በሽታውን በአግባቡ ያላዎቀ በሽተኛ መጨረሻው አያምርም

ከበደ ተድላ

ዕለት 31-12-2015

እውቁ ግሪካዊው ፈላስፋ ሶቅራጥስ ለመጀመሪያ ግዜ የተፈላሰፈው ”እኔ ማን ነኝ” ሲል እራሱን በመጠየቅ ነበር:: ከዚያም ባደረገው የፍልስፍና ጉዞ የተቀዳጅው ውጤት ቢኖር ”ራሰን ማዎቅና መሆን የእዉቀት ሁሉ መሰረት ነው” የሚለውን ነበር:: ባለቅኔው ዊልያም ሽክስፒርም ይህን አስመልክቶ ሲናገር ለራስህ እውነት ከሆንክ ለሌላ ለማንም ሰው ውሽት ልትሆን አትችልም ነበር ያለው::

File Photo

ይህን ከላይ የጠቀስኩትን አባባል ማንሳት የፈለኩበት ምክንያት አገራችን ኢትዮጲያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ ገምግሞ ትክክለኛ የሆነውን ፈውስ ለማግኝት ያስችለን ዘንድ ውይንም የሃገራችንን እውነተኛ ችግር በትክክል ማዎቁ ግዴታ መሆኑን የሚያጠናክርልኝ አባባል ሰለሆነ ነው:: ችግራችንን ለማዎቅ ደግሞ እራሰን መፈተሽ ዋናው መፍትሄ እንደሆነ በማዎቅም ጭምር ነው:: እራሰን ማዎቅ ስል የአንድነት ሃይሉ ሺንገላዉንና ትክክል ያልሆነውን አመለካከቱን ትቶ እውነተኛ የአገሪቱን ችግር መርምሮና እራሱንም በበቂ ገምግሞ ድክመትን በማሻሻል ለችግራችን መፍትሄ የሚሆን ነገር በመፈለግ አገራችንን እንድንታድ ከሚል አሰተሳሰብ በመነሳት ነው::

ይህን ጹህፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ጉዳይ ቢኖር ሰሞኑን በየማህበራዊ ገጾችና በብዙሃን የዜና ማሰራጫዎች እየተስተጋባ ያለዉን የዎቅቱን የመሃሉን አገር ያገራችንን ክፍል የታቃዉሞ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሲሆን በሚዲያዎቹም ሆነ የኢትዮጵያን አንደነት አናሰጠበቃልን በሚሉ ድርጂቶችም ሆነ ግለሰቦች የዎቅቱን በኦሮሚያ ክልል በሚባለው የተነሳውን ተቃዉሞ የተሳሳተና አገራችንን ዎደባሰ መፈራረስ ሊያስገባ የሚችል ትንታኔ ሲሰጥ በመስማቴ በሺታውን በአገባቡ ያላዎቀ በሺተናኛ መጨረሻዉ አያምርም በሚል እርዕስ እንድጽፍ አነሳሳኝ::

ኢትዮጵያ አገራችን በዎያኔ ጥባብ ፍልስፍና ሥር ዎድቃ አገራዊ እና ማህበራዊ አንድነቱዋ ተናግቶ ይህው ድፍን 25 አመቶችን ማስቆተርዋ ሁላችንም እያየነውና በእለታዊ ልምዳችንም እያለፍንበት ያለ ሃቅ በመሆኑ ዋቢ ማቅረብ አያስፈልገኝም:: ታዲያ በእነዚህ 25 ዓመቶች ዉስጥ ዜጎች እንደ ነጻ አሳቢ ሰብአዊ ፍቱር ማስብ እንዳይችሉ ተደርገው በሚናገሩት ቁዋንቁዋ እና ባህል ተማክለው እንዲያሰቡ ሰለተደረገ ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ያፈሩዋቸውን በጎ እሴቶች እንዲተውና የኔ የሚሉትን የጎሳ ማንንነት አጥልቀው አገራችንን እንደ ድር እና ማግ ሆኖ ያስተሳሰረንንና በረጂም ግዜ አብሮ መኖር ያካበትነውን እሴቶቻችን አጥተን እርስ በርሳችን የጎሪጥ እና በጥላቻ እየተያየን የአገራችንንም ሆነ የዜጎቻችንን ድህንነት አደጋላ የጣልን ትውልዶች አድርጎናል::

እንደሚታወቀው ሁሉ ኢትዮጵያ አገራችን ለዘመናት በነጽነት ክብሩዋን በጠላት ሳታስነካ የቆየች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር እንደሆነች እና ህዝቡዋም የራሱን የማይሰጥ የሰውን የማይነካ ፈርሃ እግዚህአቤር ያለው ህዝብ እንደሆነ እንኩዋን ኢትዮጵያውያን ቀርቶ ባዕዳንም የሚያዉቁት ሃቅ ነው:: ይህች የጥቁር ህዝቦች ፋና ወጊ የሆነች  አገር ለብዙ ጥቁር ህዝቦች ነፅነት የታገለችና በተግባርም አርዓያ የሆነች አገር በአሁኑ ሰዓት ከራስዋ አብራክ በወጡ ጉግ ማንጉጎች ነጻነትዋን እና ክብሩዋን አጥታ ዜጎችዋ በዘር፣በሃይማኖት፣ በቁንቁ ተካለው ልዩነትንና ጥላቻን ብቻ በማራገብ ህልውናዋ አደጋ ላይ የወደቀበት ግዜ ላይ ደርሰናል:: በተለይ ደግሞ አማራ የተባለዉን የህብረተሰብ ክፍል እንደጠላት በመፈረጅና እስከ ደርግ ስርዓት ድረስ ያለውን የአገሪቱን ችግር በዚህ ማህበረስብ ላይ በማላከክ የችግሮቹ ሁሉ መንስዔ እንደሆነ በመቁጥር በህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ጠላት እንዲቆጠርና በአገሪቱ ውስጥ በፖለቲካው፣ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅሰቃሴ ተገሎ እና አንገቱን ሰብሮ እዲኖር ተደርጉዋል:: ለአማራው መገደል ፣መጭፍጨፍ፣መታሰር እና መገለል ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኝቱ ብቻ ነው::

ኢትዮጵያ አገራችን በትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰር ከወደቀች ግዜ አንሰቶ የአገሪቱዋ ህልውና እና የዜጎችዋ ደህንነት አደጋ ላይ ወድቆል:: ለዚህም ተጠያቂው በሰልጣን ላይ ያለው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው:: ከላይ እንደገለጸኩት ኢትዮጵያ አገራችን ቁዋንቁን ማዕከል ባደረገ ዘጠኝ ክልሎች ተከፋፈላ አንዱ ክልል ከሌላኛው ክልል ምንም ዓይነት ግንኙነትም ሆነ ትሰሰር የሌለውና እንደ ስርዓት የተቀነባበረ ሰራ የማይሰራ ዋጋ ቢስ በሆነ መዋቅር ተዋቅሮ አገሪቱ እንደ አገር መቆም አቅቱዋት እምትገኝበት ወቅት ላይ ደርስናል:: ዜጎችዋ እርስ በርሳቸው በጥላቻና በጥርጣሬ እየተያዩ ፍቅርና አንድነትን አጥተው በመፈራረስ ሂደት ውስጥ እንገኛለን:: ያንድ አገር ህልውና ምሰሶ የሆነው መተማመን ጠፍቶ ዜጎች የጎሪጥ የሚተያዩበት ወቅት ላይ ደርሰናል:: ወያኔ ከመነሻው ጀምሮ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር አርቲፊሻልና በተረት ተረት የተፈጠረች አገር ናት ሲል ሙዋቹ ጠ/ሚኒስተር ተብየው ሲሳለቅበት የነበረ ጉዳይ ነው:: ታዲያ እችን በተረት ተረት ተፈጠረች የሚሉዋትን አገር አፈርሶ በአዲስ አወቃቀር ለትግራይ ነጻ አዉጭ ድርጅት በምትጠቅም መልኩ ማዋቀር ግድ ይላቸው ሰለነበር ይህን ህልማቸውን ዕውን አደረጉ:: ዜጎች እርስ በእርሳቸው በጥርጣሬ በሚናኮሩበትና በሚጣሉበት ግዜ ትኩረቱን ወደ ወያኔ የሚያደርግ ስለማይኖር የአገሪቱን ሃብትና ሰልጣን በማንአለብኝነት ያለ ተቀናቃኝ ለመቆጣጠር እንዲቻላቸው ለማድረግ ነው:: ቁዋንቁን መሰረት ያደረገው የአወቃቀር ዘዴ በይዘቱ ዲሞክራሲያዊ ሰለአልሆነ ዜጎችን እናንተና እኛ በሚል ከፋፈሎ መድሎን የሚያመጣ ሰለሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች እኩል እንዳይታዩ የሚደርግ አግላይ አዎቃቀር ሰለሆነ ለሰላም እጦት; ለስደት እና አገሪቱ እንደ አገር ህዝቡዋ ሰላማዊ ሂዎት እንዳይኖሩ ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱና ዋናው  የአገሪቱ ችግር ሆኑዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያየቅንጦትግድቦችንመገደብለምንአስፈለገ? (ፕሮፌሰር አለማየሁገብረማርያም)

