November 22, 2024
6 mins read

ከባሮ ቱምሳ እስከ ሐጫሉ ሁንዴሳ፤ ከደረጀ አማረ ተስፋ እስከ በቲ ኡርጌሳ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ርስ በርስ በተገዳደሉ ቁጥር በአማራ እየተመካኘ በአማራ ላይ ሲካሄድ የኖረው የዘር ፍጅት!

ከአቻምየለህ ታምሩ! ክፍል ፩]

Oromo Nationalist

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በሚቆጣጠረው በሸዋ ምድር በደራ ወረዳ ከሁለት ወራት በፊት ደረጀ አማረ ተስፋ የሚባል እና የ10ኛ ክፍል ወጣት የድኃ ልጅ በግፍ አርዶ በፋኖ ስም በማላከክ በአማራ ሕዝብ ላይ የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት የሚያስንቅ ሌላ ዙር የዘር ፍጅት እንዲካሄድ በሁሉም ልሳኖቹ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ እንደ አዲስ ከፍቷል።

አረመኔው የዐቢይ አሕመድ የፍጅት አገዛዝ ደረጀ አማረ የተባለውን የድኃ ልጅ የኦሮምኛ ቅላጼ ባላቸው አራጆቹ ሲያርድ የሚያሳየውን ቪዲዮ ከሰሞኑ የለቀቀው ሌላው ሕዝብ ባያምነኝ ኦሮሞ የነገርሁትን ሁሉ ስለሚያምነኝ የምፈልገውን አላማ አሳካበታለሁ ብሎ በማሰብ በአማራ ሕዝብ ላይ የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት የሚያስንቅ ሌላ ዙር የዘር ፍጅት ለመፈጸም ነው።

ከዚህ ውጭ ሰው ሁሉ ለማሰብ ፍቃደኛ እንዳልኾነው ተከታዩ ሁሉ ያለውን ሁሉ ሳይጠራጠርና ሳይመረምር እውነት ነው ብሎ የሚወስድ፤ ሳጣራትና ሳያረጋግጥ እንደወረደ የሚቀበል ስላልሆነ፣ በምርኮ የያዛቸውን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጅ የመከላከያቸውን አባላት ወደቤተሰባቸው ሲመልስ የሚውለውን ፋኖ አንድን የደራ የድኃ ልጅ በኦሮሞነቱ ይገድለዋል ብሎ የሚያስብ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ ቀብሮ አንጎሉን ያደነዘዘ ሕዝብ የለም።

አረመኔው ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኦሮሞ ብሔርተኞች በሙሉ ያነገቡትን ጸረ ሰው አላማቸውን ለማሳካት የራሳቸውን ሰው እየገደሉ በአማራ ላይ ማላከክና ኦሮሞን ቀስቅሰው በአማራ ሕዝብ ላይ ዘግናኝ የዘር ፍጅት የመፈጸመ የኀምሳ አመታት የዳበረ ልምድ አላቸው። ይህን በማስረጃ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ሐጫሉ ሁንዴሳን የገደሉት በኦነግ ታጣቂ ቡድን ተልዕኮ የተሰጣቸው የኦሮሞ ተወላጆች መኾናቸውን በወቅቱ “ዐቃቤ ሕግ” በነበረችው በአዳነች አበቤ አማካኝነት ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በሰበር ዜና ነግሮናል።

ሆኖም ግን ሐጫሉን ራሳቸው ገድለው ሲያበቁ ግድያውን በአማራ ስም በማላከክ ኦሮምያ በሚባለው የአማራ መታረጃ ቄራ ውስጥ በሚኖረው አማራ ላይ የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት የሚያስንቅ ፍጅት ፈጸሙበት፤ ንብረቱን አቀደሙበት፤ ከዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር እስከ ዘጠና አመት አዛውንት በጅምላ አማራ የተባለን ሁሉ በጭካኔ ጨፈጨፉት። ጅፍቱን የፈጸሙት ላለፉት አራት አስርታት ሲተረክላቸውን የኖረውን ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ለማጣራት ፍቃደኛ ያልሆኑ በአማራ ጥላቻ የሰከሩ ገዳዮች አልያም የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።

ኦነጋውያን የትግል አባት አድርገው የሚቆጥሩትን ባሮ ቱምሳን የገደለው አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ ወይም በጫካ ስሙ ጃራ አባገዳ በመባል የሚታወቀው የእስላማዊ ኦሮሚያ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ የነበረው የኦሮሞ ሸማቂ ነው። «ኦሮሞ ከፖለቲካ ሥልጣን ተገልሏል» ብሎ ኢስላማዊ ኦሮሚያን ለመፍጠር ጫካ የገባው ጃራ አባገዳ ወይም አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛና በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የአውራጃ ገዢ የነበሩት የፊታውራሪ ኢብራሂም ሀሚድ ልጅ ነው።

ባሮ ቱምሳን ጃራ አባገዳ እንደገደለው ታሪኩን የነገረን የኦሮሞ ብሔርተኛው መረራ ጉዲና ነው። መረራ ጉዲና ይህን ታሪክ የነገረን በጦብያ መጽሔት በጥር 1988 ዓ.ም. «በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይኾንም» በሚል ርእስ ባሳተመው ባለሁለት ክፍል ጽሑፉ ነው።

ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን የኦሮሞ ብሔርተኛት አባት የሚለው ዳኛ አሰፋ ዱላ ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ የተገደለው ከኦሮሞው ጃራ መስፍን ጋር በጥይት ተጠዛጥዘው ሲኾን ርስ በርሳቸው ተገዳደሉበት የጠባቸው ምክንያትም በመካከላቸው የተፈጠረው ቁርሾ ነው።

4 Comments

  1. ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ወያኔንና ኦነግን በስልጣን ላይ የጫኑ እና የዘር ጥላቻ( የአፓርታይድ ፖለቲካ) ስርዓት ያነገሡት የአለም ኃያላን መንግስታት በሚፈልጉበት ትክክለኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። የአለም ታላቁን እና እጅግ የከፋውን የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመቀስቀስ ብልጭታ ብቻ የሚያስፈልግበት ነጥብ ላይ ተደርሷል። ይህ ክስተት የኢትዮጵያን እና መላውን የምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ውድመት የሚያስከተል ይሆናል።
    በዚህ ጽሁፍ በትክክል እንደተገለጸው አክራሪው ኦሮሞ በዚህ አይነት ጥላቻ እና ድንቁርና ውስጥ የተዘፈቀ ግራ እና ቀኝ የማያይ ወጣት ትውልድ በተሳካ ሁኔታ ፈጥሯል እናም ገዳዩ ኦሮሞ ቢሆንም አማራውን ለመጨፍጨፍ ይወጣል።
    ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በዚህ ጨዋታ “ማንም ሰው የሚተርፍ አይኖርም ። ተጠቃሚዎቹ የውጭ ሃይሎች ብቻ ናቸው።” የሚለው ስሜት ወደ ሞኝ ጭንቅላታቸው ሊገባ አይችልም።
    አብይ የኔም ይሆናል ብሎ ተስፋ ያደረገው የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በማቀድ እና በማካሄድ ንቁ ሎሌ ቢሆንም፣ በምዕራቡ ዓለም አሻንጉሊትነት በስልጣን ላይ የቆየው የፖል ካጋሜን እጣ ፈንታ ነው። ከ30 አመት በፊት ሻለቃውን ፖል ካጋሜን ያሰለጠኑት እነዚሁ ሰዎች ወጣቱን አብይ አህመድን ወደ ሩዋንዳ ወስደው አስፈላጊውን ኦረንቴሽን ሰጥተውታል። አቢይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ የማሻሻያ ኮርሶች ወደ ሩዋንዳ ተመልሷል።
    እንደ አዳነች ያሉ ሎሌዎቹንም በቦታው ላይ ለስልጠና ወስዷል።

    The situation in Ethiopia has arrived at the exact point that the global powers who installed the TPLF AND OLF in power and imposed an ethnic-hate apartheid political system desired. A point where only a spark is needed to precipitate the greatest and evilest Genocide humanity has ever seen with the concomitant implosion of Ethiopia and the devastation of the entire East Africa region.
    As stated correctly in this article, the radical Oromo have successfully created a generation of youth steeped in such hate and ignorance and would come out to massacre Amhara people despite the murderer being an Oromo.
    For the foolish Ethiopian politicians, nobody can put the sense into their foolish heads that there would be no survivor in this game and the beneficiaries would only be foreign powers.
    Abiy is drooling over the fate of Paul Kagame, who, despite being an active lackey in precipitating and conducting the Rwandan Genocide, stayed in power as a western puppet. Same people that trained major Paul Kagame 30 year ago, took a young Abiy Ahmed to Rwanda and gave him the necessary orientation. Abiy has been back to Rwanda for several refresher courses since then.

  2. አቻምየለህ ትንሽሽ ሰሰትክ።ብዙ ከምታውቀው ትንሽ ብቻ ቆነጠርክልን። ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ የቦረናው ኦሮሞ ብቅ እንበል።100ሺ ያህሉ ከሁለት ዓመታት በፊት ከቀየው ተሰዷል።የሚኖረው ኬንያ ስደት ካፕ ነው።ለምን ተሰደደ? ድርቅ ገባ ተብሎ የምግብ አጥረት ፈጠሩበት።የኦሮሞው መንግስታት አቢይና ሺመልስ በቢሊዮን በሚቆጠር ብር ቤተ መንግስት እያወቀሩ ለኦሮሞው ቦረና ምግብ አጡ!?
    የቦረናው ኦሮሞ በገዳ ስርዓት ለዘመናት ከምስተዳደር ባሻግር የብልጽግና ወንጌል ኣልዋጥ አለው።ቢያባብሎት ቢያስፈራሩት የማይበገር ሆነ።
    በፋሽሽት ጀርመን ጊንቢ ወለጋ የተመሠረተው መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን 12 ሚሊዮን ብር በጀት ቋጥሮ ቦረናውን ወደ ፕሮቴስታንት ለመቀየር ጣረ።ቦረናው ንክች አላለም።የተፈረደበት ረሃብ ነው።የተገፋው ወደ ስደት ነው።አጡራ ሀብቱ በዚህ ድርቅ ወደ መቶ ሺ የሚጠጉ ከብቶቹ ሞት በላቸው።
    በዚህ ወንጀል ከአቢይ መንግስስት ባሻግር መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ሽፋን በኢትዮጵያ ወንጀል ሲፈጽም ይህ የመጀመሪያው ኣይደለም፡።ሲጀመር ደርግ ከረሸናቸው 60 ሰዎች መሐል ኣንዱ ቄስ ጉዲና ቱምሳ የባሮ ቱምሳ ወንድም የመካነ ኢየሱስ ቁንጮ ናቸው።ደርግ ኣጣርቶ የሚያውቀው የኦሮሞ ነጻ ኣውጪ መመሥረት ጥንስሱም ጠላውም መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ መሆኑን ተገንዝቧል።የኦሮሚኛ መጻፊያ ፊደል (ቁቤ) በቄስ ጉዲና በኩል ጀርመን ባሕል መሃከል ለሕዝብ እንዲከፋፈል መደረጉ ያውቃል።መካነ ኢየሱስ ወያኔ መንግስስት ምሥረታ ላይ በግላጭ ተሳታፊ ነበር።ዛሬም በዝምታ በኢየሱስ ስም አገር ማፍረሱ ላይ አጋር ቢሆን የሚጠበቅ ነው።ወለጋ አማራዎች የመካነ ኢየሱስ ቤ/ክርስቲያን አባሎች ሲታረዱ ዝምታን መርጧል። የነገ ነጻይቱ ኢትዮጵያ ፍርድ የሚጠብቀው ስመ ቤት ክርስቲያን ነው።
    የአቢይ ግድያ ለሥልጣኑ መቆያ መሠናክል የሆነውን ሁሉ ነው። ኦሮሞው መደበቂያው የጎሳ መጋረጃ ከመሆን ኣያልፍም።

  3. በነገራችን ላይ የቢቢሲ ሚናን አለማድነቅ አልችልም። መርዛቸውን በሸንኮራ ሽፋን የመሸፈን የሰላ ችሎታቸው በጣም አስደናቂ ነው። በዚህ የውሸት ግድያ ታሪክ ላይ
    ይህ የኦሮሞ በኦሮሞ ግድያ ታሪክ እንዴት ግራ እንድያጋባ እንዳደረጉት እና መረጃውን እንዳጣመሙ የግጭት መቀስቀሻ ሥራቸው ፍጹም ምሳሌ ነው።
    አንድ ወዳጄ ለታላቁ የኢትዮጵያ እልቂት የመጀመሪያውን ፊሽካ የሚነፋው ቢቢሲ ነው ይለናል። እሱን ማመን ጀምሬአለሁ።

  4. ወንድማችንና የታሪክ ማጣቀሻ መዝግባችን አቻምየለህ ታምሩ፡፤ እውነትም አቻምየለህ ነህ፡፤በርእሱ ላይ እንደተጠቀሰው ከዚህች ቁንጽል ጽሁፍህ ሰፋ ብሎ በተከታታይ የምታወጣቸውን ጽሁፎች በጉጉት እየጠበቅን ነው፡፡
    እኔ እንደሚገባኝ አማራ አንገቱ አንድ ነው ሲባል ሁሉም በየሙያው ለአማራ ነጻ ህዝብነት፣ ታላቅነትና ልእልና የየድርሻውን ፣የየሙያውን የሚችለውን….ወዘተ በማድረግ ራሱን ጭምር አሳልፎ ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በቻልነው ሁሉ መሬት ላይ ያለዉንና ፋኖ የሚመራውን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል እንደግፍ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ውጭ አገር ሆነን መሰናክል አንሁንባቸው፡፡ ያስጠላል!!!
    ወንድሜ በርታልን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop