ቀበጥ አማት ሲሦ ብትር አላት! (ምሕረቱ ዘገዬ)

“የሀገሬን ሕዝብ ለጣሊያን ቅኝ ገዢ አድረህ ተገዛ ከምል ሞቴን እመርጣለሁ” በማለታቸው በመትረየስ ተደብድበው የሞቱ አባት (አቡነ ጴጥሮስ) በተፈጠሩባት ምድር “መሣሪያችሁን በሰላም አስረክባችሁ ‹እግዜር ከሾመው መንግሥት› ከወያኔ ጋር በሰላም እየኖራችሁ ልጆቻችሁን አሳድጉ” የሚሉ ካህናትን ማየት በጣም ያምማል፡፡ ከሰሜን ምዕራብ የሀገራችን ክፍል ሰሞኑን እየሰማነው ያለው አስነዋሪና አሣዛኝ ነገር ይህን የሚመስል ነው፡፡ ይህ ክስተት ሊሰሙትም እጅግ የሚሰቀጥጥ በመሆኑ በዚህ ዓይነት ቅሌት ውስጥ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባት ተብዬዎችን በተቻላችሁ ሁሉ አስጠንቅቁ – ለፈርሳቸው ሲሉ ዕድሜያቸውንና ማተባቸውን ይህን ያህል አያዋርዱ፡፡ እግዚአብሔር ከሚወደውና ከሚያዝዘው ውጪ ለሥጋቸው በማደር ለሰይጣኑ የወያኔ ጭፍራ ዜጎችን በጭዳነት ለማስገባት የሚጥሩ ወገኖች ዋጋቸውን እዚህ እያሉ በምድርም ቢሆን ማግኘት ይገባቸዋልና የነፃነት ታጋዮች ሁሉ በዚህ ረገድ አንዳችም ይሉኝታ እንዳይዛችሁ በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም እማጠናችኋለሁ – ለነዚህ ዓይነት እስስቶች የሚራራ ልብ እንዳይኖራችሁ በማይም ቃሌ ገዝቻችኋለሁ (ግዝት አለባችሁ)፡፡ ይህን መሰሉን ቅሌታም ካህንና ሽማግሌ ተብዬ አደብ ብታስገዙት ሌላውም ይማርበትና ያርፋል፡፡ አለቦታው የዋለ ማዕረገ ክህነትና የዕድሜ ባለጠግነት አፍራሽ ነውና ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት፡፡ ስለዚህ ማፈር እውነትን እንጂ ሀሰትን አይደለምና በተለይ ታጋዮች ይህን መሰሉን ሰይጣናዊ የወያኔ ተልእኮ ለማፍረስ በጭራሽ ይሉኝታ እንዳይዛችሁ አደራ፡፡
ከሰይጣን ጋር የሚወዳጁ የሃይማኖት አባቶችና የእንጨት ሽበቶች በቀለሉ ቁጥር እኛም አብረን ልንቀል ወይም የቅሌታቸው ተባባሪ ልንሆን አይገባም፡፡ ሰው የሚከበረው የሚያስከብረውን ተግባር ሲያደርግ እንጂ የክርስቶስን መስቀል ተሸክሞና ከዘራ ይዞ ከሃይማኖቱና ከዕድሜው ውጪ ብልሹ ድርጊት ከፈጸመ ሊወገዝና እንዳስፈላጊነቱም ሊወገድ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ራሱ ምድር ወርዶ ጦርነትን አይዋጋም፡፡ ጦርነት የሰዎች ነው፤ ነፃነትም የሰዎች ናት፡፡ ስለሆነም ነፃነትን የሚያደናቅፍ ማንኛውም ኃይል ሁሉ አጋንንታዊ ነውና መወገዝና መወገድም ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ የነፃነት ኃይሎች ውስጣቸው ሰይጣን በተሞላ የረጃጅም ካባ ለባሾችና የማያምኑበትን መስቀል ከተሸከሙ ሐሣይ መሲሆች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የዜግነት ግዴታየ ነውና አደራ እላለሁ፡፡ ሀሰተኛ ካህንን የሥራውን መስጠት ኃጢኣት የለውም፡፡ በዘመናችን እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በጣት የሚቆጠሩ በጣም ኢምንት ናቸው፡፡ አብዛኛው እረኛ ወደ ተኩላነት ተለውጦ በጎችን በጠራራ ፀሐይ በቀበሮ የሚያስነጥቅ ሆኗል፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ማለት ቢቻልም በደምሳሳው ግን ዘመኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው የእፉኝቶች ዘመን ነውና በአለባበስና በአነጋገር እንዳንታለል እንጠንቀቅ፡፡ ይሁዳዎች ወርረናል፤ ማተቡን የሚጠብቅ ሰው እየጠፋ ነው፡፡ ጳጳስና ፓትርያርክ ዘረኛ ከሆኑ ምዕመንና ተራ ካህንማ ምን ይሁኑ? እግዚዖ እንል! ሀገር በኖረን ማግሥት የሚጠብቀን ሥራ ራሱ ከአሁኑ እግዚዖ የሚያሰኝ ነው፡፡ ወያኔ ያላበለሻሸው ነገር የለም፡፡ በሁሉም ረገድ ከሰው በታች አድርገውናል፡፡ ሙስናንና ኢ-ሞራላዊነትን ከያንዳንዳችን አእምሮ ለማጥፋት ብቻ ስንት ጊዜና ስንት ድካም እንደሚፈጅብን አላውቅም፡፡ የፈጣሪ ቀጥተኛ ጣልቃ-ገብነት ከሌለ ትግላችን አሣር የሚበዛበት ይሆናል፡፡
ወያኔና ሰይጣን በምን ይለያያሉ?
በመሠረቱ ወያኔንና ሰይጣንን መለየት በፍጹም አይቻልም፡፡ የሰይጣን ፍሬዎች የሆኑ ሁሉ በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ ወያኔዎች እንዲያውም ከሰይጣንም በበለጠ ሰይጣን ናቸው፤ ሊቀ ሣጥናኤል ደረቱን ገልብጦ ከሚኮራባቸው ሰብኣዊ መሣሪያዎቹ መካከል የመጀመሪያዎቹ ወያኔዎች እንደሚሆኑ በበኩሌ አልጠራጠርም፡፡ የጭካኔያቸው ደረጃ በተለምዶ ከምናውቀው “ሩህሩሁ” ሰይጣን በእጅጉ የከፋ ነው፡፡ ይቅርታና ምሕረት የሚባል በጭራሽ የላቸውም፡፡ በልተውና ጠጥተው እንደማይጠግቡ ሁሉ ገድለውና አሰቃይተውም አይረኩም፡፡ ከፉ ብቻ ሣይሆኑ ክፋት ጭምርም ናቸው፡፡ ዐረመኔና ጨካኝ ብቻ ሣይሆኑ ዐረመኔነትና ጭካኔም ጭምር ናቸው – በጭካኔያቸው የሰው ሥጋ በላ ከተባለው ኢዲያሚን ዳዳም ሆነ ሰውን በጋዝ ቼምበር ከነነፍሱ እንዳቃጠለ ከሚነገርለት ከሂትለር የበለጡ ናቸው፡፡ ወያኔዎች ከሚታወቁበት ሌላኛው ጠባያቸው አንዱ ቡድናዊ ጭካኔያቸው ነው፤ ሌሎች ብዙዎች ጨካኞች የሚታወቁት ለምሣሌ ቢስማርክ፣ ስታሊን፣ ቦካሳ፣ ሳዳም፣ መንግሥቱ፣ ጋዳፊ፣ ዚያድባሬ ወዘተ. … በግል ትዛዛቸው በፈጸሙት የጭካኔና የወንጀል ተግባር ነው፡፡ ወያኔ ግን በቡድናዊ የወል አስተሳሰብ እየተመራ ነው በተለይ ከመለስ ሞት በኋላ የምናየውንና የምንሰማውን ሀገራዊ መቅሰፍት ሁሉ በዜጎች ላይ እያደረሰ የሚገኘው፡፡ በጥቀሉ ቂመኝነት፣በቀለኝነት፣ተንኮለኝነት፣ ግብዝነት፣ አድሎኣዊነት፣ ፍቅር-አልባነት፣ ባዶነት፣ ሆዳምነት፣ ወዘተ. የዲያብሎሣውያኑ ወያኔዎች ዋና ዋና መገለጫዎቻቸው ናቸው፡፡ ይሄ ምድራዊ እንጀራ የአንድን ዘውግ አብዛኛውን አባል እንዲህ በሰይጣናዊ ገመድ ያስተሳስራል? አንዱ እንኳ ከመሀል ተነስቶ “ኧረ ይሄ ነገር ለቀጣይ ትውልዶቻችን ደግ አይደለም! እባካችሁ ልቦናችን ይሥራ!” ብሎ ወደኅሊናቸው እንዲመለሱ አይመክርም? በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ጊዜ እንኳን ደክለርክን፣ ዱንካንንና ሁድልስተንን የመሳሰሉ ነጮች የዘሮቻቸውን የአፓርታይድ አገዛዝ በመቃወም ለጥቁሮች ነፃነት የበኩላቸውን ድርሻ አበርክተዋል፡፡ እዚህ እኛ ጋ ግን ለዚህ ዕዳሪ ለሚወድቅ እህል ውኃ ሲባል ሐጎስ ገመቹ ሞላልኝ ልኬሣንና ታንጉት ግደይን በዘረኝነት ልክፍት ታውሮ በመትረየስ ይጨፈጭፋል፡፡ ምን ዓይነት መርገምት ነው? እንጀራ መብላት፣ መጠጥ መጠጣትና ልብስ መልበስ የማይርኖበት ጊዜ ቢመጣ ስንቶቻችን በትዝብት አለንጋ እንገረፍ ይሆን? ወልቃይትን የሚያዘርፍ፣ ተራራን የሚያሰርቅ፣ ራያ ቆቦን የሚያዘርፍ፣ የአፋርን መሬት የሚያሰርቅ፣ ሀብት ንብረት ከመሀል አገር የሚያዘርፍ፣ ቤንሸንጉል-ጉሙዝን የሚያስመኝ፣ ድንበርን በጊዜያዊ የውስጥ ለውስጥ ስምምነት ለባዕዳን በወለድ አገድ የሚያሰጥ፣ … ምን ዓይነት ሰይጣናዊ ርሀብ ይሆን? ኧረ ይህን ሁሉ አስቀያሚ ታሪክ ወደፊት እንዴት ይሆን የምናወራው? የወደፊት ልጆቻችንስ ምን ይሉን ይሆን? እንደ ትግሬ ወላጅ ሆኜ ሳስበው ደግሞ እጅግ ይጨንቀኛል – በውነቱ በዚህች ኢትዮጵያ ምን እየተካሄድ ነው? ከሆድና ከጌጣ ጌጥ፣ ከብር፣ ከወርቅና ከአልማዝ፣ ከቤትና ከመኪና፣ ከቆንጆ ሚስትና ከባንክ ደብተር፣ ከፋብሪካና ከሪል እስቴት … ባለፈ ለሀገር መልካም ነገር የሚያስብ ዜጋ እንዴት ይጥፋ? ሆ!!
በበቀል ንዳድ የሚንገበገቡት ወያኔዎች የሠሩትን ሁሉ እዚህ መጥቀስ አይቻልም፡፡ ግን ደግሞ ጥቂት አብነቶችን ማውሳቱ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን ለመረዳት ይጠቅማልና አይከፋም፡፡
አንድ ስሙን የማላነሳው ሰው፣ ትግሬ መስሏቸው ለአምባሳደር ያጩትና ከሌሎች ጋር የ15 ቀናት ሥልጠና ይወስዳል፡፡ ሥልጠናውን ጨርሶ ወደተመደበበት ሀገር ሊጓዝ ዕቃውን ሲሸካክፍ ሰውዬው ትግርኛ ይችላል እንጂ ትግሬ አለመሆኑን ይደርሱበታል፡፡ አይገርማችሁም? ከአምባሳደርነት አስቀሩት፡፡ ትግሬ ባለመሆኑ ብቻ ሹመቱ ተሠረዘ፡፡ ወያኔዎች ሀፍረትና ይሉኝታ የሌላቸው እንዲህ ቀትረ ቀላል ናቸው፡፡ ታሪክ የሚመዘግብ ይህንንም ይመዝግበው፡፡ ይህ እንግዲህ ከሚሊዮኖች ይህን መሰል ክስተቶች አንዱና ገራሙ እንጂ ብቸኛው አይደለም፡፡
አንዱ ትግሬ ወዳጄ ወያኔዎች ሲገቡ መምህር ነበር፡፡ በቅርቡ ሲነግረኝ እንደገቡ ሰሞን ትግሬዎችን ከየትምህርት ቤቱ በጧፍና በሻማ ነበር ይፈልጓቸውና ይሾሟቸው የነበረው፡፡ ይህ ወዳጄ ከመምህርነት ተነስቶ ምን የመሰለ ቀብራራ ሥራ አስኪያጅ ሆነ፡፡ በቅርብ ግን ጡረታ ወጣና አሁን አብረን ወያኔን እናማለን፡፡ ብዙም አይወዳቸውም፡፡ እኔ ግን ትግሬን እምብዝም ስለማላምን የልቤን አልጫወትም – ሆ! ደግሞም በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ውስጥ ሆኜ! አላደርገውም፡፡ እንደሚለኝ ከሆነ ግን የኢትዮጵያን ቢሮክራሲ ከአማራና ከኦሮሞ ተፅዕኖ ለማውጣትና እነሱ እንደልባቸው የሚፈነጥዙበት አሠራር ለመትከል ባደረጉት ጥረት በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ዜጎች ከሥራ እየተባረሩ በምትካቸው ችሎታና ትምህርት የሌላቸው ትግሬዎች ከየሥርቻው እየተለቀሙ ገብተዋል፡፡ ችሎታ የሌለውና ያልተማረ ሰው ደግሞ ቀልቡ የሚሳበው በሙስናና በምዝበራ በሚገኝ ሀብት ማደግ እንጂ ስለሀገርና ወገን ፍቅር ደንታ የለውም፡፡ ብቻ ፈረንቹ from the horse’s mouth እንደሚሉት ከዋናዎቹ ሰዎች እንዳጠናቀርኩት የሀገራችን የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎች ብቻ ሳይሆኑ ተራው ሥራ ሁሉ አመኔታ በሚጣልባቸው ትግሬዎች መያዙን ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ይህም ይመዝገብልኝ፡፡ አንዳንድ ድፍን ቅል ግን ለራሱ ብቻ ሊገባው በሚችል አመክንዮ የተነሣ “ትግሬ በወያኔ አልተጠቀመም!” እያለ የጆሮ ታምቡራችንን ያደነቁራል፡፡
ጎብልስ የሚሉት ጀርመናዊ ዐውሬ ነበር አሉ፡፡ ስድስት ልጆቹን በመጀመሪያ ማደንዘዣ አስወጋቸው አሉ፡፡ ቀጥሎ የሳይናይድ መርዝ ልክ እንደፀረ ስድስት ክትባት አፋቸው ላይ ጠብ እያስደረገ ጨረሳቸው፡፡ ይህ ናዚና ወያኔዎች አንድ ናቸው – ይህ እርጉም ሰውዬ እንዴት አፌ ላይ ገባ በል፡፡ ለማንኛውም ማንም ቢሆን ንጹሓንን አለምንም ጥፋትና አለምንም የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ በጥላቻና በበቀል ስሜት ልግደል ብሎ ከተነሣ ሰይጣን እንጂ ሰው ሊሆን አይችልም፡፡ ያ ሰው – ጉብልስ የሚሉት ሰይጣን – እንዲህ ብሏል አሉ፡፡ “A lie told once remains a lie but a lie told a thousand times becomes the truth”. “አንዴ የሚነገር ውሸት፣ ያው ውሸት ነው፡፡ አንድ ሺህ ጊዜ የሚነገር ውሸት ግን የእውነት ያህል ነው”፡፡ ይህ የገዛ ልጆቹን ሳይቀር ለጌታው ለአያ ሰይጣን ጭዳ አድርጎ ያቀረበ ጀርመናዊ ከወያኔ ጋር የሚመሳሰልበት ብዙ ነገር እንዳለው መዘንጋት የለብንም፡፡ ወያኔዎችም ለጌታቸው ግብር ሲሉ በየቀኑ ነው የኦሮሞንና የአማራን እንዲሁም የተቃወማቸውን የማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ደም የሚያፈሱት – እነሱ ምንተዳቸው አላርፍ ካለ የትግሬንም ጭምር፡፡ ሰይጣን ከፈለገ ደግሞ እንኳንስ የዘውገኛቸውን የልጆቻቸውንና የባልተቤቶቻቸውንም ደም ሣይቀር ገብሩ ሊላቸው ይችላል – በርግጠኝነት አያቅማሙም (የትኛዋን ባለቤታቸውን እንደሚገብሩለት ግን ከነሱና ከሰይጣኑ በቀር የሚያውቅ የለም)፡፡ ምክንያቱም እምቢ ማለት እንዳይችሉ በሰው ደምና አጥንት ግብር ቃል ኪዳን ገብተዋልና – ዱሮ ደደቢት ላይ፡፡ በደም የቆረበ ደግሞ መጨረሻውም በደም አላባ መነከር ነው፡፡
አሁን ግን ዘመናቸው አልቋል፡፡ ጣዕረሞታቸውን ጀምረዋል፡፡
በሰይጣን እንደጀመርኩ በሰይጣን አንድ ታሪክ ልጨርስ፡፡ አያ ሰይጣን ከገነት ተባርሮ ወደ ሲዖል ማለትም ወደ እንጦርጦስ እየተምዘገዘገ በመውረድ ላይ ነበረ አሉ፡፡ አያልቅበት ሰይጣን ያኔ ምን አለ መሰላችሁ “ ይሄውና እግዚአብሔር ፈርቶኝ ከኔ እየራቀ ነው!” ልብ አድርጉ እንግዲህ፣ ከእግዚአብሔር በብርሃን ፍጥነት እየተሸቀነጠረ መቅ ይወርድ የነበረው ሰይጣን ነው እንጂ እግዚአብሔርማ እዚያው በመንበረፀባዖቱ የሱራፌልና ኪሩቤል ዙፋን ላይ ነበር፡፡ ሰይጣን ግን መሸነፍን እንደጦር ይፈራልና እየተሸነፈም እንዳሸነፈ ይቆጥር ነበር፡፡ አምባገነኖች እንዲህ ናቸው፡፡ ሞተውም ሞታቸውን አምነው ሊቀበሉ አይፈልጉም፡፡ ለዛሬ የምለው አለቀብኝ፡፡ ሰላም ለሀገራችን ይሁን፡፡ በእጅ ልንነካት የደረሰችዋ ነፃነታችን በቶሎ ትምጣና የ“ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል”ን ትንቢተ አበው እውን ታድርግልን፡፡
ከስድብ በስተቀር ለማንኛውም አስተያየት – mz23602@gmail.com
በነገራችን ላይ በአማርኛ ተናጋሪ ማኅበረሰብ አካባቢ አማት – የሚስት እናት – በአማች በጣም ትከበራለች፡፡ ነገር ግን ክብሯን መጠበቅ ያልፈለገች አማት በትዳር ውስጥ ጣልቃ እየገባች የምታውክ ከሆነ ለሚስት የታቀደ(የተሰነዘረ) ብትር ለአማትም ሊደርስ ይችላል – በማወቅ ሆን ተብሎ ወይም ባለማወቅ በግልግል ወቅት፡፡ ስለሆነም በርዕሴ ይህን ትውፊታዊ ሥነ ቃል የተጠቀምኩት ካህናትና ታዋቂ የአካባቢ ሽማግሌዎች ከሚያስከብራቸው የሀገር ነፃነት ጥብቅና ወጥተው ለወያኔ ካደሩ ለወያኔ የሚወረወረው ዱላ እነሱንም ያካትታል ለማለት ፈልጌ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአርባምንጭ ቅስቀሳ በከፊል
Share