ሰው ከፍጥረቱ አንሰቶ እስካሁን ድረስ የራሱን ዓለም መልክ የሚያሲዘው ህብረተሰቡን በተለያዩ ዘዴዎች በመከፋፈል/catagorise በማድረግ ነው:: ለምሳሌ ወንድ፣ሴት፣የዎጣቶች ማህበር፣የሴቶች ማህበር፣የሰራተኞች ማህበር እያለ ነው የሚከፋፈለው የዚህ ዓይነት ክፍፍል ጤነኛና ተፈጥሮዊ ሰለሆነ በህብረተሰቡ ዘንድ ሊያመጣ የሚችለው ችግር አይኖርም::

በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ሊኖር የሚገባው ክፍፍል ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ክፍፍሎች ሲሆኑ ከዚህ የወጣና በአሁኑ ስዓት በኢትዮጵያችን ቁዋንቁን መሰረት ያደረገ ክፍፍል ለአገራችንና ለዜጎቻችን  ህልውና አስጊ ሰለሆነ ይህ ስርዓት ተወግዶ ሌላ ህብረተሰቡን ሊያስተሳስርና በህዝባችን መካከል መተማመን፣ መፋቀር፣ ሊያመጣ የሚችልና የዴሞክራሲ መብቶች የተጠበቁበት: የህግ የበላይነት የተከበረባት እና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሰረት ሰንችል ብቻ ነው ሰላምም እና መረጋጋትን ለናሰፍን የምንችለወ::

የአገሪቱን ፖለቲካዊ; ኢኮኖሚአታዊ እና ማህበራዊ ሁኔታው በዚህ ጠባብ ሃይል የተደነገገ/ define የሆነ ሰለሆነ እና አንጻራዊ የሃይል የበላይነት በዚህ ጠባብ ሃይል ሥር ሰላለ ዉሸቱ እውነት; የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ኢትዮጵያዊነት ከዕልት ዕለት ለድርድር እየቀረበና ለድርድር በቀረበም ቁጥር ሁዋላ ቀርና ጭቁዋኝ እንደሆነ እየተቆጠረ ዋጋዉን እያጣ ያለበትን ሁኔታ ነው እኔ በግሌ እየታዘበኩ ያለሁት:: ይህን ኢትዮጵያን የማሳነስ ዎይንም የማፈርስ ሂደትን deconstructing processe/ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሂደት እለዋለሁ:: የማፈራረሱ ሂደት ከምንጠቅምባቸው ቁዋንቁዋችና ቃላቶች ይጀመራል:: ለምሳሌ አዲሲቱዋ ኢትዮጵያን ለመገንባት; ሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ ነው አታምልኩት; ነፍጥኛ; ብሄር በሄረሰቦች; ክልል የሚሉትና ወዘተረፈ ይገኝባቸዋል:: እነዚህን ቃላቶች ኢትዮጵያዊ የሆነው ሃይል ሳያዉቅ ዎደውስጡ በማግባትና በመጠቀም ለዚህ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሂደት አባሪና ተባባሪ ዎይንም ግባዓት ይሆናል ማለት ነው:

በማህበራዊ ጥናት/ sociological perpective የዚህ ዓይነቱን ሂደት አገር አጥፊ ሂደት ይለዋል:: deconstructing process/ አገርን የማፈረስ ሂደት ሁለት ደረጃዋች አሉት::

እነሱም:

1ኛ) የቅስቅሳና ፕሮፓጋንዳ ሥራ

በዚህ የመጀሪያ ደረጃ ላይ ሁሉም ጽረ ኢትዮጵያ የሆኑት ሰብሰቦች በአንድላይ ተሰባሰበው ጽረ ኢትዮጵያ የሆነ አጀንዳዎችን በማንሳት የእኔ በሚሉት ማህበረሰብ ላይ የተሳሳተ ግንዛቤ በማሰጨበጥ የአገሪቱን አንድነትና ሰላም ያደፈርሳሉ:: ህዉሃት; ኦነግ; ህግሃኤ እና ኦብነግ ሆነው በዚህ 40 አመት ግዜ ዉስጥ ሲያደርጉት የነበረው በዚህ መልክ ነበር:: ይህን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሂደት እንዲፋጠን ገንዘብ እና አንዳንድ ሃይልን ሊያፈረጥሙ የሚችሉ resources/ቁሳቁስ በአካባቢያችን ካሉ ጽረ ኢትዮጵያ መንግስታት በቀላሉ ያገኙበትና እያገኙበት ያለ እዉነታ ነው:: እነዚህ ጽረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ሚዲያዎቻቸውን በመጠቀም የህበረተሰባችንን አብሮነት በመስለብ  በአገራችንና በህዝባችን ደህንነት ላይ  አደጋ እንዲጋረጥ አድርገዋል:: sitigamatising processe ይባላል በ ማህበራዊ ሳይንስ ጥናት:: የኢትዮጵያን ህልውና ለማሳጣት አንድን ማህበረስብ ባለፉት ሰርዓቶች ተጠቃሚ እንደሆነና ጭቆና ብሎም  ባህሉን; ሃይማኖቱን እና ቁዋንቁውን በሌሎቹ የህበረተስብ ክፍል በግድ ይጭን እንደነበር ተደርጎ በሰፊው ለረጂም ግዜ ሲቀሰቀስ እንደነበር ሁላችንም የመናውቀው ሃቅ:: ይህ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሰርቶ አገራችን በትግራይ ነፅ አውጭ ሰር ዎድቃ ህልውናዋን ያጣችብት ሁኔታ ከጣሉዋት አንዱና ዋነኛው ነገር ያልነበረውን እንድነበረ ተቆጥሮ እንዲሄድ በማድረግ ነው:: በዚህ ሂደት ሁሉም ጠባብ ሃይሎች እኩል የሰሩበትና ለአገራችን እዚህ ደረጃ መድረስ እኩል ሚና ተጫውተዋል::

2ኛ) ሁለተኛ ደረጃው ደግሞ ህበረተሰቡን የተሳሳተ ግንዛቤ ካሰጨበጡት በሁዋላ የተሳሳተወን ግንዛቤ እውቅና በመስጠት ህጋዊ ማድረግ ነው:: ውያኔዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ; ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አንደነትን ንደው ያልነበረን እዉነታ በመፍጠር ኢትዮጵያን በ 9 ክልል በመከፋፈል ክልሎቹም እርስበራሳቸው inetrconnect እንዳይሆኑ በማድረግ እንደሃገር ዉህደት የሌላቸው ሆነው በቁዋንቁም እንዳይግባቡ ሆነው ዜጎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሰርተው እንዳይበሉ የሆነበትን ስራዓት በህግ ደንግገው አገራችንን መሰቀለኛ መንገድ ጥለዋታል::

በዚህ deconstructing process ውስጥ ነው እኛም ሳናዉቀው አገራችንን ሊፈርሱ የሚችሉ ቃላቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያዊነትን ለድርድር የምናቀርበውና የሃይል ሚዛናችንን ሊያሳጡ የሚችሉ ቃላቶችን የምንጠቀመው:: ሰለዚህ የምንጠቀማቸውን ቃላቶች ማዎቅና አገራችንን ሊያፈርስ ከሚችል ነገር መጠንቀቁ ተገቢ የሆናል::  ኢትዮጵያዊነትን ለድርድር የማቅረብና ኢትዮጵያዊንትን የማሳነስ ሂደቱ ቀስ በቀሰና በስዉር እየተካሄደ መሆኑን ለብዙዎቻችን ግልጽ የሆነ አልመሰለኝም::

ኢትዮጵያ አገራችን እንደብዙዎቹ አገራት የአገር ምስረታ ሂደቱዋን/ nation building process  የጨረስችና በዚህ ሂደትም ዉስጥ  ኢትዮጵያን እንደ አገር ለመገንባት አያሌ ዜጎችዋ የሚተፈለገውን መስዋዕትነት ከፍለው ወያኔ የሚባል ጉግ ማንጉግ እስከመጣበት ግዜ ድረስ በህዝብ መካከል ምንም ዓይነት ችግር ያልነበረብንና እንዲያውም ከዚህ በተጻራሪ ፍቅር; መተሳሰብ እና መተማመን በህዝቡ መሃል የነበረባት አገር እንደነበረች ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው:: ይህ ማለት ግን በገዥዎች በኩል የሚደርስ ግፍ አልነበረም ለማለት አይደለም:: የህዝቡን ይሁንታ ያላገኙ አምባገነን መንግስታት ኢትዮጵያዊያንን በግፍና በደል ያሰቃዩ እንደነበር ለሁሉም ገሃድ ነው:: ይህንን የገዥዎች አምባገነናዊ ስራዓት ለመቀየር ዜጎች የነገድ ማንነታቸውን ማዕከል ሳያደርጉ እንደ ኢትዮጵያዊ  ሆነው እጂ ለእጂ ተያይዘው የታገሉበትን ሁኔታ ለማስታዎስ የእነ ኢህአፓን አደረጃጀት ዞር ብሎ ማየት ለግንዛቤ ጠቃሚ የሆናል:: ሆኖም ግን የእነዚህ ድንቅ ኢትዮጵያውን ትግል ጠባብ አመለካከት ባላቸው ድርጂቶች ተነጥቆ አገራችንን መስቀለኛ መንገድ ላይ የጣለ ክስተት ውስጥ እንገኛለን::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐማራው ሕዝብ ህይወትና ደህንነት ዘውግ ተኮሩን ስርዓት ከመቀየር ጋር አብሮ የሚሄድ ጉዳይ ነው - አክሎግ ቢራራ (ዶር)

የሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረው ችግር ውያኔና እሱን በመሰሉ ጠባብ ቡድኖች በተፈጠረው  ethnocentric filosofy/ የጎሳ ፍልስፍና ውጤት እንደሆነ ነው የሚረዳኝ:: ይህ በኦሮሞ ክልል በሚባለው የተፈጠርው የተቃውሞ እንቅስቃሴ የአንድነት ሃይል ተብየውን ከሁለት የከፈለ ሲሆን አብዛኛውንም ኢትዮጵያዊ ሰጋት ውስጥ የከተተ ክስተት ሆኑዋል::

የአዲስ አበባ የከተማ ልማት መስፋፋትን ተከትሎ የመጣው ተቃውሞ ብዙ ነገሮችን ገልጠን እንድናይና ላየነው ነገር ደግሞ ፈውስ ይሆናል የምንለውን መፍትሄ እንድናሰብ ያስገድደናል::  የኦሮሚያ ክልል ዎጣቶች የከተማ ልማቱን ሲቃዎሙ ከምን አንጽር እንደሆነ ማዎቁ በእኔያ ግምት መሰረታቂና ቁልፍ ጥያቄ ነው:: ይህ ጥያቄ የአንድነት ሃይል ተብየውንም ከሁለት የከፍለ በመሆኑና አገራችን ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ በቅጡ ያላገናዘበ ትንታኔ በአንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ሲስተጋባ እንሰማለን:: ይህ ግራ የሚያጋባ ትንታኔ ደግሞ ያገራችንን ችግር በትክክል እንዳናውቅ ሰለሚያደርግ እና የተሳሳተ መፍትሄም እንድንዎስድ ሰለሚያደርግ ከዎዲሁ ልናሰብበት የገባል::

አንዳድ ኢትዮጵያዊያን በኦሮሞ ክልል የተነሳውን የከተማ ልማት ተቃውሞ ማንም ያልመራውና የ 25 የኢትዮጵያዊያን ብሶት የዎለደው እንቅስቃሴ እንደሆነና ይህን እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊ ማደረግ እንደሚቻል ሲያቀነቅኑ እንሰማለን::  ይህንንም የተቃውሞ እንቅስቃሴ በ60ቹ ከተነሱት የመሬት ላራሹ እንቅስቃሴ ጋርም ሲያዛምዱት እናያለን:: በእንኔ አመለካከት የ 1960ቹ ዎጣቶች ኢትዮጵያዊ የሆነ አጀንዳ ይዘው ሲነሱ ያሁኖቹ  ዎጣቶች ደግሞ የጎሳቸውን አጀንዳ ይዘው የተነሱ ሰለሆነ  ምንም ዓይነት  ግንኙነት በማካከላቸው እንደሌለ ነው የሚረዳኝ;  አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ የለም የ 25 ዓምት የጠባብ አሰተሳሰብ ውጤት መሆኑና የኦሮሞ ዎጣቶች የእኔ በሚሉት ክልል የፈደራላዊውው መግስት መስፋፋትም ሆነ በእኔ ምጣኔ ሃብት አዛዥ ናዛዥ ሊሆን አይችልም የሚል ሲሆን አገራችንን ሊበታትን የሚችል አደጋ እንደሆነ ይናገራሉ::

በእኔ ግምት የከተማ ልማትና የጎሳ ፖለቲካ አብረው ሊሃዱ የማይችሉ ሁለት ተጻራሪ ነገሮች ናቸው:: ምክንያቱም የከተማ ልማት የህዝብን አንድነትን ; ፍቅርን; መተሳሰብን; የኛ ማለትንና የአጠቃላይ ህዝቡን ይሁንታ የሚጠይቅ ጉዳግ ነው:: እነዚህ እሴቶች በለሉበት ሁኔታ ኪሰን ለማደለበና ገበሬውን ለማፈናቅል ካልሆነ በስተቀር ህዝብን የሚጠቅም ልማት  ከቶውንም ሊሆን አይችልም:: ሰለዚህ ወያኔ ሊተገብረው የፈለገው የልማት ፕሮግራምና አገሪቱ የተዋቀረችበት አዎቃቀር አራባና ቆቦ/ compatabel አይደሉም:: ከተማ ልማት በመሰረተ ሃሳቡ ትክክለኛና ለአንድ አገር ልማት መሰረታዊ መሆን ያለበት እንደሆነ የታዎቀ ቢሆንም እንደኢትዮጵያ ያለ አዎቃቅር ያላችው አገሮች  ግን  ልማት መሆኑ ቀርቶ ሰሞኑን እንዳየነው ብጥብጥና ሁከት ነው ተርፉ:: ምክንያቱም የከተማ ልማት ከተሞችን እያለማ እበረተሰቡን በኢኮኖሚ ትሥሥር ሰለሚያያይዝና እኛ የሚል አሰተሳሰበን ሰልሚያመጣ በጎሳ ለተደራጁ ቡድኖች የተመቸ አይደለም:: ይህን ስል አሁን ዎያኔ ያቀደውን የከተማ ልማት ዓይነት ለማለት እንደልሆነ አንባቢ ሊረዱለኝ ይገባል::

ከኦሮሞ ዎጣቶች አመለካከት/perspectiv/ አንጻር ሳየው ደግሞ ተቃውሞው የጠባብ አሰተሳሰብ ውጤት እንደሆነ ነው የተገነዘብኩት:: ዎጣቶቹ ይዘውት የተነሱን መፈክር ማየት በራሱ በቂ ማሰረጃ ነው:: በ እኔ አመለካከት በዚህ 25 አመት ዉስጥ ኦሮሞ የሚባል ማንነት እየጠነከረ የመጣበትን እውነታ ነው እያየን ይለነው:: አንዳን ዎገኖች ይህን እውነታ እያዎቁ እንዳላዎቁ ሆነው እራሳቸውን እየሽነገሉ ማለፍን እንደ ፖለቲካዊ ትክክለኝነት እየዎሰዱ ለችግሩ ትክክለኛ መፍሄ እንደመፈልግ ፋንታ እውነታዉን በመፍራት የችግሩን ምንጭ እና መፍትሄ የተሳሳተ እንዲሆን ሲያደርጉት እናያለን:: አካፋን አካፍ ብሎ ያገራችንን ችግር በቅጡ መርምሮ መፍትሄውንም ማፈላለግ  ሲገባ የተሳሳተ  diagnos  እየሰጡ መፍትሄውንም ማንሻፈፍ አገራችንን ያጠፋታል እንጂ አያለማትም:: ለዚህም ነው የጹሁፊን እርዕስ በሺታውን ያላዎቃ በሺተኛ መጨረሻው አያምርም ያልኩት::

የሶቅራቶስንም ሆነ የዊልያም ሽክስፒርን ፍልስፍናዊ አባባሎችንም የተጠቀምኩት ማንንትን ማዎቅ አልፋና ኦሜጋ መሆኑን ለማሳየት የሞከርኩት: አንድ ሰው እኔ ማን ነኝ በሎ መጠየቅ ሲጀመር ደካማና ተንካራ ጎኑን አዉቆ መሻሻልን እንደሚያስግኝለት ሁሉ ኢትዮጵያዊያንም  የአገራቸውን  የተዎሳሰበ ችግርና ደካማ ጎናችንን ነቅሰን በባዉጣት ድክመታንን አርመን ለአገራችን ችግር ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ ነገር መሻት ዎቅቱ የሚጠይቀው አንገበጋቢ ጉዳይ ነው:: የአገራችንን ዘርፈ ብዙ ችግር አውቆ መፍትሄውን ለማፈላለግ; ችግራችን ምንድን ነው? ችግራችን ከየት መጣ? እንዴትስ ብናደርግ ነው ከዚህ ውሰብሰብ ችግር ልንዎጣ የምንችለው የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት መሰረታዊ  ነው::

ከላይ ያሰቀመጥኩዋቸው ሁለት ነጥቦች ሰሞኑን በመሃሉ ያገራችን ክፈል የተነሳውን የከተማ ልማት ተቃውሞ ሊመልሱ ይችላሉ ያልኩዋቸውን ነገሮች ለማንሳት እሞክራለሁ::

በዚህ ባሳለፈነው 25 ዓመት የከፋፈለህ ግዛው ዘመን ውስጥ ዜጎች እንደ አንድ አገር ሰዎች እንዳያስቡ የተደረጉበትና ልክ በ 16 ክፍለዘመን የነበረወን ዓይነት የህበረተሰብ አደረጃጀት የተከተለ አኑዋዋር እንዲከተሉ የተደረገበትን ሂደት ነው እያያየን ያለነው:: እውቁ የሶሾሎጂ ዎይንም የማህበራዊ ሳይንስ አባት ኢሚል ዶርከም/ Emil Durkheim የprimitive communal society and the modern society  በማለት የህበረተሰብን እድገትና ትስስር ሲገልጽ  ስው ሰራሽ እና ተፈጥሮዊ  አብሮነት/ mechanices and organices solodarity  በማለት ይከፍለዋል:: ትርጉም የራሴ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዝምታው ለምን ነው? (አንተነህ መርዕድ)

እንደ ዶርከም አሰተሳሰብ  ያለ አብሮነት/solidarity  ህበረተሰብ የሚባል ሰብሰብ በፍጹም ሊኖር እንደማይችል ያስረዳናል:: ሰልዚህ አብሮነት  አንድን ህበረተሰብ እንደ ደርና ማግ ሆኖ በማያያዝ የህበረተሰቡን መጭ ዕድል ብሩህ እንደሚያደርገው ነው የህበረተሰብ ጥናት ተሞክሮች የሚያስረዱን::  ጥያቄው ግን እንዴት ዓይነቱን አብሮነት ነው ለህበረተሰብ ዕድገት ጠቃሚ የሚሆነው የሚለው ላይ ነው:: እስኪ ሁለቱን ዓይነት አብሮነት ዘርዘር አድርገን በማየት የትኛው አይነት አብሮነት ነው አሁን ላለንበት አለም ተስማሚ የሚሆነው የሚለውንና በየትኛው ዓይነት አብሮነት  ነው አገራችን እየተመራች ያለችው? የሚለውን ከ ዎቅቱ የማህል አገር ዎጣቶች ተቃውሞ ጋር በማያያዝ ለመተንተን እሞክራለሁ:: እስኪ Emil Durkheim አብሮነት ሰለሚላቸው ሁለት ነገሮች እንግባ:: እነዚህ ሁለት የአብሮነት ዓይነቶች ታራካዊ እድገትን ተከተለው የኖሩና የሚኖሩ እንደሞሆኑ መጠን የምንኖርበትንና ያለፍነውን ግዜ እንድናነጻጸርና የስው ልጆችን የህበረተስብ ዕድገት ተከትሎ የሄደ አኑዋዋር እየኖር መሆኑና አለመሆኑንም ጭምር የሚያሳየን የግዜ ሰሌዳም ነው::

Mechanics solidarity/ ሰው ሰራሽ አበሮነት 

የሰው ልጆች የመጀመሪያ እና ጥንታዊ የሆነ የአብሮነት ዓይነት ሲሆን ሰው እሱን በሚመስሉ; አንድ ዓይነት ቁዋንቁዋ የሚናገሩ; እንደ ጥንታዊ የጋርዮች አኑዋኑዋር ዓይነት ቤተሰባዊና ዝምድናን ያማከለ የአብሮነት ዓይነት ሲሆን የስው ልጆች የማሰብ አቅማቸው ውስን በነበረበት ግዜ ይኖሩበት የነበረ የአብሮነት አይነት ነው:: በዚህ የአብሮነት ስራዓት ውስጥ ሰርዓቱ የሚጠይቃቸው ቅድመ ሆኔታዎች እኩልነት እና አንድ ዓይነት የጎሳ ማንነት/homogenity  እንዲኖራቸው ይጠበቃል:: እነዚህ ሁለት ነገሮች የኔ በሚሉት ማህበረ ውስጥ ሲዋሃዱ mechanices solidarity የሚሉትን ህብረተስብ ይፈጥራሉ ማለት ነው:: በዚህ የ አኑዋዋር ዜዴ ውስጥ ግለስብ ቦታ አይኖረውም:: የስው ልጂ እራሱን የቻለ በራሱ የራሱን ጉዳይ የሚፈጽምና የሚያስፈጽም ከሆነ በህበረተሰቡ ዘንድ የተዎገዘ ይሆናል:: ጎሳው ነው ሁሉንም ነገር የሚዎሰነው እንጂ ግለስብ በዚህ ዓይነት ስራአት ውስጥ ቦታ የለውም:: Emil Durkheim የዚህን ዓይነት ሰራዓት conscience collective  ይለዋል::

ሰውሞኑን ወያኔ የ ኦሮሚያ ክልል ብሎ በሰየመው የመሃሉ አገራችን ክፍል በሚኖሩ ወጣቶች የተነሳው ተቃውሞ የሚያስረዳን ጉዳይ ቢኖር ከላይ የጠቀስኩት ዓይነት የአኑዋኑዋር ዘዴ የሚረብሽና homogentity የሚያናጋ ሰለመሰላቸው አደጋውን ለመከላከል የጎሳው አባል የሆኑ ዎጣቶች ያነሱት አመጽ ነው:: ይህ ዓይነት አካሄድ አገራችንን ሊያጠፋ ዎደ ሚችል መንገድ እየመራን ሰልሆነ ኢትዮጵያን የምንወድ ዜጎች ሁሉ ልናሰብበትና ተደራጅተን ይህን የሃይል ሚዛን መቀየር ካልቻል አገራንን እያጥን እንድሆነ ማዎቅ አለብን:: ይህን ከላይ የጠቀስኩትን ቲዎሪ ማቅረብ የፈለኩበት ምክንያት አገራችን ያለችበትን ችግር የሚገልጽና ሰዎች የማሰብ አቅማቸው ባልዳበረብት ግዜ ይጠቀሙበት የነበርውን የ አኑዋዋር ስልት በ 21. ክ/ዘመን እንድናስብ በመደረጉና ይህን ተከትሎ እየመጣ ያለው ችግራችንን በአገባቡ አለማዎቅና ችግሩንም ይፈታል ተብሎ የሚቀርበው ሃሳብ ሰላሳሰበኝ ነው::

Organices solidarty/ ተፈጥሮአዊ አብሮነት 

የዚህ ዓይነቱ አብሮነት በተለያዩ የህበረተስብ ሰብጥሮች ውስጥ ሲገኝ ከላይ እንደተጠከሰው ጎሳንና አንድ ዓይነትነትን አይጠይቅም:: በዚህ አይነት የአብሮነት ሰራአት ውስጥ ስውች ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው የመሰራትና ከፈለጉት ሰው ጋር አብሮ የመኖር እና እንደ ግለስብ በራሳቸው እጣ ፈንታ ላይ የመዎሰን መብት ያላቸ ሲሆን ልክ እንድ 21. ክ/ዘመን ዘመናዊ ሰው በማሰብ የሰው ልጂ በችሎታውና በስራው እሱንና አገሩን ይጠቅማል ባለው መስክ የመስራት መብት እንዳለው የሚያውቅ የ አብሮነት ስራዓት ነው:: ሰዋች በፈለጉት አይነት አደረጃጀት የመደራጂት መብት አላቸው ለምሳሌ የሴቶች ማህበር; የዎጣቶች ማህበር: የሰራተኛ ማህበር; የመምህራን ማህበር እና ወዘተ:: ሰለዚህ ሰዎች ብዙ ማንነት እንዳላቸው የሚያውቅ ተፈጥሮዊ አብሮነት ነው:: እነዚህ ብዙ ማንነቶች ከሌላ ማንነቶች ጋር የተያያዙ ሰለሆነ አንድን ህብረተሰብ እንደ ማስትሺ ሆነው ያያይዙታል::

በ እንኔ እምነት አገራችን ተፈጥሮዊ በሆነ አኑዋኑአር ስራዓት ብትተዳደር የህበርተሰብን መተሳሰር የሚያመጣ ሰለሆነ ለአገራችን ችግሮች ፍቱን መድሃኒት ሊሆን እንደሚችል እገመታለሁ:: ምክንያቱም አግላይ ሰላልሆነና ሰው በስራውና በችሎታው የሚሰራ በመሆኑ ችግርን የመቀነስና ችግርም ቢመጣም ቀለል ያል በተደራጀብት የሞያ አካባቢ የሚፈታ ይሆናል ማለት ነው::

መፍትሄው የሚጀምረው ችግራችንን በቅጡ ማዎቅ ላይ ይሆናል ማለት ነው:: ችግራችንን ካዎቅን በሁዋላ የጠባቦቹን የሃይል ሚዛን ለመቅየር ኢትዮጵያዊ የሆነው ሃይል በአገር አድን አጀንዳ ውስጥ ተደራጂቶ ሲታገል ብቻ እንደሆነ ነው የሚገባኝ:: ኢትዮጵያዊው አሁን አገሩን ለመታደግ እየተሰባሰብ ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ዓይደለም ይሆንና በቶሎ ካልተደራጂንና የሚሆን ነገር ካላደረገን አገራችንን ባማጥፋቱ ሂደት ላይ እየተባበርን እደሆነ ማዎቅ ይገባል እላለሁ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ጠላቶችዋንም ጉልበታቸውን ቄጤማ ዓይናቸውን ጨለማ ያደርገው::

ሰላም ስንብቱ::

ከበደ ተድላ

e-mail: kebedetedla48@gamil.com

Share