“ይቅርታ” ወይም “ሰላም” | ከተስፋዬ ገ/አብ

ሃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ያደረጉት ቃለመጠይቅ አነጋጋሪ ነበር። ከኦሮሞ ህዝብ አመፅ ጋር በተያያዘ የሰነበተውን ችግር ሌላ አካል ላይ ማላከክ እንደማይገባ መናገራቸው ከኢህአዴግ ጠባይ አንፃር ያልተለመደ ነበር። በውስጥ ባለ ችግር ምክንያት የህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው ህዝብና መንግስት ተቃቅረው ጉዳዩ ወደ ግጭት ደረጃ መድረሱን ማመናቸው አንድ እርምጃ ወደፊት ነው። ችግሩ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን መግለፅ መቻላቸው ይደነቃል። ሃይለማርያም በዚህ ደረጃ ችግሩን አምነውና ተቀብለው ሲያበቁ፤ በመጨረሻ ለተፈጠረው ችግር በጥቅሉ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል። ይቅርታ ጥየቃው ካንገት በላይ ነው ወይስ ካንገት በታች ለጊዜው ባናውቅም፤ ይቅርታ መጠየቅ በራሱ ስልጣኔ ነው። 

(ተስፋዬ ገብረአብ)

እንግዲህ በመቀጠል ወደ ዝርዝር ጉዳይ እንግባ።

ሃይለማርያምይቅርታ ሲጠይቁ በመሰረቱ ምን ማለታቸው ነው? ከዚህ በሁዋላ ኢትዮጵያ ላይ በህጉ መሰረት ሰላማዊ ተቃውሞ ማካሄድ ተፈቅዶአል ማለት ነው? ከዚህ በሁዋላ የፌደራል ፖሊስ ሰላማዊ ሰዎችን በየጎዳናው አይገድልም? ባለፉት አራት ወራት እና ከዚያም በፊት በየጎዳናው ለተገደሉት ንፁሃን ዜጎች ወላጆችና ቤተሰብ ካሳ ይሰጣል? ንፁሃን ዜጎችን የገደሉና ያስገደሉ ለፍርድ ይቀርባሉ? የታሰሩት በአስር ሺዎች የሚገመቱ የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ? መሬታቸው ተነጥቆ ለተፈናቀሉ ገበሬዎች ተገቢው ካሳ ተከፍሎ እንዲቋቋሙ ይደረጋል?ይቅርታውን ተከትሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ አንዳችም ያሉት ነገር የለም። በደፈናው ሸውዶ ለማለፍ የተደረገ የለበጣ ይቅርታከሆነቅዳሴና ዳንኪራንእንደመደባለቅ ይቆጠራል።

ከአንድ ሰው ጋር ስለዚሁ ጉዳይ ስንወያይ፣ “ሃይለማርያም ይቅርታ ጠየቀ ለማለት አይቻልም።ይቅርታውን መልሶአፍርሶታል።” አለኝ። ሌላው ደግሞ፣ “ሃይለማርያም ከዚህ ቀደም ‘አስመራ ሄጄ ከኢሳይያስ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ’ ሲሉ እንደተናገረው አሁንም የግሉን ይቅርታ ደባልቆይሆናል።” አለ። ከዚህ በተጨማሪ “የይቅርታው ቃል በአሜሪካኖች አስገዳጅነት በህወሃት እውቅና የመጣ ነው።” የሚል የውስጥ አዋቂ መረጃም ሰምቻለሁ። ከአስተያየቶች ሁሉ “ይቅርታ” የምትለው ቃል በአሜሪካኖች ተፅእኖ የተነገረች ልትሆን መቻሏ ወደ እውነት የሚጠጋ ይመስለኛል። ሲፃፍ እንደሰነበተው ወያኔ ችግር ውስጥ መገኘቱ አከራካሪ አይደለም። አስረጅ ሊሆን ከሚችለው መካከል፣ “ከኦሮሞ ህዝብ አመፅ ጀርባ የኤርትራ እና የግብፅ ተላላኪዎች አሉ” የሚለውን ክስ ለመተው መገደዳቸው አንዱ ነው። የኦሮሞ ህዝብ አመፅ መነሻ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን ማመን እስከዛሬ ጌታቸው ረዳ ሲነግረን የነበረውን ይቃረናል።

