ፈተናን መስረቅ ለስብሃት ነጋ ትግል ለሌላው ወንጀል ያደረገው ማነው?

የአገራችን የሰሞኑ አብይ ፖለቲካ መነጋገሪያ

<<የ12ተኛ ብሔራዊ ፈተና አስቀድሞ ተሰርቆ መውጣት>> እና ተያይዞ የመጣው የስርዓቱ የተለመደ አስቂኝ መግለጫ ነው። <<ፈተና አልተሰረቀም ፣ፈተናው ተሰርቋል>>

የሚሉት መግለጫዎች በእርግጥም አገሪቱን የሚመሯትን ሰዎች አቅም ጭምር ያጋለጠ ነው። የፈተናውን መሰረቅ የትግል አካል አድርገው ላልቆጠሩ የሚያቀርቡት መከራከሪያ የተምታታ ነው። ፈተናውን መስረቅ እንደ ትግል ስትራቴጂ ለቆጠሩት ብቻ ሳይሆን ውለው አድረው ለገባቸውም ድርጊቱ ውጤታማ አንዱ የሰላማዊ ትግል ስልት አካል ነው። አገር ተጎዳ የአገር ሀብት ወደመ የሚሉት ይሄ በጥቅል የሚቀርቡ ጉንጭ አልፋ መከራከሪያዎች ለሞኑ የአገር ሀብት የሚባክነው በነማን ነው የሚል ጥያቄ ራሳቸውን እንዲጠይቁ የሚያስገድድ ነው።። ስብሃት ነጋ በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ታጋይነታቸውን ሲዘክሩ በረሃ ከመውረዳቸው በፊት የትምህርት ቤት ዳይሬክተር እያሉ የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ሰርቀው፤ መልስ ተዘጋጅቶ የትግራይ ተማሪዎችን መጥቀማቸውን የተናገሩትን አንረሳም።

ያኔ ስብሃትን ሲያሞግሱ የነበሩ የስርዓቱ ደጋፊዎች ዛሬ ስድስት ወር ሙሉ መከራቸውን ሲያዩና በባዶ እጃቸው ስለተቃወሙ ፍዳ ሲበሉ ለነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ፈተና ስላልተራዘመ ለጉልበት ውሳኔ የተሰጠውን የአጸፋ ምላሽ ከትግል አለመቁጠር ያስተዛዝባል።ቤተሰብ ይጎዳል፣የተማሪዎች ሞራል እና የመሳሰለው ጉዳይ ማንሳቱ ባይከፋም የዚህ ሁሉ መዘዝ ግን ስልጣን በጠመንጃ ይዘው እኛ ያልነው ካልሆነ ለሚሉት እምቢኝ በቃን ማለት የታየበት ግልጽ እርምጃ ነው። ዛሬም ሲደናበሩ የተሰረቀውን ፈተና በሮመዳን ጾም ፍቺ ወቅት ማድረግ ያው የተለመደው እብሪት ነው። በጨዋ ቋንቋ የቀረበላቸው ግልጽ ደብዳቤ ነገ ሌላ ጫጫታ ከማምጣቱ በፊት ቆም ብለው እንዲያስቡ ይጠይቃል። የኦሮሞ ሰላማዊ ተቃውሞ አራማጆች ተከታዩን ግልጽ ደብዳቤ ጽፈዋል። ልብ ያለው ልብ ይበል ነው። እነ ለአገር ተቆርቋሪዎች አሁን ለመንግስታችሁ ጮክ ብላጭሁ ይህቺን ደብዳቤ አንብቡለት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  39ኛ የካቲት ለማክበር ሽርጉድ እና የተሟጠጠው የትግራይ ህዝብ ስሜት

ለክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

ጉዳዩ: የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና (EUEE) በተመለከተ ፍትሃዊ የሆነ የመርሃግብር ምክረ ሃሳብ (program proposal) ስለማቅረብ ይመለከታል።

የተሰረዘውን ፈተና በተመለከተ መስሪያ ቤትዎ ያወጣውን መርሀ ግብር ተመልክተነዋል። ሆኖም ግን መርሃግብሩ ከታች በተገለጹት ምክኒያቶች ሊሻሻል ይገባዋል ብለን ስለምናምን የሚከትለውን ምክረ-ሀሳብ ልናቀርብ እንወዳለን። በደንብ ሊጤን የሚገባው ነጥብ ይህንን ምክረ-ሀሳብ በማጥናቀር ሂደት ውስጥ ከ5000 በላይ ተማሪዎች በግልጽ በሶሻል ሚዲያ ሀሰባቸውን ሰጥውበታል። 123 መምህራንን ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች በቀጥታ አማክረናል። ተማሪዎቹም ሆኑ መምህራን በዋናው ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም አንጸባርቀዋል። የተማሪዎቹም ሆነ የመምህራኑ ሀሳብ የሚያመለክተው በመስሪያ ቤትዎ ለድጋሚ ፈተናው የተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ በቂ አለመሆኑንና ጊዜውን ማራዘሙ ግዴታ ነው የሚል ነው። አብዛኛዎቹ የኦሮሚያ ተማሪዎች (80%) ያመለጥንን የ6 ወራት ትምህርት ለማካካስ እና ለፈተናው ለመዘጋጀት ቢያንስ 12 ሳምንታት ወይም 3 ወራት ያስፈልግናል ብለዋል።

እንደአዲስ የወጣው የፈተና መርሀ ግብር ከጊዜ ማጠር በተጨማሪም ሌላ ግድፈት እንደለው ከተማሪዎች እና መምህራኖች ጋር ባደርግነው ምክክር ተገንዝበናል። ይሄውም መርሃግብሩ በረሞዳን ጾም ወር መጨረሻ ላይ መሆኑ በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ትክክል አንዳልሆነ ተረድተና።

1) ሳይንሱም እንደሚያረጋግጠው የሰው ጭንቅላት (brain) በፈተና ጊዜ በደንብ ለማሰብ ከፍተኛ የምግብ ሃይል አቅርቦት (high energy supply) ይጠቀማል። የጾም ወቅት ደግሞ የጿሚዎቹ ጭንቅላት ባንጻራዊ መልኩ ሃይል-አጠር (hypo) ስለሚሆን ጿሚ ተማሪዎችን በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች ለዛውም ሙሉ ቀን ረጃጅም ፈተናዎች ላይ እንዲቀመጡ ማድረግ አይመከርም። በተለይ ደግሞ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ሆኖ የሚጾሙና የማይጾሙ ተማሪዎች የሚወስዷቸውን ፈተናዎች በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች መስጠት ትክክል አይደለም ። ግልጽ የሆነ መድሎ (clear discrimination) የማድረግ ያህልም ሊቆጠር የሚችል፤ ማህበራዊ መተሳሰብን ብሎም ህገ-መንግስቱን የሚጥስ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደመቀ መኮንን: ልምድ ያለው ውሸታም

2) በድጋሚ ባወጠችሁት መግለጫም ፈተናው የኢድ አልፈጥርን ቀን እንደሚዘል ገልጻችኋል። ይህ ማለት በኢድ ዋዜማ እና በማግስቱ ፈተና ይኖራል ማለት ነው። በማህበረሰባችን የበዓላት ሰሞን በግርግርና ለፈተና ትኩረት ፍጹም በማይመቹ (exam mood eroding) ማህበራዊና ቤተሰባዊ መስተጋብሮችና ፌሽታዎች የተሞላ መሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው። ይህ ደግሞ ተረጋግቶ ለማጥናት የሚያስቸግር ከባባዊ ሁኔታ (distractive environment) በመፍጠር ተማሪዎች ለፈተናው ሙሉ ትኩረት እንዳይሰጡ ያደርጋቸዋል። እናም ፈተናን በእንደዚህ ዓይነት ትልቅ ዓመት በዓል ወቅት ማድረግ ለሃይማኖቱ ተከታይ ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚኖረው ግልጽ ግልፅ ነው።

የምናቀርበው ምክረ-ሃሳብ በተማሪዎቹ ምቾትና አስተያየት ላይ ብቻ በመመርኮዝ እንዳይሆን ሌሎች ባለ ድርሻዎችንም አማክረናል። አዲሱ ፈተና ተዘጋጅቶ፣ ታርሞ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ያለውን ሂደት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ከዚህ በፊትና አሁንም በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በፈተና ጉዳዮች ላይ የሰሩ ባለሟያዎችን አማክረናል። እንዲሁም ፈተናው የዩኒቨርሲቲዎችን የሚቀጥለውን አመት መርሀግብር ሊያውክ ስለሚችል ፕረዚደንቶችን ጨምሮ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞችን አማክረናል።

ስለሆነም ከዚህ በላይ ከገለጽናቸው ምክኒያቶችና ባሰባሰብናችው ሙያዊ አስተያየቶች ላይ ተመርኩዘን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የመረሃግብር ምክረ ሃሳቦችን እናቀርባለን። ለተፈጻሚነታቸውም ከእርሶ መስሪያ ቤት በኩል በጎ ምላሽ እንደሚኖር ተስፋ እናደርጋለን:

1) ለተማሪዎቹ ሁለት ወር ቢሰጣቸው እና ፈተናው ከሃምሌ 25 እስከ 28 ወይም ከዚህ ጊዜ በኋላ በሚመቻቹ ወቅት ቢሆን ፍትሃዊ ይሆናል።

2) ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ ተማሪዎች በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከዚህ ቀደም ያስረከቧቸው መጽሃፍትና ሌሎች የጥናት መርጃ መሳሪያዎች ቢመለስላቸው ጥሩ ይሆናል።

 

3) በተለይም በኦሮሚያ ተማሪዎች ላልተማሯቸው ክፍለጊዜዎች መምህራኑ ማካካሻ (make up classes) እንዲሰጧቸው ማድረግ ያስፈልጋል። ክረምቱ የእረፍት ጊዜያቸው መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ለመምህራኑ ማበረታቻ (incentives) የሚደረግበት መንገድ ቢዘጋጅ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  [በአባይ ግድብ ዙሪያ የተጻፈ አጭር ሀተታ]ትንሹዋ ወያኔና ትልቁ ወያኔ አላኖሩኝም

4) ጊዜው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለእረፍት ወደ ቤታቸው የሚመለሱበት በመሆኑ እነዚ ተማሪዎችም የየኣካባቢዎቻቸውን ተፈታኝ ተማሪዎች በቱቶር ማስጠናት ወይም በሌሎች መንገዶች ለፈተናው ዝግጅት ይረዷቸው ዘንድ የማበረታቻ መንገዶች ቢመቻቹ።

5) ለክረምቱ ወደየትውልድ ቦታቸው የሚመልሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተፈታኞቹ የማስጠናት (tutorial) ድጋፍ እንዲሰጡ ትምህርት ቤቶች እና የአስተዳደር ክፍሎች ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ማድረግ።

6 ) በተለይም በኦሮሚያ አካባቢ በፖሊስና በመከላከያ ሃይሎች በተማሪዎች ላይ የሚደረገው ወከባና ተጽዕኖ እንዲቆም፣ እነዚ የታጠቁ አካላት ከትምህርት ቤቶች አካባቢ እንዲርቁ፣ የታሰሩ ተማሪዎችም ተለቀው ከላይ በተጠለተው መልኩ ለፈተናው ዝግጅት እንዲጀምሩ ቢደረግ።

በመጨረሻም፣ ከዚህ በፊት የወሰድናቸው እርምጃዎችም ሆኑ አሁን ያቀረብነው ምክረሃሳብ መነሻነቱ ፍትሃዊነት፣ የእኩል እድል ተጠቃሚነት እንዲሁም የተወዳዳሪነት መርህን የተከተለ የፈተና ስርዓት በሃገሪቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ እንደሆነም ደግመን መግለጽ እንወዳለን። ለዚህም ከኛ በኩል ያለውን መልካም ፈቃድ (good faith) ይበልጥ ለማረጋገጥ በእጃችን ያሉትን ሌሎቹን የፈተና ቡክሌቶች ሚስጥራዊነት እንደምንጥብቅና አዲስ ለምታዘጋጁት ፈተናዎች ሚስጥራዊነት መጠበቅም የበኩላችንን አስተዋጽዕ እንደምናደርግ ቃል እንገባለን። ያቀረብነውን ምክረሀሰብ በሚገባ አጢናችሁ በበኩላችሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለጉዳዮች አማክራችሁ ፍትሃዊ ውሳኔ ላይ እንደምትደርሱ ተስፋ እናደርጋለን። ነገር ግን አሁን ያቀረብነው ምክረሀሳብ ወደጎን ተትቶ፣ እንደክዚህ በፊቱ የኦሮሚያ ተማሪዎች እሮሮ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ ፍርደገምድል በሆነ መልኩ አሁን የተቀመጠውን የፈተና መርሃ ግብር ወደ ማስፈጸም የምትሄዱ ከሆነ በእርግጥኝነት ለሚደርሰው ዳግም ሀገርዊ ኪሳራ ተጠያቂነቱ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን ከወዲሁ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን።

ከሰላምታ ጋር!

#‎OromoProtests

6 Comments

  1. Ethiopia was one of the proud nations in the World.however this nation ruled by shifta that called itself government more than 25 years.they destroy the unity of the people,steal the country resource’s money from national bank around 25 billions birr as a reporter disclose,steal the Gold resreve by changing fake golden metals,steal sugar factory money 750 million,stealing document from federation office,stealing 88 condimnum. So at the end if get a price sold all Ethiopian land and people together.so who can believe this government if he talks about exam.no one believe about woyane bother about education.please rise up against shifta.

  2. there should be a major correction to this article. Sebhat Nega a.k.a the master of devil banda, intentionally stole the matriculation exam papers during the 60’s and distributed to his ‘Negiste Saba’ (the one and only high school of Adwa) students ONLY, particularly and purposely. Not to students of TIGRAY entirely. His intention was a banda PR as usual that to mislead the general public with his factious banda story that ‘students from Adwa are smarter than the rest of tigrians and other ethiopians in general). History shows that students during that time from mekelle and rest of tigray were opposing and against that evil bandas misbehavior.

    death to the Adwa bandas
    long live ethiopia

  3. There is nothing wrong with this action of postponing the exam. TPLF doesn’t care about Oromo people nor other Ethiopians. Over z last 25 years we have witnessed a lot of crimes committed by this group. The consequences of some of z crimes will affect z country for generation.
    TPLF’s agenda, i.e. controlling z economy, providing high level of education for selected group and attaining political dominance is already achieved. For the majority of Ethiopians it is time to make critical decision now- either to accept the capitalist system TPLF designed and live under slavery or strengthen the fight and retake the resource from TPLF for Ethiopia’s benefit.

Comments are closed.

Share