ኦባማ መጣ ኦባማ ሄደ ምን ፈየደ ? ህወሃት መሩ መንግስት ተጋለጠ::መጭው አኬል ዳማ ተበሰረ

ቢላል አበጋዝ ዋሽግቶን ዲ ሲ

ጁላይ 31፡2015

ህወሃት መሩ መንግስት ልዩ በዓል፤ልዩ ድምቀት፤ልዩ ምልክት፤ታሪዊ ንግርት ሌላም ጨመር አርጎ የፕሬዜዳንት ኦባማን ጉብኝት ቢያስወራውም አለቀ:: የተረፈ ምንም የለም። የተለወጠም ምንም የለም።ከታፈገው እስር ቤት በጣት የሚቆጠሩ ተፈተዋል። ህወሃት በዚህ አይመሰገንም።ህዝብም ዓለምም የታፈገውን እስር ነው የሚመለከተው። ይልቅስ የወያኔ መሃይም መንጋ ያደረገው የፕሮቶሎል ስተተት ሲያስቅ ሰነበተ።

ምን ደስ አለህ ብባል ፕሬዜዳንት ኦባማ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን አንስተው፤የሰው ልጅ መገኛ እያለ አክብሮት፤ ፍቅሩን እምቅ ስሜቱን ለናት አገሩ ስለገለጠላት ባለቅኔ መናገራቸው ነው።ጥቁር አማሪካውያን የባርነት ውርደትን አንቀበልም ሲሉ ኮከባቸው ኢትዮጵያ ነበረችና ገጣሚ ፖል ዱንባርን፡”ለኢትዮጵያ ከልብ” (Ode to Ethiopia) ብሎ የተቀኘውና ላግስተ ኁስ  ኢትዮጵያ በፋሽስ መንጋጋ ስትገባ “የኢትዮጵያ ጥሪ” ብሎ የገጠመውን ሌላ አኩሪ ገጣሚ ማንሳታቸው አልረሳም (Call of Ethiopia)። በተለይ በዘረኞች፤ በቂመኞች በከዳተኞ እጅ ባለችው አገር፡ይህ መሆኑ ይገርማል።ወይታሪክ? ያሰኛል።

ፕሬዜዳንት ኦባማ ወያኔን ሊያወድሱ ነው ወደ ኢትዮጵያ የተጔዙት የሚለው ጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ነው።ፕሬዜዳንቱ ዓይናቸው ሽብርተኞች ላይ ነው።አልሸባብን ለመውጋት ከሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች ቢያገኙ ኖሮ ህወሃትን አይፈልጉም ነበር። ሰራዊቱን ለማቅረብ ሽርጉድ ደግሞ መለስ የጀመረው ነው። የተለወጠ ነገር የለም።የጥንቱ ኢትዮጵያ ጦር ድንበር አስከበረ።ጠበቀ።ይሄው ነበር።ለሰላም ጥበቃ ቢሰለፍ በተባበሩት መንግስታት ነበር።ሌላ አዛዥ አልነበረም።አዳኖም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ምንድነው ቢባል የህወሃት በስልጣን መቆየት ነው የሚል ነው።ለዚህ ደግሞ ማንስ ቢያዘው አይጨንቀውም።

ጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ፕሬዜዳንት ኦባማ “መንግስታችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ብለውልናል” አለ ባደባባይ።ኦባማ ምን አገባቸው? አማሪካስ ? ባለቤቱ መስካሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እያለ ? ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ያለውን የመንግስታቸው አቌም ነው የሚንጸባርቁት።እንዴት የውጭ ጉዳይ ሆኖ ይህን አይረዳም? ጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ይህ ሊገባው አይችልም። ባድር ባይነት ላገኘው ሹመት የሚበቃ አይደለምና።ሱዛን ራይስ ለምን ሳቅ አፈናት ? በዲሞክራሲያዊ መንገድ ነው ወይ የተመረጡት ስትባል? የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን አይከታተልም? እስቲ ይችን እመቤት ክሰሳት ? እስቲ ውቀሳት ?የት አባክ ትገባለህ? ቪኦኤ እድሉን ሰጥቶህ ነበር። ሱዚ አርባክንድ ምላስ ነው ያላት! ከፈለግህ አሁንም ሞክር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ልደቱ አያሌው፤ ፖለቲከኛ ወይስ ፖለቲካ ተንታኝ?

ሌላው ነገር ፕሬዜዳንት ኦባማ አፍሪካ የሙስና ነቀርሳ አለባት ብለዋል።የሙስና ሙከራ ጣቢያ ሆና ቆይታ ዛሬ የሙስና ማዕከል የሆነችው አዲሳባ መጥተው ይህን ማለታቸው ለወያኔም ለሁሉም የአፍሪካ ሞሽላቆች ነው።የሚሰረቀው መጠን፤ የት እንደተደበቀ፤በማን? ሁሉን ከስለላ ድርጅታቸው ያገኙታል።ሟቹ ሞሽላቃው መለስ ዜናዊ የዘነጠላቸው ቢሊዮኖች ምስጢር አይደሉም። በነገራችን ላይ የናጄሪያ አዲሱ መሪ አገሬን ግጠው የበሏት ባለስልጣናት የዘረፉትን ለማስመለስ እርዱኝ ለማለት ነው ወደ አሜሪካ የመጡት፡የቦኮ ሃራምም ጉዳይ ቢቀድምም።ውጭ ጉዳይ የሚያናግሩህ ፋይልህን በጃቸው አርገው ነው።ዳሩ ምን ይገባሃል?

ፕሬዜዳንት ኦባማ የደቡብ ሱዳንን፡የኬንያን ጸጥታ ጉዳይ አንስተዋል።ኢራቅ፤ሶሪያ፤አፍጋኒስታን ያለው ሁኔታ የበለጠ የሚሳስባቸው ይሆናል።ስለፓርቲያቸው የመጭው የምርጫ ውድድር ከማሰባቸው አንጻር የአፍሪካ ጉዳይ ቅድሚያ አይዝም ማለት ያስችላል።ንግዱም ከቻይናው አፈሰማይ ይተርፈኛል ማለት ያውም ይህን ያህል ጌዜ ተተኝቶ የሚያዋጣ አይደለም።በኔ አስተያየት ፕሬዜዳንት ኦባማ ለጉዞ ያነሳሳቸው እንዲው በስልጣን ዘመኔ ያባቴን አገርና ዘመዶቸን ልጠይቅ ማለት ነው ማለት ይቻላል።

ይህ የፕሬዜዳንት ኦባማ ጉብኝት ህወሃት መሩን መንግስት በጣም ያጋለጠ ነው።ከጉብኝቱ ትንሽ ቀደም ብሎ በአበኞች ግንቦት7 ተኩስ ቢከፈት መላው የወያኔ መንጋ ተርበተበተ።ወፋፍራሞቹ የህወሃት ድመቶች ግራ ተጋቡ።ጄኔራሎቹ መወቃቀስ ጀመሩ።ሚስጥር ይሾልክ ጀመር።ጨዋታው ባጭር ጊዜ መቀየሩ ግራ አጋባቸው።አጭበርባሪው መለስ እያለ በተማሪ እንቅስቃሴ ከተማራት ተንኮል መነጋገሪያ የምትሆን አንድ ነገር ጣል ያደርግ ነበር።የድል አጥቢያ አርበኛው ቴድሮስ አዳኖም፤የውሸት መዝገብ የሆነው በረከት፤ሰካራሙ ሽማግሌ፤ ሹላፉ አባይ ጸሃዬ አንዳቸው ብልሃት የላቸውም።በተለይ ቴድሮስ አዳኖም የት ?ምን ሲያደርግ ነበር ባለፉት ቅድም ወያኔ ዓመታት ? በሜዳው ትግል ምን ድርሻ ነበረው ? ያለው ዋና ሰርተፊኬት የመለስ ተላላኪነት ነው። በቪኦኤ ራዲዮም ያስረገጠው ይህንኑ ነው።ዛሬመ “ታላቁ መሪያችን ይላል” ይህ ሰው መሳቂያ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሚኒሶታ መድኃኔዓለም ደብረሰላማችን ፣ ትንሿ ኢትዮጵያ ምትክ አገራችን - ለሰላምና አንድነት የቆሙ ምእመናን ያስተላለፉት ጥሪ

ልክ ጌታው ያሰለጠነው ውሻ አይነት ነበር የጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ቃለመጠይቅ በቪኦኤ ራዲዮ። ያልተፈቱት ጋዜጠኞችስ ሲባል “የፍርድ ቤት ውሳኔ “ እያለ ቀላመደ።ልክ እንደ ጌታው እንደ መለስ።ስለ መቶ በመቶ ማቸነፍም ሲጠየቅ ራሱን ለትዝብት ዳረገ።ከዚህ ሰው ዲግሪ የቆስጤ በርሄ የተሻለ ነው ወይ ያሰኛል። ጌታው ያሰለጠነው ውሻ የሚያሰኘው አዳኖም ሲናገር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳ መሄዱን አስመልክቶ ልክ እንደሟቹ ድውይ “መንገዱን ጨርቅ ያርግለት” ማለቱ ነው።ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤረትራ አልሄደም። እደግመዋለሁ።ወደ ኤርትራ አልሄደም። ብርሃኑ ነጋ የሄደው የትግል እቶቹንና ወንድሞቹን ሊቀላቀል ወደ ትግል ሜዳ ነው የሄደው።በኤርትራ በኩል ? አዎን። በኤርትራ በኩል:: ደህና ካምፒንግ እንኳን ወጥቶ የማያቅ የወሬ ቋት ቴድሮስ አዳኖም : “ጨርቅ ያርግለት” ማለቱ አስቂኝ ነው። ራሳቸው ህውሃቶች(መኮንኖቹ)የሚስቁበት ይመስለኛል።

የጅሉ ቴድሮስ አዳኖም በዳያስፖራ ያለው ሁሉ የደርግ አባል የነበረ ይመስለዋል።እሱ እንጀራ በወጡን ሲዝቅ ደርግን ይታገል የነበረና ዛሬ በስደት ያለው ብዛቱ እንደሚያይል፤ህወሃትም አላስቀምጥ ብሎት የተሰደደ እጅግ ብዙ እንዳለ አያውቅም።አሁን እሱ ድፍን አፍሪካን አስሶ፤ የአፍሪካ አንድነት አርኪቴክት ከነበረው ክቡር አቶ ከተማ ይፍሩ ወንበር ላይ ይቀመጥ? አይ ኢትዮጵያ ? ቴድሮስ አዳኖም ታሪክ ይወቅስሃል የሚባል አይደለም።ትልቅ አፍ ያለው ትንሽ እንሰሳ በመሆኑ።ታሪክ ደግሞ እንዲህ ላለው አይጨነቅም።

ቴድሮስ አዳኖም “በዘዴ” በቪኦኤ ቃለ መጠይቁ ላይ አንዳርጋቸው ጽጌን አንስቷል።ይህ የሚያመለክተው ምንያህል ወያኔ ስለ አርበኞች ግንቦት 7 ሲጨነቅ እንደሚያድር ነው።አንዳርጋቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ  ከመሰል የየመን ወሮበላ አረብ አብራችሁ ከያዛችሁ በኋላ ያሻችሁን አርጋችሁታል።ሁኔታውን የብሪጣኒያው አምባሳዶር ግልጥ አርጎታል።ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከምትጠቀሙበት መጀመሪያ ከቤተሰቡ ታገናኙት ነበር። ከሰብእና ጎዳና ሳይሆን እናንተ ያላችሁት ከተንኮልና በቀል ጎዳና ነው።ውጭ ጉዳይ ቴድሮስ አዳኖም ለቀንደኛው ቂመኛ ለበረከት ስሞን ይህን ንገረው። የላከህም እሱ ነው። አንዳርጋቸው ጻፈ ያልክው መጽሃፍ ተነባቢነትም ታማኒነትም የሚያገኘው አቶ አንዳርጋቸው ተፈቶ፤ቤቱ ሎንዶን ተመልሶ ቢያሳትመው ብቻ ነው።ከዚህ የተረፈው ያው አኬልዳማችሁ ነው።መለስ ሲሞት መንደራችሁ ለጥቆ የጅል ሆነ።የሚታዘብ ያለ አይመስላችሁም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምድራዊ እረኛ ያጣች ሃገረ ኢትዮጵያ!!

ባጭሩ የፕሬዜዳንት ኦባማ ጉብኝት ለወያኔ የፈየደው ምንም የለም ከመጋለጥ፤መሳቂያ ከመሆን ሌላ።የእሳቸው ጉብኝት የምስራቅ አፍሪካን የሰላም ሁኔታ ያሻሽለዋል ማለት አይቻልም።በትንሹ የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ ብቻ ቢያዩ የት ነበሩ ብሎ ያስጠይቃቸዋል። ግራ ቀኙ ፋይዳ ቢስ ነው።የህወሃት መሩ መንግስት ስንብት አዲስ ምእራፍ መክፈት መቻሉን “መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ” የተባሉት እነ ብርሃኑ ነጋ ቀድመው አውቀውታል።መንገዱ ግን ጨርቅ አይደለም።ለወሬኛ ይመስለዋል እንጂ። እድሜ ይስጠን የኢትዮጵያ አምላክ።

 

ኢትዮጵያ በነጻነት በአንድነት ለዘላለም ትኑር!

ሽብርተኛ ድርሽ የማይልባት፡የተረጋጋች፡የበለጸገች አገር በህብረት እንገነባለን!

በግፍ የታሰሩ የስልምና ሀይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን ይፈቱ!

አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች ታጋይ ሃይሎች ጎን ለጎን ወደፊት ይራመዳል!

በአገራችን ውስጥና በውጭ ያላችሁ አገር ወዳዶች ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ተባበሩ!

1 Comment

Comments are closed.

Share