ስደት የፍርሃት ውጤት ነው – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

ከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል፤ አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ‹‹ነጻነት›› የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል፤ እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም፡፡

በዚያው እነሱ አስተያየታቸውን በጻፉበት ገጽ ላይ የራሴን አስተያየት ለጥፌ ነበረ፤ በበነጋታው ባየው የሁላችንም አስተያየቶ ድራሻቸው ጠፍቷል፤ አንድ ቀን ሙሉ ፈልጌ አጣኋቸው፤ ያሬድ ጥበቡና ቴዲ ልዩ ዘዴ እንዳላቸው አላውቅም፤ ሌላም ሰው ያንን ጽሑፍ ለማጥፋት ምን ምክንያት እንዳገኘ አላወቅሁም፤ ለማናቸውም ያንን ሀሳቤን እንዲያውም አስፋፍቼ ለማቅረብ ዕድል አገኘሁ፡፡

ያሬድ ጥበቡና ቴዲ በእውቀቱን በአሜሪካ ለማስቀረት የሚፈልጉበት ምክንያት ምንድን ነው? ምክንያቱን በትክክል እንኳን እኔ እነሱም የሚያውቁት አይመስለኝም፤ ግምቴን ግን ላቅርብና አይደለም ካሉ እንሟገትበት፤ አንደኛ ሊክዱት በማይችሉት ሐቅ ልጀምርና ሁለቱም ሰዎች በጣም ፈሪዎች ናቸው፤ ስለዚህም ፍርሃታቸውን ወደበእውቀቱ አዛምተው ጨለማን ተጋፍጦ በነጻነት ከቆመበት የማይመችና የማይደላ የእናቱና የአባቱ ዓለም ወደአሜሪካ የምቾትና የስድነት ባዕድ ዓለም ከእነሱ ጋር እንዲደባለቅ ይፈልጋሉ፤ ለምን እንዲደባለቃቸው ይፈልጋሉ? ትልቁ ጥያቄ ይሄ ነው፤ መልሱም እኔ እንደምገምተው እሱ እነሱን ሲሆን፣ እነሱ አሱን የሆኑ ስለሚመስላቸው ነው፤ ትንሽ ቢያስቡበት (ፍርሃት ለማሰብ ጊዜ አይሰጥም እንጂ!) በእውቀቱ እነሱን ሲሆን አሁን ያለውን ለነጻነት የመቆም ዋጋ እንደሚያጣና እንደሚያንስ መገንዘብ ጊዜ አይፈጅባቸውም ነበር፤ ቴዲም ሆነ ያሬድ ለበአውቀቱ ‹‹የቸሩት›› ፍርሃታቸውን ነው፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ወኔ የሌላቸው የሚሆኑት እንደዚህ ያሉ የፍርሃት ጠቢባን በሰላ ዘዴ እየነደፏቸው ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹‹አርቲስት›› እያለ ከሚጠራቸው ሰዎች ውስጥ በአንድ እጅ ጣቶች የሚቆጠሩ መኖራቸው አጠራጣሪ ነው፤ እኔ እርግጠኛ ሆኜ የማውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁንን ነው፤ አሁን ደግሞ በእውቀቱ ብቅ ቢል በመንፈስ ከከሰሩት ከአላሙዲን ስብስብ ውስጥ ሊያስገቡት ይጥራሉ፡፡ (አላሙዲን በገንዘቡ ወርቅም ይግዛበት ወይም ሰው ገበያው ከፈቀደለት (በጎንደርኛ አማርኛ ወርቅ ባሪያ ማለት ይሆናል ሲባል ሰምቻለሁ፤) በብሩም ሆነ በወርቁ ላይ ባለመብት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መላዉ ኢትዮጵያ ከግፍ እስር እና ፍትህ ዕጦት ነፃ አስኪሆን መሰራት አለበት

ፍርሃት የግል ነውና በፍርሃት ተገንዞ መኖርን አልቃወምም፤ አጥብቄ የምቃወመው ግን ፍርሃትን (ሕመምን) ወደሌላ ሰው ማስታለፍን ነው፤ ፍርሃት እንደማናቸውም ተላላፊ ሕመም በንክኪም ሆነ በንግግር ይተላለፋል፤ አጥብቄ የምቃወመው ወኔ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በፍርሃት ቆፈን እየተጠፈረ ስደተኛ እንዲሆን መገፋፋትን ነው፤ አጥብቄ የምቃወመው ለመብቱና ለነጻነቱ ግፉን እየተቀበለ የግፈኞቹን አረመኔነት በመንፈሳዊ ወኔው የሚጋፈጠውን ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ነው፤ እኔ አጥብቄ የምቃወመው ኢትዮጵያን በሀብት ደሀ የሆነች አገር ብቻ ሳትሆን በሰውም፣ በአእምሮም፣ በመንፈስም ደሀ የሆነች አገር እንድትሆን በማወቅም ባለማወቅም የሚደረገውን ጥረት ነው፤ የፈረንጅ አገር ኑሮ እንደሚደላና እንደሚጥም እያየን ነው፤ በፈረንጅ አገሮች ላይ የሚውለው የኢትዮጵያ አካል፣ አእምሮና መንፈስ በኢትዮጵያ ላይ ቢውል ኢትዮጵያም የምትደላና የምትጥም አገር ልትሆን ትችል ነበር፤ ጠፍሮ የያዘንን ሰንሰለት በጣጥሰን ችሎታችንን ሁሉ በግንባታ ላይ እንዳናውለው ባንድ በኩል ፍርሃት በሌላ በኩል የሥልጣን ፉክክር አደንዝዞናል፡፡
ቴዲ ገብርኤል በእውቀቱ ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጠሩ አኮራለሁ›› ይልን ወዲያውኑ ያንን በኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጠሩ የኮራበትን በእውቀቱን ለስደተኛነት ያጨዋል፤ በእውቀቱ በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ ቢቀር በቁሙ ሞቶ ኢትዮጵያ አላጣችውም?አያድርግበትና በእውቀቱ አገሩ ገብተ ወያኔ ቢገድለው ወይም ቢያስረው በወያኔ አረመኔነት በእውቀቱ ሕያው አይሆንም?
ሌላው ያልታሰበው ጉዳይ በሚስተር ቴዲ አስተሳሰብ ‹‹የሚያኮሩ›› ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከአገር ከወጡ አገሩ በሙሉ የነሚስተር ቴዲ መሆኑ አይደለም እንዴ! እግዚአብሔር ያውጣን! በእውቀቱንም በደህና ይመልሰውና በአገሩ በሰላም ያኑረው!
ለቀልድ የተባለነው ማለት ‹‹ቢያዩኝ እስቃለሁ፤ ባያዩን እሰርቃለሁ›› የሚለውን ዘዴ መከተል ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን በተለይ በደርግና በወያኔ የአገዛዝ ዘመናት በብዛት ለስደት መደረጋቸውን ማንም የሚያውቀው ነው፤ የስደቱ ምክንያት ብዙ ነው፤ ስደተኛው ሁሉ አይወቀስም፤ ነገር ግን የሚወቀሱ ሞልተዋል፤ ምናልባትም የኢትዮጵያን ስደተኞች ልዩ የሚያደርገው ስደተኛውና አሳዳጁ በአንድ አገር ስደተኞች ሆነው፣በአገራቸው ተከባብረው መኖር ያቃታቸው ሰዎች በሰው አገር በግዳቸው ተከባብረው መኖራቸው ነው፤ መቻቻል ማለት እንዲህ ነው!

ተጨማሪ ያንብቡ:  አድዋን ከሚኒልክ የመለየት አባዜ የኦነጋውያን ቅዥት - ጥሩነህ

7 Comments

  1. “በእውቀቱ በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ ቢቀር በቁሙ ሞቶ ኢትዮጵያ አላጣችውም”. Here you go again with your deadly poisonous statement Mr. Mesfin. How can you call your fellow immigrant citizens coward and a walking dead? Let’s remind you what the diaspora had accomplished the last 25 years:
    1.The Diaspora has been subsidizing and feeding million of Ethiopians that Meles and his cronies systemically looted to its bones in broad daylight
    2.The Diaspora has been working tirelessly to bring awareness the atrocities that is being committed by fascist TPLF
    3.Diaspora founded and currently financially support ESAT that you spend 5 hours discussing about your pointless life history
    4.The only “haqegna Teddy afro” that you so admire is on the diaspora’s pay roll. His bread and butter is the diaspora, he makes money here and only go to Ethiopia to sleep. If Teddy afro works for TPLF, he becomes a diaspora in a heartbeat……so much for his haqegninet!
    5.The diaspora funds any opposition party (including you), how on earth can any one of you survive financially in Ethiopia without us?
    We the diaspora don’t want to be killed by some mindless monkeys that are in power just like how Derg (with your suggestion) rounded up and eliminated the educated 60 officials and almost half a million Ethiopians during Red/white Terror. What did you contribute to Ethiopia the last 40 years except create confusion? How can an Ethiopian be effective if they wind up in jail and be killed? You need to realize that an Ethiopian abroad is just as effective to the struggle as the ones in Ethiopia. Also be mindful that Ethiopia don’t just exist in east Africa anymore. The Diaspora created the New Ethiopia all over the world -Thanks to Menelik II. The Menelik effect is inheriting the land we Ethiopians set foot on. We shall be back soon after the troops that we “the Diaspora” financially support take over the palace!!…….till then just keep quiet and don’t bite the hands that feeds you.

    • Thank you my friend Mesfin W. for your article. I want to listen similar articles from you. This is the only truth as as been witnessed by Mesfin in his life time. Bravo Keep it up! My boy. I wish you stability and consistency in your health and soul.

  2. ሀፍረተ ቢሱ ፕሮፌሰር በዘወርዋራ ጀግና ነኝ እያለን ነው። ከየዘመኑ አምባ ገነኖች ጋር አማካሪና ጎጆ አውጪ ሆኖ በደም ጎዳናቸው ተባባሪ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ጠንቅቀው ያውቃሉ። እንደ ወዳጆቹ መለስ ዜናዊና ክንፈ ገብረ መድህን ህዝባዊ ፍርድን በሞት ካላመለጠ በነጻዋ ኢትዮጵያ ስብሀት ነጋን ከመሰሉ ቀሪ ወንጀለኛ ወዳጆቹ ጋር ለህዝብ ፍርድ መቅረቡ አያጠያይቅም። መስፍን የፍርሃት ትርጓሜ ነው። በዘመነ ደርግ 60ዎቹን የአጼ ሀ/ስላሴ ባለስልጣናት በማሳረድ ‘ያለ ምንም ደም’ የተሰኘውን የደርግ አብዮት ወ ደም ባህር የለወጠውን የእልቂት ጎዳና ያመቻቸ ወንጀለኛ ነው። ‘ጀግናው’ መስፍን አስራሰባቱን የደርግ አመታት ጭራውን ቆልፎ ድምጹን አጥፍቶ የከረመ ቡከን ሲሆን እንደ ልማዱ ደርግ ሊወድቅ በዋዜማው የወያኔነት ተልዕኮውን ሲጀምር ነው ድምጹ የተሰማው። በሱ ቤት ይህ ሁሉ ምስጢር ነው። መስፍን ‘ጀግና’ ከሆነ እነ ፕሮፌሰር አስራት ምን ሊባሉ ነው? እንደሱ መኖር ጠልተው ህይወት ሳታሳሳቸው ቀርታ ይሆን? ወይስ ምፕኞች ሆነው? የሚያቃጥለው ይህን ሁሉ ወንጀል ተሸክሞ ዛሬም አርፎ ያለመቀመጡ ነው።

  3. ውድ ኑፍ ሰይድ፣
    የፕሮፌሰር መስፍንን ጽሑፍ ጊዜ ካገኘህ ደግመህ አንብበው። 1/ ስትቸኩል ልብ አላልክ ይሆናል እንጂ “የስደቱ ምክንያት ብዙ ነው፤ ስደተኛው ሁሉ አይወቀስም” ብለዋል። 2/ “ለቀልድ የተባለ ነው ማለት ‹‹ቢያዩኝ እስቃለሁ፤ ባያዩን እሰርቃለሁ›› የሚለውን ዘዴ መከተል ነው” ያሉት ገብቶሃል? 3/ ጽሑፋቸው ያሬድ ጥበቡና ቴዲ ገብርኤል በፌስቡክ ለጻፉት ምላሽ ነው። የያሬድንና የቴዲን ጽሑፍ ያነበብክ አይመስልም፤ ብታነብ ኖሮ ስለ ኢሳት ወዘተ ባልዘበዘብክ። 4/ ፕሮፌሰር መስፍንን “What did you contribute to Ethiopia the last 40 years except create confusion?” ብለህ ጠይቀሃል። ከአጠያየቅህ ልጅ እንደሆንክ ያስታውቃል። ወይም አንባቢ እንዳልሆንክ። ወይም ካንተ አሳብ ጋር የማይስማማውን ሁሉ በጅምላ የምትነቅፍ ዓይነት። ለማንኛውም ስለ ጽሑፍህ ልትመሰገን ይገባል። ያንተም ዓይነት አስተሳሰብ እንዳለ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲማሩ ይረዳልና። አንተም በጎ መንፈስ ካለህ ስትታረም ምናልባት ትምህርት ታገኝ ይሆናል። መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልህ።

  4. Nuf_said እምትባል ጉድ አሁን አልታወቅም ብለህ ነው? ወያነ: ስንት ነው የሚከፈልህ?

  5. Dear Nuf-Said,
    I guess you miss the point! What the professor has attempted to say, in my opinion, is that it is better to assume ownership over our country and work had and prosper! What you seem to suggest is that we should continue to remain a run away coward and feed our people to prolong the misery whatever people have been financed by diaspora! As for Teddy Afro and professor, please refer to international trade to get a good sense!

Comments are closed.

Share