June 16, 2015
3 mins read

አቶ አላሙዲንን እንደ በጎ አድራጊ፣ ቸር እና ደግ ሰው የምትቆጥሩ ሰዎች በጣም አስቂኝ ናችሁ

ዓበጋዝ ዤዓንግት

አላሙዲ ሞራል እና ስነምግባር የጎደለው ሰው ነው፣ አላሙዲ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ትዳር አፍርሷል፣ አላሙዲ ወርቅን ያክል የኢትዮጵያ ሀብት በብቸኝነት ያለ ማንም ከልካይ እየዘረፈ ያለ ሰው ነው።

ብዙዎች አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያንቀሳቅሰው ንግድ ትርፍ እንደሌለው እና ይልቁንም በተለያየ ጊዜ ለግለሰቦች በሚያደርገው የገንዘብ ዳረጎት ብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚከስር ግለሰብ አድርገው ማየታቸው አንድም ካለማወቅ ነው በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ሰውየው በተደራጀ መልኩ በጎ ነገሮች በሚያወሩ እና በሚያስወሩ ሰወች ተሸውደው ነው ብለን እናስባለን።

ቢሆንም ግን አላሙዲ ህወሀት/ወያኔወች በራሱ ምንም ሊያደርጉት የማይችል ግለሰብ ነው፤ ምክንያቱም እሱ የአይነኬወቹ ሰይጣን አምላኪ ኢሉምናቲወች አባል ነው (ይህን አላምንም የሚል ሞባይል እና ለፕቶፕ ላይ አፍጥጦ ፎቶ ላይክ ከማድረግ ይመርምር)፤ እስከዛሬ ህወሀት/ወያኔወች በእሱ ምክንያት አይናቸው እየቀላ ምንም ሊያዳርጉት ያልቻሉት ሰው ነው፤ ስለዚህ ምርጫቸው እና የሚያዋጣቸው አብረው ተሞዳሙደው መዝረፍ ነው።

በአጠቃላይ አቶ አላሙዲ (ሼኽ የማልለው ሙስሊም ስላልሆነ ነው) መታየት ካለበት እንደ በጎ አድራጊ ሳይሆን እንደ ሞራል እና ምግባር የሌለው ዘራፊ ሰው ነው፤ ሊመሰገን አይገባውም። ምናልባት የወሎ ሰወች ከሚዘርፈው ነገር ቆንጥሮ ስታዲዬም ገንብቶላቸዋል፣ ኮምቦልቻ ላይ የህወሀት/ወያኔን መሰፍን ኢንጅነሪንግ ጉሮሮ የሚዘጋ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ሊገነባላቸው መሰረት ድንጋይ ጥሏል፣ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆን ቴሪሸሪ/ ሦስተኛ ደረጃ የህክምና ማዕከልም ሊገነባላቸው ስለሆነ ቢያመሰግኑት አይከፋኝም።

ይህን የፃፍኩት አሁን በታክሲ ስሄድ ማንነቱን ባላወቅኩት ኤፍ ኤም ራዲዮ አንድ የሰውየውን ዳረጎት የሚፈልግ አይነት ጋዜጠኛ ሰውየውን ሲያቆለጳጵስ፣ ሲክብ እና ሲያሽቃብጥ ሳልፈልግ ሰማቼ አድርባይነታችን አብሽቆኝ ነው።

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop