February 14, 2016
8 mins read

ያድዋ ስንኞች – ከበዕውቀቱ ስዩም | የቅዱስ ቫላንታይንን በአል ምክንያት በማድረግ ስለ አድዋ ጦርነት እንጽፋለን

የቀድሞ ሰዎች የቃልና የዜማን ኃይል አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ሁሌም ወደ ጦርሜዳ ከመሄዳቸው በፊት አዝማሪ እና አረሆ ይመለምላሉ፡፡ ባድዋ ጦርነት ብዙ አዝማሪዎች ማሲንቆ ታጥቀው ዘምተዋል፡፡ አንዳንዶች ለውለታቸው ከድል በኋላ ማእረግና መታሰቢያ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ከኒህ አዝማሪዎች መካከል ጣዲቄ የተባለችው ስመጥር ሴት፤ አዲሳባ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሠፈር በስሟ ተሰይሞላት ነበር፡፡ በኀይለሥላሴ ዘበን የቸርቺል ጎዳና ሲነጠፍ፣ በቦታው የነበረው የጣድቄ መታሰቢያ ሳይደመሰስ አልቀረም ፡፡ አሁን፤ “ ያዝማሪ አጣዲቄ ሉባንጃ ግባ የቸርቺል ትምባሆ ” ውጣ እላለሁ ፡፡ በቅርቡ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በሚወጣው ”ከአሜን ባሻገር “በተባለው መጽሐፌ ጣዲቄን ከትቢያዋ ላስነሣት ሞክርያለሁ፡፡(ይቺ አረፍተነገር እንደ ማስታወቂያም እንደ ጉራም ትመዝገብልኝ)

በጊዜው፤ከጠላት ጎን ተሰልፈው ተናዳፊ ግጥም ወደ ወገን ጦር የሚወረውሩ አዝማሪዎችም ኣልጠፉም፡፡ ለምሳሌ አንዱ የጀኔራል ባራቴሪ ኣዝማሪ የጣልያንን ሠራዊት ታላቅነት በማካበድ የሚከተለውን ተጎርሯል፡፡

ዥኔራል ባራተሪ
ዥኔራል ባራተሪ
ማን ይችልሃል ያለ ፈጣሪ

ባንዳው አዝማሪ እንደገመተው ሳይሆን ቀርቶ የጥልያን ጦር እንደማሽላ እንጀራ ተፍረከረከ፡፡ ኩሩው ጄኔራል ባራቴሪም ተማረከ፡፡ በምርኮው ማግስት ዳግማዊ ምኒልክ ድንኳን ተይዞ ቀርቦ ምን አባቱ አቅብጦት እንደተዋጋ ሲጠየቅ በቁጣ የተሞላ ምላሽ ሰጠ፤ ንጉሡም ” ቁጣ ትናንት የጦርነቱ ቀን ነበር እንጂ ዛሬ ምን ይረባል “ብለው ስቀው አሰናበቱት ፡፡

በድሉ ማግስት የዘመኑ ጥቁር ሆሜሮች የጦርነቱን ውሎ በቅኔ ዘግበውታል፡፡ አንዱ የሚከተለውን ብሏል፡፡

ሰላም ለአፉከ ለፈጣሪ ዘየአኩቶ
ዘኢይትናገር ስላቀ ወኢይነበብ ከንቶ
ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ለኢትዮጵያ ማህቶቶ
ኀልቀ ማንጀር ወስእነ ፍኖቶ
ዤኔራል ባራቴሪይ ሶበ ገባ ደንገጸ ኡምበርቶ

ትርጉሙ እንደሚከተለው ግድም ነው፡፡

ሰላም ላንደበትህ፤ ለሚያቀርብ ለእግዜር ምስጋና
ዘበት፤ ስላቅ ፤ ከንቱ ወሬ፤ መናገርን መች ያውቅና
ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፤ የኢትዮጵያ መብራት ፋና
ተጨነቀ ማጆር፤ እግሩ ዛለ በጎዳና
ደነገጠ ኡምበርቶ፤ በባራቴሪ ምርኮ ዜና ፡፡

ቅኔይቱ ከወገቧ በላይ ውዳሴ ከወገቧ በታች ዜና እወጃ ናት፡፡ በቅኔይቱ ማጆር ተብሎ የተጠቀሰው አምባላጌ ላይ ወድቆ የተሰለበው ማጆር ቶሌዚ ሲሆን ”ደነገጠ “የተባለው ኡመበርቶ የጣልያኑ ንጉሥ ነው፡፡ ባለቅኔው ስለ ጣልያን ሁኔታ ነቄ ነበር ማለት ይቻላል፡
“ያድዋ ድል የብሄርብሄረሰቦች ድል ነው ”ይላል የሰባተኛ ክፍል ይሁን የስምንተኛ ክፍል የሲቪክስ ማስተማርያ መጽሐፍ፡፡ እውነት ነው !ያም ሆኖ፤ብሄርብሄረሰቦችን ባንድ ወታደራዊ ሥርዓት ጠምዶ ወደ ድል የመራቸው ዋናው የጦር አዝማች ምኒልክ ነበር፡፡በጊዜው ለዋናው የጦር አዝማች የውዳሴ ግጥሞች ጎርፈዋል፡፡ አንድ የሸዋ ኦሮሞ አዝማሪም እንዲህ ብሎ እንደ ዘፈነ ተመዝግቧል፡፡

Mootin baar gamaa ce’ee
Daanyoo faranji reebe.
አዛማጅ ትርጉም በስለሺ፤

ንጉሥ ወንዙን ተሻገረው
ዳኘው ፈረጅኑን ወገረው፡፡

ባድዋ ጦርነት ብዙ የወገን ወታደር አልቆ ሜዳ ላይ ቀርቷል ፡፡ ይህን በትካዜ ያስተዋለ አዝማሪ፤

የዳኘው ኣሽከሮች ፤እነሞት አይፈሬ
ርግፍ ርግፍ አሉ፤ እንደ ሾላ ፍሬ

ብሎ አንጎራጉሯል፡፡

እንደ ሾላ ፍሬ ቀይ ለብሰው ፤ከረገፉት አንዱ ኣሠላፊ ገበየሁ የተባለ ወታደር ነበር፡፡ (ቸሩሊና ዴልቦካ የተባሉ የታሪክ ጸሀፊዎች አሠላፊ ገበየሁን ከስመጥሩ ፊታውራሪ ገበየሁ ጋር እያምታቱ ጽፈዋል፡፡ ቼሩሊ፤“ አሠላፊ ”የተባለውን ማእረግ “አሳላፊ” ብሎ በመረዳት ፊታውራሪ ገበየሁ የንጉሡ አሳላፊ (cup-bearer ) ነበር በማለት ስቷል ፡፡ በአድዋ ጦርነት ሁለት የተለያዩ ገበየሁዎች እንደነበሩ የምንገነዘበው በጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ የተመዘገበውን የጦር አለቆች ኣሰላለፍ ስናይ ነው ፡፡ ) ለማንኛውም አሠላፊ ገበየሁ በጦር ሜዳ ከወደቀ በኋላ ያልታወቀ አዝማሪ ያንጎራጎረለት አንጀት የሚበላ ግጥም Folk-literature of the Oromo .. በተባለው መዝገብ ተካቷል፡፡ ታድያ፤ እኔ እንጉርጉሮውን መነሻ አድርጌ የራሴን ግጥም ብጽፍ ማን ይከለክለኛል?

አሠላፊ ገበዮ!
እንደ እግዜር ስጋጃ ፤ምድሩ ላይ ተሰፍተህ
እንደ ብረት ቁና አፈር ላይ ተደፍተህ
“ጓዶች ወዴት አሉ?” ብለህ ስትጣራ
ጓዶች ተመለሱ ከንጉሡ ጋራ
“ሚስቴ ወዴት አለች ?”
ብለህ ስትጣራ
ሚስትህ ወዲያ ቀረች
በሞትህ በማግስቱ ለሌላ ተዳረች
ይልቅ “እናቴ ሆይ !” በማለት ተጣራ
የናት ኀዘን ዶፍ ነው፤ ቶሎም አያባራ፡፡

ይችን ወግ ለመጻፍ መነሻ የሆኑኝ መጻሕፍት ከታች ቀርበዋል፡፡
ተክለጻድቅ መኩሪያ (አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት)ሜክስኮ ቡክ ኮርነር
• Enrico Cerulli, Folk-literature of the Oromo of Southern Abyssinia
• Del Boca, Angelo. Gli Italiani in Africa Orientale La caduta dell’Impero Editori Laterza, 1982.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop