ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አንገብጋቢ ሁኔታ ሚዛናዊና አስተዋይ አንድነትን አርቆ የሚያይ ሃይል ያስፈልጋታል።

#መደማመጥና_ቀናነት ቡድን

 

#መደማመጥና_ቀናነት ቡድን — እኛ በተሻለ ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን በነፃ ሀሳብን ማንሸራሸር ለድምፅ አልባ ወገኖቻችን ድምፅ መሆን እንችላለን ።የተሻለ ዕድሉ አለን።በውጭው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲን በተግባር ምን እንደሚመስል ከሀገር ቤቱ ወገን በበለጠ እናውቃለን የሕግ የበላይነት ምን እንደሆን እናውቃለን።ያወጣው ሕግ በማያከብረው የሕወሓት መንግሥት ሥር ሆነው ስለሕገ መንግሥት ትርጉም አልባነት በተግባር እያዩና ለዚያም ሰለባ ሆነው የኖሩት ወገኖች ያን የመሰለ አነጋገር ከነሱ ብንሰማ ቅር ልንሰኝ አይገባም ።

በውጭ ሀገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ሀገር በምንኖርበት ሀገር እና በትውልድ ሀገራችን የበለጠ ጠቃሚ መሆን እንችላለን ።በኛ አማካኝነት የዕድገት የዕውቀት የኢኮኖሚ ሽግ ግር መፍጠር የምንችል ይመስለኛል ።ነገር ግን የአእምሮ ድኩማኖች ስግብግቦች ሥልጣኑን ተቆጣጥረው የሀገሪቱን ሕዝብ አንጡራ ዜጋ እየናቁና እያወረዱ በሕይወቱና በንብረቱ ዋስትና እንዲያጣ ተደርጎ ሕግ በማይከበርበት ሀገር ራሱን ልማታዊ እንደሆነ አድር የቆጠረ የደንቆሮዎች ክምችት ሀገር ሊመራ ብሎም ያለተቀናቃኝ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ሁኖ የመኖር ሕልሙ ነው ዛሬ ላይ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወጣቶች እየታሰሩ በአስከፊ ድብደባ በከፍተኛ የሥነ አዕምሮ የሞራል ውድወት እያደረሰ ያለው ።

በውጭ ሀገር መልካም ኑሮ ከኖርን ብለን አይተን እንደሰላየን ሰምተነን እንዳልሰማን ሁነን መቀመጥ ይብቃ ።እውነቱ ለመናገር እንድፈር ።ጥሩውን የመደገፍ ሴረኛንና ተነኮለኛን በጋራ መቃወም አለብን ።የመጀመሪያዎች የወያኔ ኮሜንት ሰጭዎች ተመርቀው ወደ ስራ መግባታቸውን መዘገቡ ይታወሳል፥እኛ ኢትዮጵያውያኖች መቸም ቢሆን የዘመኑን ፖለቲካ እንደ ፖለቲካ ለይተን ልናየው አልቻልንም ያደግሞ ለወያኔ አሁን ካለበት ጫና ትልቅ ሎተሪ መሆኑ ነው፦የማንኛውም ፖለቲካዊ ድርጅት አባል እና ስራ አስፈጻሚ የሚዲያ ሰዎች ሁሌም ዝንባሌያቸው ስሜት ጋር ነው አካሄዳቸው ከስሜት የነጻ አይደልም፦ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አንገብጋቢ ሁኔታ ሚዛናዊና አስተዋይ አንድነትን አርቆ የሚያይ ሃይል ያስፈልጋታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውድ ወንድሜ ታማኝ በየነ፤  አህያውን ፈርተህ ዳውላውን? - መስፍን አረጋ

ባንታደል ነው እንጂ አለም በቴክኖሎጂው በጣም አሩጣለች እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከነሱ ለመድረስ ለመመራመርና አዳዲስ ግኝቶችን ለመፍጠር ምንም አያንሰንም እንዲያውም የስልጣኔ ፈር ቀዳጆች ነበርን እንዳለመታደል ፖለቲካችን ጋር ሁሉንም ነገር እያያዝነው ተቸገርን እንጂ፥፥ዛሬ አዳዲስ ግኙተችን አዳዲስ ያልተፈበረኩ ለ አለም ይጠቅማሉ እሚባሉ ነገሮች ላይ ከማተኮር እድሜ ለወያኔ ኮሜንት ሰጭነትን እንደ ትልቅ ስራ አይቶ ስልጠና ሲል ምን ያህል ድርጅቱም በስሩም ያሉት አለቅላቂዎች ነን ባዮች የፊደል ሽፍቶች። መሆናቸውን አስመሰከረባቸው። ያብቻ አይደልም ወያኔ ትንሽ ሰከን ብሎ ቢያስብ በእነዚህ ስልጡን ኮሜንት ሰጭዎች የኢትዮጵያውያን ወደ ነጻነት ጉዞ በቀላሉ አይከሽፍም ሊከሽፍም አይችልም፦ ያም ሆን ይህ የአማራውም ሆናቹህ የኦሮሞ ነጻን አውጭ መሪ ነን ባዮች ህዝቡ ሞኝ አይደልም አክራሪነታቹህን አጉል ስድባቹን በሶሻል ሚዲያዎች እስካላቆማቹህ ድረስ ለወያኔ ድርጅት ከሚሰሩ ስልጡን ኮሜንት ሰጭዎች በምንም አትለዩምና ለውጥም አታመጡም፥ ይባስ ለወያኔ ከመጥቀማቹና አድሜ ማራዘሚያ ከመሆናቹህ በስተቀር፥ በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚታዩትን አጉል ዘለፋዎች ልናቆም ይገባል ።

Share