ርግጥ ነው፤ ከሃይለማርያም ይቅርታ መጠየቅ ጋር በተያያዘ ከሚሰሙጭምጭምታዎች ዋናው የአሜሪካኖች ተፅእኖ ሚዛን የሚደፋ መስሎ መታየቱ ነው። የፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ“ሰላም” የተባለው የማሸማገል ሂደትም የቀጠለ በመሆኑ ምን መልክ ይዞ ይፋ እንደሚሆን በቀጣዩ ጊዜያት የምንሰማው ይሆናል። በአንድ ወቅት CUD የተባለውን ቅንጅት ይመሩ የነበሩ ሰዎች በፕሮፌሰር ኤፍሬም አሸማጋይነት ከእስርቤት ከወጡ በሁዋላ የወያኔ ፍላጎት እንደምንም ተያይዘው ከአገር እንዲወጡለት መንገድ መክፈት ነበር። በርግጥም አብዛኞቹ ባገኙት እድል ሁሉ ተጠቅመው የታገሉላትን አገር ትተው እንደማይመለሱ ሆነው ርቀው ሄደዋል። ይህ ለህወሃት አገዛዝጥሩ እድል ነበር።አብዛኞቹየCUD ሰዎች ከኮበለሉ በሁዋላ ወያኔ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳ ያሉትን ነጥሎ ለመምታት አልተቸገረም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ተፈታታኝና ወጣሪ ሁኔታ ኢ.ሕ.አ.ፓን መተንኮስ ለምን አስፈለገ? (ፍየል ወዲህ፣ ቅዝምዝም ወዲያ!)

ህወሃት ቅንጅትን አዳክሞ ባጠፋው መንገድ የኦሮሞ አማፅያንን በዚያው ዘዴ ለማኮላሸት ማሰቡ ገና ያልተፈፀመ በሂደት ላይ ያለ ተግባር ነው። እንደሚሰማው የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆ እስረኞችን ለመፍታት ለአሜሪካኖቹ ቃል ገብቶ ከሰነበተ እንግዲህ ይቅርታዋ እንደምንምተነግራለች።  እስረኞችን መፍታትግን ገና አልተፈፀመም። እንደ ውስጥ አዋቂዎች ጥቆማ ከሆነ በእስርቤት ካጎሯቸው በአስር ሺህዎች የሚገመቱ ኦሮሞ እስረኞች መካከል የአመፁ አስተባባሪ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው የገመቷቸውን በመለየት ስራ ተጠምደዋል። አመፁን ያስተባብራሉ ብለው የሚገምቷቸውን ለይተው ካበቁ በሁዋላ ወደ ስደት የሚሄዱበትን መንገድ ያመቻቻሉ ተብሎ ይታሰባል። ይህን ማድረግ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ያዳክማል፤ ስርአቱ ትንፋሽ እንዲያገኝም ፋታ ይሰጠዋል ብለው ቢያስቡ ከልምዳቸው አንፃር ስህተት አይሆንም። የነቃው እና የተደራጀው ግለሰብ ከሜዳው ገለል ካለ አመፁ ጠቅልሎ ባይቆም እንኳ ፋታ ሊገኝ ይችላል።በርግጥ እንደ እስክንድር ነጋ፤ እንደ በቀለ ገርባ ለመኮብለል ፈቃደኛ የማይሆኑ ሲገጥሙ ቀመሩ ተገላቢጦሽ ይሆናል።

የኦሮሚያ ወጣቶች ሴራውን ባለመረዳት ለአዲስ ዙር ስደት ከተነሱ ‘በአገሩ የሌለ – የትም የለም።’ እንደሚባለው ለህወሃት ድል ይሆናል።ኮብላዮች ድጋፍ ሰጪ ከመሆን ያለፈ አቅም አይኖራቸውም።የኦሮሞ ህዝብ አሁን ከደረሰበት የተሰሚነት አቅም ላይ እንዲደርስ ያደረጉት በግንባር ቀደምትነት ተጋፍጠው መስዋእትነት የከፈሉት ጥቂት ወጣቶችናቸው። ድጋፍ ሰጪ ስደተኛ የማድረግ ችሎታው በጣም ውሱን ነው። ሃርቫርድ ከሚገኝ አንድ ተራ ፕሮፌሰር፤ ሃሮማያ የሚገኝ አንድ ተራ የገበሬ ልጅ የተሻለ የማድረግ ችሎታ አለው።ህወሃት ከዳያስፖራ ይልቅ አጠገቡ ያሉትን ተራ ዜጎች ይሰጋል። ስለዚህ የማስቸገር ብቃት ያላቸው ይኮበልሉ ዘንድ ተግቶ ይሰራል። ማሰርና መግደል የህወሃት የመጀመሪያ ምርጫ ሆነው አያውቁም። የኮበለለ ሁሉ የወያኔን የመጀመሪያ ምርጫ እንደተቀበለና እንደተሸወደ ማወቅ አለበት።

ባለፈው ሳምንት “የቅዳሜ ማስታወሻ” ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅን በጨረፍታም ቢሆን ነካ አድርጌያቸው ነበር።በላኩልኝ ኢሜይል ስለርሳቸው ያለኝ ግንዛቤ ስህተት መሆኑን ጠቁመውኛል። እርሳቸው እንደገመቱት ሳይሆን ስለ ፕሮፌሰሩ ብዙም ባይሆን ጥቂት አውቃለሁ። የት ከማን እንደተወለዱ፣ የት ምን እንደተማሩ፣ የት ምን እንደሚያስተምሩ አውቃለሁ። ደረጀ ደሬሳ በአጤ ሃይለስላሴ ዘመን በወቅቱ የ31 አመት ጎረምሳ ለነበሩትለአቶ ኤፍሬም ይስሃቅ የፃፈውን መወድስም ኢትዮጵያ ሳለሁአንብቤያለሁ። በተማሪዎች እንቅስቃሴ ዘመን ለአገራቸው ብዙ ቁምነገር የሰሩ ሰው መሆናቸውን ቀደም ብዬም አውቅ ነበር። ሽማግሌው ፕሮፌሰር በጎልማሳነታቸው ዘመን ለደቡብ አፍሪቃ ጥቁሮች መብት መከበር መታገላቸውን በርግጥ አላውቅም ነበር።ዞረም ቀረ የተሰራው መልካም ነገር ሁሉ በቦታው አለ። ታሪክ አይረሳውም፤ ታሪክ ያመሰግናቸዋል።ፕሮፌሰሩ የአባት አገራቸው ታማኝ ልጅ ቢሆኑም፤ መወለድ ቋንቋ ነውና ልክ እንደኔው እሳቸውም የትውልድ አገራቸውን እንደሚወዱ እረዳለሁ።

ፕሮፌሰር ኤፍሬም በደርግ ውድቀት ማግስት የመሸጋገሪያው መንግስት ምስረታ ላይ፣ ታምራት ላይኔን ለማሞገስ፣ “ተአምራት ለአይኔ፣ ተአምር በአይኔ አየሁ” ብለው ቅኔ ሲቀኙ በደማቁ ካጨበጨቡላቸው አንዱ እንደነበርኩ አልክድም። በወቅቱ ሁላችንም ተአምራት በአይናችን ያየን መስሎን ነበር። ታምራትና መለስ የተሸፈነ ጠባያቸው ሳይገለጥ ጥቂት አመታት እንኳ መጓዝ እንደማይችሉ አልገመትንም ነበር። ጃኬትና መኪና ወደ ማማረጥ ይገባሉ ብሎ የጠረጠረ አልነበረም። የሆነው ሆኖ የስካሩ አቧራ ገለል ሲል ፕሮፌሰር ኤፍሬም በአይናቸው ተአምራት ሳይሆን መቅሰፍት ነበር ያዩት። ያም ሆኖ ወዳጅነታቸውን ከወያኔ ጋር ቀጥለዋል።እዚህ ላይ እንግዲህ መነፅራችንን ዝቅ አድርገን፣ “ጤናይስጥልኝ ፕሮፌሰር!” ለማለት እንገደዳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፈራ ይመለስ! (ከተመስገን ደሳለኝ)

ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የኦሮሞን ህዝብ ከገዢው ግንባር ጋር ለማስታረቅ በሚያደርጉት ሙከራ፣ “ሰላም” የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ “የማን ሰላም?” የሚለውንም ጥያቄ ይመልሱት ዘንድ ይጠበቃል።ሰላምን ለማስገኘት ሽምግልና ከመጀመራቸው በፊት “ፀረ ሰላም ማነው? ለሰላም ጠንቅ የሆነው ማነው?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽማግኘት ይገባል። የቀድሞ በጎ ስራ ለዛሬው ስህተት ላጲስ ሆኖ አያገለግልም። “ሰላም ወዳድ” የሚለው ማእረግ “አሻጥረኛ”  ወደሚል ከተለወጠ ለመመለስ ያስቸግራል። የኦሮሞ ህዝብ በአገሩ ላይ የተረጋገጠ ሰላም ለማግኘት መስዋእትነት መክፈል እንዳለበት የተረዳበት ጊዜ ላይ ነው። በርግጥም የአዲሱ ትውልድ መሪ መፈክር አንድ ብቻ ሆኖአል። ይህም፣ “ዛሬ አንድ ነገር ማድረግ አለብን። ወይም ደግሞ መሞት አለብን!” የሚል ነው። እና ማገዙ ካልተቻለ ቢያንስ “እንኳን ለዚህ አበቃችሁ!” ማለት ይገባል።

ርግጥ ነው፤ “የሰላም መጥፎ፣  የጦርነት ጥሩ የለውም” የሚለው ነባር አባባል በጥቅሉ ተቀባይነት አለው። ልጇ የሞተባት እናት፤ አባቱ የሞተበት ልጅ ሃዘን ላይ ናቸው። ሃዘናቸውን ለመረዳት እግራችንን እነርሱ ጫማ ውስጥ መጨመር ይገባል። ቢሆንም ግን ለሰላም ሲባል ሰላምን ለማደፍረስ፤ ጦርነትን ለማስወገድ ጦርነት መለኮስ ግዴታ ሆኖ ሊመጣ ይችላል። ሲደፈርስ በርግጥ ብዙ ህይወት ይቀጠፋል። ባይሆን ጥሩ ነበር። ህይወት ሳይከፈል የብዙሃን ሰላም የማይገኝ ከሆነ ግን መደፍረሱ ግድ ይሆናል። ህይወት በሚቀጠፍበት መንገድ ብቻ ማለፍ ግድ መሆኑ ያሳዝናል። በጦርነት ድል ቢገኝም እንኳ ከድሉ ባሻገር አሸናፊውም ልክ እንደ ተሸናፊው እኩል ኪሳራ ይቀበላል። ሰላም አንፃራዊ ነው። በሚዛናዊ መነፅር ስንመለከተው ዚምቧቡዌ ከቀድሞ ሰላሟ ይልቅ የአሁኑ መተራመሷ ይሻላት ይሆናል። በዚህ የዚምቧቤ መተራመስ ውስጥ 300 ሺህ የአገሬው ሰዎች ከዘበኛነትና ከግርድና ስራ ተላቀው ባለመሬት መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም። የኦሮሞ ወጣቶች በዚህ ዘመን የተተወላቸው ስራ በተነጠቀ መሬታቸው ላይ ዘበኝነት መቀጠር ሆኖአል። ከመሬታቸው የተፈናቀሉ የገበሬ ልጆች በዘበኛነት የስራ ዘርፍ አዲሳባን እንደወረሩ፣ በበረንዳ አዳሪነት ከተማዋን እንዳጥለቀለቁ  በቂ መረጃ አለ። እነዚህ ወጣቶች ከጥቂት አመታት በፊት ባለመሬት ነበሩ። ሃብታም መሬት ያርሱ ነበር። ሳሞራ ማሼል ስልጣኑን በያዘባት ሌሊት ያንን ዝነኛ አዋጅ ያወጀው የነፃነትን የተሟላ ትርጉም ለወገኖቹ ለማቅመስ ነበር። ነፃነት ሲባል የከበርቴ ሰዎች ዘበኛ ሆነህ መለፍለፍ መቻል ማለት አይደለም። ነፃነት ከመሬት ባለቤትነት ይጀምራል። እና ሞዛምቢካውያን ከነሙሉ ችግራቸው ዛሬም ቢሆን ሳሞራን በበጎ ያስታውሱታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የትናንቷን እሁድ በወፍ በረር ስንቃኛት

የኦሮሞ ህዝብ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስርአቱ የጫነበትን የሰቆቃ ህይወት እየተቃወመ ረጅም ተጉዟል። ሸክሙ ሲበዛበት ግን ቀንበሩን ወረወረና አታላዩን ሰላምና ፀጥታ ክፉኛ አደፈረሰው። የህልውና ጉዳይ ሆነበት። አይኑ እያየ የማያውቃቸው ሰዎች መጥተው የአያቱን መሬት ሲሸጡ ሲመለከት የሰላም ትርጉሙ ጠፋበት። መሞትን መረጠ። እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው “ለሰላም ሲባል”፤ “ለአንድነት ሲባል” ብለህ ልታግባባው አትችልም። አይሰማህም። በአንድ ወቅት የOPDO ምክትል ሊቀመንበር እንደነበረው እንደ ኢብራሂም መልካ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ለኦሮሞ ያልሆነች ኢትዮጵያ አስር ቦታ ትበጣጠስ!!” ሊልህ ይችላል። በመሆኑም ፕሮፌሰር ኤፍሬም ለማን ጥቅም እየሰሩ እንዳሉ ማወቅ አለባቸው። ለኢትዮጵያ አንድነት? ለተጨቆኑ ህዝቦች ሰላም? ወይስ ለአንድ ቡድን ስልጣን? ምላሹ ለህሊናቸው ይሁን።

የጃዋር መሃመድን መረጃ ከያዝን ሌላው ይቆይልንና ባለፉት አራት ወራት በኦሮሚያ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 500 አሻቅቦአል። ይህ ብቻውን እንኳ ለወያኔ ትልቅ እዳ ነው። ክፍያው ሊቸግር ይችላል። የህይወት እዳ ወለዱ ውድ ነው። ሃይለማርያም በቅርቡ ሴት ልጃቸውን በሞቀ ሰርግ ድረዋል። ሟቾቹ ወጣቶች በተመሳሳይ ለወግ ለማእረግ እንዲበቁ ወላጆቻቸው ይመኙ ነበር። ልጆቻቸውን ያጡ፣ አባታቸውን የተነጠቁ ወገኖች ሃዘኑን አይችሉትም። ሃይለማርያም ይቅርታ የጠየቁት በራሳቸው ተነሳሽነት ከሆነ ከዚያም በላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ርግጥ ነው፤ “የኦሮሚያ አመፅ” የሚለው የጨዋታ ካርድ ላለፉት አራት ወራት ከፖለቲካ ሜዳው ላይ ሊወርድ አልቻለም። ከቀዳሚ ዜናነቱ ሊገፈተር አልቻለም።ሰበር ዜና ከመሆን ሊታቀብ አልቻለም።ሃይለማርያም የበታች አለቆቻቸውን ስነልቦና መረዳት ይጠበቅባቸዋል። አባይ ፀሃዬ እና ስብሃት ነጋ “ጥቂት ታገስ! ከዚያም ጊዜ ጠብቀህ የጨዋታውን ካርድ ቀይረው” የሚለውን የሰርቫንቴስ አባባል ደጋግመውም ይጠቀሙበታል። የ“ይቅርታ” እና የ“ሰላም” ወጎች የትእግስት ምእራፍሲሆኑ፤ ከረምረም ብለው የጨዋታውን ካርድ ለመቀየር መሸጋገሪያ ይሆናሉ። ያንጊዜ ጊሎቲን አንገት ቆረጣውን እንዳዲስ ይጀምራል።

በመጨረሻ አንድ ነጥብ ላይ ላስምር። የኦሮሞ ህዝብ እየከፈለ ያለው የህይወት መስዋእትነት ኪሳራ አይደለም። ግብና አላማ አለው። ለመጪው ትውልድ እየተከፈለ ያለ የክብር ዋጋ ነው። እና የኦሮሞ ህዝብ ጨክኖ እንደጀመረ ከመግፋት በቀር አማራጭ የለውም። ወደሁዋላ ማየት እንደገና መቶ አመታት ሊያስተኛ ይችላል። መስዋእትነቱን አያስቀረውም። ከመሬት መፈናቀሉን፣ ስደቱን አያስቀረውም። የኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ህዝብ እንደመሆኑ ሌሎችንም ኢትዮጵያውያን አስተባብሮ፣ አቅፎ ወደ ተሻለው ዘመን የመጓዝ ብቃቱና ችሎታው አለው። ያለ ኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ምትባል አገር የለችም። እና የኦሮሞ ህዝብ ራሱን ነፃ ከማውጣት ባሻገር ከባድ ሃላፊነት አለበት። የተረጋገጠውን ሰላም ለማግኘትና በረጅሙ ለማረፍ ጨለማማውን ጫካ በድፍረት ማለፍ ይገባዋል። ይቻለዋልም። አሳምሮ ይቻለዋል። ታግለው ነፃ የወጡ የአለም ህዝቦች ታሪክ የሚነግረን ይህንኑ ነው።

11 Comments

  1. ተስፋየ ገብረ እባብ; በማያገባህ እየገባህ አስቸገርክ አይደል? ሺ ብትጽፍ ከቁብ የሚቆጥርህ የለምና ባትለፋስ? እስቲ ለቅያሬ ስለሚሰደዱት ኤርትራዊያን: ባህር የሚውጣቸው ወገነችህ አንድ ሁለት ሞነጫችር?
    ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ተው: ኤርትራ ከናት ሓገርዋ እስክትቀላቀል ድረስ::

  2. አንተ ሰውየ መቼ ነው ከዚህ የርጎ ዝንብነትህ የምታቆመው ? አንተ ለምን ስለኤርትራ አትጽፍም, እናት ሀገርህ
    ኢትዮጵያ ሳትሆን ኤርትራ ነች: እሰው ቤት ገብተህ ለምን ታለቀልቃለህ ? ይህንን በማር የተለወሰ መርዝ
    እየረጨህ እስክመቼ ይሆን የምትቆየው ?

  3. Dear Tesfaye,the way you are analyzing and argument is very attractive.please keep it up. You are one of the best writer.

  4. The very excellent idea for all ethipian;but not good some mainorities./hulunim mermiru yemetekimewin tekebelu/.

  5. ተስፍሽ ኢትዮጵያን በቲቪ እሺ:: ታራለህ ትበግናለህ…. ወያኔ አባረረህ… ሻዕቢያ ገረደህ…. ጃዋር እንደ ሴት አገባህ ምናባሕ ታመጣለህ ? አንድ ያልገባህ ነገር እኛ ወያኔን እንጂ ኢትዮጵያን አንጠላም:::::: ለማንኛውም ከጃዋር ጋር ጋብቻችሁ እንዴት ነው ? መቼም አህያ እንጂ ልጅ አትወልዱም:: የስንት ወር እርጉዝ ነሽ?

  6. ተስፋየ ገብረአብ ጥሩ እይታ ነው ፡ በአብዛኛው የፃፍካቸው እውነት ነው፡፡ የብርቱካን ሚዴቅሳን አወጣጥ ጠንቅቄ አውቃለሁ ፡፡ EPRDF ጥሩ ጥሩ PROFESSIONAL ደላሎች አሉት ( እድሜ ለፈረንጆቹ ) እንዴት አድርገው ከአገር እንደሚያስለቅቁህ ያውቁበታል፡፡ ያስቸገራቸው ሀብታሙ አያሌው ነበር አሁንም
    ሌላ ዘመቻ አየነደፉ ነው፡፡

    ወንድሜ ደፋር ፀሀፊ ነህ በረታ፡፡

    አገራችን የሆዳም ሀገር ነው፡፡ በጫት እና በሱስ በጥቅም ህዝቡን አኮላሽተውታል፡፡ ከአሁን በሁዋላ ምንም ተስፋ የለም፡፡

    የኢትዮጵያ ባለስልጣን በ Land cruser መኪና ሕዝቡ አይኑ ስር
    ሲረማመዱበት እርምጃ መውሰድ ከተሳነው እንዴት ነው ነገሩ ?

    ለነገሩ ይቀጣ ይቀጣ፡፡ ሆዳም ህዝብ ሲያንሰው ነው፡፡ የራሱን ወገን አሳልፎ የሚሰጥ ነው፡፡ የተረገምን ነን፡፡

    አሁንም እውነትን ፃፍ በረታ

  7. አንተ እርኩስ ደግሞ ብለህ ብለህ እኔም እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢትዮጵያን እወዳለሁ አልክ ቅቅቅቅቅ ምን አይነት ፈጣጣ አርተራዊ ነህ ??????? አንተ ፓለቲካ መጻፍ ሳይሆን የሚያስፈልግህ እላይህ ላይ የሰፈረውን ሰይጣን መንፈስ የሚይባርር ጸበል ነበር.

    አሁን ሰሞን ደግሞ ከ እነ ጃዋር አማራውን አትሳደብ ከአማራው ጋር አታጣለን የሚል ትእዛዝ ደረሶሃል መስለኝ የፈረደበትን አማራን መሳደብ አቁምሃል,,,
    እርግጥ ነው አማራን መሳደብህን ገታ በማድረግህ ተስፋየ ገብረ እባብ አማራን መሳደብ አቆሙአል እያሉ ከበሮ የሚደልቁ ደደብ አማሮችን ልናይ እንችላለን አንተ ግን ኢትዮጵያን ለማጥፍት አማራውን ማጥፍት የሚለውን ዋና ሻባዊያዊ አጀንዳህን መቸም ቢሆን አትተውም የሚገርመው ግን የዘሃበሻ ድህረ ገጽ ለምን ሃገርን የሚያፈርስ ፕሮፓጋንዳህን እና መርዝህን እንድትረጭ ለምን እንደሚፈቅድልህ ነው ????? ደስ የሚለው ግን ሌሎች ድህረ ገጾች ስይጥናዊ ጽሁፍን ስለማያትሙልህ አንተ እንደ ደራሲም እንደ ጸሃፊም ተደራሽነትህ ሞቷል እንደ ደራሲም እንደ ሰው ከሞትክም ቆይተሃል ምክንያት አንድ ሰው የአንተን አይነት ጥላቻ እና ተንኮል እና ክፍት ተሸክሞ የእለት ተለት ሂወቱን መመራት አይችልም በቁሙ ካልሞተ በስተቀር ……

    ኤርትራዊያን እና የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአማራ ጥላቻ አጥምቀው እንደሚያሳድጉ የታወቀ ነው ያንተ ሽርሙጣ እናት ግን እንዴት አድርጋ በአማራ ጥላቻ አጥምቃ እንዳሳደገችህ ሳስብ ሁሌም ይገርመኛል …….
    እናትህ ያን ጀዝባ እና ቆዳ አባትህን ሳታገባ ኤርትራ ውስጥ ታዋቂ ሽርሙጣ እንደነበረች በሰማሁ ጊዜ እናትህ ምን አይነት ጭንቅላቷ በጥላቻ የተሞላ እርኩስ ሽርሙጣ እንደነበርች እና አማራ ጎረቤቶቻም በዚህ ዜማዊ ባህሪዋ ይጸየፉአት እንደነበረ የደብረ ዘይት ልጅ ጽፎ አንብቤ ተገረምክ ምንም ማድረግ አይቻልም አማራ ኩሩ ህዝብ ነው በባሏ ላይ የምትሽረሙጥ ሴት አይወድም

  8. አንተ እርኩሥ ሠይጣናዊ ምላሥ የትሸከምክ ሥለ አገራችን ጉዳይ ማነው ተቆርቃሪ ያደረገህ ምነው ሥለ አገርህ ብትፅፍ በባህር ውሥጥ በአሣ የሚበሉት ወገኖችህ የማትፅፍ አገራችን ላንተ ምንህ ናት እንዲህ አሣቢ የሆንከው

  9. ተስፋዪ ገ/ እባብ አንተም ብሎ ጸሀፊና ደራሲ ይህን ያልከበት ምክንያት መቸም ሰው በሁለት መንገድ ስሙ ይነሳል በጥሩ / በመጥፎ ። እርግጥ ነው ጥሩ ሁሌም ጥሩ ነው መጥፎም እንደዚሁ። ግን አንተም ሁለቱም አይገልጽህም። እናም ምን እንደምልህ አሰብኩ ከዚያም ይህ ሀሳብ መጣልኝ ። ገብረግም.ገብረግም.ገብረግም….

Comments are closed.

Share