March 14, 2017
13 mins read

የአማራ ምሁራን የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ  ሊጠነቀቁ ይገባል! – በፍሥሃ ጽዮን

እድለኛ የሆኑ ሀገሮች የተማሩ ዜጎቻቸውን ተጠቅመው ድህነትን ታሪክ  ካደረጉ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ የትምህርት ዋና ግቡም ድህነትንና ኋላቀርነትን ማስወገድ ፤ መልካም አስተዳደርን ማሰፈንና በአመለካከት መበልጸግን የሚያካትት ነው፡፡

ማስተማር  እርግማን ይመስል  ደሀዋ ኢትዮጵያ ግን በድህነት ቤቷ የምታስተምራቸው ልጆቿ ብድራቸውን ለመክፈል ሲታትሩ የሚታዩ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ አብዛኛው ምሁር ነኝ ባይ የግል ምቾቱን  ለማድለብ ነው ቀን ተሌት ሲሮጥ  የሚታየው፡፡ ጥቂት የማይባለው ምሁር ተብየም የወገኑ ድህነት፡ ውርደት፡ ጭቆና እና ሰቆቃ ትርጉም አይሰጠውም፡፡እንዲውም ጨቋኝ ስርአት በመጣ ቁጥር ከስረዓቱ ጋር በመወገን ያሰተማረውን ህዝብ የሚመዘብር፤ በእስራት የሚያሰቃይና የሚገድል ነው፡፡በአሁኑ ወቅት በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኘው አብዛኛው ምሁር ነኝ ባይ  ቤቱ ውስጥ ተጎልቶ  ቡናውን እየጠጣ ዛሬ ደግሞ  ወያኔ እንዲ፡ እንዲህ አደረገች  በማለት አሰልች ወሬ ከማውራት ውጭ ለውጥ ሊያመጣ በሚችል መልኩ ሲወያይም ሆነ ሲሰራ አይታይም፡:

በተለይ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የዘመናዊ ትምህርት ግብ ሀገርን ማፍረስ መስሎ ነው የሚታየው፡፡በጀግኖች ልጆቿ አጥንት የታጠረውን የኢትዮጵያን ዳር ደንብር አሳልፈው  ለውጭ ጠላት በመስጠት ላይ የሚገኙ የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ትናት ሀገራቸው በጥሩ ትምህርት ቤት ያስተማረቻቸው  ናቸው ፤ እንበታትናታለን የሚሉ  ልጆቿ ትናንት  ኢትዮጵያ ተበድራ ያስተማረቻቸው ናቸው፤  በደም የተፃፈውን የረጅም ጊዜ  የኢትዮጵያን የተጋድሎ ታሪክ ዛሬ  እንደተፈጠረ አድርገው ለመተረት የሚፈልጉትም እነርሱው ናቸው፡፡

 

ከትምህርት ጥቅሞች መካከል አንዱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በበቂ  መረጃ ላይ ተመስርቶ በመተንተን  እራስን ማስተካከልና የሚወክሉትንም ማህብረሰተብ ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ ማሸጋገር/ከሚኖርበት የድህነት ቀንበር አላቆ በሰከነ  አመራር ወደ እድገት ጎዳና መምራት ነው፡፡

በተለይ በአሁኑ ሰዓት ህወሓት ትግሬ በሁሉም የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ላይ  ግፍ እየፈጸመ ቢገኝም እንደ  አማራ ብሄረሰብ  ግን  በታሪካዊ ጠላትነት   ተፈርጆ  በደል እየተፈጸመበት ያለ ብሄረሰብ አለ ለመለት ያስቸግራል፡፡ ዳር ደንብሩንና ለም መሬቱን  ተንጥቆ በችግር መንገላታቱ አልበቃ ብሎ  በማንነቱ ምክንያት ጥፋት የተደገሰለት ብሄረሰብ ነው፡፡

እጅግ የሚገርመው ህወሓት ትግሬ እስከ አሁን በዘረፈው የአማራ አንጡራ ሀብትና በጨረሰው የንጹሀን ህይወት ማቆም የማይፈልግ መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሓት እውን ማድረግ የሚፈልግው የሳጥናኤል ወንድም  የሆነውን  የአቶ መለስ ዜናዊን ራዕይ ነው፡፡ የአቶ መለስ ራዕይም    ’’አማራ መንገድ ለይ ውጥቶ ሲለመን ማየት እፈልጋለሁ’’  ነው፡፡ እያንዳንዱ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣንም  በአማራ ህዝብ  ላይ የሰቆቃ ራዕይ ሰንቆ ሌት ተቀን  እየሰራ ይገኛል፡፡

 

ታዲያ አሁን እጅግ ሊገርም የሚገባው ህወሓት ትግሬ የአማራን ህዝብ  የወደፊት  ሀልውና ለመፈታተን የሚፈጽመው ግፍ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ህወሓት አማራ ጠላቴ ነው ብሎ አውጇል፤ አዋጁም ተግባራዊ መሆነ ከጀመረ 40 አመት  አልፎታል፡፡ ስለዘህ ህወሓት እየተመራ የሚገኘው ባወጣው የእልቂት  አዋጅ መሠረት ነው ፡፡ ይህን የእልቂት አዋጅ ደግሞ በአሁኑ ወቅት መላው አማራ በተለይም ምሁሩ ክፍል በሚገባ ያውቃል፡፡ስለዚህ ሊደንቅ/ሊገርም የሚገባው አማራው  የህወሓትን የመጨረሻ ግብ እያወቀ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ጊዜ መውሰዱ ነው፡፡ በተለይም የአማራው  ምሁር  በመካከሉ ያሉ ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትቶ በወገኑ ላይ እየተፈፀመ የሚገኘወን ግፍ ለማስወገድ ተባብሮ  ለመስራት ጊዜ መውሰዱ ነው የሚደንቀው፡፡ የተወሰነው የምሁር ክፍል አማራ የሚደርስበት ችግር ለመቋቋም መደራጀት አለበት ሲል ሌላው በብሄረሰብ መደራጀት የአማራ ባህል አይደለም በሚል ንትርክ ጊዜ ይባክናል፡፡  በዚህ መካከል ህወሓት  ወደ ፀረ- አማራ  ራዕዩ በፍጥነት  ይገሰግሳል፡፡ በአንድ ወቅት የህወሓት  ትግሬ  ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አቶ መለስ ዜናዊ በሬዲዮ ስለ መደራጀት ጥቅም  ሲናገር ’’ ካተበታተነ/ካልተደራጀ አንድ ሺህ ሰው የተደራጁ አስር ሰዎች በእጅጉ ያስፋራሉ’’ ብሎ ነበር፡፡  ይህ እውነት ለመሆኑ የአቶ መለስን ንግግር መጥቀስ አያስፈልግም ነገር ግን ጸረ-አማራ ክፍሎች የአማራን መደራጀት የማይፈልጉት ከዚህ እይታ ተነስተው መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡

የአማራ ተጋድሎ ከተጀመረ ወዲህ  በአማራ ምሁራን  በኩል ብዙ ጊዜ እየባከነ  የሚገኘው ሾሳል ሚዲያ ላይ በሚከፈት ጦርነት ነው፡፡ አብዛኛዎች የሶሻል ሚዳያ ጦርነቶች  የአማራውን ህብረተሰብ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ህወሓትና ግብረ አበሮቹ በእቅድ የሚያካሂዷቸው እኩይ ተግባሮች ናቸው፡፡አዎ! ሶሻላ ሚዲያ ላይም መትጋት እንደሚያስፈልግ ይታወቃል፡፡ በሶሻል ሚዲያ እየተካሄዱ በሚገኙ የብዕር ጦርነቶች ብዙ ጸረ-ኢትዮጵያውያን ቡድኖች አንገታቸውን ለመድፋት ተገደዋል፤ የጎበጡ አመለካከቶችመ ከፍጹም ጠማማነት ወደ ወልጋዳነት እየተቀሩ  ይገኛል ፡፡ እድሜ  ለኢትዮጵያ  የክፉ ቀን   ልጆቻ እንጅ በህወሐትና በኦነግ የተቀነባበረው ልብ ወለድ  የኢትዮጵያ ታሪከ እየተናደ ይገኛል፡፡  ኢትዮጵያውያን  በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተነፈጉትን  እውነተኛ የሀገራቸው ታሪክ በሶሻል ሚዲያው  እያወቁ  ነው፡፡ ይህ ታዲያ አሁንም  የልብ ወለድ ታሪክ እየፈበረኩ የሚገኙተን፤  ከቁም ነገር ይልቅ ተራ ስድብ ላይ ጊዚያቸውን የሚያባክኑትንና የባንዳንት ተልኮ አንግበው የሚወራጩትን ሳልዘነጋ  ነው፡፡

ይሁን እንጅ ከሶሻል ሚዲያው ጦርነት ይልቀ  ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የህይወት/የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የብሄረሰቡ ህልውና ፈጽሞ አደጋ ላይ ከወደቀ በኋላ ወደነበረበት ለመመለስ ከባድ  ነው፡፡ የሶሻል ሚዲያ ጦርነቱ  የአማራን ህዝብ ከማደራጀትና ወደ ድል ጎዳና ከመምራት ጎን ለጎን ሊካሄድ የሚችል እንጅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ አይመስለኝም ፡፡

የአማራ ምሁራን  በአማራ ላይ የተደቀነው ችግር በማውሳት ላይ ብቻ ማተኮራቸው ለአማራ  ችግር መፍትሄ አያመጣም፡፡ እርሱ ሳይማር  አስተምሮ ከምሁር ደረጃ ያደረሳቸው ደሃው አርሶ አደር ወገናቸው የተጫነበትን የህወሓት እርጥብ ቀንበር ለማስወገድ በጥጃ ብረት እየተፋለመ ይገኛል፡፡

በዚህ ወቅት የአመራ ምሁር ከአረበኛና አርሶ አደር ወገኑ ጋር በመሰለፍ የብሄረሰቡ ታሪካዊ  ጠላት  የሆነውን ህወሓት ትግሬን መፋለም ይጠበቅበታል፡፡ እንደ ምሁር ትግሉ የሰከነ አመራር  እና  ጠንካራ ውስጣዊ ዲሲፕሊን እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ ነው፤ ሁሉንም የአማራ ኃይል በአንድ ላይ በማሰባሰብ ወደ ነፃነት ጎዳና እንዲያመራ ማስተባበር ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት ከልብ  ከሚፈልጉና ጸረ-አማራ አቋም ከሌላቸው  ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራተ እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡  በእያንዳንዱ ደቂቃ የወገን ህይወት  በህወሓት ትግሬ    እያለፈ በመሆኑ  በንትርክ/ ሆን ተብሎ በሚከፈት የሾሳል ሚዲያ ጦርነት የሚጠፋ  ጊዜ ሊኖር አይገባም፡፡

በአሁኑ ወቅት የአማራ ህዝብ  ድራማ  ተመልካች የሆኑ  የአማራ ምሁራንን አይሻም፡፡ በእጅጉ  የሚፈልገው የገንዘብ፤ የጉልበትና የህይወት መሰዋትነት እየከፈሉ የሚገኙትንና ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ ምሁራንን ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን የአማራ ምሁራን በአሁኑ ወቅት የአማራ ህዝብ በተለይም አርሶ አደሩ  እያካሄደ የሚገኘውን የሞት ሽርት ትግል በተግባር ሳይደግፍ ቢቀርና ትግሉ ቢከሽፍ ነገ ከታሪክ ተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ ራሱና ቤተሰቡም  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከአማራ ጠላቶች ኢላማ ሊያመልጡ አይችሉም፡፡  ስለዚህ ጊዜው የወሬ ሳይሆን የተግባር ነው፤ መተግበር  ያለበትም  ዛሬ ነው፡፡

 

ድል ለኢትዮጵያ!

 

 

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop