December 9, 2014
5 mins read

ከብሔረሰብ በዓል ወደ ለታላቁ ሩጫ! – በእውቀቱ ስዩም

ከአምስት ዓመት በፊት ይመስለኛል፣ በደቡብ የሚገኝ የግብርና ዩንቨርሲቲ የብሔር ብሔረሰቦቸን ቀን ምክንያት በማደረግ የክብር አንግዳ አድርጎ ጠራኝ። ትንሽ ካቅማማሁ በኋላ ማየት አይከፋም ብየ ሚኒባስ ተሣፈርሁ። ካምፓስ እንደ ደረስሁ የምግብ ትርኢት ወደ ሚካሄድበት ትልቅ አዳራሽ መሩኝ። ባዳራሹ ትልቅ የግብር ማብያ ጠረጴዛላይ ብሔሮችን የሚወክሉ መብሎችና መጠጦች ተደርድረዋል። ሁሉንም ብሔር ላለማስከፋት ሰማንያ ጉርሻ መጉረስ ይጠበቅብኝ ይሆን በማለት በልቤ እያጉረመረምሁ ለቅምሻ ተሰናዳሁ። ሥጋና ወተት የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች ተወዳጅ ምግቦች መሆናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አስተዋልሁ። ያም ሆኖ፣ ተማሪ ሁላ የራሱን ብሔር ምግብ ልዩ ግኝት አድርጎ ሊያሳይ ይጥራል። አንዱ በተለጎመ ቅል ያቀረበውን ወተት፣ሌላው በሸክላ ጥዋ ያቀርበዋል። አልተሸወድሁም። ወተቱም የላሚቱ ፣ ቅሉም የተፈጥሮ ግኝት እንደሆነ አውቃለሁ።

ቀጣዩ ፕሮግራም፤የብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ ትርኢት ማየት ነበር። በዩንቨርሲቲው አነስተኛ ስቴድየም ውስጥ በተዘጋጀልኝ ቦታ ላይ ጉብ አልሁ። ስቴድየሙ የተለያዩ የብሔረሰብ ዩኒፎርሞች በለበሱ ተማሪዎች ተሞልቷል። ተሜ ፣እዚም እዚያም ትንንሽ የሰው ደሴት ሰርታ ፣ ወልመጥ ወልመጥ እያለች ጭፈራውን ታስነካዋለች። ብሔረሰብ ይወክላል ተብሎ የሚታሰብ ጥንታዊ እቃ የቀረ አይመስልም። መንሽ፣ጎፈር፣አጎዛ፣አንቀልባ፣አገልግል፣ ሞፈርና ቀንበር፣ጦርና ጋሻ፣ቆልማማ ጩቤ፣ መውዚር ጠመንጃ በየተማሪው እጅ አለ። እንድያውም፣ትንሽ ብጠብቅ የድሮ መድፍ ከነመንኮራኩሩ ሲገባ ማየቴ አይቀርም ነበር።

ዝግጅቱ ተጀመረ። አራት ጎረምሳ ተማሪዎች ርቃን ሰውነታቸውን እንደ ጥምቀት ሽመል አዝጎርጉረው እንጣጥ እንጣጥ እያሉ ባጠገቤ አለፉ። የያዙት አርማ የኦሞ ሸለቆ ብሄሮች ይላል። አንዱን አተኩሬ ሳየው ሸገር የማውቀው መሰለኝ። መጠራጠሬን የታዘበ አጠገቤ የተቀመጠ ተማሪ ምስጢሩን ተነፈሰልኝ፤‹‹የሰውነታቸውን ቅርጽ ለሴቶች ለማሳየት ብለው፣እንደ ኦሞ ለብሰው ነው እንጂ አራቱም የቦሌ ልጆች ናቸው›› አለኝ ።
በነገሩ የሌሉበት ሌሎች ተማሪዎች በስቴድየሙ ዙርያ ተበትነው፣የባለንጀሮቻቸውን ጫንቃ ተደግፈው ከፊታቸው የሚካሄደውን በጥርጣሬ ይመለከታሉ። እኔም መመልከቴን ቀጠልሁ። ከጥቂት ሰላም በሁዋላ አንድ ችግር ተፈጠረ።የትኛው ብሔር ቀድሞ ይለፍ የሚለው ጥያቄ በሁለት ብሔሮች መሀል ውጥረት ለኮሰ። አንዱ ተማሪ የሌላውን ተማሪ ባህላዊ ኮሌታ ጨምድዶ ይዞ ሲተናነቅ አየሁት። ሌሎች ተማሪዎች ለማገላገል ሙከራ ያደርጉ ጀመር። አቧራው መጠብደል ሲጀምር ስጋት ሰቅዞ ያዘኝ። የግቢውን ውበት የማደንቅ መስየ ድብድቡ ሲጀመር ወጥቼ ማመልጥበትን ቀዳዳ መፈለግ ጀመርሁ። በዚህ ዓይነት፣ ለብሔረሰብ በአል መጥቼ፣ለታላቁ ሩጫ ራሴን ሳሟሙቅ፣ ሽማግሌ ገባና ነገሩን አበረደው።

ሰሞኑን ባንድ ዩንቨርሲቲ ግቢ ብሔር መራሽ አምባጓሮ ተቀሰቀሰ ሲሉኝ ትዝ ያለኝ ይሄ ነው። እንደምታውቁት የብሔርና የእግዚአብሔር ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ፣ለወሬ አይመቹም። Taboo ናቸው ለማለት ነው። ለደንበኛ ውይይት ሲቀርቡ ሰዎች ይቆጣሉ። ግን ዝምታ፣ የችግሮቻችንን ጥፍርና ክራንቻ ከማሳደግ በቀር ጥቅም የለውም። ወደድንም ጠላንም አገርን ከሥር የሚነቅል ጠብ የሚያስነሡ ሁለቱ ነገሮች ናቸው።

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop