ሰበር ዜና፡ ጳጳሳት የፓትርያርክ ምርጫው ወደ ግንቦት እንዲዛወር ጥያቄ አቀረቡ

(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ የቤተክህነት ምንጮች እንዳረጋገጡት የሲኖዶሱ አባቶች ለሁለት መከፈላቸውንና አብዛኛው አባቶችም አቡነ ሳሙኤል እንዳይመረጡ ግፊት እያደረጉ ቢሆንም በተለይ ከወ/ሮ አዜብ ሕወሓት ድጋፍ ያላቸው አቡነ ሳሙኤል ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው ለመቀመጥ ተግተው እየሰሩ መሆኑን አድርሰውናል። ድረ ገጻችን የቴክኒክ ችግሮች ስለነበሩበት የዚህን ዜና ትንታኔ በድምጽ ያዳምጡ።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ የሚከተለውን ዘገባ ጽፏል
አቡነ ሳሙኤል ቀጣዩ ፓትሪያሪክ ለመሆን
የምረጡኝ ዘመቻ ጀመሩ

(በጋዜጣው ሪፖርተር)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስን የሚተካ ስድስተኛው ፓትሪያሪክ ለማስመረጥ በዝግጅት ላይ ትገኛለች። ከዚህ የፓትሪያሪክ ምርጫ ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስትያኒቷ የተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስና ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩበት ወቅት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው የነበሩት አቡነ ሳሙኤል በቀጣዩ ምርጫ ስድስተኛው ፓትሪያሪክ ሆነው እንዲመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የቤተክህነት አመራሮችን፣ የተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ስራ አስኪያጆችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በማግባባት ላይ መሆናቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ለዚህ ይረዳቸው ዘንድ ከፍተኛ ገንዘብ መድበው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በጥቅምት ወር በተካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን 31ኛው ጉባኤ ወቅት ተሳታፊ ለነበሩ ቁጥራቸው ወደ 900 የሚጠጋ ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተሰባሰቡ ተሳታፊዎች 500 ሺህ ብር በአበል መልክ እንዲከፈል አድርገዋል። ይህም ለሚካሄደው የፓትሪያሪክ ምርጫ ይጠቅማቸው ዘንድ ያከናወኑት መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
አያይዘውም ገንዘቡ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ለሚሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲውል ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የተገኘ እንደሆነና ተሳታፊዎቹም ከየሀገረ ስብከታቸው አበል ተከፍሏቸው የመጡ መሆናቸው ነገር ግን አቡነ ሳሙኤል ተወዳጅነት ለማግኘት ሲሉ የልማት ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስነታቸውን በመጠቀም ገንዘቡ ለተሳታፊዎች እንዲበተን ማድረጋቸው ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።
በዚህ የምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት ድምፅ ለሚሰጡዋቸው እና ከጎናቸው ለሚሆኑ ሰዎች ፓትሪያሪክ ሆነው ከተመረጡ በኋላ በተሻለ የኃላፊነት ቦታ እንደሚሾሟቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው የውጭ ዕድል እንደሚያመቻቹላቸውና ቤተ ክርስትያኒቷ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በምታስገነባቸው ህንፃዎች ውስጥ የንግድ ቦታ እንደሚሰጧቸው ቃል እየገቡላቸው እንደሆነ ምንጮቻችን አስረድተዋል።
ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ በአዲስ አበባና በአሜሪካው ሲኖዶስ መካከል ሲደረግ የነበረው እርቀ-ሰላም እንዲቋረጥ እና የቀድሞው ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ አቋም ከነበራቸው ጳጳሳት መካከል አቡነ ሳሙኤል ግንባር ቀደሙ እንደሆኑ ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ከዚህ በተጨማሪ አቡነ ሳሙኤል አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናትን እንዳግባቡና መንግሰት ፓትሪያሪክ ሆኜ እንድመረጥ ይፈልጋል የሚለው አቡነ ሳሙኤል ተናግረውታል የተባለው ወሬ በአሁኑ ሰዓት በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ በሰፊው እየተነዛ ይገኛል። አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳትንና የቤተ ክህነት አመራሮችን በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርን ሲሆን አቡነ ሳሙኤል እያደረጉት ያለው ተግባር ከአንድ ኃላፊነት የሚሰማው የሀይማኖት አባት የማይጠበቅ እና ሀይማኖታችን የማይፈቅደው ተግባር ነው ብለዋል። ፓትሪያሪክነት የሚገኘው በምረጡኝ ዘመቻ ሳይሆን በአምላካችን ፈቃድ ስለሆነ ምዕመናን ቤተ ክርስትያኒቷን በበለጠ መንገድ የሚያገለግላት ፓትሪያሪክ ቸሩ እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው በፀሎት ላይ መሆናቸው እና ፀሎታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እየመከሩ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ይገልፃሉ።
አቡነ ሳሙኤል ዕድሜያቸው ከ50 የማይበልጥ በመሆኑ እና በስነ ምግባራቸውም በተደጋጋሚ ከሲኖዶሱ አባላት ጋር ግጭት ሲፈጥሩ የነበሩ አባት በመሆናቸው ለቤተ ክርስትያኒቷ ትልቅ ኃላፊነት እንደማይመጥኑ አንዳንድ ምዕመናን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የአስመራጭ ኮሚቴው ባወጣው መርሃ ግብር መሠረት በዕጩነት ከቀረቡት አምስት አባቶች መካከል የሚመረጡት 6ኛው ፓትሪያሪክ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በዓለ ሲመታቸውን ይፈፀማል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የፓርላማውን ሥልጣን በመጣስ ዳኞችን ሰይሟል - የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ማኅበር

2 Comments

  1. We need to know who killed Abune Poulos…..I heard that some one intoxicate the pop …..The Ex pope was also fought with Abune Samuel, the one who is curruntly running to be the newly elect POPe…I think there is some conspiracy……
    God Bless Ethiopia
    and Death to Woyane

  2. ጋለሞታዋ እጅጋየሁ ሙሉ ለሙሉ የገዛቻችሁ ይመስላል። እሷና የሷ የሙስና አባላት መሆን አለባቸው መጨበጫ የሌለው አርቲ ቡርቲ የሚያስወሯችሁ። አቡነ ሳሙኤልማ ቤተ ክርስቲያኗ ማንም ባልነበራት ጊዜ፥ ጋለሞታዋ በአባ ጳውሎስ ተመክታ ሙስናዋን ስታጧጡፈው ከጎኗ የቆሙ ጋለሞታዎቹም በመፅሃፍ ሳይቀር ስማቸውን ሲያጠፉት የከረሙ አባት ናቸው። የዛሬውም ይህ ፅሁፍ የዛ ዘመቻ ቀጣይ ምዕራፍ ነው። አንተም ሳታውቀው የሷ መጠቀሚያ ሆንክ። በአቡነ ጳውሎስ ሞት ቀኑ የጨለመባቸው ተሃድሶዎቹና ሙሰኞቹ የጨለማው ቡድን አባላት በአቡነ ሳሙኤል መመረጥ የመጨረሻ የሬሳ ሳጥናቸው በምስማር ይመታል። ይህ ከመሆኑ በፊት ቢንፈራገጡ፥ ቢላላጡ ምን ይገርማል? 

Comments are closed.

Share