ዋሽግተን ዲ ሲ
ረቡዕ ፣ ዲሴምበር 9 ቀን 2015
በዋሽንቶ ዲሲ የኢትዮጵያ ህዝብን ድምጹን ማሰማት የማይታክታቸው አገርና ወገን ወዳድ የሆኑ ወጣትም በእድሜን የገፉ ይገኛሉ።ለወያኔ ኢሃዴግ ብሽቀቱ፤ራስምታቱ፤መጋለጡ፤እርግማኑ እኒህ ናቸው።ዋይት ሀውስ ደጅ ይቆማሉ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቢሮ ደጃፍ ሆነው ይጮሃሉ።ባደባባይ ተሰልፈው ወያኔ የሰራውን በደል ጩኸው ያሰማሉ።ፀሀይ፡ዝናብ፤በረዶ የሚያግዳቸው የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ባለውለታው ጠበቆቹ ናቸው።ወያኔ ኢሃዴግ ቁጥራቸውን ለማሳነስ እኒህን ጠበቆች ጥቂት ናቸው ብሎ፤ሰልፍ ያልወጣውን ደግሞ “ዝም ያለው ብዙሃን” (The silent majority)ብሎ ለመከፋፈል ያምረዋል።የወያኔ ድንቁርና በአሜሪካ አንድ ሰውም ቢሆን ተቃዋሚ ሆኖ መቆም መቻሉን ለማየት ይጋርደዋል።ለነገሩ ወያኔ ሃያ ዓመታት የተኛ የኩሬ ውሃ ነው።እኒህ ቆራጦች ወያኔ ኢሃዴግን ሳያሰናብቱ ክንዳቸውን ላይንተራሱ የቆረጡ፤ ኢትዮጵያ ሲባል ብድግ የሚሉ ጀግኖች ናቸው! ስለሰልፈኞቹ ይህን ብዬ የዛሬውን ልንገራችሁ።
ቪየና ቨርጂኒያ ካለው ሰፈሬ የብርትኳን ቀለም መለያው ከሆነው የከተማ ባቡር ተሳፍሬ ጆርጅ ዋሽግተን ዩኒቨርሲቲ ከሚገኝበት ጣቢያ ወርጄ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት አመራሁ።ስቃረብ ድምጽ ሰማሁ።ጠጋ ስል የኢትዮጵያ ባንዲራ በብዛት ይውለበለባል።ቀጥሎ ከፍ ያለ ድምጽ መሰማት ጀመረ።በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የሚደረገው ግድያ፤የኦሮሞ አርሶ አደር የተነጠቀው መሬት ተነሳ።የአማራው መፈናቀል፤የጋምቤላው ህዝብ የተቀማው መሬት፤የአፋሩ በደል፤የሶማሌው ክልል ጭፍጨፋ፤የድፍን ኢትዮጵያ ተራ በተራ በወያኔ መመተር ተደጋግሞ በጩኽት ተነገረ።ይህ ሁሌም የወያኔ እርግማን ያልኳቸው አይበገሬዎች የሚጮሁት ነው።የዛሬው ለየት ያለ አዲስ ምዕራፍን ያበሰረ በርግጥ የወያኔን ሽኝት አብሳሪ ነበር።ደስ ያሰኘኝም ይኸው ነው።የሰማሁት “አንከፋፈልም”።”የኦሮሞው ደም የአማራው ነው” “የአማራው ደም የኦሮሞው ነው” “ወያኔ የትግራይን ህዝብ አይወክልም” ሰልፉ የኢትዮጵያ ህዝብን ስሜት፤ተባብሮ መነሳትን የጠየቀ ነበር።በኦሮምኛ አልነው ባማርኛ ዘዴው፤ተመራጩ ቃል ህብረት ነው።
ለሃያ ሶስት ዓመታት ወያኔ ደሀው አማራን ሲገል፤ሲያፈናቅል፤ ኦሮሞውን በዳይህ አማራ ነው ሲለው ኑሯል።ለአማራው ደግሞ ኦሮሞውን ማስፈራሪያ ሲያደርገው ቆይቷል።የዛሬው ሰልፍ ይህ የተባ ተንኮል መክሽፉን ያየንበት፤”መክሸፍ እንደ ወያኔ” የምንልበት ትክክል ለወያኔ ድቀት ቅድመ ሁኔታ የተተገበረበት ቀን ነበር።ኢትዮጵያን “እንኳን ደስ ያለሽ” አልኳት።ወርቅ ከሆነችው ኢትዮጵያ መፈጠሬን በሰልፉ ላይ እቶቸንና ወንድሞቸን ሳያቸው ስሜቴ ጋለ። ልዩ ቀን ነበር።የሞቱት ሰማእታት ወያኔን እንድንፋረድ በብቱ እያስነሱን ነው።ወያኔ የከፋ እሚመጣ እንደሆነ ልስበክ ቢል እንደምን ብሎ ?ከተባበርን ከተደማመጥን ሰላም ሳይርቀን ወያኔን አንገዋለን፤ ለይተን አጨብጫቢዎቹን አሳፍረን በህግ፤በስርዓት፤ተከባብረን ባገራችን እንደማንያው ህዝቦች ጎሳ ክልል መከፋፈልን ታሪክ አድርገን አገራችንን በጋራ እንኖርባታለን።ወያኔን ይጭነቀው።የወደፊቱ ብሩህ ነው።ወገኖቸ ደስ ብሎኛል።ኢትዮጵያን ፈጣሪ አምላክ ሲታረቃት እንዳይ እድል ሰጠኝ።አላህ ወአክበር!
ይህ የዛሬው ሰልፍ ርእሱ፤መግቢያው፤አካሉና መደምደሚያው አንድ ቃል ነው። ህብረት።ያጣነው ይህን ነበር።ዛሬ ወያኔ ሃያ ሶስት ዓመታት የሰራው ግድብ ፈነዳ።በሩ ተከፈተ።ህወያትን ማስጨነቅ ጀመረ።ሳይታሰብ የወያኔ እብሪት ከዛሬው ቀን አደረሰን።ወያኔ በገዛ እጁ ወደኋላ የማይመልሰው ችግር፤አጣብቂኝ ውስጥ ገባ።ሞት ግድያውንማ ወያኔ እንድንለምደው አድርጎን አልነበር ? አዲሱ ነገር ህብረት እያበበ ወያኔ እየጨነቀው መሆኑ ነው።”ወያኔን በብረት፤ሰይጣንን በጸሎት” “ሁለገብ ትግል ብህብረት”
ዛሬ በዓለም ተበትነን ያለነው ወገናዊ ግዴታ አለብን።የተገደሉት ወጣቶች ከኦሮሞ ህዝብ አብራክ የወጡ የአገር የወገን ተስፋዎች ናቸው በህብረት ተነስተን ወያኔን መፋረድ አለብን።ምርጫችን አንድ ነው።መተባበር ብቻ!ካልተባበርን ወያኔን መኮነናችን ባቻውን አይጥለውም።የድሮ ታሪክ ላይ ሙጭጭ ብለን ክርክር ይሻላል ካልን የወትሮውን ስተት ደገምን ማለት ነው።የኦሮሞ ህዝብ በዳይ ወያኔ ኢህአዴግ ነው።የህብረቱ አዝመራ በያለት ይጎመራል።መክሸፍ እንደ ወያኔ!
የተበደሉ ህዝቦች በጋራ ጠላታቸው ላይ ሲነሱ የሚያቆማቸው ሀይል የለም!
የኦሮሞ ህዝብና የአማራ ህዝብ አንድ አካል ናቸው! ጠላታቸው ወያኔ ነው!
ወያኔ ከነጥላቻው ጥርግ ይበል!የወገኖቻችንን ሞት በጋራ እንፋረዳለን!
የጥላቻው መጋረጃ ተቀደደ! ወያኔን ይጭነቀው!
ድል ለዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ሁሉ!
ኢትዮጵያ በአንድነትዋ በነጻነት ለዘለዓለም ትኑር!