September 30, 2014
10 mins read

አቶ ኃይለማሪያም እንዳሉት የዲሞክራሲ እጦት አብዮትን ያመጣል (ግርማ ካሳ)

አገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ፣ በረእቡ መስከረም 7 እትሙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከቱርክ የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ አናዶሉ ጋር በቅርቡ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ለአንባቢያኑ አቅርቧልል። ከቃለ መጠይቁ፣ በተለይም በምርጫውና በፖለቲካ እስረኞች ረገድ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የመለሱትን ቀንጭቤ ለማቅረብ እወዳለሁ።

“ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ዓመት በአገር አቀፍ ምርጫ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ምርጫውን የሥርዓቱ አካላት በሕግና በደንብ እንዲሠሩ በማድረግ ለማካሄድ ምን ዓይነት ዝግጅት እየተደረገ ነው? በኢትዮጵያ ስላለው የመድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ ያለዎት አጠቃላይ ግምገማ ምንድነው? “ ለሚለው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲመለሱ   “ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ እንደሆነ ነው፡፡ ያለዲሞክራሲ ሰላማዊና ጠንካራ ኢትዮጵያን ማሰብ አንችልም፡፡ ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ ከመሆኗ አኳያ የሁሉንም ብሔሮች ፍላጎት ለማካተት የግድ ዲሞክራሲያዊ ሒደት ያስፈልጋል፡፡ ያለዲሞክራሲ እንሂድ ብንል ብጥብጥ ነው የምንጋብዘው፡፡ ኢትዮጵያ ባለብዙ ሃይማኖቶች ናት፡፡ በዓለም ላይ ያሉት ሁለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ክርስትናና እስልምና ለዘመናት ተቻችለው የሚኖሩባት አገር ናት፡

ተቻችለው መኖራቸው የሚቀጥለው ዲሞክራሲያዊ ከሆንን ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ዕድሜው ከ30 ዓመት በታች በመሆኑ ወጣቶች የሚበዙባት አገር ናት፡፡ ወጣቶች ደግሞ ንቁና ለውጥ ፈላጊዎች ናቸው፡፡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመራሃቸው ለልማት እሴቶች ናቸው፡፡ ዲሞክራሲ ከሌለ ግን ለሥርዓቱ አደጋ ይሆናሉ፡፡ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወጣቶች እያመጡት ያሉት አብዮት በዲሞክራሲ እጦት የመጣ ነው፡፡ ጎረቤት አገሮቻችን በቀላሉ ተሰባሪ ናቸው፡፡ ይህንን ተፅዕኖ ለመቋቋም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ግድ ይለናል፡፡ ሌላው አሁን ባለው ተጨባጭ የዓለም ሁኔታ ያለዲሞክራሲ ሕይወትን መምራት አስቸጋሪ ነው፡፡ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያስፈልገናል” ሲሉ እርሳቸውና ድርጅታቸው ኢሓዴግ ለዲሞክራሲ ግንባታ ቁርጠኝነት  እንዳለው ነበር ለማሳየት የሞከሩት።

“ ምርጫዎች ደግሞ የእዚህ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አንዱ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ፍትሐዊ፣ ነፃና ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፡፡ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገቡና በምርጫው ለመሳተፍ የሚችሉ ከ90 በላይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ “ ሲሉም የሚደረገው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ነጻና ተቀባይነት ያለው ምርጫ መሆን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይናገራሉ።

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ መድረክ፣ አረና ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በመርጫ ቦርድ የተመዘገቡ፣ አዲስ ከተቋቋመው ከሰማያዊ በስትቀር ባለፉት ምርጫዎች  የተሳተፉ ፣ ከ ”ዘጠና በላይ” ካሏቸው ድርጅቶ መካከል ያሉ ናቸው።  “ምርጫ የማይፈልጉ፣ መንግሥትን በጦርነት ለመጣል የሚፈልጉ አማፂ ቡድኖችም አሉ፡፡ እነሱን ለመዋጋትና ራሱን ለመከላከል መንግሥት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሳይሆን ወታደራዊ መንገድ ነው የሚከተለው” እንዳሏቸው ድርጅቶች አይደሉም።

ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች የመሰባሰብ፣ ጋዜጣዎች የማተም፣  ሰላማዊ ሰልፎች የመጥራት ፣ ዉህደት የመፍጠር መብታቸው እየተገፈፈ ነው። በገዢው ፓርቲ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። ከፍተኛ አመራሮቻቸው በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ እየታሰሩ ነው። ከአንድነት አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳን ኤል ሺበሺ፣ አንዱዋለም አየለ፣ አበበ ቀስቶ፣ ሻምበል የሺዋስ  ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ የሺዋስ አሰፋ፣ በፍቃዱ አበባ፣ ጌታሁን አያለ፣  ከመድረክ በቀለ ገርባ፣ አብርሃ ደሳታ ፣ ኦልባና ለሌሳ  ታስረዋል።

ታዲያ ይሄ፣ በሕግ በተመዘገቡ ሰላማዊ ፓርቲዎች ላይ፣  በግልጽ የተከፈተ ጦርነት እና ወከባ ካልተባለ ምን ሊባል ነው የሚችለው ? ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማሪያም እንደው ደረታቸውን ነፍተው ይህን አይነት መለስ ሲመልሱ፣ እኛ በተቃዋሚው ጎራ ለምንለው ግድየልም አይጨነቁ፣  አብረዋቸው ያሉ ጓደኞቻቸው ምን ይሉኝ ይሆን ብለው እንኳን አይፈሩም?

“የፖለቲካ እስረኞችን በተመለከተ ምን ይላሉ?” ተብለው ሲጠየቁ ደግሞ የመለሱት መልስ ከማስገረም አልፎ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። “ የፖለቲካ እስረኞች የሉንም፡፡ የታሰሩት የአማፂ ቡድኖች አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ‹‹አክቲቪስቶች›› ሳይሆኑ ጦር ያነሱ ኃይሎች ናቸው፡፡ የሚፈልጉትን ነገር በትጥቅ ትግል ለማሳካት የመረጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሽብርተኞች ናቸው “ የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። የሚሰቀጥጥ መልስ !!!!!!!

ያሳያችሁ የመቀሌው መምህርና ብሎገር አብርሃ ደስታን  ነው ጦር አነሳ የሚባለው ? ሃብታሙ አያሌው፣ አንዱውዋለም አራጌ ፣ የተከበሩ አቶ በቀለ ገርባ ናቸው ጦር አነሱ የሚባሉት ? እነዚህ ወገኖች ቤታቸው፣ ቢሯቸው፣ ኮምፒተራቸውና  ያላቸው ንብርት በሙሉ  ተበርብሯል። ፈንጂ፣ ቦምብ፣ የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች አልተገኘባቸውም። በድበቅ ፣ በሚስጠር የጻፉት፣ የተናገሩት ነገር የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን  መዉደዳቸው ነው። ጥፋታቸው እነ አቶ ኃይለማሪያም ጓዶቻቸው እንዲነገርና እንዲጻፍ የማይፈልጉትን በመጻፋቸውና በመናገራቸው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም በርግጥ ሐቀኛ  ነኝ የሚሉ ከሆነ፣ በርግጥ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲደረግ ቁርጠኝነት ካላቸው፣ “ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ የሕልዉና ጉዳይ ነው” ያሉትን ከልብ የሚያምኑበት ከሆነ ፣ እንግዲህ እርሳቸውና ድርጅታቸው የዘጉትን በር በመከፈት በተግባር ያሳዩን። የታሰሩ እስረኞችን በሙሉ ይፍቱ። ተቃዋሚዎች በነጻነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሕዝቡን እንዲያደራጁና እንዲቀሰቅሱ፣ አማራጭ ፖሊሲዎቻቸዉን እንዲያቀርቡ ይፈቀድላቸው። በፖሊስ፣ በደህንነት በካድሬ መዋከባቸው ይቁም።

አለበለዚያ  “ዲሞክራሲ ከሌለ ግን ለሥርዓቱ አደጋ ይሆናሉ፡፡ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወጣቶች እያመጡት ያሉት አብዮት በዲሞክራሲ እጦት የመጣ ነው፡ “ እንዳሉት እርሳቸው ቁንጮ የሆኑበት ስርዓት አደጋ ላይ ነው የሚወደቀው። በሚሊዮንኖች የሚቆጠሩ ወጣቶችም፣ ሰሞኑን በየ ዩኒቨርሲኦቲና ትምህርርት ተቋማት እያደረጉት እንዳለው መነሳታችቸውና አብዮት መምጣቱ አይቀሬ ነው።

 

 

 

 

 

 

 

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop