ይችን ሁለትና ሶስት ወራት የማስተር ፕላኑን ግርግር ተገን በማድረግ ኤርትራዊዉ የሻብያ ሰላይ ተስፋየ ገ/አብ መርዛማ ሀሳቦችን ዳግም ሊያዘንብብን ሲወራጭ እያየን ነው።እነ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻና አለማየሁ ከቀበሩበት መቃብር ዉስጥ ድንጋዮችን እየፈነቃቀለ፣ ያለበሱትን አፈር እየጠራረገ ወደ ሚዲያዉ ለመግባትና እኩይ ስራዉን ለመቀጠል ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል። ይህ ግለሰብ ማንም እንደሚረዳዉ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ለምትባል ሀገር በተለይ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ የመረረ ጥላቻ ያለው ሰዉ ነው።ይህንንም ጥላቻውን በገሀድ የሚናገርና ከዚህም ቀደም በሰራቸው ስራዎቹ ከባድ የሚባል ጉዳት ያደረሰ የሀገርና የሕዝብ ጠላት ነዉ።
እስኪ እንደመግቢያ ጥላቻ (Hatred) ምንድን ነዉ ?? ብለን እንደርደር።
ጥላቻ ማላት በጣም በመረረና ከመጠን ባለፈ ሁኔታ አንድን ነገር ያለመዉደድ ስሜት (deep and emotional extreme dislike) ነዉ ። በአጠቃላይ ሲታይ የጥላቻ መሰረታዊ ምንጮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያዉ አንደ ግለሰብ ላይ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ የሆነ ከባድ በደል ሲፈፀም ፤ ለምሳሌ ጥረዉ ግርዉ ያፈሩትን ሀብትና ንብረት መዘረፍ ፣ በግዴታ መደፈር፣ በጣም የሚወዱትንና የሚሳሱለትን ሰው ላይ የግድያ ወንጀል ሲፈፀም የሚፈጠር ጥላቻ ነዉ። ሁለተኛው ነጮች Learned hatred የሚሉት በአስተምሮት የሚወረስ ጥላቻ ነዉ። ይህ አይነቱ ጥላቻ መሰረቱ እዉነት ወይንም ዉሸትም ሊሆን ይችላል።አባቶች በዘመናቸዉ የተፈፀመ ግፍ ነዉ የሚሉትን ፣ ወይንም በአባቶቻቸዉ ዘመን ተፈ ፅሞ ነበር ተብለዉ በዉርስ የተቀበሉትንና መወራረድ አለበት ብለዉ የሚያስቡትን ግፍ ለልጆቻቸዉ በትምህርት ያወርሳሉ።ልጆችም ከሚወዶቸዉ ወላጆቻቸዉ የወረሱትን የጥላቻ ዉርስ ከቻሉ በእነሱ እድሜ ለማወራረድ ይሞክራሉ ካልተቻለ ደግሞ እነሱም ለሚወልዶቸዉና ለሚወዶቸዉ ልጆቻቸዉ አዉርሰው ያልፋሉ።
ሌላዉ ጥላቻ (Hatred) አድማሱም ይለያያል። ለምሳሌ አንድ ግሰብ የሚጠላዉ ግለሰብን፣ ቡድንን ወይንም ቡድኖችን፣ ዘር (ነገድን)፣ ሀገር ሊሆን ይችላል።አንዳንዴ ደግሞ ቁሳዊ አካል ፣ባሕሪን ፣አመለካከትን እና የመሳሰሉትን አምሮ ጠልቶ መከራዉን የሚያይ ሰዉም ይኖራል። ከላይ በተዘረዘሩት በአንዱም ሆነ በሌላ ምክንያት የሚፈጠር የመረረ ጥላቻ በሽታ ነው። ከመጠን ያለፈ ጥላቻ ብስጭት፣ፍርሀትና ጭንቀት ይፈጥርና የሰው ተፈጥሮአዊ በሽታ የመከላከል አቅም በማዳከም ከፍ ሲሊም ጨርሶ በማጥፋት የበሽታዎች ቁንጮ ለሆነዉ ካንሰር (cancer) ለተባለዉ ገዳይ በሽታ መፈጠርና በአጭር ግዜ መስፋፋት ምክንያል ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ በመስኩ ያሉ ጠበብት። ለገሰ ዜናዊ የዚህ ተጠቂ ነበር።ለካንሰሩ መፈጠር አማራ ላይ የነበረዉ እጅግ የመረረ ጥላቻ ፣ ካንሰሩ በአጭር ግዜ (በአንድ ወር ዉስጥ ብቻ) የመጨረሻው ደረጃ ላይ እንዲደርስ ደግሞ አበበ ገላው በዓለም ፊት ያደረሰበት ማሸማቀቅ ከፍተኛ ሚና ነበረው።
ጥላቻ አመለካከትን የማዛባት አቅም አለው። በተፈጥሮ የአንድ ጤነኛ ሰዉ ጭንቅላቅ ዲዛይን(design) የተደረገዉ ጠንካራና አሳማኝ በሆኑ መረጃዎች ላይ እየተመሰረተ ጠቃሚና ችግር ፈቺ የሆኑ ሀሳቦችን እንዲያፈልቅና ዉሳኔዎችን እንዲያሳልፍ ነዉ።ችግሩ ይህንን የተፈጥሮ ሀብታችንን በመልካም ስነምግባርና በትምህርት ተንከባክቦ ፣ ኮትኩቶ የሚያበለፅገው ሀላፊነት የሚሰማው ቤተሰብ፣ማሕበረሰብና ተቋማት ያስፈልጉታል።ያ ሳይሆን ቀርቶ ህሌናን በዘር ከአባት ከሚወረስ ወይ ደግሞ ለአንድ የተወሰነ አላማ ሲባል ብቻ በሚፈጠር የውሸት ድርሰትን አንብቦ ጭንቅላትን በክፋትና በተንኮልን ሞልተን ካሳደግነዉ በጥላቻ ይታወራል። ጥላቻ አመለካከትን ያንሸዋርራል ። ከፍ ሲልም ደግሞ ከነ አካቴዉ ያጠፋና ጭንቅላት ግልብና ግብታዊ የሆኑ ድርጊቶች ላይ እንዲተጋ ይሆናል።
ወደ ዋናው ሀሳብ ልመለስ። አንድ ሰው ለአቅመ አዳም/ሔዋን ሲደርስ ለእርሱንም ሆነ ለቤተሰቡን ቀለብ መስፈሪያ ስራ መስራት ግድ ይለዋል።ጎልማሳው ተስፋዮ ገ/አብም እንደ ማንኛዉም ሰዉ ስራ አለው።ተቀጣሪነቱ ለአባት ሀገር ኤርትራ የደንነት ቢሮ ዉስጥ ሲሆን የስራ ድርሻዎቹ ሁለት ናቸዉ።
>> የመጀመሪያ ግዳጅ ለኦነግ ሰዎችና ደጋፊዎች መታገያ የሚሆን የፈጠራ ድርሰት እየደረሰ በሕዝቦች መካከል ጠላትነትን ማንገስ ነዉ። ከዛም አባት ሀገር ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ጎልታ ትታይ ዘንድ ትናንሽና ደካማ ጎረቤት ሀገራት እንዲፈጠሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ።ይህንን ተልኮዉን ባብዛኛው አጥጋቢ በሚባል መልኩ ያገባደደዉ ይመስላል ። ይህ መርዘኛ እባብ በኢትዮጵያዊነትና በደራሲነት ዉስጥ ተደብቆ፤ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሸረባቸዉ ሴራወቹ ነፍስና ስጋ ነስተዉ በአካል በመካከላችን ሜንጫቸዉን እያወናጨፉብን ነዉ። እነዚሁ ክፉ ቡድኖች “ሰዉ እና እንጨት ተሰባሪ ነዉ” በማለትም ከግለሰቦችም እድሜ በላይ ይኖሩ ዘንድ ቆሚ የጥላቻ ሀዉልት ተክለዋል።
>> ሁለተኛዉ ግዳጅ ዛሬ ዛሬ እንደ ዋና ሙያ አድርጎ የያዘ ስራ ደግሞ በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ አማራንና የአማራ የሆነዉን ሁሉ መዝለፍ፣ማሳነስና ማጥላላት ነዉ። ይህ ከይሲ የአማራ ጠላት በትምባሆና በአልኮል ከገለማ ሳምባዉ ዉስጥ የሚወጣዉን ፀያፍና መርዛማ ጠረኑን አማራን እንዲሸተዉ አድርጎ ነዉ የሚተነፍሰዉ። ይህንን ፀያፍ ጠረኑን ደግሞ ንፋስ ሆነው ተሸክመው በመላዉ ዓለም ለሚገኙ አማራ ወገኖችና ለአማራ ጠላቶች የሚያደሱለት ሚዲያዎች ሰሞኑን ተበራክተዋል።
ሚዲያን ካነሳሁ ዘንድ አንድ ትዝብቴን ልግለፅ። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የአንዳንድ ሶሻል ሚዲያዎች ነገር ግርም ነው የሚለኝ። መችም እያንዳንዱ ሶሻል ሚዲያ ከቢዝነስነት ያለፈ አንዳች ዕራይና ግብ አለዉ ብየ ነዉ የማስበዉ። ዕራይና ግብ ደግሞ እንደየ ሶሻል ሚዲያ ባለቤቱ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል እሙን ነዉ። ለምሳሌ የፓርቲ/የቡድን/ የድርጅት ልሳን ከሆኑ የፓርቲውን/የቡድኑን/ የድርጅቱን ዕራይ በሚያሳካ መልኩ ነዉ የሚንቀሳቀሰዉ ። ከየትኛውም ቡድን/ፖርቲ/ድርጅት ውጭ ሆነዉ ሀገራዊ አጀንዳ ካለዉ ደግሞ ለሀገር መፃሂ እድል ይጠቅማል በሚል ማእቀፍ ዉስጥ ሆኖ ይሰራል። ይህንን መሰል ሚዲያዎች በሕብረተሰቡ ዘንድ ያሉ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በማንሸራሸር ትዉልዱ ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያገኝ የሚል ሰፉ ያለ ዕራዮ ይዘዉ ይንቀሳቀሳሉ። የሚዲያዉ ኤዲቶሪያ ቦርድም ስራዉ የሚሆነዉ በሚዲያዉ የሚተላለፈዉን መልክት በተቀመጠለት አቅጣጫ መሆኑን ለመከታተል ይሆናል ማለት ነዉ። ከዚህ አንፃር ስናየዉ አንድ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ ዘመን ሊሻገር የሚችል ከባድ ደባ የፈፀመን ግለሰብ ሊያስተናግድ የሚችል ኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ስም የሚንቀሳቀስ ሚዲያ ማየት እጅግ የሚደንቅ ነገር ነዉ።
እርግጥ ነዉ የዚህን መርዝ ግለሰብ ሀሳቦች ማስተናገድ “ሀሳብን በነፃነትና ያለገደብ መግለፅ” ከሚላዉ ዋና (basic) ከሚባሉት የሰዉ መብቶች ጋር እያነፃፀሩ የሚሞግቱ እንደሚኖሩ እገምታለሁ። አዎ ማንም ሰው በነፃነትና ያለ ገደብ ሀሳቡን የመግለፅ ሰባዊ መብት አለዉም ይገባልም። ነገር ግን አንድ መገደፍ የሌለበት ሀቅ አለ።ከአንዳንድ ከባድ ወንጀለኞች ላይ ሀሳባቸን የሚገልፁበትን መብት ብቻ ሳይሆን ሕይወታቸዉንም የመንጠቅ የሕግ አግባብ መኖሩን መርሳት አይገባም። በዓለም ላይ ባሉ አብዛኛ ሀገራት ዉስ እንደ ከባድ ወንጀል የሚወሰድና የወንጀለኛውን ሕይዎት እስከመንጠቅ የሚደርሱ ጥፋቶች መካከል አንዱና ዋናዉ በሀገር ላይ ክህደትን መፈፀም ነጮች treason የሚሉት ነዉ። ከፍተኛ ክህደት (High treason) ዉስጥ ከሚካተቱ ወንጀሎች አንዱና ዋናዉ ደግሞ የሚኖሩበትን ሀገር በመሰለል(spying) መረጃዎችን ለሌላ አካል ማቀበል የሚለዉ ነዉ። እንግዲህ ይህ ግለሰብ ይህንን ወንጀል መፈፀሙ በማያሻማ መረጃ እጅ ከፍንድ ( red hand) የተያዘ ወንጀለኛ ነዉ።ዛሬ ግለሰቡ በሚስጥር ሲሰራዉ የነበረዉን ሀገር የማጥፋት፣ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ስራ በብርቱ ዜጎች ማንነቱ ተጋለጦ ፀሀይ የሞቀዉ ጉዳይ ሆኖል። የሀገርና የሕዝብ ፀር መሆኑ ተረጋግጦል። ይህ በሆነበት ሁኔታ የዚህን ግለሰቡ መርዛማ ሀሳቦቹን ለሕዝብ ጆሮ በማድረስ እየተባበሩት ያሉት ሶሻል ሚዲያዎች አላማቸው ምንድን ሊሆን ይችላል?? ብየ እራሴን ደጋግሜ ጠይቄ መልስ ማግኘት እቸገራለሁ።
እንደገናንወደ ዋናው ሀሳብ። የዚህ ግለሰብ ጥላቻ ከማንና ለምን የሚሉትን ሁለት ጥያቄዎች እንፈትሽ። ይህ ግለሰብ ከማን ጋር ነዉ ብለን ስናይ እንደ ሀገር ከኢትዮጵያና እንደ ሕዝብ ደግሞ አምርሮ የሚጠላዉ የአማራዉን ብሔር ነዉ። በመሰረቱ አንድን ሕዝብን ብሔር መጥላት ጤነኛ ጭንቅላት ካለው አካል ሰው የሚጠበቅ ነገር አይደለም። ጅልነትም ነዉ። አንድ ግለሰብ በተለያዩ ምክንያት ሌላዉ ሰው ወይን ቡድን ሊጠላ ይችላል። ቡድን ሊፈርስና ሊጠፋ የሚችል ነገር በመሆኑ ጥላቻዉም አብሮ ሊጠፋ ይችላል ተብሎ ይታሰባል። ግለሰብም ከሆነ ከአካባቢዉ ርቆ ሲሄድ ወይ ደግሞ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያት ከጠይዉ በፊት ቀድሞ ካለፈ ጥላቻዉም አብሮ ይጠፋል። ጥላቻ ግን ከአንድ ብሔር ጋር ሲሆን እብደት ነዉ። ጠይዉ እንደ ግለሰብ የሚያደርሰዉ ጉዳት አይኖርም ባይባልም ሕዝብን ግን በጥላቻ ሆነ በሌላ ሀይል ማሸነፍ አይቻልም።
ሕዝብን በመጥላት ተስፋየ የመጀመሪያ ሰው አይደለም። ሂትለር በወቅቱ የነበሩ ወገኖችን አስተባብሮ በርካታ ሐይሁዶችን ገሏል ። ግለሰቡ አዳፋ ታሪኩን ለትዉልዶቹ አዉርሶ ሲሞት እስራኤላዊያን ግን ትላንትም እንደነበሩ ዛሬም በሰፊዉ አሉ ነገም ይኖራሉ። የኛ ሂትለር ለገሰ ዜናዊም በአላማ የሚመስሉትን አስተባብሮ ቀላል የማይባል አማራ ወገኖችን ጨፍጭፎል። እርሱም እንደ ብጤዎቹ አዳፋዉን ታሪኩን ትቶልን ለአማራ የነበረው ጥላቻ ነቀርሳ ሆኖ ታሪክ አድርጎታል።የአማራ ሕዝብ ግን ትላንት እንደነበረ በመከራ ዉስጥም ሆኖ ቢሆን ዛሬም አለ። ነገ ደግሞ የቀድሞዉ ሀያልነቱንና ክብርኑ አስመልሶ ይኖራል።
በመቀጠል እስኪ ይህ ግለሰብ ይህን ያህል የመረረ ጥላቻ የቆጠረዉ ለምንድን ነው?? ብለን ስንጠይቅ እኔ እስከማዉቀው ግለሰቡ በግሉ እንደ ሀገር በኢትዮጵያ ስምም ሆነ እንደ ሕዝብ በአማራ ደረሰብኝ የሚለው አንዳች በደለ ሲያሰማ አይታይም። ምናልባት በዚህ ዙሪያ የጠቀሰው ነገር ካለም የጋዜጠኛ ማስታዎሻ በሚለው መፀሀፉ ዉስጥ በጎጃሜዉ ሙሉጌታ ሉሌ የነበረዉንላይ የነበረዉን የተዛባ አመለካከት ነዉ። በአንድ ወቅት ታዋቂዉ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በሚመራ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዉስጥ ስራ ለመቀጠር ማመልከቻ በአካል አስገብቶ እንደነበር ፣ በሐሜት ደረጃ ያ ሊሰራበት የሚመኘው ቢሮ የጎጃሜዎች ቤት ነው የሚል የተሳሳታ ግምት እንደነበረዉ ፣ በኋላም ቢሮዉን ለመምራት አጋጣሚዉን አግኝቶ ሐሜቱ ውሸት መሆኑን ማረጋገጡን ማንበቤን አስታውሳለሁ።ከዚህ ዉጪ ከአማራ ጋር ያገናኘው የግል ታሪኩን በግሌ አላዉቅም። ያደገው ደግሞ በኦሮሞው ማሕበርሰብ አካባቢ በመሆኑና ዛሬም ድርስ እያጭበረበር ያለው ለኦሮሞዉን ማሕበረሰብ ተቆርቆሪ ነኝ በሚል ስሌት በበመሆኑ ያደገበትም ማሕበረሰብ የበደለው ነገር የለም ማለት ነው።
ሌላው ማህቀፍ ደግሞ እሱና ፀረ አማራዉ ኦነግ እንደሚሉት “ኦሮሞው በአማራው በመጨቆኑ” ለኦሮሞ ተቆርቆሪ በመሆኑ ይሆን እንዴ?? ብለን እንዳናስብ በነ አለማየሁእና ወልደሚካኤል መሸሻ የወጣው መረጃ የሚያሳየው ሌላ ነዉ። የግለሰቡ ዋናው አጀንዳው የኦሮሞዉ ማሕበረሰብ ጉዳይ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህንን ማሕበረሰብ የሚጠቀምበት በአባት ሀገር ኤርትራ ለተሰጠው ሀገር የማፍረስ አጀንዳዉ ብቻ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ እንደውም ለኦሮሞው ማህበረሰብ ያለዉን ንቀት ነው የሚያሳየው።ስለዚህ የዚህ ግለሰብ ጥላቻው ከየት መጣ?? ለሚለው ሀሳብ መልስ ሊሆነን የሚችለዉ በህዉሃትና ሻብያ ደደቢት እና ሳህል በረሀ ዉስጥ ከተደረሰው ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ የውሸት ድርሳናት ውስጥ ብቻ ሆኖ እናገኛለን።ስለዚህ ግለሰቡ ውሸት ላይ ተመስርቶ ፤የፅሑፍ ክህሎቱን በመጠቀም ሀገር ዉስጥ በነበረበት ውቅት በህዉሃት እየታገዘ ከሀገር ከተባረረ በኋላ ደግሞ በኦሮሞው ኢሊቶች አይዞህ ባይነት ሀገር እንዲያፈርስና አማራን እንዲሰድብ መድረክ ተመቻችቶለት ሲንቀሳቀስ ቆይቶል። በመጨረሻም ከላይ በተጠቀሱት ግለሰቦች ብርቱ ጥረት የቁም ሞት እንዲሞት ተደርገ።ለበርካታ ወራቶች ምላሱን እንዲሰበስብና ከሚዲያዎች እንዲርቅ ሆነ ።ይኸዉ ይችን ሰሞን የታጠፈ ምላሱ ተዘርግቶ፣ የነጠፈው ብዕሩን ዳግም አንሰራርቶ መርዛማ ቅርሻቱን በአማራ ሕዝብ ላይ እያቀረሸ ነዉ።
ይህንን ሀሳብ እንዳነሳ ያደረገኝ በቅርቡ ግለሰቡ የበዕውቀቱ ስዩም ወጎች በሚል እርህስ በዘ አበሻ ላይ የለጠፈዉንና የበዉቀቱ ቀደምት ስራዎቹን ከኦሮሞ ማንነቱ ጋር ያያያዘበትን መጣጥፍ በመታዘቤ ነዉ። እዛ መጣጥፍ ዉስጥ የተወሰኑ የበውቀቱን ግጥሞች መርጦ አማራን ማንቆሸሽ በሚችልበት መልኩ ትንታኔዉን አስቀምጦል። አንዱን ግጥምና ትንታኔዉን እንደተቀመጠ ልቅዳ።
“በዕውቀቱ አያቱን ከተሸሸጉበት አውጥቶ ለነፃነት ከማብቃቱ በፊት በዚሁ ቁጭት የፃፋቸው የሚመስሉ ስንኞችን ማስተዋል ችዬ ነበር። ለአብነት በአንድ ግጥሙ ኦሮሞ – አማራንና ትግሬን በገፀባህርይነት ያመጣና እንዲህ ሲል ያላግጣል፣
በታሪክ ሜዳ ላይ
አሉላ ጎበና
ወንዱን አስከትለው – ሲገድሉ ሲሞቱ
አባ ገብረሃና
እርስዎ ባይኖሩ – ምን ይውጠው ሴቱ፧
ጨመረልኹ መሰል – ባባ ነፍሶ ፈንታ
እንደ አንደበትዎ – እንትንዎ መንታ
አንዱ ለቀን ሲሆን – አንደኛው ለማታ
“ባባ ነፍሶ ፈንታ” ማለቱ ባልቻ አባነፍሶ ስልብ ነበሩ ስለሚባል ሲሆን፤ “እንትንዎ መንታ” ማለቱ ደግሞ አለቃ ገብረሃናን እንደ ምላስዎ መሾል (የቀጣፊነት ችሎታ) ሁለት ብልት ይዘዋል ማለቱ ነው። ሌሎች ጦር ሜዳ ሲሞቱ እርስዎ ውሎና አዳርዎ ከሴት ጋር መዳራት ነው ማለቱ ነው። በዕውቀቱ እንዲህ በመረረ ሁኔታ ሊሳለቅ የቻለው ምን ተሰምቶት እንደሆን ባውቅ በጣም ደስ ባለኝ ነበር። በተለይ ገዢዎች ላይ ቅሬታና ቂም እየያዘ እንደመጣ የሚጠቁሙ ከጥቂት በላይ ስንኞቹን ታዝቤያለሁ። ”
ሁለት ነገሮችን ብዮ ሀሳቤን ልሰብስብ። የመጀመሪያዉ ይህ ከላይ የተቀመጠው ግጥምና የተሰጠዉ ማብራሪያ እዉነት ነዉ፣ የደራሲዉን ሀሳብ ይገልፃል ብለን መደምደም አንችልም ። ለምን ደራሲውን በዛሬዉ አይን አይተነው ባለማዎቃችንና ከአንደበቱ ባለመስማታችን። በሌላው ጎን ደግሞ አይ ይሄ የዚህ ከይሲ ሀሳብ እንጂ የገጣሚው ሊሆን አይችልም ብለንም መደምደም አንችልም። ለምን በእናትና በአባቱ እቅፍላይ ያደገ፣ በስነፅሁፍ ዉስጥ በርካታ አመታትን ያሳለፈና ለተዋቂነትም የበቃ፣ ከሶስት ሺህ በላይ የእድሜ ባለቤት የሆነችን ሀገር ታሪክ እበረብራለሁ ብሎ የደፈረ ሰዉ ፤ አንድም በህፃንነቱ ጎዳና ላይ ተጥሎ በማደጎነት እንዳደገ ፣ አንድም መመርመርና መመራመር እንደማይችል መሀይም ሰዉ ኦሮሞው ማንነቱን ፈልጎ ያገኘዉ ዛሬ በ 40 ዓመቱ ነው የሚለውን ቀልድ መቀበሉ ይከብዳልና ነዉ።
ሁለተኛዉ ነጥብ በግጥሙ ላይ የተቀመጠዉ ንፅፅር በራሱ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም። ግለሰቡ እንደሚነግረን ገጣሚዉ ኦሮሞ አማራንና ትግሬን አወዳደር ብለን እንኮ ብንወስደዉ ፤ አሉላ ጎበናና ባልቻ የሚታወቁት የጦርሜዳ መኮነን በመሆን ሲሆን አለቃ ገብረሃና የሚታወቁት በቤተክርስቲያን ሊቅነታቸው፣ እንደ ገጣሚው በተረታ ተረታቸዉ ፣ በጨዋታ አዋቂነታቸዉ፣ በባለቅኔነታቸው በአጠቃለይ በደፍተራነታቸው ነዉ። ስለዚህ ዉድድሩ ሲጀመር አቻ ለአቻ አይደለም። በጦርሜዳዉ ግንባር አማራን ለመወከል ቢፈለግ ከላይ ንጉሱን ጨምሮ ከበርካታ አማራ የጦርሜዳ ጀግኖች አንዱን መምርጥ በተቻለ ነበር። እንደዉም በአግባቡ ለማስቀመጥ ከተፈለገ በዚህ ማህቀፍ ማወዳደሩ ከመጣ ከሌላዉ ወገን ከተጠቀሱት ዉጭ ፈልጎ ማግኘቱ ነዉ ከባዱ።
ማጠቃለያ
“መጥፎ ቁራኛ ያለ መቃብር አይለቅም” እንዲሉ አበዉ ይህ ግለሰብ ለአማራና ለኢትዮጵያ ያለዉ ጥላቻ ካንሰር ሆኖ እንደ መለሰ ዜናዊ እስኪወስድልን ድረስ ከኢትዮጵያም ሆነ ከአማራ ራስ ላይ እንደማይወርድ የታወቀ ነው። እስከዛች ሰሀት ድረስ ግን ቢያስ ሀሳቡን እንዳይሰራጭና ጥላቻው ብቻውን እንዲበላው ማድረግ የሚዲያዎች ሀላፊነት ነዉ ብየ ነዉ የማስበዉ። ከንደዚህ አይነት ክፋ ጭንቅላቶች የሚረጩ መርዞችን ወደ ሌላዉ ወገን ማዛመት በራሱ ሀላፊነት የጎለዉ ስራ ነዉ።
ግዜነዉ ደም መላሽ