February 19, 2013
8 mins read

የማተሚያ ማሽኑን ለመግዛት ውጤታማ እንቅስቃሴ ጀምረናል


ኤዲቶሪያል ቦርድ የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ

አቶ ስዩም መንገሻ
የማተሚያ ማሽኑን ለመግዛት ውጤታማ እንቅስቃሴ ጀምረናል 1

የዛሬው እንግዳችን አቶ ስዩም መንገሻ ይባላሉ፤የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሰብሳቢ እና የፓርቲው ኤዲቶሪያል ቦርድ የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ናቸው፡፡ በፓርቲው ልሳን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዙሪያ ጥቂት ቆይታ አድርገናል፡፡

  • የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ህትመት ከተቋረጠ ከሁለት ወራት በላይ አስቆጥሯል፤ህትመቱ የተቋረጠው ለምንድነው?

ጋዜጣችን ህተመቷ እንዲቋረጠው የተደረገው በህግ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንዲቋረጥ የተደረገው ህግ በመጣስና የፕሬስ አዋጁን ተላልፈን ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ በአስተዳደራዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ነው፡፡ ለምሳሌ የምናሳትምበት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ስራ ስለበዛብኝ በሚል አላትምም ብሏል፣ የግል ማተሚያ ቤቶችም ሁለቴ ካሳተምን በኋላ በገዥው ስርዓት በሚፈጠር ጫና አናትምም ብለውናል፡፡ ስለዚህ የጋዜጣችን ህትመት የተቋረጠው በማተሚያ ቤት እጦት ነው፡፡

  • በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከተውን የመንግስት አካል ጠይቃችኋል? ከጠየቃችሁስ ምን ምላሽ ተሰጣችሁ?

የሚመለካታቸውን ሁሉንም ጠይቀናል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፓርቲው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትን የጋዜጣችን ህትመት ለምን እንዲቋረጥ እንደተደረገ በደብዳቤ ጠይቀናል፤የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትን በግልባጭ ደብዳቤ ሁሉ ጠይቀን እስካሁን ምላሽ አላገኘንም፡፡

  • ታዲያ በአሁን ሰዓት ምን አስባችኋል? ምንስ ለማድረግ አስባችኋል?

በአሁን ሰዓት ሁሉንም ማተሚያ ቤት ጠይቀን ስላልተሳካልን ዝም ብለን አልተቀመጥንም፡፡ ምክንያቱም ጋዜጣችን ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ላይ ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትም አብሮ ነው የታገደው ብለን እናምናል፡፡ ስለዚህ ይህ የሰው ልጆች ተፈጥሯዊ መብት የሆነውን ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው፡፡        ምንም እንኳ የጋዜጣችን ህትመት ቢቋረጥም የፓርቲውን የህትመት ማሽን ለመግዛት ከምናደርገው እንቅስቃሴ ጎን        ለጎን  በ  www.fnotenetsanet.com  ድህረ-ገፅ ላይ የምንችለውን ያህል መረጃ ለህዝቡ በማዳረስ ላይ እንገኛለን፡፡ ነገር ግን በዋነኝነት በማተሚያ ማሽን እጦት ምክንያት የተቋረጠውን ጋዜጣ ለማስቀጠል ፓርቲው የራሱን ማሽን ለመግዛት የተለያዩ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስልቶችን በመቀየስና የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር በሀገር ውስጥና በውጭ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

  • ለማሽኑ መግዣ ይረዳናል ያላችሁትን ገንዘብ ለማግኘት በምን ዓይነት ዘዴ ነው እየተንቀሳቀሳችሁ ያላችሁት?

ፓርቲው ለማተሚያ ማሽኑ ግዥ የሚሆን በኤዲቶርያል ቦርዱ አማካኝነት መፅሐፍ በማሳተም ለንባብ ማብቃት፣ ሌላው የ 30፣ የ50፣ የ100 ፣ የ300 ፣ የ500 እና የ1000 ብር የኩፖን ሽያጭ አዘጋጅተን በሀገር ውስጥ ተግባራዊ በማድረግ እየተንቀሳቀስን ነው፤ እንዲሁም ከኩፖን ግዥው ውጭ ሊረዱን ለሚፈልጉም አቢሲኒያ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የሒሳብ ቁጥር 47 ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ኩፖን በመግዛት ለሚተባበሩ ኩፖኖቹን በፓርቲው ጽህፈት ቤት በተጨማሪ ባሉበት ቦታ ድረስ ሄደን ለመሸጥ ተዘጋጅተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በውጭ ሀገር ያሉ ሀገርና ወገን ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ለዚሁ ማሽን መግዣ እንዲረዳ በአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች አማካኝነት የራሳቸውን ኮሚቴ በማዋቀር የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሰው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

  • ለመግዛት ያሰባችሁት ማተሚያ ማሽኑ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ብቻ ነው ወይስ…?

አይደለም፤ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ህትመት ባይቋረጥ ኖሮ በኦሮሚኛ ቋንቋ ሊታተም የነበረው ዳንዲ ቤሊሱማ ጋዜጣ እና ለሀገሪቱ የሚጠቅሙ የተለያዩ ንድፈ ሐሳቦች የሚንሸራሸሩበት ዳንዲ መፅሔትን ጨምሮ የተለያዩ የፓርቲውን እንቅስቃሴና ዓላማ ለህዝብ ለማድረስ የሚረዱ የህትመት ውጤቶችም ይታተሙበታል፡፡ በነገራችን ላይ የኦሮሚኛ ጋዜጣው ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በሌሎች የሀገራችን ቋንቋዎችም የተለያዩ ጋዜጦችን ለማሳተም በፊትም ቢሆን ዕቅዱ ስለነበረን የማተሚያ ማሽኑን ከገዛን ቶሎ ወደ ስራው እንድንገባም ይረዳናል፡፡

  • ያሰባችሁት እንዲሳካ ከህዝቡ ምን ይጠበቃል?

ይህ የማተሚያ ማሽን መግዛት ጋዜጣና መፅሔት የማሳተም ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የዜጎች ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ጉዳይም ስለሆነ ሁሉም በሚችለው አቅም ቢረዳን የሁላችንም ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በሀገራችን እንዲረጋገጥ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ እኛም ህዝቡን በመተማመን ለማተሚያ ማሽኑ ግዥ የሚሆን ገቢ ማሰባሰቢያ የጀመርን ስለሆነ ሁሉም በሚችለው አቅም ከላይ በጠቀስኩልህ ኩፖን በመግዛት፤ እንዲሁም በባንክ ገቢ ማድረግ የሚፈልግም በአቢሲኒያ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 47  ገቢ በማድረግ እንዲተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop