ኦቦ ሌንጮ ለታ ተመላሽ ዲያስፖራ የመሆን መብቱ ለምን ተከለከለ?

ከአብሼ ገርባ

የዛሬ ስድስት ወር ገደማ ኦቦ ሌንጮ ያለኝ የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እፈልጋለሁ ብሎ ጏዙን ጠቅልሎ ሀገር ቤት መግባቱ ይታወቃል:: ሆኖም በፍጥነት በመጣበት እግር ሀገሩን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ::

የሌንጮ ለታን መባረርና አሁን ያለውን የዲያስፖራ ጥሪ ስንመለከት የተለየ የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እንደማይፈቀድና ዶላርና ቦዶ ሀሳብ ብቻ ይዞ መምጣት እንደሚቻል ነው::

አንድ የኦሮሞ ዲያስፖራ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በዚህ ሀገር ውስጥ አንድም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም ብሎ በአንድ ቀን አዳር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለመኖሩን ገምግሞ ምስክርነት መስጠት የሚችል ጭንቅላት ያለው ዲያስፖራንም ለማየት ችለናል::

ኢህአዴግ ፖለቲካውን መቶ በመቶ ዝግ በማድረግ ዶላሩን ብቻ አምጡ እያላቸው ነው::

ዋናው ቁልፉ ግን ሀገሪቱን አንቆ የያዘው የዶላር ችግር ሳይሆን ፖለቲካው ስለተቆለፈበት ነው::

በኔ ግምት የዲያስፖራ ዶላር አይደለም የአሜሪካ ዶላር ጠቅላላ ተሰብስቦ ቢመጣ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር እስካልተፈታ መፍትሄ ሊሆን አይችልም:

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሀገር አድን የጋራ ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ እና መጪ የፖለቲካ ጉዳይ አንፃር ሲፈተሽ

3 Comments

  1. “ይናገራል ሠንደቅ ገሃድ አይደበቅ! ….. ህወአት/ኢህአዴግ ሆደ ሰፊ ነው ቂመኛ አደለም ሲል የኦነግ አመራር ለቤተሰቦቻቸውና ለትግል አጋሮቻቸው ለቅሶ ፣ ለዓመታዊ የባሕል ክብር፣በሰላም ክልላዊ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይፈቅዳል።ኦቦ ሌንጮ ለታ “የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እፈልጋለሁ ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ሀገር ቤት መግባቱ ይታወቃል:: ህወአት/ኢህአዴግ አትፎግረን እንተዋወቃለን ከውጭ ሆነህ ያልቻልከውን ከውስጥ ልትሰርስር ነው ብሎ ቀይ ምንጣፍ ሳያናጥፍ እንዳውም የፖለቲካ ቢሮ ባለሙሉ ሥልጣን ስብሃት ነጋ አሁን ለአንተም ለእኛም አደጋ ነው ሲረጋጋ እንጠራሃለን ለሚቀጥለው ሀገራዊ ምርጫ ሁሉን ነገር አመቻችተን ትሳተፋለህ ተብሎ በመጣበት እግር ሀገሩን ለቆ ወደ ካናዳ ተመልሶ እራሱን እንዲያደራጅ በታላቅ አሸኛነት እንዲወጣ ተደረገ::
    ===== ግን ሌንጮ ለታን የሚተካ አዲስ ሀሳብ አፍላቂ ኦሮሞ ወጣት እንዴት አልተወለደም?….የሌንጮ ራዕይ በጃዋር መሐመድ ይራመድ የለምን!? አሮሞ ምን ያረጀ ያፈጀ የፖለቲካ እንቨስተር ያስፈልገዋ? ..የራሱ ተለጠተ ክልል አለው፣ እራሱን በራሱ ያስተዳድራል፣ በራሱ በሕልና ቋንቋ ተደራጅታል…ያነባል ይፅፋል ይናገራል ይህ መከላከያውን መቆጣጠር አለብኝ የሚለው ጉዳይ የህወአት፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ግንቦት ፯፣ ሻዕቢያንና መስከረም ፪ ጨምሮ ገና ብዙ የፖለቲካ ኢንቨስትመንት ሳይሆን የሥልጣን ሜዳ ቅርሚያ ስለሚሆን አፈታቱ ግዜ ይወስዳል።
    ===== አንድ የኦሮሞ ዲያስፖራ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በዚህ ሀገር ውስጥ አንድም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም ብሎ በአንድ ቀን አዳር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለመኖሩን ገምግሞ ምስክርነት መስጠት የሚችል ጭንቅላት ያለው ዲያስፖራንም ለማየት ችለናል::”
    ***መቼም ይህ ሰው የምንይልክ ወይም የቀ/ኀይለስላሴ የልጅ ልጅ ወይንም የመለስ ዜናዊ ወንድም እንዳልሆነ እርግጠኛ ነን፤ አባ ዱላ ገመዳም ሆነ መራራ ጉዲና አውሮፓና አሜሪካ አውስትራሊያ ሲሄዱ የሚነጋግሩት የኦሮሞ ተወላጅ ነው ምን ብለው ቢጠሩት ይህንን ሊናገር ቻለ!? “ኦሮሞ ምንም የዓላማ ልዩነት የለውም ከአማራ ህወአት ይሻላል ብዙ ድል ተጎናጽፈናል የፖለቲካው ተንታኝና በታኝ የኦሮሞ ሙስሊም ፈረስት ጃዋር መሐመድ። ታዲያ ይህ ግለሰብ ያለው ስሕተቱ ምንድነው?የምን በክረምት አቧራ ማስነሳት ነው? ግለሰቡ ኢንቨስትር ከመሆኑ በፊት በዲያስፖራው ውስጥ ምን የሥራ ድርሻ ቢኖረው ነው!? ታዲያ እነኛ ባንክ፣ የግል ድርጅት፣ፍርድ ቤት የሚያፈርሱና የሚቃትሉ የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች ይህንን ሰምተው እንዴት ዝም አሉት!? እየበሉ ማልቀስ ካልሆነ!?
    ===== ኢህአዴግ ፖለቲካውን መቶ በመቶ ዝግ በማድረግ ዶላሩን ብቻ አምጡ እያላቸው ነው::”
    ** በእርግጥ ከወሬ ዶላሩ ይሰራል! እዚህ በእየሥርቻው ወሬ ከመቁላትና ዘርን በዘር ከማናከስ ሜንጫ ከመሳል፣ ለድሃው ኦሮሞ የሚጠቅም፣ ሥራ አጥ የሚቀንስ፣ ከግል ጥቅምና መሬት ለመቀራመት የውጭ አጓጉል ባሕልና ትውልድ አጥፊ እርካሽ ኢንቨስትመንት እስከሆነ ድረስ ምንም ችግር የለውም። ግን ሀገር ለማተራመስና ህዝብ ለማበጣበት ከሆነ ግን ኢንቨስተሮቹ ሳይሆኑ ጠሪዎቹ ኃላፊነት አላባቸው።ይህ የውጭውን ተቃዋሚ ሀይል ለመቀነስ የሚደረግ እንቨትመንት ከውስጥ ገብቶ እራሱን ይፈነቅለውና ያስተዘዝበናል።
    ==== የዲያስፖራ ዶላር አይደለም የአሜሪካ ዶላር ጠቅላላ ተሰብስቦ ቢመጣ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር እስካልተፈታ መፍትሄ ሊሆን አይችልም:
    *** የኢኮኖሚ ችግርና ፖለቲካ ችግር መለየት አለበት። “ርሃብና ድርቅ፤ ሶስት ግዜ በቀን መብላትና ተመጣጣኝ ምግብ ማግኘት እንደተምታታባቸው ኢኮኖሚስቶች ሰሞኑን አንድ ቀልደኛ “የአዲስ አባባ ጎርፍ ኢትዮጵያ አየር ሁኔታ ትንብያ (meteorology)ቢሮ ሰትት ብሎ ገባ… “እንኳንስ ለሌላው ለራሳችሁም አታውቁም አላቸው አለ።”
    ____ እኔም እላላሁ ዲያስፖራው እንዲሁ በተጠራበት ቢያጨበጭብና ቢጨፍር ይሻላል እያንዳንዱ በግል ቁርሾ፣ በቡድን የጎንዮሽ ፀብና መጠላለፍ ፣ በአስመሳይና አድርባይነት ከማፍረስ በቀር በውጭው ያልተሳካለት በጋራ መሥራት ያልቻለ፡ ሀገር ውስጥ ለትውልዱ የተሻለ አዲስ አስተሳስብና የዕድገት ለውጥ፣ ሠላም፣ እኩልነት፣ አብሮ ሠርቶ አብሮ ማደግን ያመጣል ያስተምራል የሚለው ነገር ተስፋ የለውም ቢቻል ትንሽ ግም ቢል ለመብላትነ አለማባላት አሰፍስፎ የሚጠብቅ የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላ ይታያል ።ባላሶስት ባንዲራ አንድ ኢንቨስተር ድንቄም!

  2. Lencho went to Ethiopia to buy OPDO in the name of the Oromo people. He has misread the auction. Woyane sent him back empty handed.

  3. ኦቦ ሌንጮ በጭንቅላታቸው ከማደንቃቸው ግለሰቦች አንዱ ናቸው ከወያኔ በነጠላቸው ጫፍ ስልጣን ይዘው ለመምጣት ሂደው እንደ ውሻ ወገባቸውን በፍልጥ ተመተው የተመለሱ ልብ ውልቅ ።በዚህ አስተሳሰባቸው ጭንቅላታቸው ከአሳ የተሰራ ይመስላል ። መሰሎቻቸውን እያፈሩ ስለሆነ እግዚአብሔር ፓስፖርታቸውን ቢልክላቸው ጥሩ ነው።

Comments are closed.

Share