ተሂዶበት ከሚፈለገው ቦታ ባላደረሰ መንገድ ተመላልሶ መጓዝ ችግሩ የመንገዱ ሣይሆን የተጓዡ ነው

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ረቡዕ የካቲት ፭ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.                       ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲

 

ሰሞኑን የትግሬ-ወያኔ እጀታ የሆነው የምርጫ ቦርድ፣ በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና በአንድነት ለፍትሕና ዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ላይ «ከምርጫ ውድድር የማገድ» ውሣኔ ማሣለፉን ሰምተናል። ይህም ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ፣ አቃቢ ሕግ፣ መከላከያ ሠራዊቱ እና መሰል በ«ሕገ-መንግሥቱ ተቋቋሙ» የተባሉት ተቋሞች በሞላ የወያኔ ሕዝባዊ ድርጅቶች መሆናቸውን በይፋ እና በማያሻማ መንገድ ከታዩባቸው አያሌ ተግባሮች መካከል አንዱ ሆኖ የሚጠቀስ ነው። የምርጫ ቦርዱ ውሣኔ በራሱ ምርጫ ቦርድ የወያኔ ሕዝባዊ ድርጅትና እጀታ ከመሆኑ የመነጨ ብቻ ሣይሆን፣ የተቃዋሚው ጎራ ደጋግሞ በሄደበት እና ምንም ዓይነት ውጤት ባላስመዘገበበት መንገድ መጓዙ ጭምር እንደሆነ ሊስተዋል ይገባል።

የትግሬ-ወያኔ በምርጫ ተሸንፎ ሥልጣን እንደማይለቅ ያለፉት አራት የይስሙላ ምርጫዎች ከበቂ በላይ ነቃሾች ናቸው። ይህን በተመለከተ የ1997ቱን የምርጫ ውጤት ተከትሎ የትግሬ-ወያኔ በወሰደው የድምፅ ነጠቃ፣ ታዛቢ የነበሩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር አቶ መለስን ለማለስለስ ባደረጉት የማግባባት ሙከራ ያረጋገጡት ሃቅ ነው። አቶ መለስ በወቅቱ የሰጣቸው መልስ፦ «ኢሕአዴግ በምርጫም ሆነ በኃይል ሥልጣን ከለቀቀ የሚጠብቀን አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ይኸውም በአገር ክህደት ተከሰን ወህኒ መውረድ ነው። በመሆኑም ለ፲፯(አሥራ ሰባት) ዓመታት አፈር ግጠን የጨበጥነውን ሥልጣን በሕዝብ ድምፅ አንለቅም።» ሲል ነበር እቅጩን እና የማይለወጠውን የትግሬ-ወያኔን ዓላማ የገለጸው። በተመሣሣይ ሁኔታ የሕወሓት እና የኢሕአዴግ የፖሊት ቢሮ አባል የነበረው አቶ ገብሩ አሥራትም «ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ» በሚለው መጽሐፉ የሚነግረን ይህንኑ ነው። ስለዚህ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን የሰጠውም ውሣኔ የዚሁ ተከታይ አካል በመሆኑ፣ ድርጊቱ አስገራሚም፣ አስደንጋጭም አይሆንም። ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት የኖርንበት ዓለም የታዘበው ዕውነታ ነውና። አስገራሚና አስደንጋጭ የሆነው ተቃዋሚው በወያኔ ሁለንተናዊ ፍላጎት ቁጥጥር ሥር መሆኑን አለመገንዘቡ ነው። እኒህ ተቃዋሚዎች ጉዟቸው ያልተለወጠ እና በየአምስት ዓመቱ በሚደረግ የምርጫ ዘመቻ የተገዛ ነው። ይህ ጉዞ ለውጤት ያላበቃ መሆኑ ተደጋግሞ እየታዬ፣ ውጤት እንደማያስገኝ በታወቀ መንገድ መጓዙ፣ ችግሩ ከመንገዱ ሣይሆን፣ ከተጓዡ እንደሆነ ትግሉ የሚገኝበት ሁኔታ ያሣያል። ስለሆነም ተቃዋሚ ኃይሎች ከ1997ቱ የምርጫ ሂደት እና ውጤት ከታዩት አዎንታዊ እና አሉታዊ የጉዞ አቅጣጫዎች ትምህር የቀሰሙ አይመስልም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት” በሁለት ሺህ አስራ አራቷ ኢትዮጵያ እይታ ሲገመገም፣

