የሴራ እርካብ የደም መንበር | የሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ ቅንብር | ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ|

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኩሽ፣ ሴም፣ ኑቢያ፣ አበሻ እና ኢትዮጵያ (በግል የቀረበ ዳሰሳ/ ደረጀ ተፈራ)

1 Comment

  1. ተፈጥሮ ከችሎታ ጋር ከተሰጣቸው ምጡቅ ጋዜጠኞች መካከል አንድ ያየሰው ሽመልስ ነው። ይሁን እንጂ መጽሃፉ አፍቃሪ ወያኔ በመሆኑ እምብዛም አልተዋጠለኝም። ግራም ነፈሰ ቀኝ የመጽሃፉ መጻፍ ተመሳሳይ ነገሮችን ይዘው አሁን በገቢያ ላይ ለሚገኙና ወደፊትም ለሚጻፉት መጽሃፍት ማጣቀሻና ማነቃቂያ ይሆናል። መከተቡ ማለፊያ ነው! ከዚያ ውጭ የሃበሻውን የፓለቲካ ሽኩቻና ሴራ ከሥሩ ተረድቶ፤ የዘርና የቋንቋውን ፓለቲካ አክ እንትፍ ብሎ ዛሬ ላይ እኔን ስሙኝ እውነቱ ይህ ነው የሚለን ማንም ጸሃፊ አልተገኘም። ሁሉም በብሄሩና በልቶ ባደረበት ሲወሸክት ጊዜ እየበረረ፤ ሃሳብና እውነታው እየዛገ፤ አመሳካሪ ሰዎችና መጣጥፎች አፈርና እሳት እየበላቸው ነገሩ በጠራ ሁኔታ ሳይጻፍ ተረት ሁኖ እየቀረ ነው። ቀርቷልም።
    ከዚህ ባሻገር በዘር ፓለቲካው የተለከፉትና ከሞት የተረፉት የሚጽፉት ዝናቸውንና ጉራቸውን በመሆኑ እውነትን ሁሌም ይዘሏታል። ከከፋም የድርጅት ሚስጢር አላወጣም በሚል የደንቆሮ እይታ እውነትን እንደያዙ አፈር ይመለስባቸዋል። መጽሃፍ መጻፍ አዕምሮ ሳይዝግ ነው። አይን ከፈዘዘ፤ ጭንቅላት ከደነዘዘ በህዋላ አምጣ ቢሉት ትውስታ ብልጭ አይልም። በወደቀ ዛፍ ላይ ምሳር ከማብዛት ይልቅ ግፍ የበዛበት ህዝባችንን ባለፈውም ሆነ ዛሬ ላይ እንደ በረት ላሞች የሚያንከላውሷቸውን ሰዎች ለይቶ ከነክፋታቸው መጻፉ ለመጭው ትምህርት ይሆናል። ነገርየው ሁሌ አሞሌ እንዳየች ላም መላሴን በምላሴ እንዲሉ ሆነና በህቡዕም ሆነ በይፋ የተጻፈ ሰው የሚናፍቀውና እየተቀባበለ የሚያነበው መጽሃፍ በኢትዮጵያ ምድር ከተጻፈ ቆየ። ያ ቀን ይናፍቀኛል። የኢትዮጵያ የውሃ ወቀጣ ፓለቲካና በዚያ ዙሪያ የተጻፉ መጽሃፍቶችም ሆነ ሃሳቦች ሙሉነት የጎደላቸው ስለሆኑና ስለሚሆኑ አይጥሙኝም። ጋዜጠኛ ያየሰውም የተሰጠውን የተፈጥሮ ችሎታ ከእውነትና ከሚዛናዊነት ጋር አጣጥሞ በሌላ ስራው ላየው እናፍቃለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share