ታላቅ የጀግንነት ጥሪ! – ከሐሊው ጌታ

ለውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን

የታላቋ  ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ  ድርጅት ኢትዮጵያውያን በሙሉ በያለንበት ስመጥር ወላጆቻችን ያስረከቡንን የጀግንነት ሱሪ ታጥቀን እናት አገራችንን ለማስከበር በአንድነት እንድንነሳ የቁርጥ ቀን ብሄራዊ ጥሪ ሊያደርግ መዘጋጀቱን ለመግለጽ ይወዳል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያን ለማጥፋት አሲሮ በመጣው ጎጠኛ የወያኔ ቡድን የወገኖቻችን በግፍ መገደል: የሰቆቃ  እሥራት: የመሬት ንጥቂያውና መፈናቀል: የማያቋርጥ ዝርፊያ: ርሀብ : ስደት በአውሬና በውሀ መበላት : ከዚያም አልፎ በአረመኔዎች መታረድና መገረፍ: እጅግ የሚዘግንን ግፍ መሆኑን አስታውሷል:: በመቀጠልም ወያኔዎች የኢትዮጵያን ህዝብ በተክታታይ ያረገፉት ከአርባ ዓመታት በላይ ሲሆን እየባሰባቸው እንጂ  እየተለወጡ አለመሄዳቸውንና : ለዚህም የአገር ዳር ድንበር መጠበቅ በሚገባው  ጦር ንጹሀንን ማስጨፍቸፋቸው በቂ ማስረጃ መሆኑን በምሬት ገልጿል:: ከዚሁ ጋር በማያያዝ ዛፉ” የበለጠ የጎዳኝ መጥረቢያው ሳይሆን የኔው ጠማማ ነው” እንዳለው ሆኖ አንዳንድ እበላባዮች ወደ ህሊናቸው ተመልሰው  ወገን ማገዝ ሲገባቸው በወያኔዎች እየታዘዙ ዘመድአዝማድ እያሳደዱ መግደላቸው ተጨማሪው አሳፋሪና መደመድ የሚያጠፋ እርግማን ሆኗል::

ያም ሆኖ ይህ ሁሉ ግድያና አፈና እያለ ጀግናው የኢትጵያ ህዝብ በማድረግ ላይ ያለው ተጋድሎ የሚደነቅ ነው:: የተናጠሉ ትግል ግን ለጠላት ቀዳዳ ስለሚከፍት የጋራው መደጋገፍ  መጎልበት:: ቅድሚያ የምንሰጠው ቁልፍ ተግባር ነው:: ይህንን ችግር ሁላችንም ተረባርበን መፍትሔ ካልሰጠነው ጉዳቱ ” ሲያይ የሞተን ሲሰማ ቅበረው” እንደተባለው የሚጠብቀን ተራ በተራ ማለቅ ይሆናል:: የቁም ሙትነትም ልብን እንደሳት የሚያቃጥል ውርደት ነው::

 

ይህንን ደግሞ የምንፈልገው አይደየለም::  ድግሞስ እስከመቸ ? ስለዚህ ሁላችንም በከፍተኛ ወኔ መነሳት አለብን: የሚያስተማምን ጀግንነት አለን:: በብዛትም ቢሆን አሁን በለው ሁኔታ ከ102 ሚሊዮኑ ህዝብ መካከል 97 ሚሊዮኑ ያህል የእኛ ነው :: ይህንን አስተባብረን ከተነሳን ስንዝር መራመድ ስለማይችል የወያኔ ጉዳይ” የድፍድፍ ኩራቱ ውሃ እስኪገባው ነው” ይሆናል:: ባጭሩ ከአሰብነው ግባችን ለመድረስ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃገራዊ ፖለቲካና የብሄር ፖለቲካ፣ የዛሬ 31 አመት በ“አማራ ህዝብ ከየት ወዴት” መጽሃፍ ውስጥ - አንዳርጋቸው ፅጌ

ሀ.  አንድነት

ለ.  በሳል አመራር

ሐ.  ንቁ ተሳትፎ

መ.   አስተማማኝ ዝግጅት

ሠ.  ለድል የሚያበቃ ተግባር

ያስፈልጉናል:: በእነኝህ ላይ ተመስርተን የምናከናውናቸው

᎗በመሰሪዎች ውዥንብር ሀሳባችን ሳይበታተን ባንድ ልብ ሆነን ወደፊት መራመድ

᎗ሁላችንም በምችለው ሁሉ መተባበር

᎕ትግሉ በዐቅም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ

᎕አገር ውስጥ አሁን በመዋደቅ ላይ ያሉትን ጀግኖች ማገዝ

᎕ወያኔ አሁን ድርድር የሚለው ቀለም ተቀባብቶ ለመቀጠል የሚያደርገው  የፖለቲካ ቁማር መሆኑንም ተገንዝበን ትግሉን ሥርነቀል ማድረግ ነው:

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይህ የአንድነት ኃይል የእግዚአብሔርን ምርቃት ለማግኘት አንድ ዓለም አቀፍ የፀሎትና የቃል ኪዳን  ቀን ለማድረግ አስቧል :: ፕሮግራሙ ለወደፊት የሃይማኖት አባቶች በሚሠጡት መመሪያ መሠረት ይሆናል: በማለት አበይት ነጥቦች አመልክቷል::

 

የታላቋ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች በጥንቃቌና ሥርዓት ባለው ሁኔታ በዝግጅት ላይ የቆየ እንቅስቃሴ ሲሆን ዓላማውም ኢትዮጵያውያንን በጎሳ በሃይማኖት በቋንቋ በቀለምና በፆታ ሳይከፋፍል አንድነታችንን የበለጠ በመገንባት ኢትዮጵያን ማዳንና ሁሉን የሚያሳትፍ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማቋቋም ነው::

ድል ለኢትዮጵ ሕዝብ !

ከሐሊው ጌታ

 

 

Share