ሼኩ ይህን የገለፁት አቶ አብነትገብረመስቀል የገንዘብ እግድ ይነሳልእ ብለው ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ በሰጡት መልስ ነው ።
አቶ አብነት ገብረመስቀል ከዚህ በፊት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የውል ጉዳዮች ፍታብሔር ችሎት የተጣለብኝ የገንዘብ እግድ ይረሳልኝ ብለው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል ።
አቶ አብነት ገብረመስቀል ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ ም በድጋሚ ፅፈው ባቀረቡት እግድ ይረሳልኝ ጥያቄን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም ተመልክቶቷል ።
ችሎቱ በእለቱ በቀረበው የአቶ አብነት ጥያቄ ላይ ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቆ አራት ገፅ የያዘ የፅሁፍ ምላሽለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል ።
በዚህ ሰነድ ላይ የአቶ አብነት እግድ መነሳት የለበትም ብለው የገለፁት ሼክ መሐመድ አቶ አብነት በናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኋላ የተ የግ ማህበር ከሰጠሆቸው የ አስራ አምስት ፐርሰንት የአክሲዮን ድርሻ በየአመቱ በመቶ ሚሊዮንኖች የሚቆጠር የትርፍ ድርሻ የሚያገኙ እስከአሁን ድረስም ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የወሰዱ ቢሆንም ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሒሳባቸው የለም እነዚህ እውነቶች በፍርድ ቤት ጭምር በተሰጡ ትዕዛዞች የተረጋገጡ ናቸው ።
ይህ ገንዘብ የት ደረሰ የሚለውን ምላሽ ከህግ አካላት የምንጠብቀው ይሆናል ። ባሳለፍነው የ2015 እና 2016 ዓ ም ብቻ ከናሽናል ኦይል ጂቡቲ 2 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ብር ከ 250 ሚሊዮን ብር ወደ ባንክ ሂሳባቸው ገቢ የተደረገ ቢሆንም በተመሳሳይ በኘሁን ወቅትም ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ የለም ሲል የሚያብራራው የሼኩ መቃወሚያ ሲቀጥልም
አቶ አብነት ገብረመስቀል ዐቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ተመስክሮባቸው እንደንፁህ የመቆጠር መብታቸው ቀርቶ በፍርድ ቤት ብይን የተሰጠ በመሆኑ ተከላክለው እስካላስተባበሉ ድረስ እንደወንጀለኛ እንዳይቆጠሩ መከላከል ይገባቸዋል ።
መንግስት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከፍተኛ ህመም ላይ በመሆናቸው የቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው ብሎ ጤንነታቸው እስኪመለስ ለጊዜው ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጓል ።
ተከሳሹም በዚህ እድል ተጠቅመው ወደ ውጪ ሃገር የሄዱ ሲሆን አሁን ላይ ግን ጤንነታቸው ተስተካክሎ ጊዜአቸውን በኳስ ሜዳ እና እንደ ካሲኖ በመሳሰሉት መዝናኛ ቤቶችበማሳለፍ ላይ የሚገኙ ናቸው ።
አቶ አብነት ገብረመስቀል መንግስት ያደረገላቸውን ትብብር ዋጋ በመስጠት ወደ አገር ቤት ተመልሰው የፍርድ ሒደታቸውን መከታተል ሲገባቸው ይህንን አለማድረጋቸው ሌለላው ቢቀር እንካን ዐቃቤ ህግ ያስመሰከረባቸው በመሆኑ እንደወንጀለኛ እንዳይቆጠሩ ለራሳቸውም ስምና ክብር ሲሉ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን በማቅረብ እንደ ንፁህየመገመት ህገመንግስታዊ መብታቸውን ለማስመለስአልፈለጉም ። የሚለው የባለሐብቱ መቃወሚያ ይህንን አለማድረጋቸው አቶ አብነት ግልፅ በሆነ እና በማያሻማ ሁኔታ እራሳቸው እና ገንዘባቸውን ለማሸሽ ተግባር ቅድሚያ የሚሰጡ ስለመሆናቸው አረጋጋጭ በመሆኑ በዚህ የአፈፃፀም ችሎት የተሠጠው ትዕዛዝ የሚነሳበት የህግ ምክንያት የለም ሲል ይቀጥልና
ስለዚህም የተከበረውፍርድ ቤት በዚህ ረገድ ቢሆን የፍርድ ባለዕዳ አቤቱታ የፍሬነገር መሠረት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦልኝ አቤቱታቸው ውድቅ እንዲያደርገው አጠይቃለሁ ሲሉ ባለሐብቱ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ አስፍረው ተመልክተናል ።
ፍርድቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 አም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን በችሎት ተገኝተን ታዝበናል ።
ዘገባው የፋስት መረጄ ነው
ምን ገባባቸው በነዚህ ሁለት ወንድማማቾች መሀል። አላሙዲን ታስሮ አቶ አብነት ምን ያህል ተብሰክስኮ እንደነበር በሚዲያ ተመልክተናል። ነገር የመሸቅጥ እንጅ የሚያበርድ ጠፍቷል ያሳዝናል።
“አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ የትርፍ ድርሻ ቢከፈላቸውም በአሁን ሰአት ግን ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሒሳባቸው ውስጥ የለም ሲሉ ሼህ መሐመድ ለፍርድ ቤት ገለፁ”
ጌታ አላሙዲ እንዴት የአቶ አብነትን አካውንት መረጃ ማግኘት ቻሉ ጎበዝ በዚህ አይነት ምን ምስጢር ቀረን? ፍርድ ቤቱም ይህንን ሊጠይቅ በተገባ ነበር፡፡