“ዝግጅቱ የህወሓት ፌስቲቫል እንጂ የኢትዮጵያዊያን አልነበረም”

ከካሳሁን ይልማ (የኢሳት ጋዜጠኛ)

ኢትዮጵያዊያን ለአንድ ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ ከትመው ሀገራቸውን፣ ባህላቸውን፣ ቀዬአችውን፣ ቤተሰባቸውን እያሰቡ በአንድነት በዓመታዊ ቀጠሯቸው የማይቀርበትን ፌስቲቫላቸውን አክብረዋል። በተመሳሳይ ሳምንት እና ቀናት ከሥስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያዊያን በጋራ የሚያከብሩትን ዓመታዊ የስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል ESFNAን ለማፍረስ የተመሠረተው የከፋፋዮች ቡድን AESONE ዝግጅቱን በኮሎራዶ አሰናድቷል።

ይህ በጥቂት ገንዘብ አሳዳጅ ወረበሎች የሚመራ ቡድን ዓላማው እና ዒላማው የሼኽ መሐመድ አላሙዲን ሚሊዮን ብር ስለሆነ የሚፈልገውን ቅርጫ እስካደረገ ድረስ “ሕዝብ እና አንድነቱ ሲዖል ይግባ” የሚል ነው። አላሙዲ ዋናውን የስፖርት ፌዴሬሽን ESFNA ስፖንሰር ያደርጉ ስለነበር የእሳቸው ገንዘብ ሲቆም ፌድሬሽኑም ሕዝቡም በቀላሉ ይበተናል ተብሎ ታልሞ ነበር።
ሌላው ተያይዞ ያለው ዐቢይ ጉዳይ ደግሞ ህወሓት ዲያስፖራው ውስጥ ሰረስሮ ገብቶ በሀገር ቤት የፈጠረውን የአፋና ና ቁጥጥር መረብ በውጭ ሀገርም የማንሰራፋት ስሌት ነበር።

ሆኖም ይህ በክፋት እና በሴራ የተመሠረተ ቡድን AESONE ከዋናው ፌዴሬሽን ተሰንጥቆ በመውጣት አንድነትን ለመሰንጠቅ ያደረገው ጥረት ሊሳካ አልቻለም። ከዚያ ይልቅ ከፌዴሬሽኑ መርዝ ተነቀለለት ማለት ይቀላል። ይሁን እንጂ አሁንም በአንዳንድ የአላሙዲን ገንዘብ ናፋቂዎች በመጠቀም ሕዝብ ከሀገሩ ርቆ በአንድነት ህብር ሰርቶ ተደስቶ ቀጣዩን የሚናፍቅበትን የኢትዮጵያዊያን ስፖርት በሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽንን ለማፍረስ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። በፌድሬሽኑ ያሉ ኢምንት ልዩነቶችን ወይም ስህተቶችን በማጉላት ውስጥ ለውስጥ ለመከፋፈል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተልዕኳቸውን ሊፈጽሙ ይፍጨረጨራሉ።

ነገር ግን ንቁው ማህበረሰብ ሴራውን በመገንዘቡ የተነቀለው መርዝ ላለፉት ሦስት ዓመታት ባዘጋጀው ተመሳሳይ ዝግጅት ላይ ለመታደም እግሩን አላነሳም። እባብ መኖሩን አውቆ ወዳለበት የሚሄድ ሞኝ የለምና። ሰው እንዴ ሊታለል ይችላል ሁልጊዜ ገን ከቶ አይታሰብም::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው! "መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ"

በAESONE ውድድር ላይ የሚሳተፉ ተጨዋቾች በብዛት የጊዮርጊስ ተጨዋች የነበሩ፣ በተለይም ከአብነት እና አላሙዲ የክለቡ ባለቤትነት ዘመን ተጫውተው ያሳለፉ ናቸው። በቀጥታ ሲጠየቁ ይሉኝታ ይዟቸው እና ፈርተው ይሄዳሉ። ከሪም፣ሙልዓለም ረጋሳ፣ አሸናፊ ሲሳይ፣ አዳነ ግርማ፣ የሙሉጌታ ከበደ ልጅ ሳይቀር በእነ አብነት ቡድን ተጠርተው ተሳትፈዋል። ፈርዶባቸው!

ይሄ ቡድን ከሼኹ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ እየወሰደ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ለሁለት ዓመታት በግዙፍ ስታዲየም ዝግጅት አዘጋጅቶ ከፋፋዮች እና ጥቂት የህወሓት ደጋፊዎች በተገኙበት ወና ሆኖ በአሳፋሪ ሁኔታ ተጠናቋል።

ይህ ክሽፈቱን በመረዳት ዘንድሮ ወደ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር በመሄድ ከስታዲየም ወረድ ብሎ በትምህርት ቤት ሜዳ ሌላ ዕድሉን ሞክሯል። ወደ ዴንቨር ሲወሰድ ዋናው ቀመር በከተማዋ በረካታ የትግራይ ብሔር ተወላጆች በመኖራቸው ቢያንስ እነርሱ ገብተው በድኑን ቡድን ነፍስ ይዘሩበታል ተብሎ ነው።

አንድ በዝግጅቱ ላይ ከእንግዲህ በፍጹም እንደማይሄድ በምሬት የነገረኝ ተጨዋች “ዝግጅቱ የህወሓት ፌስቲቫል እንጂ የኢትዮጵያዊያን አልነበረም። እዛ በመሄዴ ለራሴ አፈርኩ” ብሎኛል። ገንዘብ ይሰጣችኋል ተብለው የሚሳተፉት ቡድኖች ወጣት ተጨዋቾች በቀን አስር ዶላር ብቻ እንዴት ይሰጠናል ብለው አኩርፈዋል። “አላሙዲ የሚለግሰው ገንዘብ በጥቂቶች እየተበላ እኛ ምን ቤት ነን? በዚያ ላይ ከሕዝባችን ተለይተን እስከመቼ” ብለዋል።

ከዋናው አንጋፋ ፌዴሬሽን ESFNA ተሰንጥቀው የተነቀሉት መርዞች ቡድኑን ሲመሠርቱ መፍጠር የፈለጉት ይህንኑ ነበር፣ መከፋፈል። ለሆዳቸው እስካደሩ ድረስ የማህበረሰብ እና የእሴቱን ዋጋ የሚያሰላስል ህሊና የላቸውም። ገንዘብ ፍቅር አይገዛም። የአላሙዲ እርድታ ቢቀር የሕዝቡን አብሮነት አልበተነውም። በተቃራኒው የጠላት ስሌት የገባው ሕዝብ በእልህ ዓመታዊውን ፌስቲቫል ማድመቅ ውዴታው ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ግዴታው አድርጎታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአድዋ ድል፦ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ትውልድ የማንነት ፈተና - ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ተመሳሳይ ሴራዎች እና ሸፍጦች በቤተክርስትያን፣ በመስጊድ፣ በጓደኛሞች ማህበራት እና ፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ይፈጸማሉ። ከድርጊቶቹ ጀርባ ያለው አውራ አቀናባሪ ደግሞ ህወሓት ነው።

በመሆኑም በማንኛውም ህብረት ውስጥ ላሉት ችግሮች ህጸጾችን ከማጉላት ይልቅ እልባት በመስጠት እና ልዩነቶችን ለማጥበብ በመስራት መተራረሙ ከመበታተን ያድናል።ስለዚህ ማህበርን፣ ማህበረሰብን፣ ብሔርን፣ ጎረቤትን፣ ቤተሰብን እና የራስን አዕምሮ በጥቃቅን ጥቅማ-ጥቅም የሚሸነሽነው የህወሓት ሥርዓት እንዲወድቅ ሁሉም ተቆርቋሪ ዜጋ የበኩሉን አስትዋጻዖ ማበርከት ግዴታው ነው።

2 Comments

  1. True we witnessed that the money given by Alamoudi is being stolen by Abinet and his friends and the festival was a failure it was like a Tigray festival than an Ethiopian one and it is really shame and this will be the last time for me to go there

Comments are closed.

Share