ሁለተኛው የተቃዋሚ ድርጅቶች መሠረታዊ ችግር በአደረጃጀታቸው ላይ ያጠነጠነ ነው። የትግሬ-ወያኔ በማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ብቻ ሣይሆን በዕድሮች ሣይቀር የራሱን ሥውር መዋቅር አስርጎ አደራጅቷል። ሰሞኑን በመኢአድ እና በአንድነት ላይ የተከሰተው ችግር ግን፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች የትግሬ-ወያኔን የሤራ ስልት ባለመገንዘብ ከነ አየለ ጫሚሶ ዓይነት ሠጎ ገቦች ድርጅቶቻቸውን ማጽዳት አለመቻላቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሣያል። ሰለዚህ የአደረጃጀት ሥልታቸው የወያኔን ሠርጎ ገቦች ሊያንተረትር በሚችል መልክ እስካልተቃኘ ድረስ፣ በምንም ሁኔታ የትግል ጉዞ አቅጣጫቸው በወያኔ እና በአጋሮቹ ላይ ተጽዕኖ ሊያሣድር አይችልም። ይህም ብቻ አይደለም፤ ተቃዋሚው የሙጥኝ ብሎ የያዘው «በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ የትግሬ-ወያኔን በምርጫ አሸንፈን ሥልጣን እንይዛለን» የሚለውን ብቸኛ የትግል መሣሪያው አድርጎ መያዙ፣ ለትግሬ-ወያኔ ሠርጎ መግባት የተመቻቸ ሁኔታ ከመፍጠሩ ባሻገር፣ የነቁትን የኅብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ የአገዛዙ ዒላማ እንዲሆኑ አድርጓል። ይህም ትግሉን ተተኪ መሪዎች በማሣጣት መሪ አልባ በማድረጉ፣ የሕዝቡን  የወኔ ሥንቅ እንዳሟጠጠ በድርጅቶቹ ውስጥ በቂ ትኩረት የተሰጠው ያለመሆኑን ያመለክታል።

የተቃዋሚው ኃይል የትግሬ-ወያኔን ባሕሪ የሚመጥን የትግል ሥልት መከተል ባለመቻላቸው፣ ወያኔ «ግሞ» ሲል «ጥንቦ» ማለት አልቻሉም። በተደጋጋሚ በአገር ቤት ካሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚደመጠው የትግል ስልት፦ «በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ የትግሬ-ወያኔን በምርጫ አሸንፈን ሥልጣን እንይዛለን» የሚል ነው። ሆኖም የሰላማዊ ትግል ሥልት በምርጫ ዘመቻ ብቻ የተገደበ አይደለም። የምርጫ ዘመቻ ለሰላማዊ ትግል ጠቃሚ የሚሆነው ዲሞክራሲያዊ ተቋሞች የሚባሉት ማለትም፦ ነፃ እና ገለልተኛ የሆነ የምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አቃቤ ሕግ፣ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና ወገንተኛ ያልሆኑ የብዙኃን መገናኛ ተቋሞች መኖር፣ ወዘተርፈ፣ በአጠቃላይ የሕግ የበላይነት ሰፍኖ ከማንም ተፅዕኖ ውጭ በነፃ የመሥራት የዜግነት መብት ሲረጋገጥ ነው። እነዚህ ተቋሞች በሌሉበት ሁኔታ ግን፣ በምርጫ ፖለቲካ ወያኔን ከሥልጣን እናወርዳለን ብሎ ምርጫን በብቸኛ የትግል መሣሪያነት የሙጢኝ ብሎ መያዝ፣ ታጋዩ ሕዝብ ሥቃይን እና በደልን ተለማምዶ የ፵(አርባ) ቀን ዕድሌ ነው ብሎ እንዲያምን እና ለወያኔ አገዛዝ ምቹ እንዲሆን ሠፊ በር የሚከፍት መሆኑ በግልፅ ሊታመንበት ይገባል። በተግባርም የሚታየው ይኼው ነው። የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ መዋቅር፣ የፍትህ አካሎች እና የብዙሃን መገናኛ ተቋሞች በአንድ ዘረኛ ቡድን ፍላጎት እና ቁጥጥር ሥር በዋሉበት ሀገር፣ በምርጫ ሥልጣን እረከባለሁ ማለት ሸንበቆ ያፈራል፣ በቅሎ ትወልዳለች፣ ዝንብ ማር ትጋግራለች፣ ፀሐይ በምሥራቅ ትጠልቃለች እንደማለት ይቆጠራል። እንደሞረሽ-ወገኔ እምነት፣ ሰላማዊ ትግሉ የተለየ መንገድ መከተል ይኖርበታል። ወቅታዊ የትግሉ መፈክር «ለዲሞክራሲ፣ ለዕኩልነት እና ለብልጽግና» ሣይሆን ቅድሚያ ለነፃነት ትግል መሆን አለበት። አገር እና ሕዝብ ሳይኖሩ፣ ዲሞክራሲ እና ዕኩልነት ሊታሰቡ የሚችሉ ጉዳዮች አይደሉምና!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዝናሽ ታያቸው እንደ ክላራ ፒታቺ 

በመሆኑም፣ የተቃዋሚው ጎራ፣ የትግሬ-ወያኔን እንደተኩላ ከብቦ የሚቦጫጭቅበትን፣ አጠቃላይ ሕዝባዊ እንቢተኝነትን የትግሉ መርህ አድርጎ ሊንቀሣቀስ ይገባዋል። ስለዚህ ቀዳሚው የትኩረት አቅጣጫ መሆን ያለበት በየአካባቢው ያለውን የትግሬ-ወያኔን የስለላ መዋቅር በመበጣጠስ፣ ሕዝቡ የራሱ አለቃ የሚሆንበትን ዘዴ በመሻት፣ የትግሬ-ወያኔን እና አጋሮቹን ለነፋስ በመስጠት፣ የአገዛዝ ዕድሜያቸውን ለማሳጠር መንቀሣቀስ ነው። ይህ ደግሞ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከመሀል እስከዳር ሕዝቡን በማደራጀት በእንቢተኝነት ስሜት እንዲነሣ ማነቃነቅ ያስፈልጋል። የትግሬ-ወያኔ አፋኝ ቡድን የኃይል መከፋፈል የሚፈጠርበት፣ ለቅልብ ጦሩ ሆድ መሙያ የሚከፍለው በጄት የሚያጣበት፣ በገዥው ቡድን መካከል የኃሣብ መከፋፈል የሚፈጠርበት፣ የማስፈጸም አቅሙ የሚሟሽሽበት፣ እርስ በርሳቸው የሚጠራጠሩበት ሁኔታን የሚፈጥር ሥራ መሠራት አለበት። ለዚህም በደህንነቱ፣ በሠራዊቱ፣ በፖሊሱ፣ በቢሮክራሲው መሀል ሠርጎ በመግባት ዓላማ እና ዕቅዳቸውን ማክሸፍ ያስፈልጋል። ሕዝቡም «ላልወከልነው አካል ግብር አንከፍልም፣ የእኛ ባልሆኑ ተቋሞች አንገዛም፣» የሚለውን ስሜት እና እምነቱን ሊያጎለብት ይገባል። በትግሬ-ወያኔ የተለያዩ የንግድ እና የአገልግሎት ተቋሞች፣ ማለትም፥ የትራንስፖርት፣ የሆቴል፣ የንግድ ቤቶች እንዳይጠቀም በልዩ ልዩ መንገዶች በማስተማር ወያኔ እና አባሎቹን ከማናቸውም ማህበራዊ እና ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በማግለል ብቻቸው እንዲቆሙ መደረግ አለበት። «መጡብን» ሳይሆን፣ «መጣንባችሁ» ሊባሉ ይገባል። ከእንግዲህ ተቃዋሚው ጎራ ሙሾ ማውረዱን ማቆም አለበት። መርዶ የሽንፈት እንጂ፣ የድል ምልክት ባለመሆኑ፣ «እንዲህ ሆን፣ እንዲ,ህ ተደረገን» የሚሉት እሮሮዎች ሊገቱ ይገባል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የትግሬ-ወያኔ በሁለቱ የሰላማዊ ትግል አራማጅ ድርጅቶች ላይ የወሰደውን እርምጃ የተመለከተው ከትግሬ-ወያኔ ጉዞ እና ዓላማ አንፃር የሚጠበቅ እንጂ፣ ዱብ ዕዳ እና እንግዳ ነገር አድርጎ አይደለም። በአንፃሩ «ማሽላ ሲያር ይስቃል» እንዲሉ፣ ይህ እርምጃ ለፀረ-ወያኔ ትግል እልህ፣ ቁጭትና የመጠቃት ስሜትን የሚፈጥር ነው ብለን እናምናለን። ስለሆነም የተቃዋሚው ጎራ በአንድ ብሔራዊ ዓላማ ዙሪያ እንኳን መሰባሰብ ባይችል፣ በፀረ-ወያኔ አቋሙ በአንድ ግንባር ወይም ኅብረት ሥር እንዲሰለፍ ሠፊ በር የከፈተ ያህል ይቆጥረዋል። ስለዚህ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚገኘው ተቃዋሚ ኃይል ከምንጊዜውም በበለጠ ተቀራርቦ በመነጋገር በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ላይ የተጠናከረ እና ሁሉን- አቀፍ ትግል እንዲያደርግ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ስም ጥሪያችንን እ,ናቀርባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መች ይሆን ሁከት ከኦሮምያ፣ ሽምቅ ግድያ ከቤንሻንጉል፣ እብሪት ከትግራይ፣ ሃሰተኛ ነብይነትና ሽንጋይ ፓስተርነት ከሃገራችን የሚወገዱት? - በየነ ከበደ

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ ቡድን ነው፤ በመሆኑም መወገድ አለበት!

——————

9 Comments

  1. የ እናንተ አጋሰስ የ አንድነት ድርጅቶች ምነው ቀን አይወጣላቸው? ቀድሞም በ አማራ ስም ሲነግዱ ነበር! እርሶ እና መሰሎችዎ አሁንም በ አማራ ስም ይህን የ አጋሰስ ስብስብ ለመጫን ትፈልጋላቹ! ዉሾች! እና በዚ ስብስብ ያላቹ እንክርቶች! ሲጀመር አማራው ማን እንደሆነ እወቁ! የ አማራው ፍላጎት ምን እንደሆነ እወቁ! ይህን አማራ ብላቹ ለራሳቹ ስም ያወጣቹ ቆረቆንዳዎች ራሳቹ አማራ እንደሆናቹ እርግጠኛ ሁኑ! ቀደም ሲል የ አማራን ጭንብል አጥልቃቹ ይህን ህዝብ ከ ሌላው ጋር ያላተማቹ እና ከርሳችሁን ስትሞሉ የነበረ ሁሉ, በ ቀይ ሽብር ከደርግ ጋር ሆናቹ የ አማራን ወጣት እና ነጋዴን እንዲሁም ሙህራንን የ ጨረሳቹ ሁላ(ተክሌ የሻው-የ ቀድሞ የ ደርግ ፕሮፖጋንዳ ጥሩንባ እና ፈጂ እና አስፈጅ) ከ እዚ ህዝብ ጫንቃ ላይ ራሳችሁን እንደ ሙቀጫ አንካባላቹ ካልጣላቹ ለ ህዝቡ ቀናኢ የሆነ የ አማራ መሲ ሲነሳ አመድ እንደምትሆኑ እወቁ!

  2. “Gimo” silu ” tombo”… Min malete new? LeneTsanet tigil yetetsafe ayimeslim.
    Please neqa belu. Amharoch maninim anfelgim. Eskahun Balew tarikachin bizu hizibachin zare betelatinet leferejun hizboch hulu meswaet mehonu yangebegibal. Amharoch baynoru yih hizib zare enfegorebetochu benechoch lay yalewn kursho sianebenib yinor neber. Ers berasu endewusha tenakso yalq neber.
    Ahunm bihon Amara keTigray woim KeOgafen alyam kegambela yemiagegnew minim neger yelem. Minalibat keOromo ena Debub buna binor new. Silezih We Amharas want to seccede and establish our own clean empire. No more stupid and uncivilized life with riff- raff.

  3. የጠላቱን ምንነትና ማንነት ያልተረዳ ትግል ከየትም አይደርስም:: ትልቁ የአንድነትና የመኢአድ ችግር ደግሞ ይህ ነው:: ሞርሾች ጥሩ ብላችሁአል:: ልብ ያለዉ ልብ ይበል:: አመሰግናልሁ::

  4. @ sayint you better analze the current status of Amharas in the ethnic politics of the state… jumping into the victim is immoral

  5. sayint: ከቃል አጣጥልህ እንደገመትሁህ ምንአልባት በኢጫት፣ በሰደድ እና በሌሎች ድርጅቶች ወዘተ ስር ተሰግስገዉ ንጹህ የዐማራዉን ደም ካፈሱስት መካከል ሳትሆን አትቀረም። ኢሕአፓ ዉስጥ ያለዉት ውድ የዐማራ ልጆች ናቸዉ። ድርጅቱንም የተቀላቀሉት አላማውን በደንብ ተገንዝበነው ሳይሆን በጋለ የወጣትነት ስሜት እና በቡድን ግፊት (peer pressure) እንጂ በትግሬዎች የተመሰረተ፣ ለትግሬ እና ኤርትራ “ነጻነት” መሆኑን አውቀን ቢሆን ኖሩ ለእስር፣ ለስደትና ሞት ባልተዳረግን ነበር። አንተን የመሰሉት ጥቅመኞች እና አገር ካህዲዎች ግን መስለዉ መጀመሪያ በተጠቀሱት ድርጅቶች ተሰግስገው የማታ የማታ ግን ጭምብላችሁ ሲወልቅ በሻብያ የተመሰረተው የኦንግ አባልነታችሁ ብቅ አለ። ዐማራዉን በኢሕአፓ ስም ጨረሳችሁት፣ ከዛያም ከወያኔ ጋር ስትገቡ በቁሙ ገደል ከተታችሁት። የዜ ጉዳይ ነው አንተን እና መሰሎችህን ሞረሽ ወገኔ ከያላችሁ እና በከገባችሁበት የምዕራ አገር ጉድጓድ ጎትቶ አዉጥቶ ለፍርድ ያቀርባችኋል። የአንተ እና የሐሰን ዓሊ አይነቱ በደበቅ ከፍርድ አያስመልጣችሁም። አቶ ተክሌን በስም ጠቅሰህ አዋርደሀል። የተዋረድከው ግን አነተ ነህ! የርሳቸዉን ታሪክ ታቃለህ ብየ እገምታለሁ፤ ስንቱን የኢህአፓ አባል ከመላኩ የሞት ቅጣት እንዳዳኑት። እንኳን ዐማራዉ ትግሬዉ ራሱ ይመሰክራላቸወል ለሰዉ ልጅ ሰበዓዊ መብት ምን ያህል ጥብቅና እንደሚቆሙ። ደፋር ብትሆን እዉነተና ስምህን እና አድራሻህን በገለጽክ። ግና ቅሉ የሰው አራዊት ነህ።

    ሞት ለጸረ ኢትዮጵያ!

    • መጀመርያ እኔ ደሞ እንዲ እልሃለው-ሞት ለ ጸረ አማራ አጋሰስ ስብስብ ሁላ! በ አማራ ህዝብ ላይ እንደ ቁንጫ እና መዥገር ሆናቹ የ አማራን ደም ስትመጡ የነበራቹ እና ያንን ዳግም ለመመልስ እምትፍጨረጨሩ ባተሌዎች, በ አማራ ስም ይህቺ የ ባቢሎን ግንብ ሆና እንድትሰራ የምትፈልጉ የ ባቢሎን ግንበኞች, ራሳቹ ተዋርዳቹ በ አማራ ስም ስለነገዳቹ ይህን ህዝብ ያዋረዳቹ እና ያለ መሪ, ያለ ራስ ያስቀራቹ ድንፋታሞች አሁንም በድጋሜ ታቀቡ እላለው አስረግጨ!
      ለጥቆ ደሞ! ኢሃፓን የመሰረቱት እንደሚገባኝ ከሆን በመጀመርያ ረድፍ የ ቁጩ አማራዎች(እነኝ ቁጭዎች ዲቃሉ ሲሆኑ ከ እንሱ ጋር ልክ እንደነሱ ዲቃሉ የሆኑ ትግሬዎች እና ሌሎች ጭፍራዎች) ናቸው! አይ ተሳስተሃል ብትለኝ እንኩዋን እሺ ይሁንል ብየ እና ምን ይጠበስ እልሃለው! ምክንያቱም በዚ ስብስብ ዉስጥ የነበሩት ሰዎች እንክዋን በ ሰፊዋ ኢትዮጵያ የተለያይ ማህበረስብ በሚኖርበት ምድር ለ ብዙሃኑ የሚሆን መፍትሄ ሊያመጡ ቀርቶ ራሳቸውም ይወክላሉ ተብለልው ለሚታሙበት ለ አማራውም ህዝብ አልበጁ! ይልቅስ እንደ አልቂት ደሙን ሲመጡ ና በሌላው ማህበረስብ ዘንድ እንደ በዳይ, ዘራፊ, ጨቁዋኝ, ትምክተኛ ወዘተርፈ ጉድፍ አይን እንዲታይ ሲያደርጉ ነበር! በ ንጉስም እንዲሁም በደርግ ዘመነ መንግስት! ስለዚ ይህ ስብስብ እና የ እነሱ ቅሬዎች የ አማራን ህዝብ ለመምራት ሞራልም እንዲሁም ብቃትም የላቸውም! ስለዚ ይህን አውቀው ገለል ይበሉ!
      ጋሽ ተክሌ የ ደርጉ ኢሰፓ እንዲሁም ፕሮፖጋንዳ መሪ የነበረ አሁን ብድግ ብሎ የ አማራ መሪ ነኝ ሲል-ማን አባክ ውክልና ሰጠክ ብለን የመጠየቅ መብታችን በ ህግ የተጠበቀ ነው! እናም ከ ነደምክ አብዝቶ ይንደምክ! ተንጨርጨር!
      በመጨረሻን ስለራሴ-እኔ አጥንቴ ከበድ ያለ የ ቤተ አማራ ሰው ነኝ! ከ ዋለልኝ አገር! አማራው የ ማንም እንክርፎ መሸሸጊያ አይደልም! ማንም ና ልጫን ብሎ እንደ ፈረስ የሚጋልበው ከንቱ ህዝብ አይደለም! ወያኔን ለመታገል ቢሆን, አማራው ራሱ ብቁ ነው! ከ በቂም በላይ ነው! ስላነሳሃቸው የ ኦሮሞ ጠባቦች ከ እኔ ይልቅ በ ዛ ኢትዮጵያ ኢትዮጳያ ብለው ለሚሰበሰቡ አጋሰሶች ቅርብ ናቸው! ማን ነበር የ ንጉሱ ጋሽ ጃግሬዎች? እንደው ከ ግማሽ በላይ የሚሆኑት ኦሮሞዎች እና ሌሎች ቅልቅሎች አልነበሩ? እስቲ ባለስልጣኖችን ዝርዝር አምጣ ከ ንጉሱ ዘመን ጀምሮ! ከ ደርግ መንግስቱ ውስጥ አማራው ነበረበት? የ እዛ ስብስብ ዉስጥ የነበሩ አማራዎች በቁጥር እምብዛም ነገር ግን አማራው የ አንበሳ ድርሻ እንደያዘ ተደርጎ ሲሰበክ, ሲሳል ነበር! በማን? በጥቂቶች! ስለዚ ያ አልፍዋል አሁን! አማራው የ ማንም ተልካሻ መሸሸግያ አይደለም! እድሜ ለ ዋለልኝ መኮንን! ዳግማዊዎቹ ደሞ ለ እውነተኛው የ አማራ ህዝብ ዋልታ ይሆናሉ!
      ሞት ለ ጸረ አማራ ስብስብ!

  6. Tigre nek.sayint i believe mr tekle yeshaw is a real am hara.which means free people.mhara said we amhara do not need tplf juntaw,last time the head of tplf was eliminated by cancer poison.so so good.now what is left is the remainder,next berket simon will also be eliminated by heart failur,this is a good infication of tplf will soon down one by one.just be patient.you know it it is not for long,all tplf friends have blood in their hands.just type in google,gebremedihin araya or asrat gebru tplf past leader they all agree your hands full of blood.so God is after you. Melese bucher zenawi i was so happy he is gone for good,the rest of you are ye e.ahilalit chira angetu siqoret min yihonal.you know. It.

  7. You including tirayi people are minority,you will also know what will happen to you when. Tplfis gone think about it.tplf is getting older.did you know all oromos are olf,icluding o.p.d.o,whare as gibot 7are merging now.amhara ,moresh is the result of well educated union including asrat weldeyes,the star of ethiopia,scintist kitaw egigu nasa. Chief of staf,this people pit what is so good for ethiopia,that is nothing except putting tplf aside.you name any amhara working tirelessly to end tplf. Juntaw.so even every amhara told the truth is standing on the grave of melese biucher zenawi.u will not have a place in tigrayi.you are banda of killer for mosoloni,you are killer of abune petros of. Ethiopia.tplf and shabiya are the two faces of coin,they look alike.they have a dream of dismantling ethiopia.you think you are exist.ethiopiaywinet will exist becouse pf God. Said,read book of ermiyas chappter 15,in amharic,you will read this,if you wanted to change ethiopiyawinet.first try to change the color of tiger,then try to chamge the ethiopiainet.

  8. በጣም ቆንጆ ፖለቲካዊ አስተያየት ነው ችግሩ የተቃዋሚ ኃይሎች የሕዝቡ ነጻነት ስይሆን የሚታያቸው ወንበሩ ስለሆነ ህወሃት በተአምር ወድቆ ሥልጣን ቢይዙም ጤና የሚኖራቸው አይመስለኝም::በተፈለገው ቁዋንቁዋ ይጻፍ አንብቦ ሀሳቡን መረዳት ይቻላል ነገር ግን ሀሳብ ሰጭዎች ባለዘመኖች የህወሃት ቡችላዎች ስለሆኑ ከነሱ ሊያስተምር የሚችል ነገር ይመጣል ተብሎም ስለማይታሰብ የድሕረ-ገጹን መስኮት ባያጣብቡት ይመረጣል::

Comments are closed.

Share