January 27, 2017
3 mins read

አገሬን ሊያፈርሱ ተመካከሩባት

ጠላታችን ነግሶ በደም የሚኖረው ሰው-በላው ስርዓት

የወያኔ መንግስት ህጻናት ገዳዩ በትረ-አጋዚ ህውሃት፣

ምን ነክቷቸው ይሆን የጥበት ቁንጮዎች እነ አባ ሜንጫ

ምሁር ነን የሚሉ  የጥላቻ ጠበብት የሰይጣን መፈንጫ፣

አውሬው ተቀምጦ የሁላችን ጠላት

እምዬን ጠመዱ ተመካከሩባት

አገሬን ሊያጠፉ ዘግተው አሴሩባት

የናት ጡት ነካሾች  ኢትዮጲያን ሊያፈርሷት፣

ዥጉርጉሯ ነብር ቁስል ቢበዛባት

ጅቦች ተጠራሩ ቁርሳቸው ሊያደርጓት፣

ቀን አይቶ እንዲነሳ ተላላፊ ተውሳክ ጥገኛ በሽታ

እምዬ ስትደክም የገባች መስሏቸው ከሚሞቱት ተርታ

ልጆች እንደሌሏት ቀድመው የሚሰዉ ሊሆኗት መከታ

ዘረኞች ፎከሩ፣ ተስማሙ፣ እማማን ሊያጠፉ በመለስ በሽታ፣

ያለቀውን ወጣት መሰላል አድርገው

ኢትዮጲያዊነትን አጥላልተው ተዋግተው

ተረት ተረት ታሪክ፣ ጥላቻ አሰራጭተው

እቅዳቸው ሆኗል፣ ንጉሣን ሊሆኑ በየመንደራቸው፣

ደም እንደጎርፍ ፈሶ፣ በሃረር በባሌ በሸዋ በአርሲ በጎንደር በጎጃም

የወላጆች እንባ ወደ አምላክ ሲፈስ ፍትህን ፍለጋ ከእውነተኛው ዓለም

ለአገር የተሰዉት ቃላቸው ይህ ነበር፣ ለሞት ያበቃቸው፣ የወጣቶቹ ህልም

ፍትህ እንዲሰፍን በኢትዮጲያ ምድር፣ ዘረኝነት ጠፍቶ ሰብዓዊነት ይቅደም፣

የወጣቶቹ ራዕይ ወዳው ተካደና እንዳልሆነ ሆኖ ጭራሽ ተቀያይሮ

ጥላቻ ተዘራ በህሊና ቢሶች ሰልጥነው በወጡ ከወያኔ ጉያ ከገንጣዮች ጓሮ፣

የመለስ በሽታ በነሱ ላይ ሰፍሮ ቤቱን ሰርቶባቸው

በጭንቅላታቸው የጥላቻውን ድር ስላደራባቸው

እምነትን ከእምነት፣ ዘርንም ከዘሩ ማጣላት ስራቸው

ተምረናል ቢሉም፣ ከዘረኝነት ዉጭ ማሰብ ተሳናቸው

በሚነግሩንና በሚያከናዉኑት እኩይ ተግባራቸው

በሩቅ ይኑሩ እንጂ፣ ከወያኔ ጋራ ፍጹም አንድ ናቸው።

ወለለተ አገሬ

ታህሳስ 24፣ 2009 ዓ. ም

Previous Story

በወልቃይት ‹‹ዐማራ ነኝ››በማለታቸው ይቅርታ እንዲጠይቁ የተነገራቸው የሃይማኖት አባት ታሰሩ | በባሕር ዳር ለስብሰባ የተጠሩ ወጣቶች የብሔራዊ ውትድርና ግዳጅ እንዲሔዱ ተነገራቸው

Next Story

One for four, four for one, this we guarantee

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop