ የማረከቻት::በወያኔ ልብ ዉስጥ ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር የለም::ኢትዮጵያ የምትባል ጋለሞታ እና በጊዚያዊነት የተማረከች የጠላት ሚስት ግን አለች:: ወያኔ ኢትዮጵያን ሀያ አምስት አመት በቅኝ ሲገዛት አሁንም የትግራይ ነጻ አዉጭ ሆኖ ነዉ::አሁንም በልቡ ወያኔ የሚያልመዉ ከዚህች ከጋለሞታ ኢትዮጵያ ትግራይን ነጻ ማዉጣት ነዉ::ወያኔ ለዚህም ነዉ የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ የሚለዉን ስሙን የማይለዉጠዉ::የወያኔ ግቡ ኢትዮጵያ አይደለም::ኢትዮጵያ የጠላት ሚስት ናት::ምናልባት የተገደለዉ የኢትዮጵያ ባል መቃብሩን ፈነቃቅሎ የተነሳ እንደሆነ ወይም ምናልባትም የተገደለዉ የኢትዮጵያ ባል ልጆች ወልዶ ከሆነ እና ኢትዮጵያ የሚል መዝሙር ከተነሳ ወያኔ ኢትዮጵያን አዉድሞ ትግራይን ነጻ አዉጥቶ ይሄዳል::ከዚህ የከፋ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ጠላት በምድር ላይ የለም::ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነዉ::በገሃድም የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ያወጀ ሀይል ነዉ::
5. አሁን የተነሱት እና እናታቸዉ የተማረከችባቸዉ የኢትዮጵያ ልጆች ምን እያሉ ነዉ?
ወያኔ በጠላትነት የማረካትን እና በጋለሞታነት በጉልበት የያዛትን ኢትዮጵያን አብረዉ የሚራገሙ ፈሪዎች ተነስተዋል::የአባታቸዉን ሀገር እና የአባታቸዉን ሚስት ከወራሪዉ እና ከጸረ ኢትዮጵያዊዉ ወያኔ ማላቀቅ ሲገባቸዉ ብሎም ክብሯን መመለስ ሲገባቸዉ እናታቸዉን ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ እያሉ እየሰደቧት ነዉ::ወያኔን እንጅ እናታቸዉ ኢትዮጵያን ማስተዋል የተሳናቸዉ ፈሪዎች ወያኔን ለማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት የሚል ፍልስፍና ታጥቀዋል::ቤቴ በትኋን ተወሯል እና ቤቴን አቃጥለዋለሁ ይሉሃል::ከዚያስ ? ስትላቸዉ ከዚያ እማ እፍርስራሹ ላይ ትንንሽ ጎጆዎችን አቆማለሁ ብለዉህ ቁጭ:: የተሰራዉን ቤት ከወራሪ ማላቀቅ ያቃተዉ ፈሪ ቤት አፍርሼ ቤት እሰራለሁ ይልሃል:: ይሄ መታመም ነዉ::ይሄ ፍርሃት ነዉ:: ይሄ አለማስተዋል ነዉ::
እግዚአብሄር እራሱ ኢትዮጵያዊነትን ልጄ ያለዉ ቅዱስ ነገር ነዉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉን ማንነትህን መልቀቅ ወደ መጨረሻዉ የመሸነፍ ጠርዝ መሄድ ብቻ ሳይሆን ወደ ሽንፈት እንጦርጦሮስ መዉረድ ነዉ ብለህ ብትነግራቸዉ እግዜር እራሱ የለም ይሉሃል::ወይም ጠላት እንደነገራቸዉ መጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ያለዉ ኢትዮጵያ ይሄ አሁን ያለዉ ኢትዮጵያ አይደለም ብለዉህ ቁጭ::እንዴታ ? ገና መጽሀፍ ቅዱስ ትርክቱን ሲጀምር የግዮን ወንዝ የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከባል ብሎ የሚያስረግጠዉ እኮ ይህችኑ የኛኑ ቅድስት ኢትዮጵያን ነዉ የተባሉ እንደሆነ ይከፋሉ::ወይ በቂ እዉቀት ወይም በቂ ወኔ ያስፈልጋል::አጼ ቴዎድሮስ 179 አመታታ በመሳፍንት ተረጋግጣ እና ተከፋፍላ የነበረች እናት ኢትዮጵያን ሊያድኗት ፎክረዉ ሲነሱ “የኢትዮጵያ ባል : የእየሩሳሌም እጮኛ” ብለዉ መፎከራቸዉን እና ኢትዮጵያን እነ ራስ ስሁል ከበተኗት ብኋላ በብዙ ድካም ሊሰበስቧት ብዙ ዋጋ ለመክፈል ጀግኖች እንደነበሩ ያስታወስካቸዉ እንደሆነ አንዳንዱ ያኮርፋል:: ጥሬ ሀቁ ግን አጼ ቴዎድሮስ እና ሌሎችም የአለም ጀግኖች እንዳደረጉት ጠላት በሀይል እና በእዉቀት ብቻ ይነቀላል እንጅ አገር አጠፋለሁ : ድንበር አፈልሳለሁ ተብሎ ስለ ተፎከረ አይጠፋም::
ይልቅ እናት ኢትዮጵያን ከጠላቷ ከወያኔ ማላቀቅ እና የተከበረች ሀገር ማድረግ ብቸኛዉ መፍተሄ ነዉ::ጀግና አባቶች የገነቡትን መሰረት ወደ ታላቅ መሰረትነት ማሸጋገር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነዉ::ለጊዜዉ በብሄሬ ተደራጅቼ ወይም በኢትዮጵያዊነት ተደራጅቼ ወያኔን እንደመሰለኝ እፋለማለሁ ማለት መብት ነዉ::ግን ጥቂት ነገር መሳት ነዉር ነዉ::አንደኛ ወያኔ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት መሆኑን መካድ ነዉር ነዉ::ሁለተኛም ኢትዮጵያን ከወያኔ ማላቀቅ ሲገባ ኢትዮጵያን አጥፍቼ ነዉ ወያኔን የማጠፋዉ ብሎ መነሳት ነዉር ብቻ ሳይሆን ስንፍናም ነዉ:: ሶስተኛም ወያኔ የዚህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ጠላት መሆኑን በገሃድ እየተናገረ እና እያስመሰከረ ወያኔን የኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ማለት ታላቅ ሀሰት ነዉ::
ወያኔ የኢትዮጵያ እዉነተኛ ጠላቷ ሲሆን ይሄ እዉነታም ሲመነዘር ወያኔ የአማራዉም: የኦሮሞዉም : የጉራጌዉም : የሶማሌዉም: የደቡቡም : የአፋሩም የሁሉ ኢትዮጵያዊ መሰረታዊ ጠላት ነዉ::ስለሁለት ነገር::አንድም ማንም ወያኔን ተቃዉሞ ቢነሳ ወይም እንደሚቃወም ወያኔ እርግጠኛ ከሆነ የሚደርስበት ድምሰሳ አንድ ነዉ::አንድም ኢትዮጵያን ወያኔ ድምጥማጧን አጥፍቶ ሲያፈርሳት የሚፈጠረዉ ትርምስ አሁን አንዳንዶች ቁጭ ብለዉ እንደሚያስቡት አንድን ወገን የሚጎዳ ሳይሆን መላዉ ኢትዮጵያን ወደ ፍጹም ሲኦልነት የሚከት እና መሰረታዊ ትርምስ የሚያመጣ ነዉ::በዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጎጅ ነዉ::ወያኔም የሚፈልገዉ ይሄንኑ ነዉ::ከዚህም የከፋ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ጠላትነት ከቴም የለም:: በታሪክ ከተመዘገቡት የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ሁሉ የከፋዉ ጠላት ማለት ይሄ ሀይል ነዉ::

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop