ደም እና አጥንት የተከፈለውም ሆነ እየተከፈለ ያለው፥ በነፃነት ለሚቋጨው ኢትዮጵያዊነት ነው። የቀደመ፤ ቀላል ስሌት

ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
እንደመግቢያ፤
             ለኢትዮጵያ አገራችን ዛሬም የኢትዮጵያን ሕዝብ አመፅ የሚቀላቀል ኢትዮጵያዊ ሁሉ:-መጀመሪያ ጠላቷን “የወያኔ ጉጅሌን” ለመዋጋት፥የጀርመን ናዚዎችን እና የፋሺሽት ጣሊያኖችን ዕውነተኛ ታሪካቸውን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል።እነዚህ ሁለት አሕጉራትበተጨማለቁበት የሕዝብ ደም ምክንያት አንገታቸውን ቢሰብሩም ገና ትውልድ ረግሟቸው አላበቃም።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓንን ጨምሮ  ሁለቱንም አገሮች የዓለም ሕዝብ ለምን አንቅሮ እንደተፋቸውና:- ዛሬም ድረስ የናዚናየፋሺሽት አባላት የነበሩት እየታደኑ እንደሚገደሉና፥ጃጅተውም ከተገኙ ከእነአልጋቸው ወደ ወይህኒ ቤት የሚወረወሩበት ምክንያት በታሪክየተመዘገበ አሰቃቂ ግፎችን ስለፈጸሙ ነው። ለዚህም አንዱ ማሳያው በክፍለ ዓለማችን አፍሪቃ ውስጥ በሁቱ እና በቱሲዎች የተከሰተውንያስታውሷል።
እናም ዘረኝነት እና ከዘረኝነት ጋር ከሚመጡ ርኩሰት ወንጀሎቻቸው በመነጩ ሰበቦች እና ተግባራቸው መሆኑን ልብ ልንል ይገባል።ያኛውአስቀያሚው የዘረኝነት ልክፍት መልኩን እንደዕስስት እየቀያየረ በድንቁርና አማካኝነት እየተሹለከለከ ዛሬም በየአገሮች ይገኛል።ከዚያየዘረኝነት ጦርነት ገፈት ቀማሽ ከነበሩት አገሮች አንዷ ደግሞ፤አገራችን ኢትዮጵያ ናት።
              እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ከአባቴ የአምቦ ጉደር ሙቱሉ ኦሮሞነቴ ወደኋላ አስር በሚቆጠሩ ዘሮቼ  ከአያቴ ተቆጥሮልኝባጠናሁት፤እና በእናቴ ደግሞ ከኮንሶ-ኦሮሞነት በተነገረኝ የዘር ሓረጓ አዲስ አበባ ተወልጄ ነው ያደግኩት።እናም ኢትዮጵያዊነቴንእንጂ የኦሮሞ ወይም የኮንሶ ብቻ ሳልሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነኝ።
          እራሴን በሁለት ብሔሮች ብቻ ገድቤ አሊያም አንድ ብሔር ነኝ ብዬ በፍጹም አላሳንስም። የሚገርመኝ እንዴት ሰው አንተ ቢያንስ የአስራአራት ሕብረብሔር ዘር ነህ ሲባል ራሱን ዝቅ አድርጎ አንድ ዘር ብቻ ነኝ ይላል???ዕውነት ነው እናትና አባቱን የሚያይ ፊትለፊቱ ባለው ብቻማንነቱን ሊወስን ይችላል።ከኋላው ያለው ትውልድስ ከየትስ እንደመጣ ምን አውቆ ነው የተሳሳተ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችለውና ከሰማንያስድስት የዘር ግንዶች ይልቅ ሁለት ወይም አንድ ብቻ ሊሆን የሚቻለው???እንዴት ራሳችንን ብንንቅ ነው ምሁራንን እንኳን ትተን ታሪክንየምንክደው???
    አንዳንዶች ትግሬነትን እንዳሸመቁበት ወያኔ-ጉጅሌዎች፤ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ቋንቋ እያስተማረና ለምድ እያለበሰ ሲያሰለጥናቸውእንደነበር አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ሐቅ ነው።ለዚህ ሁሉ መገለፅ ምክንያቱ የኢትዮጵያዊነትን አሊያም የኦሮሞነትንም ሆነየኤርትራዊነትን*^ ጭምብል አድርገው ነፃነታችንን የሚወጉትን በአደባባይ አጋልጠን ለመታገል ነው። ትግሬዎቹ*^
የርዕሳችን መነሻዎች ግን ሁለቱ አበይት ቃላት ማለትም ኢትዮጵያዊነት እና ነጻነት:- ሲሆኑ፤ውጤታቸው ሲሰላ ደግሞ አንድነው።የቃላቱን መተርጎም አስፈላጊነት፣ቅድመ አያቶቻችን”ነገር ከሥሩ ውሃ ከጥሩ፤” እንዲሉ:- የምናውቃቸው ቃላት ቢሆኑም እንኳ፣ከመነሻችን ትንሽ ነገር ታዘናጋናለች እና እንዳናቃልላት ውስጧን በዝርዝር እንየው።
       እናም እነዚህ በኢትዮጵያ የሕልውና ማሕጸን ውስጥ የሚነሱት ቃላት፤*-ብሔር:*-ዲሞክራሲ:*-እኩልነት:*-ነፃ ነት:*-ኢትዮጵያዊነት:*-ሥራ:*-ምግብ:*-መጠለ ያ ናቸው፤አንዴ እየተብራሩ፤ሌላ ጊዜ እየተሰነጠቁ፤ሲያሻም እየተጦመሩ፤እየተለጠጡና እየተቀናጁ ወደ አልተጠበቁተራ ጉዳዮች ቁልቁል አስተሳሰብ ያዘቅጡናል።
         እነዚህን ቃላት የመረጥኳቸውም ከልብ:- “ልብ” እንድንላቸው እንጂ”እንድናስተውላቸው”አይደለም።ማሸነፍም ልብን ነውና፤አስተዋይከምንላቸው ሰዎች መካከል ብዙዎቹ “ልባቸው”ለሚጠቅማቸው የግል ጉዳይ ተሸንፏል።ለዚህም ነው ጥቂት ልባሞች ብቻ ስላሉን በጉጅሌ:- የጣሊያን ፋሺሽት ፍልፍል የጭካኔ አካፋና ዶማ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጆች ደማቸው በየጎዳናው፣በየፍሳሽ ቆሻሻ መድፊያዎች ውስጥ እንደውሻከንቱ ሆኖ ባደባባይ እስኪደርቅ ድረስ ተመልካች ያጣው።ወገኖቼ:- ደም ግን ሙት አይደለም፤ፈሰሰም አልፈሰሰም፣ሕይወት አለውለዘላለም።የብዙዎቻችንም ልብ ከሕዝብ ጋር ቢሆንም ለሰፊው ሕዝብ የቆምን ጥቂቶች ነንና የማይሞት ልብ ያለን “ለነፃነት” አለን!!! እንላለን፤ትንፋሻችንንም ይዘናልና ጊዜ ዳኛውን እየጠበቅን እንታገላለን።
    “ልባቸው” የተሸነፈ አንዳአንድ አስተዋዮች (ምሁራን) ግን ሥልጣን፣ገንዘብና ሆድን አወቀና “ተሸነፈ”እንጂ:- ተሸንፎም ኣላበቃ፤ ባርነትአደረ።ማረጋገጫችንም ዜጎች ሲገደሉ እያዩ እንዳላዩ፤በሕግ ሥም ዳኞች በግፍ ፍትህን ሲያንቋት፣ሲያስሯትና ከውህይኒ ቤትሲያጉሯት፤ሲቃውን እንዳልሰሙ ሆነው እንዲኖሩ፤ወይ ይተባበራሉ፤አሊያም ዝምብለው ይመለከታሉ።ሲታዩ ደግሞ ሥልጣን የሕሊናስብዕናቸውን ገፎባቸው፣ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች አቀርቅረው፤በሆዳቸው እንደወደቁ “እየኖርን ነውi i i”ይሉናል።አንድ ቀን ግንተራቸው ደርሶ እነሱም እንደነዚያ ታኝከው እንዳበቁት ሲ-ተ-ፉ ነገ ልናያቸው ዕድሜ ይስጠን።
***የትግላችን ቃላት
፩ኛ    ነጻነት ሲተረጎም፤ዐርነት፣እንደልብ መኾን፣ባለቤት፣አዛዥ አለመኖር።
፪ኛ    ባርነት ሲተረጎም፤ነጻነት የሌለው፣በጌታው ዐሳብ አዳሪ፣ባለመከራ፣ እንደበሬ በግድ የሚሰራ።
፫ኛ    ኢትዮጵ/ጲስ ሁለተኛ የኩሽ ሥም፣የአገር ሥም፣የኖባ ልጆች ከግብጽ ቀጥሎ ያለው አገር ፣ቆላ አገር፤ኋላም ኢትዮጵያ (ኢቲዖፒኣ) ተብላየተሰየመች (ሱዳን-በዐረብኛ) አገር።(አለቃ ኪዳነ፡ወልድ፡ክፍሌ)እንደገለጹት:የኢትዮጵያዊነት አፍሪቃዊ፤ ምሥጢሩ ጥቁረትና ቆለኛነትነው።የነገድ፣የሕብር፣የመልክ፣ኢትዎፕስ።
