እንደ ትላንትናው ፣ እንዳባቶቻችን
ከመሃል ከተማ ፣ እስከ ጠረፋችን
ካመፀኞች ጋራ ፣ ይጀመር ፍልሚያችን
ምንሽር ጓንዴውን ፣ ያጩኸው ህዝባችን ።
አገሬ ኢትዮጵያ ፣ ቴዎድሮስ ያደገባት
ጋራው ሸንተረሩ ፣ ታሪክ የሰራባት
ሜዳ መስሎት ዛሬ ፣ ባንዳው ፈነጨባት ።
ሞቅ ሞቅ አድርገው ፣ ወያኔ ይሸበር
ትንፋሽ አሳጥረው ፣ በማሰው ይቀበር ።
ለእናት ኢትዮጵያ ፣ ባንድነት ዝመቱ
ትርጉም አልባ ፣ እንዳይሆን አገሬ ማለቱ
ግዴታን መወጣት ፣ ይሁን እንደጥንቱ
ሬሳን ይመስል ፣ ይብቃ መጨመቱ ።
ሁሉም ጦሩን ያንሳ ፣ ጠላት ላይሆን ወዳጅ
ሉአላዊነቱን ፣ ያስከብር በግዳጅ ።
ጀግና የጀግና ልጅ ፣ የሃገር አለኝታ
ግንባሩን የሚሰጥ ፣ ሳይፈራ ላንዳፍታ
ና ግጠመኝ የሚል ፣ ሞልቶ በየቦታ
ውድ የሚሞትላት ፣ አገሬ መች አጥታ ።
ህጻን ሽማግሌ ፣ ወጣት ወንድ ሴቱ
ዝናን ያተረፈ ፣ ዛሬም እንደጥንቱ
ባገሩ የሚኮራ ፣ ቆፍጣናና ብርቱ
ችግር የማይፈታው ፣ የጥንት የጠኋቱ
ንቅንቅ የማይለው ፣ ቆርጧል አንዴ ሃሞቱ ።
ያሳለፍነው ይብቃ ፣ ጠንክረን እንስራ
ሸክማችንም ይቅለል ፣ እኛ በኛ እንኩራ
ንፋስ ሳይገባብን ፣ ባንድነት በጋራ
ፋኖው ተነስና ፣ ጓዶችህን ጥራ
ልክህን አሳየው ፣ ለባንዳው ኩታራ ።
ታዛቢው