የማህበራዊና የህብረተሰብአዊ ጥያቄ ወይም የብሄር/ ብሄረሰብ ጥያቄ ?„ እባብ ወተት ጠጥታ መርዝ ትተፋለች፣ ቅዱስ ግን መርዝ ጠጥቶ ወተት ይተፋል !“

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)
ጥቅምት 24 ፣ 2016 መግቢያ !

አሁን ያለንበት ዘመን 21 ኛው ክፍለ- ዘመን ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ ብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገሮችና አሜሪካንንም ጨምሮ፣ እንዲሁም ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ፣ ዛሬ ደግሞ ቻይና በሳይንስ አማካይነት የቴክኖሎጂ ምጥቀትን በማግኘት አነሰም በዛም የተረጋጋ ህብረተሰብ ለመገንባት ችለዋል። በተለይም ባለፉት 40 ዓመታት የተፈጠሩትና ገበያ ላይ የዋሉት ቴክኖሎጂዎች ቀደም ብለው ከነበሩት ቴክኖሎጂዎች ጋር ሲወዳደሩ በጥራትም ሆነ በምቾት እጀግ ተሽለው የሚገኙ ናቸው። የዛሬ አርባ ዓመት ገበያ ላይ የነበሩና ለፍጆታ የቀረቡ ምርቶች ዛሬ በፍጹም አይታዩም። እንዲሁም ቴክኖሎጂዎች እጅግ ከመሻሻላቸው የተነሳ በተወሰነ ሰዓትና የሰው ኃይል ብዙ ምርቶችን ማምረት የሚቻልበት ወቅት ውስጥ ነው የምንገኘው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ መኪናንና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች በግማሽ ወይም በሙሉ አውቶማቲክ ወይም ሮቦታ እየታገዙ ነው የተለያዩ ክፍሎችን የሚገጣጥሙትና ወደ አንድ ወጥ ምርትነት የሚለውጡት። ሰልሆነም በዚህ የቴክኖሎጂ ዓለም በመታገዝ እኛም በብዙ ሺህ ማይልስ የሚቆጠር ርቀትን አልፈን መጥተን አውሮፓና አሜሪካ፣ እንዲሁም ሌላ ሰለጠን የሚባለው ዓለም ውስጥ ተበታትነንና ተደላድለን በመኖር የቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚዎች ለመሆን በቅተናል። አዳዲስ መኪናዎችን የምናሽከረክር፣ በኢንተርኔት ዓለም ውስጥ በመኖር ኢንፎርሜሽኖችን አንድ ደቂቃ በማይፈጅ ጊዜ ውስጥ የመለዋወጥ እድል አለን። የምንኖርበት ቤትም ማንኛውንም ነገር ያሟላ ነው። እነዚህ ሁሉ ቴክኖሎጂዎች የተገኙት ዝም ተብለው አይደለም፤ ወይም ከሰማይ ዱብ ብለው የወረዱ አይደሉም። ከፍተኛ ምርምርንና ሙከራን በማድረግ ነው ቴክኖሎጂዎቹ የተገኙት። የጥቂት አገሮችና ህዝቦች የስራ ውጤቶች በመሆን ከእነሱ አልፈው የዓለም ማህበረሰብ እንዲጠቀምበት አድርገዋል። እስቲ እናስብ የአውሮፓ አገሮችና ሌሎችም የሃይ- ቴክ ባለቤት የሆኑ አገሮች እድሜያቸውን በሙሉ የሚሆን የማይሆን ነገር አንስተው ቢጨቃጨቁ ኖሮ እንደዚህ ዓይነቱን የቴክኖሎጂን ምጥቀት ማየት ይችሉ ነበር ወይ ? በፍጹም ! አንድም እርምጃ ወደ ፊት መራመድ ባልቻሉም ነበር። የእነሱ እጣ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የዓለም ህዝብም እጣ የጨለማና የድህነት ኑሮ በሆነ ነበር። እንደኛው በድህነትና በረሃብ እንዲሁም በስደት በማቀቁ ነበር። ወደ እኛ አገር ስንመጣ፣ ምናልባት ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የተነሳ የብሄረሰብ ችግርና ጭቆና የሚሉት ነገር ጭንቅላታችንን ወጥሮት ዛሬም እንደ አዲስ አጀንዳ ይዘን ስንጨቃጨቅ እንገኛለን። ዋናው ችግራችንና የስልጣኔውም ቁልፍ እሱን በመፍታት ብቻ ይገኝ ይመስል፣ ብሄሬ ተበደለ፣ ተጨቆነ፣ ተናቀ፣ አማርኛን ተገድጄ ነው የተማርኩት፣ መለያዬን እንደገና መልሼ ማግኘት አለብኝ በማለት ያልተወራረደ ሂሳብ ያለን ይመስል በዚህና ሌሎች እልክ አስጨራሽና፣ የሰውን ጭንቅላት ወጥረው በሚይዙ፣ ግን ደግሞ የአንድን ህብረተሰብ ችግር ለመፍታት በማይችሉ ነገሮች ላይ ስንጨቃጨቅና ሰሚናርም ስናዘጋጅ እንታያለን። ይህንን ያረጀና በታሪክ ውስጥ ካለማወቅ የተነሳ የተደረጉ ስህተቶችን እየደጋገምን በማንሳት የታዳጊውን ትውልድ ጭንቅላት በርዘናል። ለማቲማቲክስ፣ ለፊዚክስ፣ ለኬሚስትሪ፣ ለባዮሎጂና፣ እንዲሁም ለሌሎች የህዝባችንና የአገራችንን ችግሮች መፍቻ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ ከመረባረብ ይልቅ የብሄር ጥያቄ የሚሉትን የቅኝ ገዢዎችን የመከፋፈያ አስተሳሰብ የራሳችን በማድረግ ሃምሳ
ዓመት ያህል ርስ በራሳችን ተከሳክሰናል። ጦርነት ከፍተን በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲያልቁ አድርገናል። ከፍተኛ የታሪክና የባህል ወንጀል ሰርተናል። የዛሬው የአገራችንን ሁኔታ እንዳለ ሆኖ፣ ህዝባችንም የመረረ ትግል በሚያደርግበት ወቅት አንዳንዶች የትግሉን አቅጣጫ ለማዘናጋት የብሄረሰብን አጀንዳ እንደዋና የችግሩ ምንጭ አድርገው በማንሳት ወጣቱን በስሜት እየቀሰቀሱትና የማሰብ ኃይሉን ችግርን በማይፈታ ነገር ላይ እንዲያተኩር በማድረግ ላይ ናቸው። እንደሚታወቀው፣ በተለይም ኋላ- ቀሩ በሚባሉ አገሮች ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችና በህዝብ ላይ በተለያየ መልክ የሚደርሱ ጭቆናዎች አብዛኛውን ጊዜ ካለማወቅ የተነሳ ነው። ህብረተሰብአዊ ተሃድሶ በሌለበትና ብዙ ነገሮች በዘልማድ በሚሰሩበት አገሮች ውስጥ ስልጣንን የጨበጡ ኃይሎች የአንድ ህዝብ ኑሮ መሻሻልና ነፃ መውጣት ጉዳይ እስከዚህም ድረስ የሚታያቸው አይደለም። እስከ 1966 ዓ. ም ድረስ የነበረው የአገራችን አስተሳሰብ ይህንን ይመስል ነበር ብሎ ከሞላ ጎደል መናገር ይቻላል። ከዚህ ስነነሳ ቀደም ብለው የተነሱት የመደብና የብሄረሰብ ጥያቄዎች የአገራችንን መሰረታዊ ችግሮች ያላገናዘቡ፣ የሳይንሰን መሰረተ- ሃሳብ ያልተከተሉ፣ በተለይም በጭንቅላት ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን ያላወጡና ያላወረዱ ነበሩ። በመሆኑም ዛሬም እንደትላንትናው ከዚህ ዐይነቱ አስተሳሰብ ባለመላቀቅ ያለንበትን ሁኔታ በመረዳትና ትግላችንን በሃሳብ ዙሪያ አሰባስበን ከመታገል ይልቅ ጊዜው እንዳያመልጠን በማለት ኃይልን በሚበታትንና የአገራችንንም ችግር በማይፈታ ላይ እንረባረባለን። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ዛሬ ስልጣን ላይ ያለውን ኃይል በጭፈጨፋው እንዲገፋበትና ስልጣኑንም እንዲያራዝምው እየረዳነው ነው። ይህንን መሰረት በማድረግ በምንም ዐይነት የአንድን ህብረተሰብ መፍታት የማይችለውን የብሄረሰብ ጥያቄ እየተባለ የሚወተወተውን ኢ- ሳይንሳዊ ጽንሰ- ሃሳብ ለማሳየት እሞክራለሁ። ከዚህም በመነሳት የአንድ ህዝብ መሰረታዊ ችግሮችና አትኩሮዎች የማህበረሰባዊ ችግሮች(The Social Question) መሆናቸውን ለማረጋገጥ እሞክራለሁ። ለመሆኑ ብሄር የሚባል ነገር አለ ወይ ? በመጀመሪያ አንድ ሰው ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ብሄረሰብ ከሚባለው ክፍል መወለዱ ተፈልጎና ተመርጦ አይደለም። አንድ ሰው እንደ ሰው ሆኖ ነው እንጂ የሚወለደው እንደ ብሄረሰብ ሆኖ አይደለም የሚወለደው። ስለሆነም የአንድ ሰው መለኪያው ልክ እንደማንኛውም ሌላ ሰው፣ ሰው መሆኑን የሚያረጋግጡ አካልና ልዩ ልዩ ባህርዮችን ያዘለው አዕምሮ ሲኖሩት ብቻ ነው። ሁለተኛ፣ የሰው ልጅውስጠ- ኃይል ስላለው አንድ ቦታ ረግቶ ስለማይኖር ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመጋባት ልጆች ይወልዳል። በዚህም የተነሳ በተለያዩ ብሄረሰብ እየተባሉ በሚጠሩ የሰው ልጆ ዘሮች ዘንድ በመጋባት የተነሳ አንድ ወጥ ባህል ሳይሆን ከተለያዩ ብሄረሰቦች ተጨምቆ የወጣ ባህል የሚሉት ነገርና በአንድ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን የሚያግባባ ቋንቁ ይፈጠራል። በሌላ አነገጋር፣ በአንድ አገር ውስጥ የተለያዩ ብሄረሰብ እየተባሉ የሚጠሩ ሰዎች ቢኖሩም ይህም ማለት በንጹህ መልክ አንተ ኦሮሞ ነህ፣ አንተኛው ደግሞ አማራ ነህ፣ አንቺ ኩሎ ኮንታ ነሽ እያሉ መናገር በፍጹም አይቻልም። አንድ ሰው የአንድን ብሄረሰብ ቋንቋ አቀላጥፎ በመናገሩ ብቻ አማራ ነው ወይም ኦሮሞ ነው የሚያስብለው አንዳች ነገር ሊኖር አይችልም። ስለሆነም አንደኛው አንድ አካባቢ በመወለዱና በማደጉ ብቻ ኦሮሞ ወይም ኩሎ ኮንታ እየተባለ እየተፈረጀበት፣ ከሌላው እሱን መሰል ከሆነው በእግዚአብሄር አምሳል ሆኖ ከተፈጠረው ወንድሙ ወይም እህቱ ጋር የሚያጣላው ምንም ምክንያት የለም። ወደ ታሪካዊ ሁኔታዎች ስንመጣና የአገራችንን ሁኔታ ስንመረምር፣ በተለይም ከአንደኛው ብሄረሰብ የተውጣጡ የገዢ መደቦች፣ ለመስፋፋት ሲሉ በሃይማኖትና እንዲያም ሲል በጦርነት አንዳንድ ግዛቶችን በመያዝና በቁጥጥራቸው ስር ካደረጓቸው የገዢ መደቦች ጋር በመጋባት ልዩ ዐይነት ህብረተሰብአዊ እምርታን ሊሰጡ ችለዋል። ስለሆነም አማራዎችን ይወክላል የሚባለው የገዢ መደብ በ 14 ኛው ክፍለ-ዘመን በመጀመሪያ ግዛቱን ለማስፋፋት ሲል የክርስትናን ሃይማኖት አስተማሪዎች በደቡቡ ክፍል በማሰማራት እዚያ ካሉት ብሄረሰብ ተብለው ከሚጠሩት ጋር በመጋባት በአካባቢው ልዩ ዐይነት ባህል ሊስፋፋና ሊዳብር ችሏል። በመሆኑም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ግዛትና የደቡቡን ክፍል በሚገዙት አምስት ንጉሳዊ አገዛዞች መሀከል የጠበቀ ግኑኝነት እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል። ይህ እንግዲህ ኦሮሞዎች ዛሬ ኦሮሚያ እያሉ የሚጠሩትን ግዛት ከመውረራቸው በፊት ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ኦሮሞዎች ከአንድ አካባቢ በመነሳትና ቀስ በቀስ አምስቱን የደቡቡን ንጉሳዊ አገዛዞች በመደምሰስ የራሳቸውን ግዛቶች ይመሰርታሉ። ቀድሞ የነበሩ የከተማና የመንደሮችን ስሞች በመቀየር ሌላ የኦሮምኛ መጠሪያ ስም ይሰጧቸዋል። ቀስ በቀስም ከከብት አርቢነት ወደ ተቀማጭ አራሽነትና መሬትንም በመቆጣጠር የገዢ መደብ ባህርይን ያዳብራሉ። ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሲያመሩ ደግሞ በዚያ አካባቢ ብዙ ጉዳት ካደረሱና ብዙ ህዝብ ከጨረሱ በኋላ ቀሰ በቀስ ከተቀረው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመጋባት እዚያ ለነበረው ባህል ልዩ እምርታን ይሰጡታል። ወደ ገዢ መደብነትም በመቀየር ታሪክን ሰሪ ለመሆን ችለዋል። በሌላ አነጋገር፣ ልክ እንደ ሌሎች አገሮች መዋጥና መዋዋጥ እንዳለ ሁሉና፣ አንደኛው ሌላውን አሸንፎ አንድ ትልቅ አገር ለመግዛት እንደፈለገ ሁሉ ይህም ዐይነቱ ታሪካዊ ግዴታና ድርጊት በኛ አገርም ተካሂዷል። የሚያሳዝነው ግን ከአንድ ብሄረሰብ የተውጣጡ ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች የራሳቸው ብሄረሰብ ሲስፋፋ ያደረሰውን በደልና ዝርፊያ ወደ ጎን በመተው እነሱ ብቻ ተጎጂዎች በመሆን ታሪክን በማጣመምና የማይሆን ነገር በማውራት ሰውን ለማሳመን ሲሞክሩ ስናይ እነዚህ ሰዎች የቱን ያህል የታሪክ ሂደትና የህብረተሰብ ዕድገት ያልገባቸው መሆኑን እንመለከታለን።ከ 20 ኛው ክፍለ- ዘመን ጀምሮ በአገራችን ምድር አዲስ የተፈጠረው ህብረተሰብአዊ ግኑኝነት ከካፒታሊዚም ጋር በጥብቅ የሚገናኝና የሚተሳሰር ነው። ውስን በሆነ መልክ የገባው ካፒታሊዝም የተወሰነ የህብረተሰብ ግኑኝነት እንዲፈጠር ቢያደርግም፣ በሌላ ወገን ደግሞ ባልተስተካከለ ዕድገት ምክንያት የተነሳ በአንድ አካባቢ የሚኖር የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ሳይሆን ከ 90% በላይ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል በድህነትና ኋላ- ቀር በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚኖር ነበር። ይሁንና ግን ይህ ዐይነቱ ያልተስተካከለ ዕድገት ከተሳሰተ የዘመናዊነት(modernization) አገባብና ሂደት ጋር የተያያዘ መሆኑ ቀርቶ የብሄረሰብ ጭቆናና የመደብ ችግር ተብሎ በመወሰዱ እንደዚህ ዐይነት የተሳሰተ ምሁራዊ ግንዛቤ ያላቸው አሉታዊ ኃይል(Negative Energy) ያላቸው ኃይሎች ብቅ እንዲሉና አለመረጋጋት እንዲኖርና፣ በተለይም በተወሰኑ አካባቢዎች ጦርነት እንዲስፋፋ በማድረግ የአገሪቱን አንድነትና ቀስ ብሎ በጥገናዊ መልክ የማደግ ዕድል መፈታተን ጀመሩ። ረጋ ካለና ጥልቅነት ካለው ምሁራዊ ጥናትና ውይይት ይልቅ በተወሰኑ ነገሮች ላይ ብቻ በማትኮር ማህበራዊና ህብረተሰብአዊ፣ እንዲሁም የሳይንስና የቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ትኩረት እንዳይሰጣቸው አደረጉ። የኢትዮጵያ ዋናው ችግር አገሪቱ የብሄረሰቦች እስር ቤት በመሆኗ ነው የሚለውን ኢ- ሳይንሳዊና ምሁራዊነት የሌለውን ተረት በማስፋፋት አንድ ህዝብ ታሪክን እንዳይሰራ አገዱት። የዛሬው በአገራችን ምድር ህዝባችንን የሚያሰቃየው ፋሺሽታዊ አገዛዝ ይህንን በተሳሳተ መልክ የተስፋፋውን ጽንስ- ሃሳብ በማራመድና የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲን በመጠቀም ነው አገራችንን የርስ በርስ ጦርነት አውድማ ለማድረግ የተቃረበው። የዛሬውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ መስፋፋትና መዳበር በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ የአገዛዙን መርበትበትና ቀስ በቀስም መሰርሰር የተገነዘቡ የመሰላቸው፣ በተለይም ማንም ሳይመርጣቸው የኦሮሞ ብሄረሰብ ተጠሪ ነን የሚሉ ኃይሎች የፖለቲካውን ሁኔታ በመጥለፍና (Highjack) ለራሳቸው የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ በማድረግ በወንድማማች ህዝብ መሀከል መተማመን እንዳይኖርና በዛሬው አረመኔያዊ አገዛዝ ላይ አንድ ላይ ተባብሮ አንዳይነሳ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠርን ወጣት እያሳሳቱና ስሜቱንም እያጋሉት ነው። በዚህ አካሄዳቸው ግን ጠቅላላውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጎዱ እንጂ የሚጠቅሙ አይደሉም። የድህነቱንናየኋላ- ቀርነት ዘመኑን ከማራዘም በስተቀር ምንም ፋይዳ ሊሰሩ አይችሉም። የሚፈልጉትንም ነፃነት ሊቀዳጁ በፍጹም አይችሉም።የአገራችን ችግር ማህበራዊና ኋላ- ቀርነት እንጂ የብሄረሰብ ጥያቄአይደለም! የአለፉትን 60 ዓመታት የአገራችንን የመንግስት አወቃቀርና ከዚህ የሚመነጨውን ፖሊሲ ለተከታተለ፣ ሶስቱም አገዛዞች በሳይንስ የተጠና፣ ፊሎሶፊንና ቲዎሪን መሰረት ያደረገ፣ አገራችንን ዘመናዊና፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት ሊያደርጋት የሚችል ፖሊሲ እንዳልነበራቸው መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም አንድ ህዝብ ኋላ- ቀር ከሆነ አኗኗር ስልት ተላቆ ምርታማነትን በማሳደግ ኑሮውን በማሻሻል ሰፋ ያለና ጠንከር ያለ ህብረተሰብ እንዲመሰርትና ተከታታይነት እንዲኖረው የወሰዱት ሳይንሳዊ ፖሊሲ በፍጹም የለም። በመሆኑም የአገራችንን ሁኔታና የህዝባችንን ፍላጎት ያላገናዘበና፣ የተከታታዩንም ትውልድ እጣ ቁጥር ውስጥ ያላስገባ በውጭ ኃይሎች የተነደፈ ወይንም ሳያወጡ ሳያወርዱ ተግባራዊ የሆነ ፖሊሲ በአገራችን ምድር በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብአዊ ሀብት እንዳይፈጠር አድርጓል። አንድ አገር ያላትን ተፈጥሮአዊ ሀብት በስነስርዓት መጠቀም የማይችልና ድህነትን ለመቅረፍ ቀን ከሌሊት ደፋ የማይል አገዛዝ በመሰረቱ ጥሎ የሚያልፈው ያልተረጋጋና በሆነው ባልሆነው የሚናቆር ህዝብ ነው። እንደዚህ ዐይነቱ በሰፊ የኢኮኖሚና የማህበረሰብአዊ መሰረት ላይ ያልተገነባ አገር ደግሞ መጥፎ ህልም ለሚያልሙ ትንሽ ተማርን ለሚሉ የውስጥ ኃይሎችና፣ የአገራችንን መዳከምና እንዲያም ሲል መበታተን ለሚፈልጉ ኃይሎች ቀዳዳ መስጠቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ስለሆነም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የብሄረሰብን ጥያቄ አንግቦ ነፃ እወጣለሁ ያለ ኢትዮጵያዊ ኃይል በሙሉ በህዝባችንና በአገራችን ላይ ጦርነት ያወጀው በውጭ የስለላ ኃይሎችና በአካባቢው የሚገኙ የአገራችንን መጠናከርና መረጋጋት በማይፈልጉ አጎራባች አገሮች በመታገዝ ነው። እነዚህ የውስጥ የነፃነት አራማጅ ኃይሎች ነን የሚሉ በራሳቸው ላይ አጉል ዝቅተኛ ስሜት በማሳደርና ወጣቱን በመቀስቀስና አመፀኛ እንዲሆን በማድረግ እንዳየነውና እንደቀመስነው ለብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ሰው ህይወት መጥፋትና፣ አገራችንም አሁን ባለችበት ሁኔታ መገኘት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክተዋል። በጆሮ ደግፍ ላይ ቆረቆር ተጨምሮበት እንደሚሉት አነጋገር፣ ሌሎችም ከብሄረሰብ ጋር ያልተያያዙ ኃይሎች የውጭ የስለላ ኃይሎች የሚሰጧቸውን ምክርና የገንዘብ ድጋፍ ተገን በማድረግ አገራችንን ከውስጥ ሆነው በፊዩዳላዊ ተንኮል ቦርብረው አዳክመዋታል። እነዚህ ኃይሎች በተለይም ቀደም ብለው ከነበሩት የገዢው መደቦች ጋር በጥብቅ የተሳሰሩና ዝምድናም የነበራቸው ሲሆኑ፣ ዋናው ዓላማቸው በተለይም ኢትዮጵያ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆን ጠንካራ አገርና ህብረተሰብ እንዳትመሰርት ማድረግ ነው። በዚህ ዐይነቱ እርኩስ ተግባርም የማርክሲዝምን አርማ አንግቦ እታገላለሁ ይል የነበረው ኃይል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የአገራችንን ውድቀት አፋጥኗል ማለት ይቻላል። ወደ ዋናው ቁም ነገር ስንመለስ፣ በተለይም እንደነ ጃዋር የመሳሰሉት አዳዲስ የፖለቲካ ተዋናይ ነን ብለው የፖለቲካን ትርጉም ሳይረዱ የተሰጣቸውን የሚዲያ ዕድል በመጠቀም የሚያስፋፉት ቅጥ ያጣና የተዘበራረቀ ልፍለፋ የፖለቲካውን ትግል እያዘበራረቀውና አብዛኛውንም ህዝብ ግራ እያጋባው እንደመጣ እንመለከታለን። ጃዋርና ተከታዮችም ሆነ በዳውድ የሚመራው የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅት የብሄረሰብን ጥያቄና ነፃነት ማግኘት አለብን የሚለውን ከማራገብና ህዝብን ከማወናበድ በስተቀር፣ ይህ ነው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲያችን ብለው ሲያስተምሩና ሲከራከሩ በፍጹም አይታዩም። በመሰረቱ ሳይንስን፣ ፍልስፍናንና ቲዎሪን መሰረት አድርጎ የማይካሄድ ትግል ወደ ፋሺዝም ነው የሚያመራን። እንደሚባለው፣ እንዳየነውና በታሪክም እንደተረጋገጠው በብሄረሰብ ላይ የተመረኮዘ ናሺናሊዝም የመጨረሻ መጨረሻ ዘረኛና ሌላውን በመጥላት ቀስ በቀስ ደግሞ ወደ ፋሺዝም የሚያመራ አካሄድ ነው። ሂትለር ለጀርመን ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉትን አይሁዲዎችን በመጥላትና ዝቅተኛ ስሜትም ስላደረበት ነው ዘመቻ ያደረገባቸውና የመጨረሻ መጨረሻም ለስድስት ሚሊዮን ሰዎች ማለቅ ምክንያት የሆነውን ሆለኮስት የሚባለውን ዘግናኝ ድርጊት የፈጸመው። እነ ሻቢያና ህወአት የሚባሉትም የዛሬው ገዢዎች በአጀማመራቸው የማርክሲዝምን አርማ ይዘው ቢነሱም ዋናውዓላማቸው የአማራውን ህዝብ ቅስም ለመስበርና እነሱ በጭንቅላታቸው ውስጥ የቀረጹትን የአማራውንንና የኦርቶዶክስን ሃይማኖት የበላይነት ማዳከምና የራሳቸው የበላይነት ለማረጋገጥ ነው። ድርጊታቸው ከፋሺዝም የሚያንስ አይደለም ማለት ነው። በአገራችን ምድር እስካሁን ድረስ የተካሄዱት ትግሎች በሙሉ ራሳችንን የሚያዳክሙ እንጂ ለማንም የሚጠቅሙ አይደሉም። የታሪክን ሂደትና የህብረተሰብን ዕድገት፣ ከዚህም በላይ ደግሞ በአንድ አገር ውስጥ ያለን ምሁራዊ ድክመትና፣ ጠለቅና ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ አለመኖር ያላገናዘቡ በመሆናቸው ርስ በራሳችን እንድንፋተግ ተደርገናል። የድንቁርናችን ሰለባ በመሆን ተባብሮና ተቻችሎ ታሪክን ከመስራት ይልቅ የውጭ ኃይሎች ተጠሪና ተመካሪ በመሆን የአገራችንን ውድቀትና መበታተን እያፋጠን እንገኛለን። የተማርነው ትምህርት ሁሉ ጭንቅላታችንን አንጾት የተቀደሰ ተግባር ከመስራት ይልቅ መጥፎ ነገር እንደተማርን ይመስል በክፉኛ መቀናናትና መጠላላት በመወጠር መስራት ያለብንን ነገር እንዳንሰራ ታግደናል። ይህ ዐይነቱ ታሪክን ያላገናዘበ ትግል ግን አንድ ቦታ ላይ መገታት አለበት። እያንዳንዱ ምሁር ራሱን በራሱ በማግኘት ታሪክ ሰሪነቱንም የሚያረጋግጥ መሆን አለበት እንጂ የአገራችንን ውድቀት ለማፋጠን ከውጭ ኃይሎች ጋር መስራት የለብትም። ርስ በርስ መመካከርና ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጥ እንጂ ከውጭ ኃይሎች ምንም ዐይነት ምክር የሚጠይቅበት ምክንያት የለውም። ለኦሮምያ ቻርተር አውጭዎች የመጨረሻ ጥሪዬ፣ በኢትዮጵያ ምድር ታሪክን ልትሰሩ የምትችሉት በዚህ ዐይነቱ አካሄድ ሳይሆን፣ ከሌላው ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ጋር በመመካከርና ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥ ብቻ ነው። ዓላማችንም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚስማምና ተደላድሎና ተከባብሮ ለመኖር የሚያስችለውን አገር መገንባት ብቻ ነው። ስለሆነም የብሄረሰብና የሃይማኖት ጥያቄዎች የህብረተሰብ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ አይደሉም። የአንድ ህብረተሰብ ችግር በሳይንስና በቴክኖሎጂ አማካይነት ብቻ ነው ሊፈታ የሚችለው። የንጹህ ውሃ፣ በቂ ዳይትን የሚሰጥ ምግብ፣ በደንብ የተሰራ መጠለያ፣ ህክምናና ጭንቅላትን ክፍት የሚያደርግና፣ ሰው መሆናችንን እንድንገነዘብ የሚያደርገው ሁለ- ገብ ትምህርት የጠቅላላው ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄዎች ናቸው። እነዚህን ለመሳሰሉት ጥያቄዎችና የህዝብ ፍላጎቶች መልስ መስጠት የምንችለው በተናጠል በመታገልና የራሴ አጀንዳ አለኝ በማለት ሳይሆን፣ በአንድ የአስተሳሰብ ዙሪያ ስንሰባሰብ ብቻ ነው። ዛሬ ሰለጠኑ የሚባሉ አገሮች ቀናውን መንገድ በመከተልና በመደማመጥ ብቻ ነው ለማደግና ዓለምን በሳይንሳና በቴክኖሎጂ ለመቆጣጠር የቻሉት። ስለዚህም ወዲህና ወዲያ ከመሯሯጣችን በፊት እስቲ አንድ ጊዜ ተቅምጠን የምንሰራውን ስራ ሁሉ እናሰላስል። አስተሳሰባችንን በሙሉ በሳይንስና በቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በፊሎሶፊ ዙሪያ እናድርገው። ለብሄረሰብ ሳይሆን ለነዚህ ነገሮች ቅድሚያ እንስጣቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፅንፈኝነት አደጋ (ከአንተነህ መርዕድ)

ፈቃዱ በቀለ fekadubekele@gmx.de

2 Comments

  1. This article is nothing but a rubbish. As Mohammed Abbasonce said, “Keep your Ethiopia and Ethiopianism in a museum.”

    The Oromo migration narration is a flat lie. There are people right now preparing themselves from the north to live in Oromo, Sidama, Konso Benishangul, Gambella…etc. areas. This trend has been for so many year.O be of the reasons for the migration of the north to the south is the resources are in the south. The weather is nice,too. We don’t see people from Oromia, Sidama, Konso, Gambella and Benishangul migrating to the north in search of land.

    If you go to Sudan, Yemen, Nigeria, Mexico and other countries the same is true – people from the north flock to the south. In Sudan, the northerns used to rule and control the resource in the south until the Southern Sudan separated in 2011. The same is true in Nigeria, Yeman and Mexico. In many parts of the world the resources are located in the south, and that is why people flock to south. The Oromo, however, portrayed in Ethiopian history as if they had migrated to the north. This narration has no a scintilla of truth. The truth is the opposite.

    The other evidence is the Afar ethnic lives in the northeast of Ethiopia. Agrews and Qimants live in the north. All these ethnic groups are Cushites ,and they are very close to the Oromo people linguistically and culturally. No historian, however, called them as migrants. It is logical to see the Oromo people next Afar and Ages and Qimants. Why the Oromoon referred as aliens or immigrants?

    The Oromo migration has never been in the Ethiopian Empire.In fact, the migration is from north to the south. The Oromo people are as old as the mountains, rivers, hills, valleys and fields Oromia. Our Waqayyoo has created us where we are living today. The narration of our enemy about Oromo people stems from fear of being dominated.

    • It is fact that Oromo (otherwise known differently by other name the first time IN WRITTEN HISTORY) is done by Abba Bahrey.
      Abba Bahrey is the primary reference for all other subsequent writers and historians (Arabs, Whites, etc..).
      With out knowing Abba Bahreys work or skipping his work, there is no way other historians would know about Oromo. This is very important.

      Secondly, it is undeniable fact there has been Oromo tribe. But the very first recorded history about Oromo started with Abba Bahrey. This you should accept it.

      It is fact a pastoral way of life would not allow to settle at one place to cultivate the land, build a civil way of life or engage in some related sedentary way of life primarily in farming. Because by the virtue of being a pastoralist you have to move with your family along with your huge number of cattle from place to place to find the next grazing area day after day. As a result there is no any opportunity for your family to sit down and cultivate your surroundings or engage with some form of crafting, writings and readings. Even today the nomads are the living evidence.

Comments are closed.

Share