February 11, 2015
11 mins read

ኦህዴድና ስሙን የቀየረው ኢህዴን – ሰይፈ ምካኤል

ኦሮሚያን የሚመራው ዛሬ በርካታ ለውጦችን አስመዝግቦአል ይህን ስል ህወሀት ከፈጠራቸው ድርጅቶች ሀቁ “ከዝንጀሮ ቆንጆ. . . “ የሚባለው እንደተጠበቀ መሆኑ ይታወቅልኝ ማለትም ሁሉም ገዳዮች ዘራፊዎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን ዘንግቼው አይደለም።

_የአማርኛ መጠሪያ የነበራቸውን የቦታ ስሞች ወደ ኦሮምኛ ለውጥቶታል

_በከፊል በኦሮሞ ታሪክ ጎልተው በሚታዩ ጉዳዮች ደግሞ የፈጠራ ተረት ላይ ተመርኩዞ የት/ት ስራት ያካሂዳል

_የክልሉ ሕዝብ 88% ብቻ ኦሮሞ ሆኖ ሳለ በክልሉ ሕገ-መንግስት ቕንቕን በተመለከተ ኦሮምኛ ግዛትን አስመልክቶ ደግሞ ክልሉ ውስጥ ያሉ ሌሎች

ብሔረሰቦች ራሳቸውን በቕንቕቸው እንዳይማሩና የመገንጠል መብት እንዳ ይኖራቸው ድንጋጌ አውጥቶአል

_የኦሮሞ ክልል ስፋት ወደፊት በሂደት ከሌሎች ክልሎች ወደ ኦሮሚያ የሚካተቱ መሬቶችን ያካትታል ይላል

_በርካታ አስፋልት የተላበሱ መንገዶች ወያኔን አግባብቶ አስገንብቶአል እያስገነባም ይግኛል

_ሁለት የግልገል ጊቤ ሀይል ማመንጫዎች የዲዴሳ ግድብና ሀይል ማመንጫ የናዝሬት ሁለት የንፋስ ሀይል ማአመንጫዎች እውን አስደርጎአል ሌላም አሁን በኢሉባቦር ግንባታው እንዲጀመር የተሳካ ስራ ስርቶአል

_ክሰበታ እስክ ጅቡቲ የሚዘልቀውም የባቡር መስመርና ወደ ናዝሬት የሚወ ስደው ፈጣን መንገድ የኦሕዴድ ስኬቶች ናቸው

_አማራውን አባሮና አማራውን የሚያጥላሉ ሐውልቶችን ገንብቶ ክልሉን የአንድ ጎሳ መኖሪያ እያደረገ ይገኛል

_በርካታ ፋብሪካዎች እንዲቕቕሙ በማድረግ ላይ ይገኛል

_ሕዝቡ የኦሮሞ አቕሙ እንዲዳብር አድርጛል ታሪካዊ ባሕላዊ በአሎች እንዲከበሩ ስርቶአል ወጣቶች በአ አ መስፋፋት ያሳዩትን ተቃውሞ መጠቆም ለዚህ ምስክር ነው ወዘተ. ኢሕዴንስ ምን እያደረገ ይገኛል?

_የቦታ ስሞችን ታሪክን አመሳክሮ ለውጥ አላደረገም

_92% አማራ ሆኖ ሳለ በክልሉ ያሉ ጎሳዎች እስከመገንጠል የሚደርስ መብት በክልሉ ሕገ-መንግስት እንዲካተት አድርጛል

_የክልሉን ግዛት በየአጋጣሚው ለትግራይ አሳልፎ መስጠትንና አማራውን አናሳ የማድረግ ስራ ይሰራል

_አማራውን ትምክህተኛ ነፍጠኛ የጨቕኞች ተከታይ መዝባሪ ወዘተ የሚሉ ስድቦችን ለጥፎበት በታሪኩ እንዳይኮራ እያንቕሸሸው አንገቱን ደፍቶና ተጎሳቅሎ ኑሮውን በመከራ እንዲገፋ አላማ ነድፎ ይሰራል

_በሌሎች ክልሎች የማይተገበር ኢህዴን በአማራ ክልል ከየትኛውም ቦታ የመጣና በክልሉ 2አመት ብቻ የኖረ ልከ እንደ ክልሉ ተወላጅ ተቆጥሮ አርሶ ሸቅሎ ወዘተ መብቱን አስከብሮ መኖር እንዲችል ደንብ ደንግጎአል በዚህም መሰረት ከ60ሺህ በላይ ትግሬዎች በአርማጭሆና መተማ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ዛሬ አካባቢው አገራችን ስለሆነ ከትግራይ መቀላቀል አለበት ብለው መሳሪያ አንስተው ያካባቢውን ተወላጅ አማራ ማፈናቀልና በይፋ የይገባኛል ጥያቄ አቅርበዋል።

_አማራው ግን ለበርካታ ዘመኖች ከኖረባቸው አሩሲ ሀረርጌ ጅማ ጅጅጋ ወለጋ ጋምቤላ ጉራፈርዳ ቀማሺ መተከል አምቦ ወዘተ መጤ ተብሎ ተጨፍጭፎና ቀሪው ደግሞ ሲባረር ኢህዴን አማራውን “አላገሩ ማን ሄደህ ኑር አለው የሰው አገር ለቆ መውጣት አለበት” በሚል ነበር ለጉዳዩ ምላሽ የሰጠው።

_አማራው የምናለብኝና የምናገባኝ ባህል በማዳበር ራሱን የመከላከል አቅሙን በመስለብ ፈሪና ምንቸገረኝ ባይነት እንዲያጠቃው ኢህዴን ለህወሀት ቀኝ እጅ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል ለምሳሌ በረከት ስሞኦን ባንድ ወቅት “አማራው ሁን ያልነውን ይሆናል አድርግ ያልነውን ያደርጋል” ማለቱ ትዝ ይለኛል

_በት/ት ወጣቶች ታሪካቸውን እንዲጠሉና ወያኔን እንዲያመልኩ በማንነታቸው የሚያኮራ አቕም እንዳይኖራቸው ማድረጉን መመሪያው አድርጛል ስለዚህም ክልላቸው ሲበጣጠስም ሆነ ታሪካቸው ሲቆሽሽ በማንነታቸው ላይ የተከፈተባቸውን ጦርነት መቕቕም ያለመቻልና ደካማ ንቃት እንዲኖራቸው የኢሕዴን ካድሬዎች አልመው ይንቀሳቀሳሉ

_በዚህ ረገድ የአማራነት አመለካከት በክልሉ ውስጥ በምንም አይነት ባለፉት 23አመቶች እንዳይኖርና ጎጃሜው ባካባቢው ሌላውም እንደዚሁ ጎጃሚያዊና አካባቢያዊ ውሱን ንቃት ብቻ እንዲያንጸባርቅ ያለመ ስራ በካድሬዎቹ እውን በማድረግ ለህወሀት ጥቅም ከፍተኛ አስተዋጾ ኢህዴንድበት አበርክትዋል

_ዛሬ ዘርፈ ብዙ ስር ነቀል የግዛት ለውጦች በሚካሄድበትና እየጠፋ ባለው የአማራ ክልል ህወሀት ጉዞው የሰመረለት ስለ ጎንደር መበጣጠስ የአማራ ውድመት ነው ብሎ በቁጭት የሚነሳ ጎጃሜ ወሎዬ ሸዌ በመጥፋቱ ነው። ከዚህ ሁሉ የሚያሳዝነው ጎንደሬዎች ራሳቸው አለፋ ሲጎመድ ቕራ ተቆርጦ ለሱዳን ሲሰጥ ሁመራን የመሰለ የሰሊጥ ሀብታም ቦታና ወልቃይትን ህወሀት ሲወስድ ዝም ማለቱና “በቡሀ ላይ ቆሮቆር” እንዲሉ ዛሬ ልቡ ያበጠውና ጎንደርን የመቆራረጥ ህልሙ የበረታው የትግራይ ታጣቂ የአርማጭሆንና የመተማን ወዘተ ወረዳዎች ሲጠቀልል እጃቸውን አጣጥፈው የመቀመጣቸው ጉዳይ ሲሆን ምን እስኪሆኑ እንደሚጠብቁ ለተመልካችም ግር የሚል ጉዳይ ሆኑዋል።

_ክልሉ ጭቃና አቧራ ለብሶ ከድህነት ማቅ እንዳይወጣ ኢሕዴኖች የወያኔን አላማ ግቡ ለማድረስ ሌት ተቀን በባንዳነት በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛሉ

_ተስፋ የሌለው ክልል እንዲሆን በጎጥ በቀበሌ በከተማ በወረዳ በዞንና በክልል ካቢኔ ቢሮዎች የህወሀት ካድሬዎች ተሰግስገውበታል እንደዚህ አይነት አሰራር የሚተገበረው በአማራ ብቻ ነው በሌሎች ከልሎች ትግሬዎች ያሉት በደህንነትና ፕሮፓጋንዳ ላይ ብቻ ነው

_ድርጅቱ በትኩረት የሚያለማው ከጎጃም ተቆርሶ አዊ በተባለው ዞን ላይ ሲሆን አማራው ከጣና በለስ የስኻር ልማት ተጠቃሚ እንዳይሆን ከአለፋ ጣቁሳ መሬት ተቆርሶና አማራዎች ተፈናቅለው ጃዊ በሚል አዲስ ወረዳ ለአዊ ተሸልሞአል ይህ ደግሞ ህወሀት አማራውን ቅስሙን ለመስበር ካለው አላማ ጋር የሚጣጣም የኢህዴን ዋነኛ የስራ አካል ነው

_ከግንቦት2007 ምርጫ ተከትሎ ወይም ከምርጫው አስቀድሞ ጠገዴ ጠለምት ሰሮቃ አብደራፊ መተማ አለውሀ አዲአርቃይ በይፋ ወደ ትግራይ እንዲቃለሉ በፌደራል ጉኡዳዮች በክልሉና በህወሀት መካከል የፊርማ ስነ-ስራት እውን ይሆናል

_በመቀጠልም ቕራን ወደ ቤኒሻንጉል በማዛወር አማራ ከሱዳን ጋር የነበረውን ጥንታዊ ድንበር ይቀማል ትግራይና የአባይ ግድብ ድንበርተኞች ይሆናሉ በመጨረሻም ህወሀት አማራውን በጣጥሶ ለማጥፋት ያለውን አላማ በአገልጋዩ የቀድሞው ኢህዴን ያሁኑ የአማራ ባለሙሉ ስልጣን ገዢ እውን ያደርጋል “አዲዮስ አማራ”

_የአማራ ምሁራን በሙሉ በተጨማሪም ራሳችሁን ጎጃሜ ወሎዬ ወዘተ እያላችሁ የምትጠሩ ጠባቦች የአማራውን ሕዝብ ለዚህ አሳዛኝ የታሪክ ጥፋትና ስተት አልተባበር ብላችህ ስላበቃችሁት ተጠያቂው ህወሀት ሳይሆን ራሳችሁ በመሆናችሁ ሀፍረታችሁን በቁማችሁ ዋጡት።

_ኢህዴን የሚለውን መጠሪያ የተጠቀምኩት ድርጅቱ ክልሉን እንዲያስተዳድር በህወህት ገጸ በረከት ሲሰጠው የተላበሰውን ስም ስላልተቀበልኩት መሆኑን አሳውቃለሁ።  ታዛቢ ነኝ የካቲት 2/2007 !!!

 

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop