የመለስ “ራዕይ” ውጤት | ጸሐፊ (በትግርኛ)  ኃየሎም አሉላ | ትርጉም ይነጋል በላቸው

መለስ ሆይ ባለህበት ደስ ይበልህ፣

የዘራኸው ሁሉ በቅሎ እሸቱ ጎመራልህ፡፡

መኸሩ ሊሰበሰብ ተለቅልቋል ዐውድማው፣

ራዕይህን ዕውን ሊያደርግ ዘብህ ቆሟል በየጎራው፡፡

ደስ ይበልህ መለስ … አንገትህን ከጉድጓዱ ቀና አ’ርግና

የ’ድሜ ልክ ልፋትህን ውጤት ተመልከት፣

አንድ ሐሙስ ብቻ ቀርቶታል የዘራኸው አዝመራ፣

ወደየጎተራው ሊከተት፡፡

የራዕይህ ምርት ሊታፈስ በቁናና ባቅማዳ፣

ካዘነብክልን የእርግማን ማርና ወተት፣

ሁላችን ያቅማችንን ልንቀዳ፣

ተሰባስበን ልንቋደስ የበረከትህን ሲሳይ ልንካፈል፣

ማዕዱ በስመ-መለስ ተብሎ ሊባረክ

ባሰለጠንካቸው የዘር ፖለቲካ ሊቃውንትህ፣

ደርሷልና ጊዜው የምንጠግብበት ከሌጋሲህ፣

ደስ ይበልህ መለስ ባለህበት፣

ምርቃታችን ይድረስህ፣

ወግ ነውና መመረቅ … ስላደረግህልን ሁሉ ልጅ ይውጣልህ፡፡

ባንተ ራዕይ ስብከት አብደው የሰከሩ፣

ላንተ ልፋፌ-ጽድቅ የተንበረከኩ፣

“ራዕይህ ከሚከሽፍ ሞቴን ያስቀድመው” ብለው የቆረጡ፣

ሠይፋቸውን ስለው ዝግጁነታቸውን ገለጡ፣

የመጣ ቢመጣ ከቃልህ ጭርሱኑ ላይወጡ፡፡

ያንዲት ሀገር ዜጎች … ያንዲት ቀየ ልጆች፣

በቡድን በጎራ ሚና አበጅተው፣

በቋንቋና በጎጥ በዘር ተከፋፍለው፣

አንዲቷን ኢትዮጵያ ላንተ ሲሉ ትተው፣

“ተው!” እሚላቸውን ገላጋይን ንቀው፣

በጦር በጎራዴ … ሊተላለቁልህ ባንተ ስም ቃል ገብተው፣

ቀጠሮ ይዘዋል፣

ባንተው ተማምለው …

ላንተው ውርስ ብለው፡፡

እናም

ደስ ይበልህ መለስ …ዐፅምህ ይገላበጥ፤

ራዕይህ ሠምሯል  ታምርህ ይገለጥ፡፡

ዕድሜ ላንተ ራዕይ ዜጎች ተበተኑ፣

ቀያቸውን ጥለው እንደጪስ በነኑ፣

እንዳይመለሱ … ሀገር አለን ብለው፣

የራዕይህ ልጆች መሬቱን ቸብችበው፣

ከዜጋቸው ይልቅ ባዕዳንን አክብረው፣

ለሆድ ተንበርክከው… ሆዳቸውን ወደው፣

እንኳን የሚታረስ መቀበሪያም ነፍገው፣

በዚያው ቀልጦ እንዲቀር ቤት አልባ ከርታታው፣

የራዕይህ ጀግኖች ትግሬን ሰውተዋል ላንተ ክብር ብለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

ወፍ እንኳን ጎጆ አላት የምትገባበት፣

ዜጎች ግን ተንቀው ተቀምተው ንብረት፣

ካ’ባት ከ’ናት ርስት በዐዋጅ ተነቅለው፣

ባይተዋር ሆነዋል ከሁሉም ተገ’ለው፡፡

የለመደው እርሽ የለመደው ጓሮ፣

የኖረበት ሥፍራ ደጁ ተመንጥሮ፣

ለባዕድ ተሸጧል ሀገር አልባ ሆኗል፣

ገመና ከታቹን ቤቱንም ተነጥቋል፣

የሀገሬ ዜጋ በቁሙ ተቀብሯል፣

የሚያወርሰው የለም ለአብራኩ ክፋይ፣

ፍትህን ተነጥቋል ቢጮህም ወደላይ፣

ሥርዓት አልበኝነት ነግሦ ባደባባይ፡፡

ደስ ይበልህ መለስ …. ባለህበት ቦታ፣

ተሳክቷል ጅምርህ እርገጥ ጮቤ ምታ፣

ሞትህን ግን ጥላት… አምርረህ አውግዛት

አገሩን ሲያምሰው … የራዕይህ ውጤት፣

ሳታነሳ ጽዋ …. ሳታደርግ ሃሤት

መውሰዷ ስህተት ነው ማፈርም አለባት፡፡

የመለስ ራዕይ ያመጣብን ጣጣ፣

ወገን ከወገኑ  እንዳይኖረው ዕጣ፣

አንደኛው በሌላው እምነትን እንዲያጣ፣

ጥላቻ ተስፋፍቶ ፍቅር እንዲታጣ፣

ግፍ ተሠርቶብናል ከሆድ የማይወጣ፡፡

“ቡሃ ላይ ቆረቆር” እንዲሉ ሆኖበት፣

በትግሬው ወገብ ላይ ራ’ይ ተጭኖበት፣

ባልበላ ጉልበቱ ሸክም ተፈርዶበት፣

ፍዳውን ይቆጥራል ያምላክ ፍርድ ቀርቶበት፡፡

ማጠቃለያ

ያቺ “አትሸራረፍም፣ አትነካም” ትባል የነበረች የመለስ ራዕይ ሞታ የቀብር ሥነ ሥርዓቷ ሊፈጸም አንድ ሐሙስ የቀራት መሆኑን ለመረዳት ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ሂደት ሰበር ዜና ከሆነ ዋል አደር አለ፡፡

ከዚያ በኋላስ ?  እነሱ አንደሚሉት “ወያኔ ከሥልጣን ከተወገደ ኢትዮጵያ ትበታተናለች” የሚሉት ፌዝ እውነት ይሆን እንዴ? በጭራሽ! እንዲያውም በታሪካዊ ስህተት ከእናቷ የተለየችው ኤርትራ በሕዝቦች መፈቃቀድ በተመሠረተ አዲስ ግንኙነት አንድነት ተፈጥሮ የታፈረችና የተከበረች አዲስ ኢትዮጵያ እንደምትፈጠር አምለሁ፡፡ የወያኔ የእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ዓይነት ራስን የማዋደጃ ተረት ከወያኔ ጋር ይቀበራል እንጂ ኢትዮጵያ በምኞት የምትፈራርስ ሀገር አይደለችም፡፡ ሁሉም በየፊናው በብዙ የሕይወት ውጣ ውረድና የደም መስዋዕትነት ብዙ ትምህርት ስለቀሰም ከአሁን በኋላ በጅልነት የሚጓዝ ሕዝብ የሚኖር አይመሰለኝም፡፡ ጊዜ ሁሉንም ነገር ገላልጦ ያሳየናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሶቪየት ኅብረት ከናዚ ጀርመን ጭፍጨፋ አስጥላቸው ኔቶ ሥር የተሸጎጡ የባልቲክ አገሮች *ከጎርባቾቭ ውሳኔ መዘዝ፤ - ከጌታቸው ወልዩ (ሜክሲኮ ባህረ-ሰላጤ)

ለወገኖቼ እንደማሳሰቢያ፡- በኦረሞና ጋምቤላ አካባቢ እየተካሄደ ያለው የመሬት ንጥቂያና ዘረፋ መቆም አለበት፤ የተበደለና ሀብት ንብረቱን የተቀማም ሊካስና የተዘረፈበት ሀብት ንብረት ሊመለስለት ይገባል፡፡ በአማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ማንኛውም ዓይነት ዘርን መሠረት ያደረገ ግፍና በደል በአስቸኳይ ይቁም፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ታሪክና ትውልድ ለሚወስዱት እርምጃ ውርድ ከራስ!! ለሚመጣው ችግር ተጠያቂው ይህን ግፍና በደል የሚያደርሰው አካልና ተከታይ አባላቱ ብቻ ናቸው፡፡

❖ሁሉንም ወያኔዊ ካርዶች ጥቅም ላይ አውለን ጨርሰናል፡፡ የቀረችዋ አንዲትና ብቸኛዋ ነገር ዜጎችን እርስ በር የማናከስ ካርድም ተነቅቶባታልና ከአሁን ወዲያ አታገለግልም፡፡

❖ የሁለት አኃዝ ዕድገቱ የ25 ዓመቱ ዘፈንም የተበላ ዕቁብ ሆኗል፤ አንድ የዝናብ ወቅት ሲያልፈን በፍየል ጭራ የምትመሰለው የዚች የሁለት አኃዝ ዕድገት ገመና ይወጣና የሕወሓት ቅጥፈት በዓለም ፊት ይጋለጣል፡፡

❖ ”ልማታዊው መንግሥታችን” በድምሩ የ25 ሚሊዮን ዕርዳታ ተጠባባቂ ወገን እንዲኖረን ያደረገ በውሸት ሰነዶች ዓለምን የሚያጥለቀልቅ አባይ(ውሸታም) መንግሥት ነው፡፡

❖ ኦሮሞ ዐምፆአል፣ በአማራው አካባቢ ሰማዩ ዳምኗል፣ በደቡብና በጋምቤላም በኩል ጥሩ ዜና የለም፤ትግሬው ቀየውን እየለቀቀ በብዛት በመሰደድ ላይ ነው…. ምን ቀረን?…. ነገር አለ!!

ይህ ትርጉም ተቀራራቢ እንጂ መሳ ለመሳ አይደለም፡፡ እንኳንስ ግጥም ስድ ንባብም ለትርጉም አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ከዋናው ጽሑፍ በጣም አፈንግጬ ከሆነ በተለይ ጸሐፊውን ኃየሎም አርአያን – ማለቴ – ኃየሎም አሉላን ባጠቃላይ ደግሞ አንባቢያንን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ yinegal3@gmail.com

4 Comments

  1. የትግርኛውም ኣንብቤው; በጣም ወቅታዊ የሆነ ጥሩ መልእክት ነው::

  2. Still you think about eritrea ? eritrea is an independent country ! So how come you wish us a back turn journy ! And waht we will benefiet from the union ? Nothing ob the other hand you guys will benefit if that happen the good thing that will not happen forever ! Let me give u an advise this time is very essential for you guys to continou as ethiopian or not so its better to work hard to keep your counntry from geting woret and this only work by woeking togther with others with respect and love time is up for croked and elates

  3. Yidres le Abebe Gellaw; ye meseriwen anget lasdefawu;balem adebabay leawaredewu.” ABE LEB BEL”YEBASE DEDEB haylemariam metobenal.

Comments are closed.

Share