“ዕብራይስጥ እና ጽርእ ቋንቋዎችን የማያውቁ ናቸው ስለ ኢትዮጵያ የተመዘገበ ታሪክ የሚዘባርቁት።”አለቃ ኪ/ወ፡ክፍሌ”«አብርሐማዊ»ሃይማኖቶች [(በዕብራይስጥ፦ תיבת נח /ተይባት ኖዋሕ/፤  በመጽሐፍ ቅዱስ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 6—9)፣ ዓረብኛ፦ سفينة نوح /ሣፊናኑህ/)በቁርዓንም (ሱራ 11 እና 71)፣ እንዲሁም በሌሎች (ክርስቲያኖች)*]በብሉይና በአዲስ የተጣፈው መደበኛው “ኢትዮጵያ” ግን ታላቁን በረሓሰሐራን ጨምሮ የኖባ ክፍል ነው፤ኢትዮጵስ የኩሽ ልጅ አይደለም።ኢትዎጲስ የኩሽ አባትም አይደለም።
በልጁ በኢትዮጲስ ስም ኢትዮጵያ ተባለች ይላሉ፤የግምት አነጋገር ነው።ይባስ የኩሽ አገር ኹሉ በልጁ በኢትዮጵስ ስም ኢትዮጵያ ተባለች  ይላሉ፤ይህም የግምትና የመላ፣አነጋገር  ነው።ዕውነቱ በጽርእ ቋንቋ ኢትዮጵስ የተባለው፣ያው በይብራይስጥ ኩሽ የተባለው የካም ልጅ ነውእንጂ።”
     ስለዚህ ኢትዮጵያ ከካም ልጅ ከኩሽ ወይም ከኢትዮጲስ ብቻ የወጣ ስያሜ ነው።ይህ ኢትዮጵያዊነት በዘመናት ተጸንሶና የትውልድባሕላትን ተሸጋግሮ፤ የኖረ፣እየኖረ ያለና ወደፊትም የሚኖር ፤ሥጋዊ፣መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ሕይወት ያለው ፤ረቂቅ ስያሜ ነው።እነሱ ሲጠሩንናእኛ ስንጣራበት ለየቅል ነው፤እኛ ታሪካችንን ስንጽፍና እነሱ ለራሳቸው ስለእኛ ሲጽፉ እንደማለት ነው።በዚያ በኩል ያለም ሆነ አዚህ’ጋየሚያገባው ባለቤቱ ራሱ ባለቤቱ ነውና፤ይህ የሐቅ መሠረት የሁሉም ዕውነታ  ነው።
ለምድ  እና ጭምብል፤ ኢትዮጵያን እናጠፋታለን ብለው ጭምብል አድርገው የተነሱትና የሚነሱት፣የሥጋ ትሎችም ሆኑ በፋሺስት ዘረኛፕሮፖጋንዳ ደዌ እና ቫይረስ የተከተቡ ባንዳዎች ሁሉ፣መጀመሪያ የሚጋጩት ከሳይንስ ጋር ነው። ኃይል{ኤነርጂ}ሊጠፋ እንደማይችልየማስገነዝባቸው ሲሆን፤ሌላው ዛሬም ካለፉት ጥፋቶች የማይማሩ ባለጊዜዎች የሚያረፍዱበት  ይሄንኑ አለመገንዘባቸው ሳይሆን፣ሥልጣንናገንዘብ ስለገዛቸው ብቻ ነው።
አንድ ሐሙስ በቀራት የመከራ ጭንቅ ውስጥ ሆነው ሽልማት ሲሸልሙ፤ሹመት ሲሰጡ፤ባጀት ሲበጅቱ፤አዋጅ ሲያውጁ፤ፕሮጄክት ሲነድፉና  ሲያፀድቁ  ያንንና ይሄንን ሲያደርጉ ትግሉ ተዳፍኗል ብለዋል።ይባስ ደግሞ ዕውነትን ለመቅበር አሳፋሪ የታሪክ ድርጊት እየፈጸሙ እንደአሉሙታን ቀባሪዎች ግብረ ኃይል አሰማርተው ማታማታ በድብቅ ያለአልቃሽ በጅምላ ሲቀብሩ፣ለማህሌት ያደሩ አባት ድንገት ስላዯቸው አፍነውወስደዋቸዋል፤የትም እንዳደረሷቸው ወደፊት የሚጣራ ይሆናል።አንባቢዎቼ አሁን ግን የመፍትሄውን ስሌት ከዚህ በታች ባለው ሁኔታልግለፅ።
aa መጀመሪያ አሁን በቅድሚያ ምንድን ነው የምንፈልገው?ነፃነት።ከነጻነት በፊት ሌሎችን ነገሮች የሚያነሳ ወይም የሚያወራ በሙሉከኢትዮጵያ መሠረታዊ ፍላጎት አጀንዳ ውጭ ነውና ይህን ገጽ አይሳተፍ።ቀጣዩ ደግሞ ምን ዓይነት ነጻነት?ሲባል” የኔነት” ነፃነት።የኔነት ነጻነትማለት ምንማለት ነው? የዜግነት ነጻነት ማለት ነው።አንድ ሰው የዜግነት ነጻነት ካለው ቀሪው ትርፍና በምናመጣው ነጻነት ውስጥ የሚመለስመብት ይሆናል።
በኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ በኢትዮጵያዊነታችን “ሁሉንም ብሔር”* ስለሆንን የትኛውም ግዛት ያለምንም ሕገ ደንብ በነጻነት መኖርናማድረግ እንችላለን፤ምንም መግለጫ አያስፈልገውም።ሁሉንም ለማድረግ ነጻነት ቢኖረንም ይህንን ነጻነታችንን ደግሞማንም አይጠብቅልንም፤ራሳችንን ጠባቂዎቹ ራሳችን ነን።በነዚህ መሠረታዊ ሃሳቦች ከተስማማን ያሉንን የነጻነት ምርጫዎች እንደቅደምተከተላቸው እንመርምራቸው። ።(ሰማንያ ስድስቱም ብሔረሰቦች በያንዳንዳችን ውስጥ አለ ብለን ስለምናምን)
የነጻነት አንዲት ስሌት:-
***ቅደመ ግንዛቤ፥ይህ የስነልቡና መመዘኛ የወረደ ቢሆንም ከመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ችላ ልንለው የማይገባን፤ቅደም- ተከተልበይዘታቸው ምክንያት ይበልጥ ይወሳሰቡ እንደሆነ እንጂ በፅንሰ ሃሳባቸው ግን አንድእና ግልጽ ናቸው።ስለዚህ የሚቀድመውን ለይቶማወቅ ነው።
        በሳይንሳዊ አቀራረብ አሃዞች ከአንድ እስከ አራት ቢጻፉ መቅደም ያለብትን ለመናገር በጣም ቀላል ነው።፩፣፪፣፫፣፬ ብለን እንጽፋለን።ከዚያ በላይ አሃዞች ሲቀመጡ ግን ለመምረጥ አይከብዱም ቢባልም፤እንደመጀመሪያዎቹ የቀለሉ አይሆኑም።በምሳሌ ስናየው፤፹፫ ፴፬ ፺፱ ፶፭፳፮ ተብለው  የተጻፉትን አሃዞች፣ከትንሹ ወደ ትልቁ በማንበብ በቅደም ተከተል እንድንጽፍ ብንጠየቅ የምንሰጠው ፳፮ ፴፬ ፶፭ ፹፫ ፺፱መልስ ማለት ነው።የሚብሰው የቅደም ተከተሉን ችግር ውስብስብ የሚያደርጉት ደግሞ፤ጥያቄዎቹ ከዓህዞች ውጭ ሲሆኑ ነው።በተለይምየማሕበራዊ፣የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጉዳይ ሲሆኑ፤በሳይንስ ቅመማን ሲከተሉ፤ነገሮች በሕግ ተይዘው ለውጤት ሲፈተሹ፤ከመላምቶች አሳማኙሲጠበቅ፤እናም ከመወሳሰባቸውም የተነሳ ችግሩን ፈቺዎች “አበዱ ወይ?” እስኪያስብል መፍትሄው እያነታረከ ወደ አልተጠበቀ ርዕሰ ጉዳዮችይዟቸው ሲጓዝ፤ለሰሚው ግራ ያጋባሉ።በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ውስጥም የሚታየው ይህ ውጥንቅጥ ነው።
*መርሳት የሌለብን ገና”ምን ይደረግ?” ስንል ውጥንቅጥ እንዲኖር የሚፈልግ አካል መኖሩን መገንዘብ ነው።ሁለተኛው ደግሞ”ግርግር ለሌባእንደሚመች” አውቀን ይህንን ሁኔታ ለመፍጠር እንደመሳሪያ የሚጠቀሙበት እንዳሉ ማወቅ ይኖርብናል።
ለነፃነት ጉዞ ወደ ተግባር፤መዘንጋት የሌለብን፤
1-   ኢትዮጵያ ወደድንም ጠላንም ዓለም የሚያውቀው፣ሕዝብ የሚጠብቀው፣ጠላት ሊደብቀው የሚፈልገው፤ ምድር ላይ የኢትዮጵያ ግዛትአላት።
2-  ኢትዮጵያ ጥንትም የነበሩ፤አሁንም የሚኖሩ፤ወደፊትም የሚኖሩ ሕዝቦች አሏት።
3-  ሕዝቦቿ ኢትዮጵያዊያን የሚያደርጋቸው በኢትዮጵያ ግዛት ስለሚኖሩ አይደለም፤በሕገ መንግሥት ስለዜግነት በተደነገጉት መሠረትነው።***(ለጊዜያዊ የፖለቲካ ሥልጣን የወጡና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረሩ ሕጎች፣ደንቦች እና ሌሎችም ማስፈጸሚያዎች ጊዜአቸውን  ጠብቀው በኢትዮጵያ ሕዝብ ይደመሰሳሉ።)
             ወደ ቀላሉ የችግር አፈታት ቅደም ተከተል እንምጣ፤እንዳንዘነጋ የቅደም ተከተል ምርጫ ውስጥ መግባት ያለበት አማራጭ ለተንኮልሲባል አይቀርብምና ሊኖር የሚገባውን አማራጭ ማንሳት የግድ ነው።አስመራጩ ባለሥልጣን ወይም ባላጊዜ የሆነ አካል ምርጫውን ገናሲያቀርብ”ያኛውስ ለምን ለምርጫ አልቀረበም?” በማለትና “ሁሉንም አንመርጥም” ብሎ መናገር:- የመምረጥ መብታችን መሆኑን መገንዘብ  አለብን።
የትኛው መቅደም አለበት???
እንግዲህ እነዚህን ቃላት በቅደም ተከተል እናስቀምጥና ስለዚያ ርዕሰ ጉዳይ አፈጻጸም ብቻ ተግባራዊ እናድርግ።
*-ብሔር:*-ዲሞክራሲ:*-እኩልነት:*-ነፃነት:* -ኢትዮጵያዊነት:*-ሥራ:*-ምግብ:*-መጠለያ
        በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እነዚህን ሁሉ ሳይሆን፤በቅደም ተከተል አንዱን ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእነዚህ መካከል መርጦ  ማስቀመጥ  ነው ያቃተን።ስለዚህ  ለያንዳንዱ ቅደም-ተከተል የአሃዝ  ደረጃ እንስጣቸው።ከዚያ በሗላ በአንደኛነት ስለተመረጠው ርዕሰ-ጉዳይ ብቻእየተነጋገርን እንወስናለን።
ስለዚህ በየግላችን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብቻ እያንዳንዳችን ስንጽፍም ሆነ ስንናገር መነጋገርም ሆነ ማውራት ያለብን አንድ ርዕስ ሊሆንይገባል።ከዚህ ርዕስ ውጭ በሚያምሩ ቃላት፣በሚያሳዝኑ ጥቅሶች፣አሊያም በግጥሞችና በመጽሃፍ ቢደገፉም፤በስዕል በስነጥበብ እናበፖለቲካ ትንታኔ የፈለገውን ያህል ልብ ቢነኩም ሐቁ ግን ስላለ ልብን ሊያሸንፉ አይቻላቸውም።ያም ሐቅ ከነጻነት ከበለጠ ልንመርጠውይገባናል።
ስለዚህም መጀመሪያ መቅደም ያለበት የቱ ነው???… ለምን???…
ማጠቃለያ:-
የምናስቀድመው ዐቢይ ርዕስ ከሁሉም በላይ የሚሆነው ለተቀሩት ርዕሶች መልስ ሊሆን እነደሚችል ስናረጋግጥ ብቻ ነው፤ካለበለዚያምርጫችን ስህተት ስለሆነ ትክክል ማድረግ አለብን።ለምሳሌ:-ምግብ የምንል እንኖራለን፤መልሱ ስህተት የሚሆነው ለምግብ ቅድሚያየሚሰጥ ለመብላት ብቻ የተፈጠረ በመሆኑና ሰው ግን ለመብላት ብቻ ባለመፈጠሩ ምግብ አንደኛ አይሆንም ማለት ነው።
የእኔ ዐቢይ ምርጫ አንደኛው ነጻነት ነው፤ለምን?ብትሉኝ ነጻነት ካለን ሁሉንም ልናገኛቸው ስለምንችል።ስለዚህ በቅድሚያ ነፃነትንተግባራዊ እናድርግ።ለምን??? ቢባል አሁን በባርነት ቀንበር ውስጥ ስለሆንን።መረጃችንስ ምንድንነው???…የባርነትን ትርጉምስለምናውቅ።የሚያሳዝነው እና ሰዎች የሚታለሉበት፤ ጉጅሌ ዲሞክራሲን ቅቤ ቀብቶበት የአይጥ ወጥመድ ማድረጉ ነው።ዕኩልነትን ደግሞየተለያዩ ቀለማትን የያዙ ባንዲራዎች በየክልሉ በመፍጠር :-የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለማርከስ የፋሽሺት ጣሊያን ዲዛይን የሆኑትን  ባንዲራዎች ጉጅሌ አስለብሶ ውስጡን በዘረኝነትና በትዕቢት አሳብጦታል።
ማገናዘቢያ፤
በመሠረቱ ነፃነት፤ዲሞክራሲም፣እኩልነትም ፣ከእስር ቤት መፈታትም ሆነ ሦስቱንም አይደለም፤ነፃነት፣”ነፃነት!!!”ብቻ ነው። ስለዚህምሁላችንም መጀመሪያ ለነፃነት ስንል እንታገል፤አንተኛ።የስሌታችን መጀመሪያ  መልሱ ነፃነት ብቻ ነውና ጉጅሌን እንገርስሰው ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንኳር ስህተቶች - አንድነት ይልቃል

1 Comment

  1. Your comment is awaiting moderation.

    You are concerned about the land not the people. The question in Ethiopia is how the people could achieve freedom and democracy in a multi-ethnic society. We know Ethiopia has a single party system that caused government corruption and citizens losing their democratic rights. The clear answer is Ethiopia needs a free multi-party democratic system, not a modified Haileselassies or DERG system in which the land is considered more important than the people.
    The above writer, and most foreign-based ambitious Ethiopian poliical groups are concerned mainly about maintaining territorial land of Ethiopia and are opposed to EPRDF govrnment on this line.
    For centuries, Ethiopia was ruled by emperors that treated the people on the farm like virtual slaves.
    Why the writer and present day educated opposition politicians think like the Emperors?

    Ethiopian society mainly constitutes various ethnic groups still using their own language and live on the land they farm for living.

    The EPRDF government allowed the communities to use their language and assigned adminisrators, public service employees, judges, and teachers who undrestand and know the language and the culture of the community.
    What is wrong is the local and regional administrators should have been chosen in a free democratic multi-party election.

    But why do you think it is wrong to allow ethnic Ethiopians to feel comfortable and confident in their own neighbourhood, school, and workplace, communicating in their own language?
    If you belive in God, be humble, check your heart and political ambition.
    I cannot understand why anyone gets angry at Ethiopians using their local languages.
    God is love. God is good.
    If you love Ethiopia and Ethipians, work for a democratic transition to a multi-party system.
    It seems you are a believer. If you fear God, open your heart to love, respect, and be equal to others. If you dream only about snatching poltical power from EPRDF, I am afraid to tell you that you remind me of Lucifer.

Comments are closed.

Share