February 20, 2017
7 mins read

ሁለት ተሳዳቢ ፕሮፌሰሮች፤ መስፍን ወልደማርያምና ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ – ጌታቸው ኃይሌ

ጌታቸው ኃይሌ
ሁለት ተሳዳቢ ፕሮፌሰሮች፤ መስፍን ወልደማርያምና ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ – ጌታቸው ኃይሌ 1

ይህም አለ። በሰው የሚደርስ ይቀሰቅሳል፤ በራስ የሚደርስ ያነቃል። በእኔ ሲደርስ ነቃሁ። የሁለቱም ፕሮፌሰሮች መነሻ “የምንጽፈውን አትተቹብን፤ ከተቻችሁት ባታነቡት ነው፤ ካነበባችሁትም ባይገባችሁ ነውና እንዳትገሠጹ ዝም በሉ” የሚል ስሜት ነው። የፍቅሬ ቶሎሳን ተረት “ተረት ነው” ብየ በመጻፌ፥ የወረደብኝን የስድብ ጋጋታ በኢንተርኔት የሚወጡትን ጽሑፎች የሚከታተል ሁሉ አይቷል። ከዚህ በፊት ዳንኤል ክብረት አንባቢ መሆኑንና የጠቀሰውም ካነበበው መጽሐፍ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ “አላነበብከውም” በማለት ውሸታም ተደርጓል። አልገባህምም ተብሏል። ግን አልገባህም ማለት የሚቻለው የረቀቀ የፊሎሶፊ መጽሐፍ ሲተች እንጂ ተራ ጽሑፍ ሲገመገም አይደለም።

ዳንኤልን ያሳዘነው አሉን የምንላቸውን የታሪክ ምሁራንን ሞያው ያልሆነ ሰው ሥራቸውን ሲነቅፍ አይቶ ነው። የታሪክ ባለሞያዎች ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን፥ ፕሮፌሰር መርድ ወልደ አረጋይን፥ ፕሮፌሰር ሥርግው ሐብለ ሥላሴን የሚያዩዋቸው ሠለስቱ የታሪክ አጋእዝት አድርገው ነው። ባለፉት አርባ ዓመታት የግዕዝ ሰነዶችን ለማጥናት ልዩ ዕድል አግኝቼ ነበር። ሁሉም የሚደግፉት ታደሰ የተለመውን የታሪክ መሥመር ነው። ገድላትና ተአምራት በሚሰጡት መንፈሳዊ ትምህርት ላይ የታሪክ ምንጮች መሆናቸውን ካስተማሩን ውስጥ ዋናው ታደሰ ታምራት ነው። ዛሬ Church and State In Ethiopia የሚለውን የታደሰ ታምራትን መጽሐፍ የማይጠቅስ የኢትዮጵያ ታሪክ ደራሲ ካለ ብቸኛ ሰው መሆን አለበት።

ለሕዝብ የቀረበን ድርሰት ሊተች የሚገባው ሲሆን ባለሞያው ነው። ካልሆነም አሳታሚ ካገኘ ማንም ሊተቸው ይችላል። በዚህ ጊዜ ደራሲው፥ “በድርሰቴ ምን ጠቀምኩ፥ ምንስ ጐዳሁ” ብሎ ሒሱን ይመረምራል እንጂ፥ “እንዳንተ ያለው የእኔን ድርሰት ለመተቸት ብቃት የለውም” አይባልም፤ በምሁራን ዓለም አልተለመደም። ከዓሥር መጻሕፍት በላይ ተችቻለሁ። ከአንድ ደራሲ በቀር ቅሬታውን አላሰማኝም። የታደሰ መጽሐፍም እንደገና ሲታተም መቅድም እንድጽፍለት ጠይቆኝ፥ ከረጅም ጊዜ ልምዴ የተነሣ ያየሁበትን ጉድለት ሳክልበት ታደሰ በደስታ ተቀብሎታል። ዓዋቂዎች ትችትን የሚቀበሉት እንደዚህ በጸጋ ነው። “ሐሳብን ከደራሲው ለይታችሁ ተቹ፤ ሐሳብ ለሐሳብ ሲፋጭ የተሻለ ሐሳብ ይወጣል፤ የሰውየውን ማንነት ወደመተቸት መሄድ አላዋቂነት ነው” የሚለውን መርሕ የሚያሣምሩ አንዳንድ መምህራን፥ በራሳቸው ሲደርስ በቅጽበት ያዳልጣቸዋል።

“እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በራየ” እንዲሉ፥ አንዳንድ መሠርይ ፈረንጆች የሠሩት ጥፋት በብዙዎች ዘንድ “ፈረንጅ ስለ ኢትዮጵያ የሚጽፈው ሁሉ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ነው” የሚል በሽታ አሳድሯል። እንዲህ ያሉ ተንኮለኛ ፈረንጆች አሁን የሉም አይባልም። ግን ካለፉት ውስጥ ለምሳሌ፥ ሂዮብ ሉዶልፍ፥ አውጉስት ዲልማን፥ ኤኖ ሊትማን፥ ቴዎዶር ኖልደከ፥ ኢግናዚኦ ጉኢዲ፥ ሴባስቲያን ኦይሪንገን፥ ዋሊስ በጅ፥ ሪቻርድ ፓንክረስት፥ ስቬን ሩበንሶን፥ ካሁኖቹ ውስጥ ደግሞ አሌሳንድሮ ባኡሲ፥ ዚግበርት ኡሊግ፥ ራይኔር ፎግት፥ ማንፍሬድ ክሮፕ፥ ሮናልዶ ራይኔሪ፥ ጀራርድ ኮሊን፥ ወዘተ. ያደረጉትን አስተዋፅኦ ለክፋት ነው ማለት ኢትዮጵያዊ ጀግና አያደርግም። ክብረ ነገሥትን ወደሃያ የሚሆኑ የብራና መጻሕፍት ቃል በቃል አመሳክሮ ያሳተመልንን ካርል ቤዞልድ ምን እንበለው? ዶክተር ሥርግው ገላዬ ወደአማርኛ የተረጐመው የካርል ቤዞልድን ጥናት ነው።

ምዕራባውያን (ፈረንጆች) በቀይ ባሕር ወዲህና ወዲያ ማዶ የሚኖሩ ሕዝቦችን ታሪክ ሲያጠኑ፥ በሁለቱ ቦታዎች ተመሳሳይ ቅርሶች አገኙ። ይኸ በዓይን የታየ፥ በእጅ የተዳሠሠ ጽድቅ (fact) ነው። ለምን እንዲህ ሆነ ሲባል የሚሰጠውን አስተያየትና ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ለአማሮችና ኦሮሞዎች መመሳሰል የሰጠውን ምክንያት (እወንዝ ውስጥ ያላባት የተጸነሱ መንታዎች) እኩል ሚሶሎጂዎች ናቸው ማለት ለዕውቀት ጕድለት ምስክርነት ነው።

በመጨረሻም፥ ዛሬ የዳንኤል ክብረትን ያህል የግዕዝን መጻሕፍት የመረመረ ኢትዮጵያዊ የለም። በኢትዮጵያ ገዳማትና በአውሮፓ አብያተ መጻሕፍት እያፈላለገ ይመዘግባቸዋል፥ ያነባቸዋል፥ ስለነሱም ይጽፋል። ታዲያ እንዲህ ያለውን ወጣት ቢያጠፋ እንኳን ይታለፋል እንጂ፥ ምን ዓይነት ኢትዮጵያዊ ሕሊና ነው በማበረታታት ፈንታ ለኢትዮጵያ ሊቃውንት ስም ለምን ተቈረቈርክ ተብሎ የሚሰደበው?

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop