የዐብይ ክህደትና አዲሱ ስምምነት / ፋኖ በበላይነት ያጠናቀቀው ውጊያ / የትግራይ ውጥረት ወደ ጦርነት ?
የዐብይ ክህደትና አዲሱ ስምምነት / ፋኖ በበላይነት ያጠናቀቀው ውጊያ / የትግራይ ውጥረት ወደ ጦርነት ?
1 Comment
Leave a Reply
Latest from Blog
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም
ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ
የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ
ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ አንድ አባውራ ምንነቱ ያልታወቀ እህል ከገበያ ገዝቶ ለሚስቱ አምጥቶ ሰጣት አሉ፡፡ ከሰጣትም በኋላ ሚስቱ ያንን እህል ፈጭታ ቂጣ ላርግህ ብትለው፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው፣ ገንፎ ላርግህ ብትለው … ምን አለፋህ
ወሰንየለሽ ኦሮሙማዊ ዕብደት!!
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ
ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN
ከሃይለገብርኤል አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ
የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’
ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም January 10, 2025 በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና
በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ዓለም ሁሉ ያስደነቀው ሚልዮኖች የተመለከቱት አስደናቂው ቪድዮ| Ethiopian Orthodox Mezmur
የተሳካው የአቢይ አህመድ ቁማር
ብዙ ሰዎች አቢይ አንካራ ሄዶ ያደረገው ስምምነት አምና የተጫወተውን የወደብ ቁማር የመበላቱ ምልክት አድርገው ሲተነትኑ ይስተዋላል። ይህም በአሳዛኝ ሁኔታ ዛሬም ድረስ የቀጠለው ስሁት አስተሳሰብ ውጤት ነው። ይኸውም አቢይ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር ማፍረስ ሳይሆን መገንባት ይፈልጋል፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚሆን ቁም ነገር ይሠራል ብሎ ከማሰብ የሚመነጭ የመሸወድ ውጤት ነው።
አቢይ አህመድ ወዶ ገቦች እንደሚጃጃሉት ኢትዮጵያን መርቶ ትልቅ ሀገር ለማድረግ የሚሠራ ሰው ሳይሆን ዛሬ መረጃው ሁሉ የሚያሳየው የተገነጠለች የታላቋ ኢስላሚክ ኦሮሚያን ሪፐብሊክ የመመሥረት ጽኑ ፍላጎት ያለው ጀሃዳዊ ግለሰብ ነው።
የሶማሌ ሕዝብ ፍላጎትና ባሕርይ እየታወቀ ሱማሊላንድ መቼም መቼም ቢሆን የኦሮሙማ የወደብ አማራጭ ልትሆን አትችልም። ታዲያ አቢይ አህመድ ይቺን ፌክ ለምን ዓይነት ቁማር ተጫወታት?
አቢይ የአሰብ ወደብ አማራጭ ነበረለት። አቢይ በልቡ የኢትዮጵያ መሪ ሳይሆን የኦሮሙማ መሪ ስለሆነ አቢይ የሚፈልገው ወደብ ሙሉ በሙሉ ከወደቡ እስከ ዋና ከተማው የሚጓዘው መንገድ ኦሮሞ በሰፈረበት መሬት ላይ እንዲሆን ነው። ለዚህም ወይም በዚህ የወደብ መስመር ላይ ያሉ ሌሎች ነገዶችን በሙሉ አፈናቅሎ ኦሮሞን ማስፈር ይፈልጋል፣ አለበለዚያም ወደቡ ሲጀመርም በኦሮሞ ምድር ላይ ብቻ የሚያልፍ መንገድ ያለው እንዲሆን ይፈልጋል። አሰብና በርበራ በአፋር፣ ኢሳና ሱማሌ መሬት ላይ የሚጓዙ መንገዶች ያላቸው ወደቦች እንደመሆናቸው ለኦሮሙማው ቁንጮ ለአቢይ አህመድ ተመራጭ ወደቦች ሊሆኑ አይችሉም።
ታድያ ፍላጎቱ ይህ ከሆነ ሲጀመርስ ለምን ይቺን ቁማር ተጫወታት? ልክ የአሰብን ወደብ ቁማር እንደተጫወተው ሌላ ሥውር ግብን ለማሳካት የተጫወተው ሸፍጥ ነው። መለስ ብለን ካየን አሰብን ከኤርትራ ወስዶ በምትኩ ለኤርትራ ወልቃይትን ለማመቻቸት እንደቆመረ ይታወቃል። ይህንን ቁማር ሕወሃትን ለማድቀቂያ ብቻ የፈለገው ሲሆን ሕዋሃት ከደቀቀች በኋላ ሻእቢያ ከአሰብ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ያለውን መንገድ ቢሠራም አቢይ አህመድ አፍንጫህን ላስ ብሎታል።
አሁንም ሱማሊላንድ የሚለውን ቁማር አቢይ በዚህ መንፈስ ነው የተጫወተው። ለኢትዮጵያ ወደብ ለማግኘት ፍላጎት ኖሮት አይደለም። የትኛውን ምርቱን ሲያስወጣ? በየትኛው ዶላር ክምችቱ የትኛውን የውጭ ምርት ሲያስገባ? የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በእርስ በእርስ ጦርነት አውድሞ ባለበት ጊዜ ወደብ አንደኛ ደረጃ ጭንቀቱ ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ያለው ይህ ግለሰብ የወደቡን ጨዋታ የፈለገው ለሌሎች የቁማርተኛ ግቦቹ ነበር። እነዚህንም በከፊል እና ሙሉ በሙሉ አሳክቷል።
1. አገሪቷን ለማፍረስ፣ ታሪኳን ለመገርሰስ፣ ተቋማቷን ለማውደም፣ በሕዝቡ መካከል የቀሩትን የትሥሥር ገመዶች ለመበጣጠስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚዳክረውን አቢይ አህመድን ዛሬም የኢትዮጵያ መሪ፣ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ አድርገው ማየት የመረጡ የዋሓን አይሏቸው ጅሎች ጥቂት አይደሉም። ለእነዚህ ራሳቸውን ማጃጃል ለመረጡ አቢይ አህመድ ወደብ ለኢትዮጵያ አስገኘ የሚል ተጨማሪ ማጃጃያ በመስጠት ድጋፋቸውን ለማስቀጠል አስችሎታል።
2. በወቅቱ በፋኖ ግሥጋሴ ከፍተኛ አጣብቂኝ እና ድንጋጤ ውስጥ የወደቀው አቢይ አህመድ በዚህ ቁማር ትንሽ ትንፋሽ ገዝቶበታል። በዚህም ትንፋሽ ከፍተኛ የሠራዊት ሥልጠና፣ ከአይ ኤም ኤፍ ብድር፣ እና ፋኖን መከፋፈያ መጠነ ሰፊ መዋእለ ንዋይ ለማፍሰስ ፋታ አግኝቷል።
3. በሶማሊላንድ ቤዝ ለምትፈልገው ለኤሚሬትስም በመላላክ ለጦርነቱ የሚያውለው የገንዝበ እና የመሣሪያ ድጋፍ አግኝቶበታል።
4. ከኦሮሞማ አጀንዳ አኳያ የሱማሌን ተስፋፊ ብሔርተኝነት ለመቀስቀስና ለማንቀሳቀስ ችሏል። በረጅም ርቀት የኦሮሙማ ታሳቢ ወደብ የሆነችው ሞምባሳን ለማግኘት የሱማሌን ብሔርተኝነት መቀስቀስና ምሥራቅ ኬንያ ተገንጥላ ኬንያ የምትዳከምበትን፣ አንድነቷ ተሸርሽሮ የኬንያ ኦሮሞ ጎሳዎች ከኢትዮጵያ ኦሮሞ ጋር አንድ ሀገር የሚመሠርቱበትን የታላቋ ኦሮሚያ የቅዠት ጉዞም አንድ ደረጃ ወደ ፊት አስኪዶታል። የሱማሌ ብሄርተኝነትን በመቀስቀስም ለኦሮሙማው ሀገር ፍርሻ ተባባሪ ተገንጣይ ክልል ለመቀስቀስም ተጠቅሞበታል።
5. ለጊዜው ቢዳፈንም የሱማሊላንድ እንደ ሀገር እውቅና የማግኘትን ፕሮሰስ አንቀሳቅሶታል። ይህንንም ኦሮሙማው የሚፈልገው ነገ ተገንጥሎ ሀገር ቢመሠርት ተመሳሳይ እውቅና የሚያገኝበትን ቅድመ ታሪክ (ፕሬሲደንት) ለመፍጠር ነው።
6. በመጨረሻም በግራኝ አህመድ ጊዜ ኢትዮጵያን በማውደም ከፍተኛ ሚና የነበራትን ቱርክ ወደ ቀጠናው ጎትቶ በማምጣት ለሀገር ፍርሻ ፕሮጄክቱ ከፍተኛ ድጋፍ ለማግኘት አስችሎታል። አሁን አንካራ ሂዶ በባዶ እጅ፣ እንዳልተቃቀፈ መገመት ይቻላል። ቱርክ ምን ሰጥታ አስማማቻቸው? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ድሮን የገዛበትን ብድር ሰረዘችለት? ተጨማሪ ድሮን እና የጦር መሣሪያዎች ልትሰጠው ተስማማች? በዋናነት ከቱርክ የሚፈልገው ነገር ከቤተ መንግሥት ሊያባርረው የተቃረበውን የፋኖን አመጽ የሚያስታግስበት የጦር መሳሪያ ነው። ይህንን ሁሉ ነገር በብላሽ አገኘ ማለት ቁማሩ ሠምሯል ያስብላል።
7. አሁንም ኢትዮጵያ የከፈለችው ዋጋና የዲፕሎማሲ ኪሣራ ምናምን እያለ ሳያውቅ የሚጃጃል ወይም አውቆ የሚያጃጅል ሰው አይጠፋም። ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ኪሣራ ላይ ብትወድቅ ለአቢይ እንዴት ጉዳት ሊሆን ይችላል? አቢይን የኢትዮጵያ መሪ አድርጎ ከማሰብ የሚመጣ የተቸንካሪነት ችግር ነው። የዲፕሎማሲ ኪሣራውና የኢትዮጵያ ጉዳት፣ ወይም ስብራት እኮ ይህ እኩይ ግለሰብ ሊያሳካቸው ከሚፈልጋቸው ግቦች መካከል ዋናዎቹ ናቸው። የፍትሕ ተቋማቱን ሽባ ያደረገ፣ የሀገሪቱን ሠራዊት ይሁነኝ ብሎ ከትግራይ እስከ ኦሮሚያ እያስማረከ ያዋረደ፣ ሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት ክብር እና አንድነት አፈራርሶ መሳለቂያ ያደረገ፣ ለግብጽና ለአሜሪካ ጥቅም ለመሞት የማለ ይህ ሰው በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ የኢትዮጵያ ኤንባሲና ቆንስላዎችን የዘጋ መሆኑን ረስተው ነው ስለ ኪሣራ የሚያወሩት?
መንግሥቱ ኃይለማሪያም ከነድንቁርናው “ኢትዮጵያ ትቅደም!”ን አራምዶ ከነበረ አቢይ እኮ በተግባሩ “ኢትዮጵያ ትክሠም!”ን የሚያራምድ ሰው ነው።