ወያኔና ትግሬ | መስፍን ወልደ ማርያም

ሚያዝያ 2008

አዳም በበደለ መድኃኔ ዓለም ካሠ፤ የተጠቀሰውን አባባል የማያውቅ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፤ ለእስላሞችም ቢሆን አዲስ ነገር አይሆንባቸውም፤ አዳም ትእዛዝ ጥሶ ዕጸ በለስን በላና ተረግሞ ከገነት ወጣ፤ አዳም በደለ የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፤ አዳም በገነት ባካሄደው አብዮት የተነሣ የሰው ልጆች ሁሉ ከገነት እንደወጡ የሚቀሩ ሆነ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አዘነ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወረደና ከድንግል ማርያም ተወለደ፤ እግዚአብሔር ይህንን በማድረጉ ሰዎች ከአዳም የወረሱት የጅምላ ኃጢአት ተሻረ፤ ከዚያ በኋላ ኃጢአት የግል እንጂ የጅምላ መሆኑ ቀረ፤ ይህ የሆነው መድኃኔ ዓለም የሰው ልጅን ከራሱ ጥፋት ለማዳን በመሰቀሉ ነው፤ ሃይማኖት ለመስበክ ሳይሆን የጅምላ አስተሳሰብ ቀና እንዳልሆነ እግዚአብሔር እንዳስተማረን ለማመልከት ነው፤ በዚህም መሠረት ፍትሐ ነገሥት ልጅ በአባቱ ወንጀል አይጠየቅም፤ አባቱም በልጁ ወንጀል አይጠየቅም ይላል፤ በአስተሳሰብና በፍትሕ ጉዳይ የሰው ልጅን የእድገት በር የከፈተው ይህ ነው፤ እያንዳንዱ ሰው የሚመዘነውና የሚፈረድለት ወይም የሚፈረድበት እሱው ራሱ በሠራው ነው፤ ይህ ቁም-ነገር ዛሬ በሠለጠኑ አገሮች ሁሉ ሕግ ሆኖ የሚሠራበት ነው፤ ወደማኅበረሰብ ደረጃ ሲወርድ ቁም-ነገሩ ሰፊውን ሕዝብ አዳርሷል ለማለት ያስቸግራል።
ከላይ እንደመግቢያ ያቀረብሁት አስተያየት ከወያኔ ጎሠኛ አስተዳደር ጋር ተያይዞ የመጣ አንድ የአስተሳሰብ ግድፈትን ቢቻል ለማረም ነው፤ ይህ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ግድፈት በአጠቃላይ የሰው ልጅን ሁሉ የሚመለከት ቢሆንም ኋላ-ቀሮችን ይበልጥ ያጠቃል፤ በተለይ ደግሞ በአንዳንድ ልዩነቶች ላይ ጎልቶ ይታያል፤ ለምሳሌ ወንዶች ሁሉ ስለሴቶች ያላቸው የተዛባ አመለካከት ከአካላዊ ልዩነት ተነሥቶ አእምሮንና መንፈስንም ጨምሮ ሴቶችን ከወንዶች በታች ያደርጋል፤ ዛሬ ሴቶች ያልገቡበትና ያልተደነቁበት ሙያ ባይኖርም አንዳንድ ወንዶች አሁንም አሮጌ አስተሳሰብን ይዘው የቀሩ አሉ፤ እንዲሁም ስለጥቁሮች ያረጀ አስተሳሰብ ይዘው የቀሩ ነጮች አሉ፤ ክርስቲያኖችም፣ እስላሞችም እንዲሁ፤ በእውቀት ዓለም አጠቃላይ ወይም የጅምላ አስተሳሰብ የሚፈቀድበት ጊዜ አለ፤ ይህ የሚሆነው ተጨንቀው፣ ተጠብበው፣ ብዙ ፈተናዎችን አልፈው ነው ወደማጠቃለያው የሚደርሱት፤ ሁለት ነጫጭ ውሻዎችን ያየ ሰው፣ ሁለት ነጫጭ ውሾች አየሁ ቢል እንቀበለዋለን፤ ነገር ግን ውሾች ሁሉ ነጫጭ ናቸው ወደሚል ማጠቃለያ ቢደርስ የከረረ ሙግት ይነሣል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትውልድ የማድን ሃላፊነት የማን ነው? በይበልጣል ጋሹ

የቀለም ልዩነት ባለበት አገር ሁሉ ቀለም ለአስተሳሰብ ግድፈት መነሻ ይሆናል፤ ነጮች ጥቁሮችን ይንቃሉ፤ የሚንቁት አንድ ደደብ፣ ወይም አስቀያሚ፣ ወይም ባለጌ … ሆኖ ያገኙትንና የሚያውቁትን አንድ ጥቁር ሰው አይደለም፤ እንዲሁ ሾላ በድፍን አይተውት የማያውቁትን ጥቁር ሰው ሁሉ ያለምንም ሚዛን በአንድ ከረጢት ውስጥ ጨምረው ነው፤ እውነትን ለሚፈልግ በአውቀት መለኪያ ከብዙ ነጮች የሚበልጡ ጥቁሮች ይኖራሉና ጥቁሮችን በጅምላ ደደብ ማለት ልክ አይደለም፤ በውበት መለኪያም ቢሆን ያው ነው፤ በሌላ በማናቸውም ነገር ቢሆን የጅምላ ሳይንሳዊ ፈተናዎቹን ያላለፈ የጅምላ አስተሳሰብ ቁም ነገርን ያበላሻል፤ እንዲህ ያለው የአስተሳሰብ ግድፈት የሚያቀራርብና የሚያሳድግ አይደለም፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደርግና ወያኔ የእውቀትን ደረጃ ሰባብረው ጉልበትን የደረጃ መለኪያ በማድረጋቸው የአስተሳሰብ ግድፈት እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ነው፤ መነሻው ጥላቻ ነው፤ ወያኔ ጥላቻን በስልቻ ቋጥሮ አመጣና በኢትዮጵያ ላይ ዘራው፤ የማሰብ ችግር ስላለ የተዘራው ጥላቻ ፊቱን አዙሮ ወደራሱ ወደወያኔም እንደሚደርስ አልተገነዘበም ነበር።

አሁን ብዙ ሰዎች የወያኔ የአእምሮ ሕመም ተጋብቶባቸው ትግሬዎችን በሙሉ ወያኔ በማድረግ ያላቸውን ጥላቻ በመረረ ቋንቋ ይገልጻሉ፤ በቅርቡ አንድ ሰው ይህንኑ እኔ በሽታ የምለውን ስሜት በፌስቡክ ላይ ገለጠና የሚከተለውን ሀሳብ ጫረብኝ፤

የእኔ አመለካከት እንደሚከተለው ነው፤ ትግሬን የማየው በሁለት ከፍዬ ነው፡– ወያኔ የሆኑ ትግሬዎችና ወያኔ ያልሆኑ ትግሬዎች፣ ወያኔን ደግሞ እንደገና ቢያንስ ለሁለት እከፍለዋለሁ፡– ዘርፎ የከበረ ወያኔና ደሀ ወያኔ፤ ዓይኖቹን ከፍቶ ደሀ ወያኔዎችን ማየት ያልቻለ ሰው ከአለ እኔ ለማሳየት ዝግጁ ነኝ፤ ጥቅም ያቅበዘበዘው ወያኔ ዘራፊው ነው፤ ግን ሲዘርፍ ያልዘረፈውን ወያኔ መሣሪያ አድርጎ ነው፤ ለምሳሌ በማእከላዊና በቃሊቲ ያሉ ጠባቂዎች ወያኔዎች የዘራፊዎቹ መሣሪያዎች ናቸው፤ ከተዘረፈው ሲንጠባጠብ ይለቅሙ ይሆናል እንጂ እነሱ መናጢ ደሀ ናቸው፤ የዘረፉ ወያኔዎች በመቀሌ ሕዝቡ ‹‹የሙስና ሰፈር›› ብሎ የሰየመውን የሀብታሞች መንደር ሠርተዋል፤ በአዲስ አበባም ‹‹መቀሌ›› ተብሎ የተሰየመውን የሰማይ-ጠቀስ ፎቆች መንደር ሠርተዋል፤ በሻንጣ የአሜሪካን ብር ወደውጭ ይልካሉ፤ ሌላም ብዙ አለ፤ እነዚህ በዘረፋ ሀብታም የሆኑ ወያኔዎች ረዳት መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙባቸው ሌሎች ደሀ ወያኔዎች እንዳሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ የተባረሩም ወያኔዎች እንዳሉ አውቃለሁ፤ የተባረሩበትንም ምክንያት አውቃለሁ፤ ወደመቀሌ የሚሄዱበት የአውቶቡስ መሳፈሪያም የሰጠኋቸው ነበሩ፤ ለሚያምኑኝ ሰዎች እነዚህን መረጃዎች የምሰጠው ለመመጻደቅ አይደለም፤ እውነቱን እንዲረዱልኝ ነው፤ እውነትን ለማየት የሚችሉ ሰዎች እንዳይሳሳቱ ለመርዳት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲስ ጉዳይ መጽሔት፡ ማኅበራዊ ሚዲያ ፕሬሱን እየተካ ይሆን?

ስለወያኔ ግፈኛነት፣ ዘራፊነትና ጭካኔ ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ ያላልሁት ያለ አይመስለኝም፤ ነገር ግን እንኳን ትግሬን በጅምላና ወያኔንም በጅምላ ለመኮነንና ለመርገም የአእምሮ ብቃትም ሆነ የኅሊና ጽዳት ያለው ሰው የለም፤ የወያኔን ፍርደ-ገምድልነት የሚጠላ በፍርደ-ገምድልነት በትግሬ ሁሉ ላይ አይፈርድም፤ ጥላቻ ኅሊናን ያቆሽሻል፤ ጥላቻ አእምሮን ያሰናክላል፤ ጥላቻ ወደኋላ እንጂ ወደፊት የማየትን ችሎታ ይጋርዳል፤ ጥላቻ በተለይ በማቆጥቆጥ ላይ ያለውን ወጣት እንደበረሀ ጸሐይ እርር ድብን አድርጎ ያጫጨዋል፡:

በአጠቃላይ ስለ ወያኔ ገዳይ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ … መሆን አንካካድም! ልዩነታችን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው፤ ስለወያኔ የምንናገረው ሁሉ ለትግሬዎች ሁሉ ይሆናል የሚለው የተሳሳተ አሰተያየት ላይ ነው፤ እኔ በማእከላዊም ሆነ በቃሊቲ ጎንደሬዎች፣ ጎጃሜዎች፣ ወሎዬዎች፣ አሮሞዎች፣ ወላይታዎች … የወያኔዎች አገልጋዮች ሆነው እስረኞችን ሲያሰቃዩ አይቻለሁ፤ ትግራይም ሄጄ ከሌለው የኢትዮጵያ ክፍል የተዘረፈው ሀብት ሁሉ እንኳን ለትግሬ ሁሉና ለወያኔዎች ሁሉ እንዳልተዳረሰና ገና ከጥቂት አልጠግብ ባዮች ወያኔዎች እንዳልወጣ አይቻለሁ።

በሌላ በኩል ሲታይ ወያኔም የተነሣው ‹‹አማራ›› የሚባል ጭራቅ በዘበዘን፤ ብቻውን እየወፈረ እኛን አከሳን በማለት በ‹‹አማራ›› ላይ ወፍራም ጥላቻውን እያስፋፋ በአፈ-ጮሌዎቹ በመለስ ዜናዊ፣ በረከት ስምዖንና ዓባይ ጸሐይ ስብከት ጀሌዎቹን አሳምኖ ነው፤ ወያኔዎች ገና ሰሜን ሸዋ ሲዘልቁ የሚያዩአቸው ሰዎች፣ የሚያዩአቸው ቤቶች ውሸታሞቹ ጮሌዎች እንደነገሯቸው አለመሆኑን ሲገነዘቡ ጥያቄ ያነሡ እንደነበረ ሰምተናል፤ ዛሬም ሌሎች የመለስ፣ የበረከትና የዓባይ የመንፈስ ደቀ መዝሙሮች ኢላማውን ገልብጠው በትግሬዎች ላይ በጅምላ እያነጣጠሩ ነው፤ አንድን ከአንድ መቶ፣ ዝርዝርን ከጅምላ፣ ፖሊቲካን ከዘር መለየት የሚችል አእምሮ ሳይኖር ከአለንበት ሁኔታ አንወጣም፤ ብንወጣም ከጣልነው ጋር ለመንከባለል ነው፤ ወያኔ ደርግን ጥሎ አልተነሣም፤ እዚያው ከሬሳ ጋር ሲንከባለል ተዳከመ! የተሻልን እንሁን!
ወያኔ ሁሉ ትግሬ ነው፤ ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም፤ የወያኔ ዘረፋ እንኳን ለትግራይ ሕዝብና ለወያኔዎች በሙሉ አልደረሰም፤ በየዕለቱ በጠዋት እየተነሣች ምን እንደሆነ የማላውቀውን ዕቃ አዝላ ወደትምህርት ቤት ከሚሄዱ ልጆችዋ ጋር ከቤትዋ እየወጣች ከሰዓት በኋላ ዕቃውን አዝላ የምትመለስ ወያኔ አውቃለሁ፤ ይቺ ወያኔ (ትግሬ አላልሁም፤) በወያኔ ሥርዓት ተጠቅማለች የሚለኝ ሰው ወደሀኪም ዘንድ መሄድ ያስፈልገዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:   ያማራ ሕዝብ ሆይ ቋንቋህን አርም፣ አረመኔን አረመኔ አለማለት ፈሪነት እንጅ ጨዋነት አይደለም

16 Comments

  1. ersewom wode hakim bet yihidu. tgre altetekemem yemilut felit wuha ayanesam. etiopian kedar edar eyanketekete yalew gojamena gondere new yibelugn’na besaq yigdelugna! ahun chigru mantetekeme mantegoda aydelem, netsanet yasfelgenal new metekleyaw hasab. woyane alin tgre anesa anteletele new. meshewawod aytekmim. balager tgre beqenat wust habtam sihon eyayen yemin machefchef new prof.? eskemeches machefchef yichalal?

  2. ሰላም ፕሮፌሰር ከአክብሮት ጋር
    አሁን እየነገሩን ያለው ገንዘብ የዘረፈውንና ያልዘረፈውን ነው
    በእኔ ግምት እሱ አይደለም የኢትዬጰያውያን ትልቁ ችግር
    እኔ እንደሚገባኝ ትልቁ ችግር ሁሉም ትግሪዎች ወይም ፂላዎች
    ሀብታም ሆነ ድሀ በአንድ ላይ በአንድ ሀሳብ የማሰሩት ለትግራዋይ ነው
    ዛሬ በኢትዬጰያ ባለሥልጣን ሁሉ ትግሬ ነው የደህንነትና የስለላው ሠራተኛ በሙሉ ትግሬ ነው
    የመከላከያ ሠራዊቱ አዛዥ ከተራ ወታደር ጀምሮ ትግሬ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሀብት ትግሬ በአጠቃላይ
    ሀገሪቱ የትግሬዎች የሆነችበት ነው ትናንት አርባ ጉጉ ወተር በደኖ እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች የገደለ ያስገደለ ትግሬ
    ህፃናትንና ሽማግሌዎችን ገደል ውስጥ የጨመረ እንዴት ብሎ የኢትዬጵያ ህዝብ ወያኔና ትግሬ ብሎ ይለያል ለምን ብሎ ጊዜ ያጠፋል እኔ በምኖርበት አካባቢ እንኮአን ትግሬዎች በኢትዬጵያውያን በአል አይገኙም የራሳቸውን በአል ያከብራሉ ስራቸውን ስለሚያቁ እና ለኘሮፊሰር የምነግራቸው it is too late that to tell the people of Ethiopia, the damage is their we Ethiopians knows what we gonna do at the end of the day, and they knows that what will comes the near future. Finally I personally don’t like ትግሬ

  3. እውነት ይህ ሰው ወያኔ የሚለውን ትርጉም ያውቀዋልን? የዘመኑ ትሮፌሰሮች ትምህርታቸውን የሚገልጹበት መስፈርት እጅጉን እየትዛባ ነው:: የአማራም ወያኔ አለ የኦሮሞም የጉራጌም ወዘተ:: ስለዚህ መዘላበዱን ያቁም::

  4. እኔ የሚገርመኝ እነዚህ ሆዳም የአማራ እርዝራዦች ከ100 አመታት በላይ የኦሮሚያ ባህል : ወግ : ስርአትና ቋንቋ አጥፍተው አንጡራ ሀብቱን ወረው የቁም ስቅል እንዳላሣዩት ሁሉ አሁን በኦሮሚያና በሌሎች አከባቢዎች የሚታየው የህዝብ ብሶት ተገን አግርገው ወያኔ ትግሬ ምንትሴ እያሉ የሚያደነቁሩን:: በትግሬ ህዝብ ላይ ማነጣጠር የፈለጉት እንደ አያቶቻቸው ታሪክ ማጣመምና ህዝብን መፈረጅ ልምድ ሆኖባቸው ነው:: አንድ ነገር በትክክል መታወቅ ያለበት አሁን ለሚታዩ የህዝብ ብሶት ተጠያቂው ወያኔ ሲሆን ምን ጊዜም ግን የኦሮሞ ህዝብ በአማራ ነፍጠኛ ስርአት የደረሰበት በደል ለአፍታም ቢሆን አይረሳውም:: የምን ጠጋ ጠጋ ነው? ዋና ጠላታችን ለይተን እናውቃለን:: ይሄ ሆዳም ነፍጠኛ አማራ ራሱ ችሎ ወያኔን መፋለም ከፈለገ ይሄው ሜዳ ይሄው ፈረስ:: ኋላ ግን “ማረኝ ማረኝ ማረኝ” እንዳይሆን ? ፈርሣም ፍጠኛ

  5. በቁም ነገር እሎታለዉ ፕሮፌሰር ይህ የዛሬ ጽሁፍዎት አልተመቸኝም:: ከትግሬዎች ውስጥ አንዳንድ ጥሩ ሰዎች ይኖራሉ ብለን ብዙ ጠብቀን ነበር:: ጠብቀን ጠብቀን ያገኘነው ሰላም ጤና እንዲህም ክብር ለሳቸው ይሁንና ዐንድ አቶ ገብረመድህን አራያን ነው:: እኔ በተለያየ አጋጣሚ ቀርቤ ካገኘሁአቸው የትግራይ ተወላጆች ውስጥ አንዴም ወያኔ በሌሎች ብሄረሰቦችና በሃገር ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና ስቃይ ሲኮንኑ አልሰማሁም:: የብዙ ኢትዮጵያዊያን ግንዝቤም ይህው ይመስለኛል:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰው ስቃይና በደል ካላሳዘነዉ ይህ የጤና አይደለም ሁሉም ከንቱ ነው:: ለማንኛዉም ወገኖቼን የምመክረው አምርረው እንዲታገሉ ነዉ:: በዝች ሰአትና ደቂቃ ወግኖቼ በወያኔ የማሰቃያ እስር ቤቶች ውስጥ አንተ አማራ አንተ ኦሮሞ እየተባሉ እየተገረፉ ነው:: አንተ ትግሬ እየተባለ
    የሚገረፍ ግን የለም:: እስቲ እኔ ነኝ ያለ ትግሬ ይህንን ስቃይና በደል በ አደባባይ ላይ ወጥቶ በማውገዝ ሰው መሆኑን ያረጋገጥ

  6. ወንድሞቸ: የብልህ ሰው ምክር መስማት ብቻ ሳይሆን በደንብ ማዳመጥ: ለራሳቹህ ጤንነትም: ፕሮፌሰሩ እንዳሉት ጥሩ ነው:: ለምሳሌ እኔ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ነኝ:: ኣሁን ያለው ስርኣት ከማንም በላይ እቃወማለሁ:: የወያኔ መሪዎች: ከደርግ መንግስት መሪዎች በላይ ወንጀለኞች ናቸውና:: ኢትዮጵያ: ኣሁን ካለው መንግስት በላይ የከፋ መንግስት ያጋጠማት አይመስለኝም በታሪክ:: ለዚህ መንግስት የሚያገለግሉ: በዝርፍያ ተጠቃሚ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉ የኔ ምስክርነትም ኣያስፈልግም: ያደባባይ ምስጢር ነውና:: ነገር ግን እኔ የትግራይ ተወላጅ በመሆኔ እኔንም ከነዛ ወንጀለኞች ጋር ጨምሬ ልቁጠርህ ብትለኝ: ብልሁ ፕሮፌሰር እንዳሉት: ሃኪም ቤት ብትሄድ ይመረጣል:: በነገራችን ላይ: ልክ እንደኔም: ይህ ስርኣት የሚጠሉና የሚቃወሙ ዘመዶችና ጛደኞችም ኣሉኝ:: ብቻየን እንዳይመስልህ ወያኔን የምጠላ የትግራይ ተወላጅ:: ይሄ ሁሉ የማይዋጥለት ካለ ደግሞ: ምናልባት የወያኔ ቅጥረኛ (ተቃዋሚ በመምሰል) ህዝብን ከህዝብ ለማፋጀት: ለዝርፍያ የተሰልፈ ወንጀለኛ: ወይም የወያኔ ልማታዊ (ከፋፍለህ ግዛ) ካድሬ ወይም ትርፍራፊ ለቃሚ የሆነ ሰው መሆን ኣለበት:: ከነዚህ ዉጭ መሆን ኣይችልም::

    ሞት ለዘራፊውና ለጨፍጫፊው የወያኔ ስርኣት!
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

  7. indih mezelabed min yilutal?…………who said tigres are not looting Ethiopia?…….the fact is now we have tigre aparthied in Ethiopia. Tigres are killing Ethiopians, Tigres are selling Ethiopia and much more……….

    please stop preaching other wise. Last time this old goat told us “Amhara does not Exist”, he actually sat down with kehadiw zenawi and told him Amhara does not exist…..i suggest you retire while you are ahead……..stop helping the banda woyanes. keep out of it, the Ethiopian people know the truth, unlike you Amharas are facing genocide and mass murder and ethnic cleansing every day under the very woyane tigres that you are trying to protect. ………..i say stop, “YERASUA IYAREREBAT YESEW TAMASILALECH”

  8. Preaching hate will not save Ethiopia. I completely agree with professor Mesfin. Putting every Tigre in one bag is the easiest road. Keeping peace among Ethiopians is the hardest.

  9. ከጅምላ፣ ፖሊቲካን ከዘር መለየት የሚችል አእምሮ ሳይኖር ከአለንበት ሁኔታ አንወጣም፤ ብንወጣም ከጣልነው ጋር ለመንከባለል ነው፤ ወያኔ ደርግን ጥሎ አልተነሣም፤ እዚያው ከሬሳ ጋር ሲንከባለል ተዳከመ! የተሻልን እንሁን!

  10. ይህ ጽሁፍ ትክክል ነው ተቀብለን መከተልም ኣለብን። በግልባጩም ለኦሮሞ፣ ለኣማራ ይሰራል እና። መነሻ ይኑረን ካልሆነ የምንሄደው ኣናውቅምና።
    ይህ ጽሁፍ ከደርግ ውድቀት ጽንስ ሃሳቡ ቢኖረን ስንት ህይወት ባልተቀጨ ነበር። “መክሸፍ” መጽሃፋቸው ስናነብ ደግሞ ሌላ መልእክት ኣለው። ቃል ኣንድ ይሁን። መልእክቱ ግልጽ ሁኖ በጽናት መናገር።

  11. it is really sad to see AMAHRA ELITES busy worrying about Tigres not being WOYANE, and why are these useless AMahra elites are the once who say ALL Tigres are not WOYANES????? Why don’t Tigrians said this? I have never heard any Tigrians saying we Tigres are not all Woyanes.

    the behaviour of stupid AMHARA ELITES has no limit, the people of WOLKAIT are suffering under Tigrians and being displaced and here this SO CALLED PROFESSOR IS writing this crap

  12. I agree with Professor all in all but I have never met a Tigre who is not a fan of woyene!! Why ?? Despite of knowing the truth, they still support woyene…..

  13. Dear Prof

    You are right. We must not generalise. But the fact of the matter is, the majority of the people of Tigray (about 90% of them)have been supporting TPLF because of their own many reasons. I estimate 10% of the People of Tigray do not support TPLF.

    Everybody knows the vast majority of the Tigre people have been beneficiaries and supporters of the TPLF apartheid system. Nobody says all of them are like that given the hero, Ato Gebremedhin Araya, an outstanding truthful person. People like him are rare to find. I respect him and would like to acknowledge the contribution of some people like him as well.

    In due time, no doubt that all Tigres will harvest what they saw.

Comments are closed.

Share