አገር በሕወሓት ቀጥተኛ አገዛዝ ስር

ኦሮሚያ በወታደራዊ አገዛዝ ስር የሚለውን ቀድመው  በወታደራዊ አገዛዝ ሰር የገቡትን የኦጋዴን የጋንቤላና የአፍር ክልልችን ጨምሮ በአሁኑ  ጊዜ ኢትዬጵያ  በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቃለች ማለት ይቻላል።  ስላሉት ነው እንጂ ጉዳዩን ወታደራዊ የሚባል ነገር  የሚገልፀው አይደለም።  ወታደራዊ አመራሮቹ በሙሉ ከአንድ ዘርና ድርጅት መሆናቸውን የምናውቀው ነው።  ህዋዋት ተቆጣጠረው መቼም እንዲሉ አይጠበቅም።  ለሁሌው ህዋዋት የሚታዘዙለትንና የተመቹትን ከሌሎች ብሔረሰቦች ይዞ በፍፁም የበላይነት ገዥ ነው። ይህም ሆኖ እንኳ እስከጭራሹ “ትግሬ” ያልሆኑ መኖራቸው ሰላም ሰጥቷቸው አያውቅም። ለዚህ ቶሽ ባለና አደጋ በሸተተቻው ቁጥር ተሯርጠው ስልጣኑን ይቀበሏቸዋል።  ሰብስቦ ማሰር የተለመደ ነው። በአንዴ እስከ ሶስት መቶ የሚደርሱ ተሰብስበው የታሰሩበት ጊዜ አለ። የተገደሉም እንዲሁ። ለተጣመሯቸው ወከልነው ያሉትን ህዘብ ባደባባይ ማዋረድና  ተቃርኖ መቆም ያገልግሎታቸው አንዱ ክፍል ግዴታም ነው። ወገኖቻቸውን ማስገደል ማሳሳር ማስደብደብም ቢያማቸውም እንዲሁ። ሌላ ቀርቶ አገልጋዬች የነበሩ ሸሽተው ሂወታቸውን አትርፈው  ነፃነታቸው ግን አሁንም በህዋዋት እጅ ያለ ብዙ መሆናቸውን እየሰማን ነው። በመሳቀቅ የሚኖሩትን እግዚአብሔር ይቁጠራቸው። ያው ሁሉም ናቸው። ለምን? የሚለው ቀላል መልስ የለውም። ለሚታገለው ይህ መሆኑ  ቢያሳዝንም ይጠቅማል።

በወታደራዊ አመራር ስር የሚለው እንደተለመደው  ያሉትን አስተዳደራዊ መዋቅሮች በሙሉ የናቀና ህልውናቸውን አጠራጣሪ አድርጓል። እያጫጫቸውም እየሄደ ነው። ። ጠቅላይ ሚንስትር ምናምነቴ፤ ፓርላማ፤ ምክር ቤት፤ ፌደራሊዝም፤  የከልል መንግስታት፤ሚኒስቴር ማስራቤቶቹን ሁሉ ጨምሮ። ያም ሆኖ መፈንቅለ ወታደር ግን አይደለም። መፈንቅለ ወታደር የሚሆነው ህዋዋቶችን በልተው የሌላ ብሄር የበታች ሹመኞች ቢመጡ ነበር።  ለዚህ የተመቻቸ ሁኔታ እየተፈጠረ ግን ይመስላል።  የሚያስፈራ ደግሞ አይደለም። የለውጡ አጋዥ አካል እንጂ ወታደራዊ መንግስት የመሆን እድላቸው ለነሱም የሞተ ነው። ዘመኑም የመሀበረሰባዊ እድገታችንም ይህን አይፈቅድም። ሂደቱ ያለየለትና ግልፅ ብሎ የሚታይ አይደለም ለጊዜው።  ምሁራኖቻቸው ግን እራሳቸውን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በሚመስል ነገር እንደእስስት  ቀይሮ ትንሽ ማሻሻያ አድርጎ መምጣቱን እንደ አንድ ማምለጫ ብልሀት አድርገው መምከር ከጀመሩ ከራርመዋል።

የቸገረው ነው ነገሩ። ጠቅለል አድርጎ ፍፃሜያቸውን ሊያደርጉ  ወደ ሚችሉና አቅሙና ፍላጎቱ ወዳላቸው ነው የተጠጉት። ፖለቲካዊ ውጥንቅጡን ያስተላለፉት ማለት ይቻላል። ጥሩነቱ ከአጋር ድርጅቶች በላይ  መሳርያ የያዘው ክፍል የህዋዋት የበላይነት እንዲያከትም የሚፈልግበት ምክንያቶች የበዛ ነው። ምሬቱና የለውጥ ፍላጎቱ  አሁን እየተጨፈጨፈ ካለው የኦሮሞ ህዝብም በላይ ነው ቢባል ማገነን አይሆንም። በዛ ላይ በሂደቱ  ወደመጡበት ህዘብ ጋር ነው የሚያደባልቃቸው። ስለዚህ እነሱም ያምፃሉ። ለዚህ  የዚህች አገር ችግሮች ህዋዋቶች መሆናቸውን ማወቃቸው ብቻ አይደለም። ዋናው ቁም ነገር ችግር ፈጣሪዎቹ ተለይተው ግልፅ ብለው ትንሽ ስብስቦች ሆነው ከመቼውም ጊዜ በላይ  አንሰው መታየታቸው ነው።  ከህዘብና ከነሱ ለመምረጥ ቀላል ሆኗል። በተጨማሪም የስርአቱን መበስበስና መበሳበስ ከውጪ ካለነው በላይ አብረዋቸው በቅርብ ላሉት ግልፅ ብሎ የሚያዩት ነው።  መሳርያ በጁ ያለውን በተመለከተ ለኛም ለነሱም አብሪ የሆኑ ለጥቃቅን ነገሮች ጥቃቅን የሆኑ አመፆችን በበቂ የማናየው የማየምች ስለሆነና አደጋው ስለሚሰላ ነው። እንደ ኦፒዲዬ ማለት ነው። ከውስጥ ስትሆን ጊዜና ሁኔታዎችን ታሰላለህ። ጠቅለል ባለ መልክ መሳርያ በጁ ባለውና በአንባገነን ገዥዎች መሀል ያለው ጠቅላላ ግንኙነት እዚህ ደረጃ ሲደርስና ይህን አይነት መልክ ሲይዝ የህዝብ አልገዛም ባይነት እየጠነከረና እየሰፋ ሲሄድ የሚሆነው  አንዴ በትልቁ ይፈነዳል። ያኔ ከቅርብ አለቆች በመጀመር በሚያስጎመጉም ሁኔታ በአንድ ቀን ውስጥ ግልብጥብጡ ይወጣል። መረሳት የሌለበት ያው ይገላሉ፤ ያስራሉ.. ምን አዲስ ነገር አለው እያለ ሊገለፅ በማይቻል ቁርጠኛነትና ወኔ የሚታገል አዲስ ትውልድ ስርአቱ ፈጥሯል። ባለመሳርያው ከዚሁ ትውልድ  ውስጥ ነው። መገደለን የማይፈራ ትውልድ ገድሎ ነፃነቱን ማወጁ የማይቀር ነው።

በአጠቃላይ ወደመጡበት የሚለውን ትንቢት እየሰሩት ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ በላይ ማለቱ  ጉዳት አለው። መንገዱችሁን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብለን እንዝጋው። ወናው ነገር እያጋመ ላለው ህዛበዊ አልገዛም ባይነት ይህ ውሳኔ ለጊዜውም ቢሆን አሉታዊ ተፅኖ አለው ወይ? የሚለው ነው። “ጦርነት ከኤርትራ ጋር”። “ችግሩ የመልካም አስተዳደር ነው”። “ተገንጣዬች ናቸው”። “በወታደራዊ አመራር ስር”  ፖለቲካ ላይ  የጅምላ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማድረግ አመፁን ልናዳፍነው እንችላለን እቅዳቸው ነው። እነ ልደቱ ሁሉ አስተዋጿቸውን ተጠይቀዋል። በወታደራዊ አመራር ስር የሚለው ለጊዜው በመሬት ላይ የሚለውጠው ምንም ነገር የለም። አስፈራሪነቱን እንጂ እነሱም ይህንን ያውቁታል። ሲጀምር የኦሮሞ ህዘብ  ጨፌን ሊቃወም አደባባይ አልወጣም። የዘረፈውም የጨፈጨፈውም ኦፒዲዬ አይደለም። ኦፒዲዬዎች ግን ኦሮሞዎች ናቸው። በአጠቃላይ ህዋዋቶች የሚያጡት እንጂ በፊት ያልንበረ አሁን የሚያገኙት አዲስ ጉልበት የለም። ህዝቡ ይህንን አሳምሮ ስላወቀ አልገዛም ባይነቱን አበርትቶ ቀጥሏል። እንቢታው እየሰፋ አገራዊ መልክ እየያዘ ነው። ሌላው በቀጣይ የሚታይ ይሆናል። አንድ ጊዜ ላይ “መግደልም ይቸግራል” ብሎ ነበር ዶ/ር መራራ።

መሪን በሚመለከት።
በአደዋ ጦርነት መሪን ማጣት ወታደሩን እንደሚፈታው ከፄ ዮሀንስ አሟሟትና ሽንፈት ትምህርት  መወሰዱንና ተገቢው ጥንቃቄ መደረጉን  “አፄሚኒልክ ጦርነቱ ላይ ከፊት ለፊት አልነበሩም” ለሚል ትችት የተሰጠ መልስ ላይ ቆየት ቢልም አንብቤያለው። ይህን ያነሳሁት “መሪ ከፍትለፊት መሆን አለበት”። “መሪ የግድ አገር ውስጥ መሆን አለበት” ስለሚመሳሰሉ ነው። ክፍት ባይኖራቸውም ትክክል ቢመስሉም ቅሉ ዶግማ እየሆነ ትግሉን እየጎዳ ግን ነው።  ይህ ህዝባዊ እንቢታ ከተነሳ እንኳ ብዙዎች አስረገጠው ተናግረውበት አድምጠናል። ፅፈውበት አንብበናል። ሀሳቡ ካንጀት  የታመነበት ስለሆነ መሪ ሆኖ ወጥቶ ለመምራትና አቅጣጫ ላማስያዝ አይደለም ከውጭ ሆኖ ቃል አቀባይ መሆን እንኳ ችግር እየሆነ ነው። ጊዜው ትግል የሚገባቸው ብዙዎች አንድ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው ከፊትለፊታቸው ጥቁር ሰሌዳ ለጥፈው። ትልቅ ካርታ ሰቅለው። ቾክና እስቢል ባለበት፤ ስልክ አሁንም አሁንም በሚጮህበት ብዙ ወረቀቶች ጠረቤዛ ላይ ተደርድረው ፀጉር ሲነጩ ማደርን በፈረቃ ሁሉ ቀንና ሌሊት የሚሰሩበትን ሁኔታ ግድ የሚል ነው። አገር ውስጥ ይህን ማድረገ አይቻልም። ስለዚህ መስራት የለበትም ወይ?። እንደጎደለ በደንብ ይታያል። መራራ በሆነ መሰዋትነት ውስጥ መሬት ላይ የሚሰሩና እያስተባበሩ ያሉ ብዙ መሪዎች አሉ። ጉድለታቸውንና በነሱ ያልተቻላቸው በሚችሉ ሊሰራ ግን ይገባል። እየጠበቁም ነው። መሰዋትነቱን መና እንዳናስቀረው አንጃጃል።

ትግሉን በሚመለከት።

የኦሮሞ ህዘብ አልገዛም ባይነቱን ቀጥሏል። እየሰፋና ቀስ እያሉ ሌሎችም እየተቀላቀሉበት አገራዊ መልክም እየያዘ ነው። የህዋዋት እስትራተጂም ሆነ የህዘብን ትግል ለማንቋሸሽ የሚሯሯጡ ክፍሎችና ትግል አረጋጊዎች መባትል ሊገታው አልቻለም። ወያኔ ከመደንዘዝ ውስጥ ወጥቶ አንዳንድ ነገሮችን ሲሞክር እንኳ ታቃዋሚዎች ግን እንደደነዘዙ ነው። በእንቅልፍ ልብ ውስጥ ሆነው እንቢታው ሲጀመርና ግድያ ሲከተል የአቋም መግለጫ ነው የሚባለው ነገር ጫጭሩና ተመልሰው ተኙ። አልገዛም ባይነቱም ጭፍጨፋወም አራት ወር ሊሞላው ነው። እንቅልፍ ላይ ባይሆኑ ሌላ ማድረግ ባይችሉ ጭፍጨፋወን እንኳ እንዲሰማ አድርገው ደጋግመው ማውገዝ በቻሉ ነበር። ካንጀት ቢሆን ከህዘብ ትግል ጎን የሚያቆማቸው ብዙ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸው ነገሮች ደግሞ አሉ።

ኦሮሞዎች እየደረጉ ያሉትን ትግል ለመደገፍ የሚቀመጡ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎች ይሰማሉ። ማድረጉ ክፋት የለውም። ብሔራዊ ጭቆና ይብቃ ብሎ መፈክር ይዞ መውጣት ይቻላል። አፍ ለማዘጋት ይጠቅም እንደው እንጂ ጠያቂዎቹን ግን መቼም ተባባሪም ትግሉን በመልካም እንዲያዩት አያደርግም። ዜጋው የጋራ የሆነው ጭቆና የተፈጠረ መልካም አጋጣሚን መጠቀም ካወቀበት ብቻ አብሮ ይታገላል አለቀ።  እያየን ያለነውም ይህንኑ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው ቅድመ ሁኔታና የጠያቂ መዓት ለማለት ያህል ብቻ ነው። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው ነገሩ። ይህንን የስልምና እምነት ተከታዬች ትግል ወቅት ታይቷል። በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ብዙ ጥረዋል። ያም ሆኖ ጥያቄው ተለጥቶ ግብፅ ውስጥ ለተገደሉ ክርሲቲያኖች ይቅርታን ካልጠየቁ የሚል ድረስ ሄዷል። ስለሌው ቅኝት መፃፍ ቀላል ነው። የራስን ቅኝት ማስተካከሉ ነው ከባዱ የሆነው። ያኔም ሆነ አሁን ይህን አይነቱ ሰበብ  የህዝብን ትግል ለማንቋሸሽ ሲባል የሚደረግ ነው። ስለዚህም በትልቁ የተሳሳተ ነው።

ስለቅኝት ካነሰው አይቀር ዘንድሮ ያደዋ ድል ልዩ የሆነ ትኩረት ተሰጥቶታል። ያከበርነው ግን አደዋን ሳይሆን አፄ ሚኒልክን ነበር። ይገባኛል መሪ ስለነበሩ ትልቅ ቦታ አላቸው። ያም ሆኖ ማንም የማይክደው የአደዋ ተጋድሎ ከሚኒሊክ በላይ ነው። የዜጎች ለነፃነት የተደረገ ታሪካዊ ተጋድሎ ነው። አንዳንዶች ቁስላቸው ላይ አመድ ደምድመው ነው አደዋ ላይ ደግሞ የተዋጉት። ከገባን ጀግንነት ይህ ነው። ያም ሆኖ አወንታዊ በሆነ መንገድ ተጠቅመንበት ቢሆን መልካም ነበር። ለርካሽ ፖለቲካ ፍጆታ ሲባል አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ አፅማቸውን አውጥተን መንጋጋና መንጋጋቸውን ይዘን ስንሳደብባቸው ነው የከረምነው። አደዋን መቃወምና ሚኒልክን መቃወም ምን እንዳገናኘው በጭራሽ አልገባኝም። አፄ ሚንሊክ ለረጅም ጊዜ አገር መርተዋል። አሁን በሂወት የሉም። ይጠቅማል ብሎ ደረቱ ላይ ለጥፎ እንደሚሄደው ዘቅዝቆ የሚለብሳቸው ካለም መብቱ ነው። ያለበለዚያ አፄ ሀይለስላሴ ስለተሸነፉ ሁሉ መልካም ስራቸው ይንቋሸሽ። መንግስቱ የሱማሊያ ጦርነት ወቅት መሪ ስለነበር ምንም ክፉ ነገር ስለሱ አይነገር። የሚያስፈራኝ መለስ ዜናዊን መቃወም የህዳሴውን ግድብ መቃወም  እንዳይባል ነው። በዛ ላይ አያቶቻችን ያን ሁሉ መሰዋትነት ከፍለውበት አሁን ከአገር አገር የለን።  ከነፃነት ነፃነት የለን። ማክበራችን ካልቀረ አሳልፈን የሰጠነውን ለማስመለስ ቁርጠኛነትን የምናሳይበት ቢሆን አይሻልም ነበር ወይ።

ዳዊት ዳባ
Monday, March 07, 2016

1 Comment

  1. Dave it is good and clear opinion. But I do not know how pepole see things. Pls pepole be good for your self and for others too. You can be free unless you accept the truth. The truth here is peploe strugle for thir existance. We are in the bottom……..got it.

Comments are closed.

Previous Story

አድዋ የድል አምባ (ተፈራ ድንበሩ)

Next Story

በኢትዮጵያ የመኪናው አምራች ድርጅት ሃገሪቱን ባመሳት የውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ በምርት ላይ ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ

Go toTop